No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዛያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጰውልስ አርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- አቶ ከሳሁን ታደሰ - ጠበቃ አቶ ዖበነ ፍቅሬ ቀርቧል።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፀዲለ ሀፍታይ- ጠበቃ አቶ ኤልያስ ወርቁ ቀርቧል።
መዛገቡ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ መንሥኤ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን መሰረት ያደረገ ነው። የአሁኗ ተጠሪ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ከአሁን አመልካች /ከሥር ተከሳሽ/ ጋር ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት በመሆን አብረው በሚኖሩ ጊዚ ያፈሩዋቸው በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 20 የቤት ቁጥር አዱስ የሆነ ቤት እና የሰላዲ ቁጥሩ ኢት 03-01-52703 የሆነ የጭነት መኪና የጋራ በመሆናቸው ተከሳሽ /አመልካች/ ንብረቶቹን እንዱያካፍለን ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
የሥር ተከሳሽ /የአሁኑ አመልካች/ የግራ ቀኙ በጣልያን ሀገር የሚኖሩ በመሆናቸው የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ተፈጻሚነት የለውም፣ የተከሳሽ ነዋሪነት ውጭ አገር በመሆኑ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጉዲዩ መቅረብ አይችልም፣ የግራ ቀኙ እንደ ባልና ሚስት ለመኖር የተስማሙት ጣልያን አገር በመሆኑ ተጠሪ/ከሳሽ/ በኢትዮጵያ ክስ መመስረት አይችለም፣ ስለ ንብረት የሚያነሱትም ክርክር በጣልያን አገር ህግ መሰረት ከጋብቻ ውጭ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች በሚለያዩበት ጊዚ በአንደ ስም የተመዖገበውን ላላኛው መጠየቅ እንደማይቸል በጣልያን አገር ከሚያገለግል ጠበቃ የቀረበ የሕግ አስተያየት አስተርጉመን ስላቀረብን እና ከሳሽ /ተጠሪ/ ለክርክሩ መነሻ ያደረጉዋቸው ንብረቶች በተከሳሽ ስም የተመዖገቡ በመሆናቸው ከሳሽ መብት የላቸውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም የአሁኗ ተጠሪ በመቃወሚያዎቹ ላይ መልስ እንዱሰጡበት ካደረገ በኃላ የአሁኑን አመልካችን መቃወሚያዎችን ውድቅ በማድረግ በከ/መ/ቁ.138413 ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ/ም ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ በፍሬ ነገሩ ላይ ክርክር እንዱያደርጉ ትዔዙዛ ሰጥቶ የአሁኑ አመልካች ንብረቶቹ ስለመኖራቸው ሳይክድ ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የአሁኗ ተጠሪ የጠየቁዋቸው ንብረቶች የጋራ ስለሆኑ እኩል እንዱካፈለ ሲል በኮ/መ/ቁ. 138413 የካቲት 24 ቀን 2007 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ብይን እንዱሁም ውሳኔው ላይ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ችልትም ይግባኙ በመቀበል ክርክራቸውን ከሰማ በኃላ በፍ/ይ/መ/ቁ. 111588 ህዲር 8 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችልት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን የአቤቱታ ይዖቱም በአጭሩ የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡቸውን መቃወሚዎችን በማለፍ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደተፈጸመበት የሚገልጽ ሲሆን ላልች ነጥቦች በፍሬ ነገር ረገድ ተፈጸሙ ያለዋቸውን ስህተቶች በመዖርዖር የቀረቡ ናቸው።
የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የግራ ቀኙ በጣሉያን አገር ሳለ የፈጠሩት ግንኙነት የባልና ሚስት ዓይነት ግንኙነት ነበር የመባለንና ይህ ቢታለፍ ግራ ቀኙ የንብረት ግንኙነት ነበራቸው ወይስ አልነበራቸውም? የሚለው የመጣራት አለመጣራቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው በጠበቃቸው በኩል ህዲር 1 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ መልስ ዛርዛር ነጥቦችን አንስተው ተከራክሯል። የአመልካች ጠበቃም ታህሳስ 5 ቀን 2009 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተው የሚመስል ሲሆን አመልካችና ተጠሪ በጣሉያን ሀገር ህግ መሰረት እንደባልና ሚስት አብረው መኖራቸው በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 5 መሰረት ላታይ ይገባል ወይስ አይገባም? በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግና በጣሉያን ህግ መካከል የሕግ ግጭት አለ ወይስ የለም? የአመልካችና የተጠሪ ንብረት ክርክር እልባት ሉያገኝ የሚችለው በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ነው ወይስ በጣሉያን ህግ መሰረት ነው? የሚለት ነጥቦች ሉታዩ የሚገባቸው ናቸው። አመልካችና ተጠሪ ጣሉያን አገር መኖራቸው፣ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብረው የኖሩ መሆናቸው፣ በዘህ ግንኙነት ልጅ የወለደ መሆናቸው በግራ ቀኙ መካከል ክህደት የለም።
በመሰረቱ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 5 ሥር በውጭ አገር የተፈጸመ ጋብቻ በኢትዮጵያ ውስጥ ለህግና ለሞራል ታቃራኒ እስካልሆነ ድረስ ተቀባይነት አለው የሚለውን በጣሉያን አገር እንደ ባልና ሚስት አብረው የኖሩበትን ሁኔታ አመሳስለው መተርጎም ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን ከድንጋጌው ዓላማና መንፈስ ጋር አያይዜ መመልከት ያስፈልጋል።
የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 5 “ በተፈጸመበት አገር የጋብቻ አፈጻጸም ህግ መሰረት ከኢትዮጵያ ውጭ የተፈጸመ ጋብቻ የህዛቡን ሞራል እስካልተቃረነ ድረስ በዘህ ህግ ተቀባይነት ይኖረዋል“ በማለት ይደነግጋል። የዘህ ህግ ድንጋጌ ዓላማ በውጭ አገር ጋብቻ የፈጸሙ ባልና ሚስት የጋብቻ ማስረጃቸው በኢትዮጵያ ህግ ተቀባይነት የሚያገኝበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው። በዘህ ድንጋጌ መሰረት ተጋቢዎች በውጭ አገር ህግ መሰረት ተጋብተው ነገር ግን ጋብቻቸው ከኢትዮጵያ ህዛብ ሞራል ጋር የማይቃረን ከሆነ ተቀባይነት ይኖረዋል ማለት ነው። ይህ አንቀጽ ከኢትየጵያ ወጭ ጋብቻው ቢፈጸምም የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቱ ጋብቻን ለመመሥረት የሚያሰችል ከመሆኑ ጋር የተያያዖ ነው። ድንጋጌውም እውቅና የሚሰጠው በውጭ አገር ለተፈጸመ ጋብቻ እንጂ ለላልች ግንኙነቶች አይደለም። በውጭ አገር በአንድ ወንድና ሴት መካከል እንደባልና ሚስት አብረው መኖርን ከዘህ ድንጋጌ ጋር በማመሳሰል መተርጎም የህግ ስህተት ነው። በዘህ ረገድ የሥር ፍርድ ቤት የደረሰው ድምዲሜ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግና በጣሉያን ህግ መካከል የህግ ግጭት አለ ወይስ የለም? የሚለውን ሁለተኛውን ነጥብ ከክርክሩ እንዱሁም ከሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አንጻር ተመልክተናል። ይህን ጭብጥ በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት በሁለቱም አገር ህጎች መካከል ግጭት እንዲለ ተቀብል መሆን የሚገባውን በተመለከተ ግን በቂ ምላሽ ሳይሰጥ እንዲለፈ የሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያሣያል። አመልካች በጣሉያን አገር ህግ መሰረት ሁለት ግለሰቦች ጋብቻ ሳይመሰርቱ እንደባልና ሚስት ከኖሩ በጋራ የሚያፈሩት ንብረት እንደላለ፣ ሁለቱም በስማቸው ተመዛግቦ የሚገኘው ንብረት ባለቤት ተደርገው ስለሚቆጠሩ ሲለያዩም በየግላቸው ያላቸውን ንብረት ይዖው እንደሚቀሩ ከሥር ፍርድ ቤት ጀምሮ ተከራክሯል። አመልካች በዘህ ጉዲይ ላይ የጣሉያን ህግ በተመለከተ ኤላክሳድሮ ለፒዙ ከሚባል በጣሉያን አገር ህጋዊ ከሆነ ጠበቃ ማብራሪያ በታች ፍርድ ቤት በማስረጃነት አስተርጉመው ጣሉያን አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር በኩል አረጋግጠው ማቅረባቸውን ተያይዜ የቀረበልን የሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። በዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ /Private International law/ መሰረት በዖርፈ እውቀት ያለ ወይም ምሁር /Scholar/ የሰጠውን አስተያየት በማስረጃነት ማቅረብ እንደሚቻል የተረጋገጠ ነው። የቀረበውን አስተያየት እንደማንኛውም ማስረጃ የመመዖን ሥልጣን ግን አስተያየቱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነው።
በልላ በኩል በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 102 /1/ ላይ የንብረት አስተዲደራቸውን አስመልክቶ የሚያደርጉት ውል እንደተጠበቀ ሆኖ፣ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብረው የሚኖሩ ሰዎች ለሶስት ዓመት ላላነሰ ጊዚ አብረው ከኖሩ በግንኙነቱ ውስጥ እያለ ያፈሩዋቸው ንብረቶች የጋራ ሀብታቸው ይሆናለ በማለት ይደነግጋል። ይህም የኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር፣ በመተማመን መንፈስ ሆነው ንብረት እንዱያፈሩ ለማድረግ እና ለዘሁም የህግ ጥበቃና ዋስትና እንዱኖር ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ መረዲት ይቻላል። በልላ አነጋገር እንደባልና ሚስት አብረው የሚኖሩ ሰዎች ከሶስት ዓመት ላላነሰ ጊዚ አብረው ከኖሩ የሚያፈሩት ንብረት የጋራ እንደሆነና ለዘህም ህጉ ጥበቃ እንደሚያደርግ ነው።
በዘህ መሰረት አመልካች ካቀረቡት ክርክር አኳያ የጣሉያን ሀገር ህግ እና የኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ የተለያየ ድንጋጌ እንዲላቸው ነው። ይህም በሁለቱ ህጎች መካከል ግጭት እንዲለ ያሳያል።
ስለሆነም ይህ በአግባቡ ሳይጣራ የሚሰጥ ውሳኔ የተሳሳተ ድምዲሜ ላይ የሚያደርስ ይሆናል።
በተያዖው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት የጣሉያን አገር ህግ አመልካች እንደሚለት መሆን ያለመሆኑን ህጉ እንዱቀርብ በማድረግ አጣርቶ መወሰን ሲገባው ይህንን ሳያደርግ እና የህግ ግጭቱን ለይቶ ሳያረጋግጥ የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል የአመልካችና የተጠሪ ንብረት ክርክር እልባት ሉያገኝ የሚችለው በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ነው ወይስ በጣሉያን ህግ መሰረት? የሚለው ነጥብ እልባት ሉያገኝ የሚችለው ከላይ በተመለከተው መሰረት የህግ ግጭት መኖር አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኃላ ነው። ስለዘህ የህግ ግጭት መኖር አለመኖሩ ሳይረጋገጥ ክርክር የተነሳባቸው ንብረቶች የጋራ ናቸው ተብል የተሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በመጨረሻም የሥር ፍርድ ቤቶች ከላይ የተመለከቱትን መሰረታዊ ነጥቦችን በአግባቡ ሳያጣሩ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፤ በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 138413 የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ይ/መ/ቁ. 111588 ህዲር 8 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በፍርድ ሀተታው በተገለጸው መሰረት በጣሉያን አገር ህግ እና በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ መካከል እንደባልና ሚስት አብረው በመኖር ግንኙነት ውስጥ የተፈራ ንብረት የጋራ አንዱሆን ለመወሰን በሁለቱም ህጎች መካከል ግጭት መኖር ያለመኖሩን የጣሉያን አገር ህግ እንዱቀርብ ተደርጎ ጉዲዩ ውሳኔ እንዱሰጥበት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔ ግልባጭ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይድረስ።
መዛገቡ ስለተወሰነ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.