No summary available.
ሚያዛያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጰውልስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- ፏርፋክት ትራንዘትና ትራንስፖርት ኃላ/የተ/የግ/ ማኅበር - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ አህመድ ዲውድ ( አቶ አህመድ ሁሴን ወኪል) - አልቀረበም መዛገቡ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው የአሁኑ አመልካች ሚያዛያ 28 ቀን 2008 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ የአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ቁ. 4627 ታኅሳስ 27 ቀን 2008 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይ/መ/ቁ. 4105 መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ዲኝነት በመጠየቁ ነው።
የክርክሩ መነሻ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3- 30303 ኢት የተሳቢ ከባድ ተሸካርካሪ መኪና ከጅቡቲ አዱስ አበባ በመጓጓዛ ላይ እያለ በአፊር ክልል ዱቸአቶ ተብል በሚታወቀው ቦታ በደረሰው ግጭት ንብረትነቱ የተጠሪ በሆነ መኪና ላይ ጉዲት በመድረሱ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በመኪናው ላይ ለደረሰበት ጉዲት ብር 350.000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ/፤
መኪናው የሚንቀሳቀስበት ከፒታል ቢያንስ ከአደጋው በኃላ ሶስት ዘር ሽያጭ ተካሂድበት ሉገኝ የሚችለው በአንድ ዘር ብር 20.000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ x የ3 ዘር 60.000.00 /ስልሳ ሺህ/ ብር፣ መኪናው አደጋው በደረሰበት ቦታ ከአንድ ወር በላይ አመልካች በ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ አስገምታለሁ ብል ሲያጉላላ በዖብ ለማስጠበቅ ብር 5.000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ የትራንስፖርት ማስጫኛና ማውረጃ ለሰራተኛ 1000.00 /አንድ ሺህ/ ብር እንዱሁም በዘህ ጉዲይ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ያወጣሁት የአልጋ፣ የምግብና የትራንስፖርት ወጪና ኪሳራ ብር 20.000.00 /ሃያ ሺህ/ እንደሆነ ገልጾ በድምሩ 441.000.00 /አራት መቶ አርባ አንድ ሺህ/ ብር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ሲል ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካችም በበኩለ በተጠሪ መኪና ላይ ለደረሰው ጉዲት ለአመልካች የመድን ሽፊን የሰጠው ሕብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ የጉዲቱን ካሳ ለመክፈል ወይም እንደአስፈላጊነቱ መኪናውን ለማስጠገን ዋስትና ሰጥቶ እያለ ተጠሪ አመልካች ለጉዲቱ ዋስትና አላቀረበም በማለት በተሳሳተ መንገድ የመዲኘት ሥልጣን ለላለው አፊር ክልል አልዲአር ወረዲ ፍርድ ቤት የእግድ ትዔዙዛ በማሰጠት የአመልካች መኪና እንዲይንቀሳቀስ ከሶስት ወራት በላይ እንዱቆም በማድረጉ አመልካች በዘህ ምክንያት የተቀቋረጠበትን አንድ ወር ገቢ 50.000.00 /አምሻ ሺህ/ ብር የሶሰት ወር 150.000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር እንዱከፍል ሲል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል።
ሁለቱንም ክሶች የተመለከተው የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን እና የጣልቃ ገቡን የህብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ክርክር ፣ የምስክሮችን ቃል እንዱሁም የሰነድ ማስረጃን መርምሮ የአሁኑን አመልካች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ በማድረግ የአሁኑ አመልካች ለአሁኑ ተጠሪ የመኪናውን ግምት 350.000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር፣ የተቋረጠ የሶስት ወር ገቢ 60.000.00 /ስልሳ ሺህ/ ብር፣ ለመኪናው ጥበቃ የተከፈለውን 5.000.00 /አምስት ሺህ/ ብር በድምሩ 415.000.00 /አራት መቶ አስራ አምስት ሺህ/ ብር ከ10% የጠበቃ አበል እንዱሁም ዲኝነት በታርፍ መሰረት እና ላልች ወጪዎች ካለ ዛርዖር የማቅረብ መብት ለረቺ ጠብቀናል በማለት ወስኗል።
ይህን ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኙን ተቀብል የግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን የአቤቱታ ይዖቱም በአጭሩ፡-
ፍርድ ቤት በገለልተኛ ባለሙያ የተገመተው ግምት እያለ በፖሉስ ግምት ተመስርቶ 350.000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር የጉዲት ከሳ መወሰኑ ያለአግባብ ነው።
ተጠሪ የተቋረጠበት 60.000.00 /ስልሳ ሺህ/ ብር እንዱሁም ለጥበቃ የወጣ ወጪ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ/ እንዱከፈለው የሥር ፍርድ ቤት ከመወሰኑ ወጪ አንዲችም ማስረጃ ሳይቀርብ የሰጠው ውሳኔ አቤቱታን ሳይሆን ማስረጃን መሰረት አድርጎ የመወሰን መሰረታዊ መርህን የተጻረረ ፍጹም የዲኝነት ግድፈት ነው።
ተጠሪ ለጠበቃ ስለመክፈላቸው ያቀረቡት ማስረጃ በላለበት እና መኪና ወደ ሀገር ቤት እየገባ እያለ በመሆኑ ገቢ ማስገባት ባልጀመረበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤት የተቋረጠ ገቢ እንዱከፈል መወሰኑ ፍርድ ቤቱ ፍትሒዊ እንዲልሆነ በቂ ማስረጃ ነው።
አመልካች በተከሳሽ ከሳሽነት ያቀረበውን ክስ የሥር ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገው በህግ አግባብ አይደለም።
ሰለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ እንዱሻርልኝ የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ኃላፉነትን በተመለከተ ያቀረቡት ክርክር ባይኖርም የከሳ መጠኑን በተመለከተ ግን ያቀረቡት ክርክር በአግባቡ በሥር ፍርድ ቤቶች ተጣርቶ ውሳኔ የተሰጠበት መሆን ያለመሆኑንና እንዱሁም በአመልካች የቀረበው የተከሳሽ ከሳሽት ክስ ውድቅ ተደርጎ የታለፈበትን አግባብ ለመመርመር ሲባል መዛገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በቀን 20/01/2009 ዓ/ም የተጻፈ ዛርዛር መልስ አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን አመልካቹም ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ/ም የተጻፈ መልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን ጉዲዩን በሶስት ጭብጮች ከፍለን እንደሚከተለው መርምረናል።
ፖሉስ በተጠሪ መኪና ላይ የደረሰውን ጉዲት ገምቶ ለማቅረብ በህግ የተሰጠ ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? በዘህ ረገድ የተገመተው ግምት በገለልተኛ ባለሙያ የተገመተ ነው ለማለት ያስችላል ወይስ አያስችልም?
አመልካች የተቋረጠበትን ገቢ ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? ለመኪና ጥበቃስ የወጣውን ወጪ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም?
አመልካች በተከሳሽ ከሳሽነት ያቀረበውን ክስ የሥር ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለ ናቸው፡፤
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ በተጠሪ መኪና ላይ በደረሰ ጉዲት ምክንያት ኃላፉነትን መሰረት አድርጎ የተነሳ ክርክር ባይኖርም ጉዲቱን ተከትል ሉካስ የሚገባው የካሳ ግምት በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ያስነሳ ከሆነ ሉጣራ የሚገባው እንዳት ነው? ግምቱን አጣርቶ የሚያቀርበውስ ማነው? የሚለ ነጥቦች በቅድሚያ ሉታዩ የሚገባቸው ናቸው። መኪናው ላይ በደረሰው ጉዲት ከጥቅም ውጪ የሆኑ የመኪና እቃዎች በማንኛውም ምስክር የሚረጋገጡ ሳይሆኑ በዖርፈ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የሚረጋገጡ እንደሆኑ መረዲት ያስፈልጋል።
እንደዘህ ያለ ነገሮች በሚከሰቱበት ጊዚ ፍርድ ቤት የፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 136 ድንጋጌን በመከተል ልዩ አዋቂ (ኤክስፏርት) በመሾም እንዱጣራ ማድረግ ይኖርበታል።
ምክንያቱም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት ያስችል ዖንድ ጉዲዩ በሚመለከው ባለሙያ እንዱጣራ ማድረግ የዲኝነት አካለ ዋነኛው ተግባር ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ወደ ተያዖው ጉዲይ ስንመለስ ትራፉክ ፖሉስ በመኪናው ላይ የደረሰውን የጉዲት ካሳ ግምት ለማረጋገጥ ሙያው ብቃት መኖር ያለመኖሩን እንዱሁም ለዘህ አካል በህግ የተሰጠውን ሥልጣን ከዋጅ ቁጥር 681/2002 አንጻርመመልከት ተገቢ ነው። የዘህ አዋጅ አንቀጽ 2 /25/ እና 37 /2/ /ሐ/ እንደሚያመለክተውየትራፉክ ተግባርና ኃላፉነት ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ ለመንቀሳቀስ አስፈላጊውን ቴክኒካዊ ብቃት እንዲላቸው መመርመር እና በአደጋው ጊዚ የአደጋውን መንሥኤ ማጣራት እንዱሁም ከአደጋው በኃላ ተሽከርካሪው መንገድ ላይ ለመንቀሳቀስ ቴክኒካዊ ብቃት እንዲለው ማረጋገጥ ነው። ከዘህ ውጭ በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰ ጉዲትን በተመለከተ የገበያ ዋጋ አስልቶ ግምት ለማቅረብ በህግ ለትራፉክ ፖሉስ የተሰጠው ተግባርም ሆነ ኃላፉነት የለም።
በልላ አነጋገር በመኪናው ላይ የደረሰውን ጉዲት ብቻ ሳይሆን ንብረቱ በወቅቱ ለገበያ ቀርቦ ሉያወጣ የሚችለው የገበያ ዋጋ /Market Value/ ገምቶ ለማቅረብ የሚችለው ፖሉስ ሳይሆን በዘህ ዖርፍ በቂ እውቀት፣ ክህልት እና ሙያ ያለው ሰው ነው፡፤ ስለሆነም በተያዖው ጉዲይ በፖሉስ የቀረበው ግምት መኪናው ላይ የደረሰውን ጉዲት በተመለከተ የገበያ ዋጋን ግምት መጠን በአግባቡ አጣርቶ ለማቅረብ በቂ ሙያዊና ቴክኒካዊ ብቃት ባለው ባለሙያ የቀረበ ግምት ባለመሆኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የተሽከርካሪ ዋጋ ግምት የመተመን አገልግልት መስጠት በአዋጅ ቁጥር 468/97 አንቀጽ 7 /1/ዖ/ መሰረት የትራንስፖርት ባለሥልጣን ስለመሆኑ የሚደነግግ ቢሆንም የገበያ ቃጋን መሰረት አድርጎ እስካልቀረበ ድረስ ተቀባይነት የሚሰጠው አይሆንም።
በልላ በኩል የአሁኑ አመልካች በግራ ቀኙ በኩል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ጉዲት የደረሰበት መኪና ወደ አዲማ ከተማ ተጓጉዜ በገለልተኛ ባለሙያ ከተመረመረ በኃላ የጉዲቱ ካሳ መጠን ብር 108.747.83 /አንድ መቶ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ብር ከሰማኒያ ሶስት ሳንቲም/ ተረጋግጦ ያለና ሕብረት ኢንሹራንስ ግምቱን ለመክፈል ፍቃደኛ ሲሆን ተጠሪ ግን የተገመተውንም ግምት ለመቀበል እምቢተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ሉወስን የሚገባውም ይህ ግምት ነው ሲል ይከራከራል። ተጠሪ በበኩለ ተገምቷል በተባለው አካል መኪናው ላይ የደረሰው የጉዲት መጠን እንዱገመት ያለመስማማቱን ገልጾ ተከራክሯል። ይህ ክርክር የሚያመለክተው በግራ ቀኙ መካከል የጋራ መስማማት እንዲልነበረ ነው። ይህ ብቻ አይደለም የተደረሰበት ስምምነት ስለመኖሩ ለሥር ፍርድ ቤት የቀረበና ያስረዲ ማስረጃ እንደላለ ውሳኔው ያመለክታል። በመሆኑም አመልካች በዘህ ረገድ የሚያቀርቡት ክርክር በግራ ቀኙ በጋራ በተደረሰ ስምምነት መሰረት ግምት የተሰራለት /የወጣለት/ ስለመሆኑ በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዲት በዖርፈ በቂ እውቀትና ክህልት ባለው /ባላቸው/ ባለሙያ /ባለሙያዎች/ ተጣርቶ ሉወሰን ይገባል ብለናል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የአሁን ተጠሪ መኪናው ጉዲት ሳይደርስበት ቢሸጥ ኖሮ በሶስት ወር ውስጥ ሉያተርፍ የሚችለውን ብር 60.000.00 /ስልሳ ሺህ/ ገምቶ ያቀረበው በሥር ፍርድ ቤት ተፈርድለታል። በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዲት ጠቅላላ ጉዲት / Total Loss/ እንደሆነ ከተጠሪ ክርክር ተረድተናል። እንዱህ ዓይነት ጉዲት በሚደርስበት ጊዚ በንብረቱ ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ግምት ከመጠየቅ ውጭ ይገኛል ተብል የሚታሰበውን ገቢ መጠየቅ አግባብነት አይኖረውም። በህጉ መሰረት የጉዲት ከሳ ክፍያ ዓላማው ተጎጂው በደረሰበት ጉዲት ልክ ጉዲት አድራሹ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ እንዱከፍል በማድረግ ወይም የደረሰውን ጉዲት በማሰራት /በማስጠገን/ ጉዲት ከመድረሱ በፉት ወደ ነበረበት ሁኔታ እንዱመለስ ማድረግ ነው። ይህንን ከፍትሒብሓር ህግ ቁጥር 2090 /1/፣ 2092 እና 2119 /1 እና 2/ መረዲት ይቻላል።
በተያዖውም ጉዲይ የአመልካች ኃላፉነት በተጠሪ መኪና ላይ ለደረሰበት ጉዲት በጉዲቱ ልክ ተመጣጣኝ ካሳ መክፈል ወይም ጉዲቱን በመጠገን መኪናው ጉዲቱ ከመድረሱ በፉት ወደ ነበረበት ሁኔታ እንዱመለስ ማድረግ ነው። ከዘህ ወጭ ከደረሰው አደጋ ጋር ግንኙነት የላለውን ክፍያ አመልካች የሚከፍልበት ህጋዊ ግዳታ ሉኖር አይችልም።
የመኪና ጥበቃ ወጪን በተመለከተ አመልካች መኪናው ፖሉስ ዖንድ ስለቆየ ተጠሪ ለመኪና ጥበቃ የሚከፍልበት ምክንያት አይኖርም ሲል የተከራከረ ቢሆንም ይህን የሚደግፍ ማስረጃ ለሥር እንዲቀረበ የሚያመለክት ነገር ተያይዜ በቀረበልን ውሳኔ ላይ ስለላለ በዘህ ረገድ በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
ሶስተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የአመልካች መኪና በወረዲ ፍርድ ቤት ትዔዙዛ ታግድ መቆየቱን የግራ ቀኙ አይካካደም። የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚያመለክተው መኪና ለጊዚው ታግድ የቆየው አመልካች ዋስትና እንዱያስይዛ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 151 እና 152 መሰረት ነው። ይህ ደግሞ ፍርድ ቤቱ የተከሰተውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባትና በማጤን የሰጠ ትዔዙዛ በመሆኑ በተጠሪ ክፈ ልቦና ምክንያት የተፈጸመ ድርጊት ሆኖ አይታይም።
አመልካች ተጠሪ ሥልጣን በላለው ፍርድ ቤት መኪናውን አሳግድ በማቆየቱ የሶስት ወር 150.000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር ኪሳራ አድርሶብኛል በማለት ያቀረበው የተከሳሸ ከሳሽነት ክስ በሥር ፍርድ ቤት ተቀባይነትን ማጣቱ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
በመጨረሻም በመኪናው ላይ የደረሰውን የጉዲት ካሳ ግምት ብር 350.000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ/ እንዱሁም ይገኝ የነበረ ገቢ ነው ተብል 60.000.00 /ስልሳ ሺህ /ብር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ከላይ በዛርዛር ከተገለጹ ህጋዊ ምክንያቶች አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
4105 መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ለተጠሪ መኪና ጥበቃ የተከፈለ ብር 5000.00 /አምሰት ሺህ/ አመልካች እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የአመልካች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተቀባይነት የለውም ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በተጠሪ መኪና ላይ ለደረሰ ጉዲት የካሳ ግምት ብር 350,000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ እንዱሁም ለተቋረጠበት ገቢ ብር 60,000.00 አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ተብል የተወሰነው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
ለተቋረጠ ገቢ አመልካች ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ/ ለተጠሪ ሉከፍል አይገባም ተብል ተወስኗል።
በመኪናው ላይ የደረሰውን የጉዲት ካሳ ግምት በተመለከተ ከላይ በፍርድ ሀተታ ላይ በአንደኛ ጭብጥነት ተይዜ በዛርዖር በተገለጸው መሰረት ስለ ጉዲዩ በቂ እውቀትና ክህልት ባለው ባለሙያ በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዲት ተጣርቶ እንደገና እንዱወሰን በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 343 /1/ መሰረት ለአውሲረሱ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልስናል።
ሐምል 20 ቀን 2008 ዓ/ም የተሰጠው የእግድ ትዔዙዛ ተነስቷል። ለሚመለከተው አካል ይጻፍ።
ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይላክላቸው። በ20/11/08 ዓ/ም የተሰጠ እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.