No summary available.
ሚያዘያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ሰብስቤ አበበ ከጠበቃ እንድሪያስ ተፈራ ጋር ቀርበዋል ተጠሪ፡ ወ/ሮ ፍቅርተ ካህሳይ ጠበቃ ወርቁ ገበየሁ ቀርበዋል መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የኮንድሚኒያም ቤት ለማስለቀቅ የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን፣ ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.170075 ሐምል 20 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት የአሁን አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፣ ከሳሽ ባቀረቡት ክስ ሟች ልጄ ዖዉደ አስራት በሕይወት በነበረ ጊዚ በአዱስ አበባ ከተማ ባልቻ ሜዲ ሳይት ቀበላ 05/08 የሕንጸ ቁጥር ቢ1 የቤት ቁጥር 11 የወለል ስፊት 48.79 ካ.ሜ ባለ ሁለት መኝታ መኖሪያ ቤት የነበረዉ ስለሆነ ተከሳሽ ሟች ልጄ ከሞተ በኋላ ባዖጋጀዉ ሐሰተኛ እና የሕጉን ፍርም ባልተጠበቀ ዉል ቤቱን ይዖው ስላለ ቤቱን ለቀዉ እንዱያስረክቡኝ በማለት ከሷል።
የሥር ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ሟች ይህን ቤት በወለድ አግድ ዉል አስይዜ ተበድረዉ ገንዖቡን መመለስ ካልቻለ መንግስት ቤቱን ለመሸጥ ያስቀመጠዉ የጊዚ ገደብ ሲያበቃ ቤቱን ለእዲዉ መክፈያ እንዱሆን እና ባለቤትነቱን ወደ ተከሳሽ ስም ለማዖዋወር ተስማምተናል ዉል ፈርመናል። በዉለ ላይ ያለዉ ፊርማ የሟች ስለመሆኑ በፍረንሲክ ተመርምሮ ሉረጋገጥ ይችላል። ስለዘህ ከሳሽ ቤቱን ለመረከብ ያቀረቡት ክስ ዉድቅ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ ይህን ቤት በወለድ አግድ ዉል ይዢአለሁ ይበለ እንጂ በፍትሐብሐር ሕጉ በተመለከተዉ አግባብ ዉለን የማይንቀሳቀስ ንብረት መዛገብ ላይ ስለማስመዛገባቸዉ ያቀረቡት ማስረጃ ስለላለ የወለድ አግድ ዉል ተቋቋሟል ለማለት ስለማይቻል ቤቱን ለከሳሽ ሉያስረክብ ግዳታ አለባቸዉ በማለት ወስኗል።
የሥር ተከሳሽ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ጳጉሜ 4 ቀን 2007 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል።
የአቤቱታዉም ይዖት በአጭሩ ሟች ዖዉደ አስራት ከአመልካች ገንዖብ ተበድረዉ ቤቱን ማስያዙቸዉን ምስክሮች አስረድተዋል፣ ዉለም በልደታ ክ/ከተማ የይዜታ አስተዲደር ዉስጥ መያያዘን ለፍ/ቤቱ በተላከዉ ደብዲቤ ተረጋግጧል፣ አመልካች ቤቱን የያዛኩት ያለአግባብ ሳይሆን በወለድ አግድ ዉል በመያዛ ቤቱና ሰነድቹን ተረክቤ እያለሁ፣ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ቤቱን ለተጠሪ እንዲስረክብ የሰጡት ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በዛርዛር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣በአመልካችና በተጠሪዋ አዉራሽ መካከል ሰኔ 30 ቀን 1999 ዓ.ም ተደርጓል የተባለዉ የወለድ አግድ ዉለን አከራካሪዉ ቤት በሚገኝበት ማዖጋጃ ቤት ከሚመለከተዉ ማህደር ጋር በወቅቱ እንዱያያዛ እንደተደረገ መሆኑን ማዖጋጃ ቤቱ ግለጾ እያለ የሥር ፍ/ቤት በዘህ ዉል ሉይዘ አይችለም በማለት ቤቱን ለተጠሪዋ እንዱያስረክቡ የመባለን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ በታዖዖዉ መሰረት ህዲር 7 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ አምስት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡- የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ የሚነቀፍበት ምንም የሕግ ምክንያት ስለላለ እንዱጸናልኝ በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመርነዉ የአሁን ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ ከሳሽን የሚያስገድድ ዉል ሳይኖር በሐሰተኛ ዉል እና የሕጉን ፍርም ባልጠበቀ ዉል የሟች ልጄ ንብረት የሆነዉን የኮንድሚኒያም ቤት ይዜ ስለሚገኝ ቤቱን ለቀዉ እንዱያስረክበኝ በማለት የከሰሱ ሲሆን፤ የአሁን አመልካች በበኩለ ባቀረበዉ መልስ ሟች በሕይወት በነበረበት ወቅት ሰኔ 30 ቀን 1999 ዓ.ም ወለድ አግድ ዉል ቤቱን አስይዜ ተበድረዉ ቤቱን እና ሰነደን ስላስረከበኝ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም የሚል ነዉ። ከዘህ አንጻር የአሁን አመልካች ከሟች ጋር ይህ ዉል ተዋዉለናል ባለበት ወቅት በሕግ የተቀመጠ በኮንድሚኒያም ቤት በተመለከተ ዉል የማድረግ ክልከላ ጊዚ ሳያልቅ መሆኑን አመልካች ራሳቸዉ ባቀረቡት ክርክር ያረጋገጡት ጉዲይ ነዉ።
No topics extracted.
በመሆኑም በሕግ የተቀመጠ ክልከላ እያለ በዘህ ኮንድሚኒያም ላይ የተደረገ ዉል ሕግን የሚቃረን እስከሆነ ድረስ ፍ/ቤት ለዘህ ዉል ዋጋ በመስጠት አመልካች በሕግ ፉት ዋጋ ባለዉ ዉል ቤቱን ይዝል ለማለት የሚቻልበት አግባብ የለም።
ከዘህም በላይ የአሁን አመልካች ቤቱን በወለድ አግድ ይዢአለሁ እያለ ስለሆነ በሕግ ፉት ዉጤት ያለዉ ዉል አለ ወይስ የለዉም? የሚለዉም ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። ወለድ አግድን በተመለከተ የፍትሐብሐር ሕግ ቁጥር 3117--3130 ሥር ተመልክቷል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3117 እንደሚደነግገዉ ‹‹ወለድ አግድ ማለት አንድ ባለዔዲ ግዳታዉን ለመፈጸም ማረጋገጫ በማድረግ ለገንዖብ ጠያቂዉ የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት ለማስረከብ የሚገደድበት ዉል ነዉ›› በማለት ደንግጎታል። የወለድ አግድ ዉልን ለማቋቋም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዡን መቋቋም የሚመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት እንዲላቸዉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3118 ተመልክቷል።
ይህ ከሆነ ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዡ ዉል የሚያቋቋሙት ድንጋጌዎች ማየቱ አስፈላጊ ነዉ። በዘህ መሰረት የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3052 እንደሚያመለክተዉ ይህ ዉል ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በማይንቀሳቀስበት ሀብት መዛገብ ካልተጻፈ ምንም ዓይነት ዉጤት እንደላለዉ ነዉ። ይህ የምዛገባ አፈጻጸም ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3053 ሥር ተመልክቷል። የአሁን አመልካች ይህን የወለድ አግድ ዉል አደርገናል የሚለዉን ዉል በዘህ አግባብ የማይንቀሳቀስ ንብረት መዛገብ እንዲልተመዖገበ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። የአሁን አመልካች በዘህ አግባብ ተፈጽሟል እና የሰበር አጣሪ ችልትም እንደጭብጥ አድርጎ የያዖዉ ይህ ዉል በቤቱ ማህደር ዉስጥ መገኘቱን ነዉ። ነገር ግን ይህ ዉል መቼ የቤቱ ማህደር ዉስጥ እንደተገኘ እና ይህ በሕጉ የተመለከተዉን የምዛገባ ሥርዓት ያሟላ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ።
በዘህ ረገድ የልደታ ክ/ከተማ ይዜታ አስተዲደር ጽ/ቤት ለሥር ፍ/ቤት በጻፈዉ ደብዲቤ ከሳሽ የቤቱ ስመ ሀብት ከሟች ወደ እሳቸዉ እንዱዙወርላቸዉ ጠይቀዉ፣ ነገር ግን ካርታ ጠፊኝ ስላለ በአዱስ ልሳን ጋዚጣ በ4/2/2004 ዓ.ም ታዉጆ፣ አመልካች በ25/3/2004 ዓ.ም የስም ዛዉዉር ቢደረግ መብቴን ይነካል በማለት በማመልከቱ በዘህ ምክንያት ከማህደሩ ጋር እንደተያያዖ ገልጸዋል። ከዘህ መገንዖብ እንደሚቻለዉ የአሁን አመልካች ይህን ዉል ከላይ በተመለከተዉ የሕግ ድንጋጌዎች አግባብ ዉለ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ የማይንቀሳቀስ ንብረት መዛገብ መመዛገቡን የሚያመለክት አይደለም። ይህ ዉል ለክርክር ምክንያት በሆነዉ ኮንድሚኒያም ቤት ላይ የተደረገዉ በሕግ የተቀመጠዉ ክልከለ ባለበት ሁኔታ ስለሆነ የልደታ ክ/ከተማ ይዜታ አስተዲደር ጽ/ቤት ዉለን ይመዖግባል ተብልም አይገመትም። በመሆኑም በሕግ ፉት የሚጻና የወለድ አግድ ዉል በአመልካች እና በሟች ዖዉደ አስራት መካከል ተደርጓል ለማለት አይቻልም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች በአመልካች እና በሟች መካከል በሕግ ፉት የጸና የወለድ አግድ ዉል መደረጉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ስለላለ አመልካች ቤቱን ያለ አግባብ ይዜ ስለሚገኝ ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክብ መወሰናቸዉ በሕጉ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ.191279 በ12/10/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.170075 ሐምል 20 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የዘህ ዉሳኔ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በ15/2/2007 ዓ.ም የተሰጠ የአፈጻጸም እግድ ትዔዙዛ በዘህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።