No summary available.
ሚያዘያ 25 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ት ማሕላት እንዲለ አልቀረቡም ተጠሪ፡- 1.አቶ አህመድ አለም አልቀረቡም 2.ወ/ሮ ዖይነባ አብደላ መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ነው።በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር አመልካች የመቃወም አመልካች፤ተጠሪዎች ደግሞ እንደ የቅደም ተከተላቸው የፍርድ ባለመብት እና የፍርድ ባለዔዲ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት ያቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ይዖት በአጭሩ የአፈጻጸም ትዔዙዛ የተሰጠበት በኮልፋ ቀራንዩ ክ/ከተማ ቀበላ 05 በደብረአባይ ቁጥር 1 እና 2 ራሥ አገዛ የመኖሪያ ቤቶች ሕብረት ሥራ ማሕበር በ175 ካ.ሜ ላይ የሚገኘውን ቤት ግንቦት 01 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል የገዘት መሆኑን በመግለጽ ተከራካሪ ሳይሆኑ በቤቱ ላይ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዔዙዛ መብታቸውን የሚጎዲ በመሆኑ ይሻርላቸው ዖንድ ዲኝነት የጠየቁ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪዎች በጉዲዩ ላይ አስተያየት እንዱሰጡበት ትዔዙዛ የተሰጠ ቢሆንም 2ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው ስላልቀረቡ ፍ/ቤቱ አስተያየት የመስጠትመብታቸውን አልፍታል።1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ በቂ ምክንያት የላለው መሆኑን፤አመልካች ቤቱ በዔዲ መያዘን እያወቁ ዖግይተው ያቀረቡት አቤታታ ከቅን ልቦና ውጪ የቀረበ በመሆኑአቤቱታቸው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የአፈጻጸም ችልቱ የግራቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካች ቤቱን ገዛቸዋለሁ በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም ያቀረቡት የሽያጭ ውለ ሥልጣን ባለው አካል ፉት ያልተመዖገበ በመሆኑ በፍርድ ባለመብት ላይ የመቃወሚያ መሰረት ላሆን አይችልም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ አከራካሪው ቤት የማሕበር ቤት በመሆኑ ለጉዲዩ አወሳሰን ተፈጻሚነት ያለው ሕግ ሥለ ሕብረት ሥራ ማሕበራት አደረጃጀት እና አሥተዲደር የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 147/91 ነው፤የዘህ ሕግ አንቀጽ 19/1/ለ በማሕበሩ ውስጥ በተሰራ ቤት ላይ መብት ያገኘ ሰው ይህንኑ መብቱን ለላላ ሰው ለማሥተላለፍ ቢፈልግ ከማሕበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ ፈቃድ ማግኘት እንደሚኖርበት ይደነግጋል፤የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በመ. ይህንኑ በመጥቀስ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፤አመልካች ያቀረቡት የሽያጭ ውል የማሕበሩ ሥራ አመራር ኮሚቴ ፈቅድ ያስተላለፈው መሆኑን፤የመተካካት ሥርዓቱም በማሕበሩ ዖንድ የተመዖገበ እና አግባብ ባለው አደራጅ መሥሪያ ቤት እንዱመዖገብ የተላለፈ ሥለመሆኑ የሚያስረዲ አይደለም፤በሰነደ ላይ የማሕበሩ ማሕተም አርፍ መገኘቱ ብቻውን ሕጉ በሚጠይቀው አሰራር የመብት ማስተላለፍ ሑደት መከናወኑን የሚያረጋግጥ አይደለም፤ከክርክሩ ሑደት መገንዖብ የተቻለውም 2ኛ ተጠሪ የቤቱን ሥመሐብት ወደ አመልካች ሣያዜሩ እየኖሩበት የሚገኙ መሆናቸውን በመሆኑ በ2ኛ ተጠሪ ሥም በሚታወቅ ቤት ላይ በመንደር የቤት ሽያጭ ውል መብት አግኝቸበታለሁ በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በውጤት ደረጃ ተቀብል አጽንቶታል።የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡-ማሕበሩ የሽያጭ ውለን ተቀብልት አመልካችም በ2ኛ ተጠሪ ምትክ ተተክቼ ማሕበሩ የሚጠይቀውን ተገቢውን ክፍያ እየከፈልኩ የማሕበሩ አባል ሆኘ እንድቀጥል ፈቅድልኝ ውለ በማሕበሩ ከገባበት ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በቤቱ እየኖርኩበት እገኛለሁ፤በአሁኑ ሰዓትም ማህበሩ ካርታ በሥሜ እንዱዖጋጅ አድርጎልኝ የፍ/ቤት ክርክር አለበት የተባለ በመሆኑ ተቀምጦ ይገኛል፤ማሕበሩ ይህን እውነታ ያሳወቀኝ የይግባኝ ክርክሩ ከተደረገ በኋላ ነው፤አከራካሪው ቤት በክፍለ-ከተማውም ሆነ በማሕበሩ ተመዛግቦ የሚገኘው በአመልካች ሥም እንጂ በ1ኛ ተጠሪ ሥም አይደለም፤የማሕበሩ ማሕተም አርፍበት ከማሕበሩ የተላከው ውልም የሚያሣየው አመልካች እና ሁለተኛ ተጠሪ ያደረግነው የቤት ሽያጭ ውል የጸና መሆኑን ነው፤በማሕበሩ ትዔዙዛ በሥሜ ካርታ ተሰርቶ እያለ 1ኛ ተጠሪ ካርታው ላሰጥ አይገባም ብለው በመከራከራቸው እንዲይሰጠኝ የተደረገ መሆኑ እየታወቀ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል በማለት የተሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአመልካችን ውል የሕብረት ሥራ አመራሮች ፈቅደው ያልተቀበለት በመሆኑ አመልካች መቃወሚያ ማቅረብ አትችልም በማለት ውሳኔ የመስጠቱን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።እኛም የግራቀኙን ክርክር እንዱጣራ ከተያዖው ነጥብ እና ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካች ለዘህ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክርክር አከራካሪው ቤት በክፍለ-ከተማውም ሆነ በማሕበሩ በአመልካች ሥም ተመዛግቦ ይገኛል፤ ከማሕበሩ የተላከው እና የማሕበሩ ማሕተም ያረፈበት ውልም የሚያሣየው ይህንኑ ነው፤በማሕበሩ ትዔዙዛ በሥሜ ካርታ ተሰርቶ 1ኛ ተጠሪ ካርታው ላሰጥ አይገባም ብለው በመከራከራቸው እንዲይሰጠኝ ተደርጓል በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም ይህን ፍሬነገር በመግለጽ በበታች ፍ/ቤቶች የተከራከሩ ለመሆኑ የክርክሩ ሑደት አያሳይም።የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 329/1 በበታች ፍ/ቤቶች ያልቀረበን አዱሰ ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መቀበል የለበትም በማለት የሚደነግግ በመሆኑ አመልካች ለዘህ ችልት ያቀረቡትን አዱስ ክርክር አልተቀበልነውም። አመልካች በበታች ፍ/ቤቶች የተከራከሩት የአፈጻጸም ትዔዙዛ የተሰጠበትን ቤት ግንቦት 01 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ ውል ከ2ኛ ተጠሪ የገዘ መሆናቸውን በመግለጽ መሆኑን፤በማስረጃነት ያቀረቡት ውልም ግንቦት 01 ቀን 1998 ዓ.ም ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ተፈጽሟል ያለትን የመንደር ውል መሆኑን፤የአፈጻጸም ትዔዙዛ የተላለፈበት በኮልፋ ቀራንዩ ክ/ከተማ ቀበላ 05 በደብረአባይ ቁጥር 1 እና 2 ራሥ አገዛ የመኖሪያ ቤቶች ሕብረት ሥራ ማሕበር በ175 ካ.ሜ የሚገኘው ቤት የማሕበር ቤት መሆኑን፤አመልካች ባቀረቡት የሽያጭ ውል ላይ የማሕበሩ ማሕተም አርፍ መገኘቱ ብቻውን የመብት ማስተላለፈ የማሕበሩ ሥራ አመራር ኮሚቴ ፈቅድ ያስተላለፈው ስለመሆኑ እና የመተካካት ሥርዓቱም በማሕበሩ ዖንድ ተመዛግቦ አግባብ ባለው አደራጅ መሥሪያ ቤት እንዱመዖገብ የተላለፈ ሥለመሆኑ የማያሳይ መሆኑ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዖን ሥልጣን ባላቸው የበታች ፍ/ቤቶች ተረጋግጧል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ሰዎች በመደራጀት ያቋቋሟቸው የሕብረት ስራ ማህበራትን በተመለከተ የተደነገገው የህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/91 ስለማሕበራቱ ዓላማ፣ ስለማሕበራቱ አመሰራረት፤ስለሚመሩባቸው መርሆዎች፣ ስለሕግ ሰውነትና ኃላፉነት፤ስለመተዲደሪያ ደንብ፣ ወዖተ በተመለከተ ዛርዛር ድንጋጌዎችን ያካተተ መሆኑን፤የአዋጁ አንቀጽ 19 የማህበሩ አባል ዔጣውን ወይም ጥቅሙን ለማስተላለፍ እንደሚችል፤የማስተላለፈ ሁኔታም የራሱ የሆነ የተለየ ስርዓት እንዲለው፤የማህበሩ አባል ዔጣውን ወይም ጥቅሙን ለማስተላለፍ ቢፈልግ ከማህበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ ፈቃድ ማግኘት እንደሚኖርበት፤በማህበር ተደራጅቶ የተገኘውን መብት የማስተላለፉያ ስርዓቱ በግል ከተገኘ መብት የተለየ መሆኑን፤መብት የሚተላለፍለት ወገንም በአስተላላፉው መብት መጠቀም የሚችለው በመተካት የማህበሩ አባል መሆን ከቻለ ብቻ መሆኑን፤ይህ የማስተላለፍ ሥርዓት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 ከተመለከተው የማይንቀሣቀስ ንብረት መብት ማስተላለፉያ ስርዓት የተለየ መሆኑን፤በማህበር በመደራጀት የተሰራውን ቤት ሸያጭ ውል በፍ/ብ/ሕግ/ቁ 1723 ከተመለከተው ድንጋጌ ጋር አያይዜ ማየቱ ትክክል እንዲልሆነ እና በማህበሩ ያለውን መብት ማስተላለፍን በተመለከተ ከአዋጅ ቁጥር 147/91 አንፃር መታየት ያለበት መሆኑን በመግለጽ በየትኛውም እርከን ላይ ላለ ፍ/ቤቶች አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
የሰበር ሰሚ ችልቱ ይህን የሕግ ትርጉም ከሰጠ በኋላ የሕብረት ሥራ ማሕበራት አዋጅ ቁጥር 147/91 ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 402/96 የወጣ ቢሆንም ተሻሽል የወጣው አዋጅ የአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 19 ድንጋጌን በተመለከተ ያሻሻለው ነገር የለም።
በተያዖው ጉዲይ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ገዛቸዋለሁ የሚለትን የማሕበር ቤት በአዋጅ ቁጥር 147/91 መሰረት ከማሕበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ ፈቃድ አግኝተው እና በመተካት የማሕበሩ አባል ሆነው የተላለፈላቸው መሆኑን በመግለጽ በበታች ፍ/ቤቶች ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ ሥለላለ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ጉዲዩን በአዋጅ ቁ 147/91 እና ይህ የሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት በማድረግ የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በውጤት ደረጃ ተቀብል ማጽናቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.