No summary available.
ሚያዘያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- ብሓራዊ የኢትዮጲያ ኢንሹራንስ /አ.ማ/ አልቀረበም ተጠሪዎች፡- የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት
መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በዘህ ሰበር ችልት ያቀረበው የግልግል ዳኞች ጉባኤ፣ የስር ከሳሾች /ተጠሪዎች/ የእቃውን ማቅረቢያ ጊዚ ካለ አመልካች ፈቅድና ስምምነት ያራዖሙ በመሆኑ በሰጠሁት የዋስትና ሰነድ መሰረት ልገደድ አይገባኝም በማለት ያቀረበውን ክርክር በማለፍ አመልካች ለክስ ኃላፉ ነው ማለታቸውና አመልካች ዔዲው እስከከፈል ድረስ 0.07 መቀጫ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጡትን ውሳኔ አግባብነት በሰበር አጣርቶ ለመወሰን የሚል ጭብጥ በሰበር አጣሪ ችልት ተመስርቶ ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው የግልግል ዳኞች ጉባኤ ነው። የግልግል ዳኞች በወቅቱ አንደኛ ተከሳሽ በነበረው ሰባተኛ ተጠሪና በከሳሾች የላልች ተጠሪዎችመካከል ያለውን ክርክር ሰምቶ መጋቢት 13 ቀን 2003 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቶ ነበር። ሁለተኛ ተከሳሽ/የአሁን አመልካች/ የግልግል ዳኞች ለእኔ በአግባቡ መጥሪያ እንዱደርሰኝ ሳያደርገው መስጠታቸው ስህተት ያለበት ነው በማለት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ፣የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የግልግል ዳኞች የሰጡትን ውሳኔ በመዛገብ ቁጥር 01-82566 ሀምላ 11 ቀን 2004 ዓ/ም በመሻር ጉዲዩን ለግልግል ዳኞች መልሶታል።
ለዘህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የግልግል ጉባኤ ዳኞች ጉዲዩ፣ ወደ ግልግል ዳኞች ከመለሰው በኋላ፣ የግልግል ጉባኤው የስር አንደኛ ተከሳሽ /ሰባተኛው ተጠሪ/ ና ሁለተኛው ተከሳሽ /አመልካች/ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ሀምላ 7 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ነው። የክርክሩ መነሻ ከሳሾችያቀረቡት ክስ ነው። ከሳሾች የተለያዩ የቢሮ ዔቃዎችን ለመግዙት ባወጣው ጨረታ አንደኛ ተከሳሽ/ሰባተኛ ተጠሪ/ አሸናፉ ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው /አራት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ አርባ ብር/ የሆኑ እቃዎችን ለማቅረብ መስከረም 12 ቀን 1991 ዓ/ም ውል የተዋዋለ መሆኑን፣አንደኛ ተከሳሽ የእቃዎቹን ሙለ ዋጋ / አራትመቶ ስልሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ አርባ ብር/ በቅድሚያ ክፍያነት የተከፈለው መሆኑን፣ አመልካች /ሁለተኛተከሳሽ/ አንደኛ ተከሳሽ እቃዎቹን ባያቀርብ፣ አንደኛ ተከሳሽ ለወሰደው ዋጋ ለመክፈል የቅድመ ክፍያ ዋስትና ሰነድ ጥቅምት 19 ቀን 1994 ዓ/ም የሰጠ መሆኑን፣ አንደኛ ተከሳሽ የውል ግዳው ከገባባቸው ዔቃዎች ውስጥ የብር 73,800 /ሰባሶስት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ የሚያወጡ እቃዎችን የቀረበና ቀሪዎቹን /ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ብር/ የሆኑ እቃዎች ያላቀረበ በመሆኑ ይህንን ገንዖብ፣ በውለ ላይ የተገለጸውን የመቀጫ ገንዖብና ወለድ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ እንዱወሰንላቸው ከሳሾች የግልግል ዳኞች ጉባኤውን ጠይቀዋል።
የስር አንደኛ ተከሳሽ/ሰባተኛ ተጠሪ/ በወቅቱ ያቀረባቸው እቃዎች የጥራት መስፈርት አያሟለም በማለት ከሳሾች አላግባብ የመለሱ በመሆኑ ለውለ አለመፈጸም ተጠያቂነት ያለባቸው ከሳሾችእንደሆኑና መቀጫም የመክፈል ኃላፉነት እንደላለበት በመግለጽ ተከራክሯል። ሁለተኛ ተከሳሽ /አመልካች/ ዔቃዎች ከሳሾች መረከብ ነበረባቸው። አላግባብ ባለመረከባቸው ለውለ አፈፃጸም ላይ ችግር የፈጠሩት ከሳሾች ናቸው። ከሳሾች ሁለተኛ ተከሳሽ ዋናው ባለዔዲ /አንደኛ ተከሳሽ/ ዔቃዎቹን ያላቀረበ መሆኑን ቢያሳውቀኝ ኖሮ እኔ ራሴ ወይም ላላ ሰው ወክዬ የውልን ግዳታ እፈጽም ነበር። ከሳሾች ያለሁለተኛ ተከሳሽ ፈቃድና ስምምነት ሀምላ 25 ቀን 1993 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ ለአንደኛ ተከሳሽ የዔቃውን ማቅረቢያ ጊዚ ያራዖመ በመሆኑ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል።
የግልግል ዳኞች የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ፣ የስር አንደኛ ተከሳሽ /ሰባተኛ ተጠሪና/ ሁለተኛ ተከሳሽ አመልካቾች/ ያቀረቧቸውን መከራከሪያዎች ውድቅ በማድረግ፣ ተከሳሾች ከሳሾች ክስ ያቀረቡበትን /ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺ ሰባት መቶ አርባ ብር/ በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ። ከዘህ በተጨማሪ ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ይህንን ገንዖብ ከፍለው ተከሳሾች እስከሚያጠናቅቅ ድረስ፣ በውለ ላይ የተቀመጠውን በቀን 0.007 መቀጫ በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ። እንዱዘሁም ተከሳሾች ጉዲዩ ለፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ጊዚ ጀምሮ /ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺህ ከባት መቶ አርባ ብር/ ከፍለው እስከጠናቀቁበት ጊዚ ድረስ ዖጠኝ ፏርሰንት ወለድ ለከሳሾች ይክፈለ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ስ/ስ/ህግ/ቁጥር 337 መሰረት ሰርዜታል።
አመልካች ለዘህ ሰበር ችልት ህዲር 18 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ ከሳሾች ለዋሱ ማስጠንቀቂያ አልሰጡም። ሁለተኛው ተከሳሽ በሰጠው ዋስትና መሰረት ኃላፉ የሚሆኑበት ምክንያት የለም። የግልግል ዳኞች መደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ጊዚ ጀምሮ እዲው ተከፍል እስኪያልቅ ድረስ ወለድ እና በቀን 0.007 መቀጫ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች ጥር 29 ቀን 2007 ዓ/ም የአመልካች ክርክር አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል። ሰባተኛ ተጠሪ በአዱስ ዖመን ጋዚጣ ተጠርቶ ስላልቀረበ መልስ የመስጠቱ መብት ታልፎል። አመልካች መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ያቀረቡት የጽሁፍ ክርከር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው፣ ጉዲዩ በግልግል ዳኞች ጉባኤ ሲታይ አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ሰባተኛው ተጠሪ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን ለማቅረብ የጨረታ አሸናፉ ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው /አራት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ አርባ ብር/ የሆኑ የቢሮ ዔቃዎች በጨረታ ሰነድ የተገለጸውን የጥራት መስፈርትና /specification/በማሟላት ለማቅረብ ውል መዋዋል አከራካሪ አይደለም።
የእቃው አቅራቢ የሆነው ሰባተኛው ተጠሪ እቃዎችን ሙለ ዋጋ ብር 468,540 /አራት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ አርባ ብር/ በቅድመ ክፍያነት የወሰደ መሆኑና፣ ሰባተኛው ተጠሪ ለወሰደው የቅድመ ክፍያ ዋስትና ይሆን ዖንድ አመልካች የቅድመ ክፍያ የዋስትና ሰነድ መሰጠቱ የግልግል ጉባኤ ዳኞች አረጋግጠዋል። ከዘህ በተጨማሪ አመልካች ዋስ የሆኑት ሰባተኛው ተጠሪ አቅርባለሁ ብል የውል ግዳታ ከገባበትውስጥ ብር 73,800/ሰባሶስትሺህ ስምንት መቶ ብር/ የሚያወጡ የቢሮ እቃዎች በውለ የተገለጸውን የጥራት መስፈርት በማያሟላ ሁኔታ ማቅረቡንና ቀሪዎችን ዋጋቸው ብር 394,740ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ብር) የሚያወጡ ዔቃዎች በውለ የተገለፀውን የጥራት መስፈርት በሚያሟላ ሁኔታ ያላቀረበና በውል የገባውን ግዳታ ባለመፈፀሙ ለውለ አለመፈፀም ኃላፉ ሆኖ መገኘቱን የግልግል ጉባኤው ዳኞች በግራ ቀኙ በኩል የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ በመርመርና በመመዖን ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነው።
አመልካች የቅድመ ክፍያ ዋስትና ሰናድ የሰጠው ሰባተኛው ተጠሪ የዔቃ አቅርቦት ውለን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ለውለ አለመፈፀምና ውለ በአግባቡ ባለመፈጸሙ ምክንያት ፈራሽ ለመሆኑ ኃላፉነት ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል። ከዘህ አንፃር አመልካች የዔቃ አቅርቦት ውለ በአቅረቢው (ሰባተኛ ተጠሪ) ባለመፈፀሙ ምክንያት በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባኝም በማለት ያቀረበው ክርክር የሰጠው የዋስትና ሰነድ የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት ያላገናዖበና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። አመልካች ስማቸው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ተራ ቁጥር የተገለጹት ተጠሪዎች የዔቃው ማቅረቢያ ጊዚ እስከ ሀምላ 25 ቀን 1993 ዓ/ም ያራዖሙ በመሆኑ ተጠያቂነት ያለብኝም በማለት ያቀረበው ክርክርም አመልካች ነሐሴ 28 ቀን 1991 ዓ/ም የሰጠውን የዋስትና ሰነድ ለማደስ ጥቅምት 19 ቀን 1994 ዓ/ም የተጻፈ የዋስትና ሰነድ የሰጠ በመሆኑና አመልካች ጥቅምት 19 ቀን 1994 ዓ/ም የተጻፈ የዋስትና ሰነድ የሰጠው በመጀመሪያው ውል የተገለፀው የዔቃ ማቅረቢያ ጊዚ የተራዖመ መሆኑን እያወቀ በመሆኑ ክርክሩ የህግ ድጋፍ ያላለው ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የዔቃ አቅረቢው (ሰባተኛ ተጠሪ) በውለ መሰረት ላላቀረበው የቢሮ ዔቃ አመልካች በሰጠው የዋስትና ሰነድ መሰረት በአንድናትና በነጠላ ኃላፉነት አለበት በማለት የግልግል ጉባኤው የሰጠው ውሳኔን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
በዘህ ሰበር ችልት ላታይ የሚገባውና አከራካሪ የሆነው ጭብጥ የእቃው አቅረቢ የነበረው (ሰባተኛው ተጠሪ) የውል ግዳታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት አመልካች ስማቸው ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 6 ለተገለፀው ተጠሪዎች ከዋናው ባለዔዲ ጋር በአንድነትና በነጠላ ለመክፈል የሚገደደው ምን ያህል ነው የሚለው ነጥብ ነው። የዔቃው አቅረቢ በቅድመ ክፍያነት ከወሰደው ገንዖብ ውስጥ (ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ብር) ዋጋ ያላቸውን የቢሮ ዔቃዎች ያላቀረበ በመሆኑ አመልካች ከዋናው ባለዔዲ ጋር በአንድናትና በነጠላ ይህንን ገንዖብ እንዱከፍል የግልግል ዳኞች የሰጡት ውሳኔ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
የወለድ ክፍያን በተመለከተ በመጀመሪያ የስር ከሳሾች ስልጣን ለላላው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ወደ ግልግል ዳኞች ጉዲያቸውን እንዱያቀርቡ የተወሰነ መሆኑን ጉዲዩ ለግልግል ጉባኤ ቀርቦ ላይቶ መጋቢት 13 ቀን 2003 ዓ/ም በግልግል ዳኞች ጉባኤ ውሳኔ አግኝቶ የነበረ መሆኑንና የስር ከሳሾች መጥሪያ ለአመልካች በአግባቡ አለማድረሳቸውን በማረጋገጥ የግልግል ዳኞች መጋቢት 13 ቀን 2003 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዛገብ ቁጥር 01-82566 ሀምላ 11 ቀን 2004 ዓ/ም የሻረው መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ከሆነ አመልካችን በተመለከተ ወለድ መክፈል የሚገባው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ከሀምላ 11 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ የሚታሰብ ዖጠኝ ፏርሰንት ታስቦ መሆን ሲገባው የግልግል ጉባኤው ክሱ መደበኛ ፍርድ ቤት ከቀረበበት ቀን አንስቶ የሚታሰብ ዖጠኝ ፏርሰንት ወለድ አመልካች ለዋናው ባለ ዔዲ (ሰባተኛ ተጠሪ) ጋር በአንድናትና በነጠላ ይክፈል በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሀምላ 11 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ ህጋዊ ውጤት ያላገናዖበና በከፉል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
መቀጫውን በተመለከተ የስር ከሳሾችና የእቃው አቅራቢ ሀምላ 12 ቀን 1991 ዓ/ም በተዋዋለት ውል አንቀጽ 6 መሰረት ውለ ባለመፈፀሙ 0.07 መቀጫ በቀን ታስቦ የሚከፈለው እስከ ሰባ ቀናት ድረስ ብቻ እንደሆነ በግልፅ ተመልክቷል። ይህ ከሆነ አመልካች ዋናው ባለዔዲ በቅድመ ክፍያነት ወስድ በውለ አግባብ ያልፈጸመውን የብር 394,740 (ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ብር) መቀጫ በቀን 0.07% ታስቦ ለሰባ ቀናት ብቻ መቀጫ የመክፈል ግዳታ ይኖርበታል። ከዘህ ውጭ የግልግል ጉባኤ ዳኞች አመልካች 0.07 ፏርሰንት መቀጫ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ዔዲው ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ እንዱከፍል የሰጡት ውሳኔ ያውለን አንቀፅ 6 የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1889 እና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1924 ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገና በከፉል መሰረታዊ የህግ ስህታት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በገለፀናቸው ምክንያቶች የግልግል ዳኞች ጉባኤ አመልካችን በተመለከተ የሰጠውን ውሳኔ በከፉል በማሻሻል።
(ሀ) አመልካች ዋናው ባለዔዲ (ሰባተኛ ተጠሪ) በቅድመ ክፍያነት ወሰድ ዔቃውን በውለ መሰረት ባለመቅረቡ ለከሳሾች መመለስ የሚገባውን (ሶስት መቶ ዖጠና አረት ሺ ሰባት መቶ አርባ ብር) ከዋናው ባለዔዲ ጋር በአንድነትና በነጠላ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስነናል።
(ለ) አመልካች ከዋናው ባለዔዲ ጋር እንዱከፍል የተወሰነበትን ብር 394,740 (ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺ ሰባት መቶ አርባ ብር) የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሀምላ 11 ቀን 2004 ዓ/ም ውሳኔ ከሰጠበት ጊዚ ጀምሮ የሚታሰብ ዖጠኝ ፏርሰንት ወለድ በአንድነትና በነጠላ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
(ሐ) አመልካች ዋናው ባለዔዲ መመለስ ያለበትን ብር 394,740 /ሶስት መቶ ዖጠና አራት ሺ ሰባት መቶ አርባ ብር) በቀን 0.07% መቀጫ ታስቦ በሰባ ቀናት ተባዛቶ የመክፈል ግዳታ አለበት በማለት የግልግል ዳኞች የሰጡትን ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348 (1) መሰረት በማሻሻል ወስነናል።
ው ሳ ኔ1. የግልግል ጉባኤ ዳኞች ሀምላ 7 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ ቁጥር 01-38894 ጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
አመልካች በዘህ ፍርድ በተራ ቁጥር 12 ከ“ሀ“ እስከ ‛ሐ“ የተገለፀውን ገንዖብ ከዋናው ባለዔዲ /ሰባተኛ ተጠሪ/ ጋር በአንድናትና በነጠላ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ወስነናል።
የግልግል ጉባኤ ዳኞች ዋናው የፍርድ ባለዔዲ (ሰባተኛ ተጠሪ) በተመለከተ የሰጡት ውሳኔ በዘህ ሰበር ችልት የልተያ በመሆኑ አልተነካም።
በዘህ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ለያረሳቸው ይቻለ።
በዘህ ፍርድ ቤት
No topics extracted.