በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረገ ውል የፍቃድ ጉድለት ስለመኖሩ ማሳያ ሉሆኑ ከሚችለ ጉዲዮች ውስጥ ከተዋዋይ ወገኖች በአንደ ውልን ለማፍረስ የሚያስችል ጉዲይ መኖሩን ማሳየት ሲቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1696፣1710/2/ XX
No summary available.
ታህሳስ 25 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አሉ መሃመድ ተኽሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ደስታ ኪዲነ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አመቴ ኤርታቦ ጉዲዩ ተከታታይ ልጣንጋ ኤርትቦ ቀረቡ መዛገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ውል ክርክር ሲሆን የተጀመርው በደ/ብ/ብ/ሕ/ ሀድያ ዜን ሆሳዔና ከተማ ስተዲደር የመጀመርያ ደረጀ ፍ/ቤት ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።አመልካች በስር የክልል ጥቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰበር ሰሚ ችልት ተፈፀመ ያለትን የህግ ስህተት ተጣርቶ እንዱወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
የአሁኑ አመልካች የስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዖት ባጭሩ ከአሁኗ አመልካች ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ህግን ያልተከተለ ውል ለመዋዋል ህጋዊ ችልታ እንደላላቸው ዔድሜያቸው 70 አመት እንደሆነ እንዱሁም በልብ እና በነርቭ ህመም እንደሚሰቃዩ በመግለፅ ከአመልካች ጋር የተደረገው ውል መብት እና ጥቅማቸው የጎዲ በመሆኑ እንዱፈርስላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ባቀረቡት መልስም ተጠሪ ቤቱን ፈቅደው እንደሸጡት ልጅ አለመኖር ፣በበሽታ የተጠቁ መሆናቸው ውለ ለማፍረስ ምክንያት እንድማይሆን፣ቤቱ በእማኞች ፉት እንደገዘት አመልካች በገንዖባቸው እንዱጦሩዋቸው ተስማምተዋል የተባለው ውለ ለማፍረስ ምክንያት እንደማይሆን የስም ዛውውር በማዖጋጃ ቤት ተደርጎ ለተለያዩ ከፍለው ቤቱን ማልማት እንደጀመሩ በመግለፅ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ውድቅ እንዱሆን አመልክቷል።
የስር ፍ/ቤትም የግራቀኙ ክርክርና ማስረጃ አጠቃላይ ይዖት ከመረመረ በኃላ የተጠሪ ምስክሮች ልጅ ይሁን ባል የላላቸው ስለመሆኑ በአመልካች ቤቱ ሲያፈርሱ ቤቱም ዔቃውም አልሸጥኩም ሲለ እንደነበር በሽተኛ እንደሆኑም በአንድ እጃቸው የያዘት ነገር የሚረሱ እና ከሚያግዙቸው ሰው የሚጨቃጨቁ መሆናቸውን እንዲስረደ የአመልካች ምስክሮች በአንፃሩ ተጠሪ ቤት ለመሸጥ ይፈልጉ እንደነበር 1ኛ መከላከያ ምስክር በነባርነት እንደተገኙ የቤቱ ሽያጭም ዋጋ በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉ መግለፃቸውን ጠቅሶ በፍታብሓር ህጉ የዔድሜ ጣርያ ገደብ የላለ መሆኑ በእድሜ መግፊት/መጃጀት/ ውል የሚፈርስበት ምክንያት መኖሩን፣አመልካች ያደረጉት የተንኮል ተግባር ባይኖርም የተጠሪ ዔድሜ ከ90 አመት በላይ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1710 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት የተዋዋይን ዔድሜ መጃጀት እና በንግድ/ሽያጭ/ ግልፅ የሆነ የልምድ እርቀት የላለ ከሆነ ውለ ሉፈርስ እንደሚችል መደንገጉን ፍ/ቤቱ ተጠሪ በማስቀረብ እንደተመለከታቸው ዔድሜያቸው እጅግ የገፊ እና ከእድሜ መግፊት ጋር የተያያዖ የሚታይ ባህርያት ያላቸው መሆኑን በማረጋገጡ የሽያጭ ውለ ሉፈርስ እንደሚገባ አመልካች እና ተጠሪ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1815(1) መሰረት ወደነበሩበት እንዱመለሱ ሲል በፍርድ ሰጥቷል።
የአመልካች የሥር መጀመሪያ ደረጃ ውሳኔ በመቃወም ለዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የቤት ሽያጭ ውል በህጉ አግባብ እንደተከናወነ ፣ ተጠሪ ቤት ለመሸጥ ሲፈልጉ እንደነበረ በአመልካች ምስክሮች መረጋገጡን፣ ተጠሪ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ የፈለጉት የቤት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት እንደሆነ ፣ በተጠሪ ላይ ህመም መኖሩ፣ ልጅ አለመውለዲቸው ከውለ ጋር ተያያዣነት እንደላለው ተጠሪ አርጅቷል፣ ጃጅቷል የሚለ የሥር ፍ/ቤት ትችት አላስፈላጊ ናቸው በማለት ውሳኔውን ሽሮ የሽያጭ ውለ አይፈርስም ሲል ፍርድ ሰጥቷል።
የአሁኑ ተጠሪ በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ፍ/ቤትም በስር ፍ/ቤቶች የተደረገው አጠቃላይ የክርክር ይዖት ከመዖገበ በኃላ ተጠሪ ባላቸው አነስተኛ ማህበራዊ ተሳትፍ እና በማርጀታቸው ያወቁት የገበያ ዋጋ የማያውቁ መሆኑን ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በ 15/08/2007 ዓ/ም ተጠሪ አስቀርቦ ቃለ መጠይቅ ያደረግላቸው ሲሆን በተደረገላቸው ቃለመጠይቅም በእድመ መግፊታቸው ምክንያት የሚሰሩት ስራና የሚያደርሰው ውጤት ለመገንዖብ የማይችለ መሆኑን የከፍተኛ ፍ/ቤት የቤት ዋጋ በመጨመሩ ነው። የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ የቀረበው የሚለው ድምዲሜ ተገቢነት እንደላለው የአሁኑ ተጠሪ በተሸጠው ቤት ላይ አንድ ክፍል እንዱሰጣቸው፣ለማስታመም የሚለ ነገሮች ጧሪ እና ዖመድ እንደላላቸው የሚያሳይ መሆኑን ፣ተጠሪ በድርድር ቤቱን በአግባቡ ይሸጣል ተብል ሉወሰድ እንደማይቻል ቤቱ ለመሸጥ ረዲት እና ደጋፉ ያስፈልጋቸው እንደነበር በመግፅ የዜኑ ክፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ሽሮ የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ አፅንቷል።በአመልካች በኩል የሰበር አቤቱታ ያቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በጉዲዩ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስሕተት የለም በማለት የአመልካች አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም በስር ፍ/ቤቶች ተፈፅመ የተባለው ስህተት ለማሳረም ነው።
አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የሽያጭ ውለ የማይፈርስበት ምክንያት በማለት ዖርዛረው ያቀረቡ ሲሆን ሲጠቃለል የሽያጭ ውለ በህጉ አግባብ የተከናወነ በመሆኑ የሚፈርስበት አንዲችም በማስረጃ የተደገፈ ህጋዊ ምክንያት በላለበት ውል ሉፈርስ ይግባኝ ተብል የተሰጠውን ውሳኔ እንዱሽር እና የሀድያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ እንደሚፈልጉ የሽያጭ ውለ በእማኝ ፉት መከናወኑ የቤቱ ስመሀብትም በአመልካች ስም መዙወሩ በፍሬ ነገር ረገድ በተረጋገጠ ቤት ሁኔታ የተጠሪ እድሜ 97 ነው መባለ እና የልብ ህመም እንዱሁም የነርቭ ህመም አለብኝ በማለታቸው ብቻ ይህ ስለመሆኑ አግባብ ባለው ባለሞያ የተረጋገጠ ነገር ሳይኖር በፍ/ብ/ህ/ቁ 1810(2) ውለ ይፍረስ መባለ ተጠሪ ባለበት ይጣራ ዖንድ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብሎል። ተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጠበቃቸው በኩል በሰጡት መልስ የስር ፍ/ቤት ውለ ለማፍረስ በህመም ምክንያት አለማድረጉን ውለ እንዱፈርስ መነሻ የተደረገው በፍ/ህ/ቁ 1710(2) በመሆኑ አጣሪ ችልቱ የያዖው ጭብጥ ተገቢነት እንደላለው ቤቱ ለመሸጥ የተገኘው ፍቃድ ከእድሜ መግፊት ጋር የተያያዖ እንደሆነ የእድሜ ምርመራ በስር ፍ/ቤት አለመቅረቡ ቤቱ በአፈፃጸም ተረክበው እየኖሩበት እንደሚገኙ በመግለፅ ውሳኔውን እንዱፀና አመልክቷል። አመልካች አቤቱታውን የሚያጠነክር የመልስ መልስ አቀርቧል።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ይዖት ያለውነው።ይህ ችልትም ግራቀኙ በፅሁፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሰኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በመገናዖብ የስር የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ በሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመ መሆን አለመሆኑ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ክርክሩ በሂደት መገንዖብ የተቻለው አመልካች የቤት ሽያጭ ውለ በህጉ አግባብ የተደረገ በመሆኑ የሚፈርስበት አንዲች ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው የሽያጭ ውለ የተደረገው የፍቃድ ጉድለት ባለበት ሁኔታ በመሆኑ በስር የክልለ ጠ/ፍ/ቤት እንዱፈርስ የተሰጠው ውሳኔ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በፅናቱ የሚነቀፍ ነጥብ የለውም በማለት መከራከራቸውን ተመልክተናል። በስር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው የአሁኑ ተጠሪ እድሜያቸው ከ 90 አመት በላይ እንደሆነ እና ተጠሪን በአካል አስቀርበው ጉዲዩን ያጣሩት የሥር ወረዲ ፍ/ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተጠሪ በእድሜ መግፊታቸው ምክንያት የሚሰሩት ስራ የሚያደርሰው ስሜት ለመገንዖብ የማይችለ መሆናቸውን ነው። በልላ በኩል የሥር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ የተደረገው የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ በመነሻነት የሥር የወሰደው የተጠሪ ጤና ሁኔታ መልካም አለመሆን ሳይሆን በዔድሜ በመግፊታቸው ምክንያት ቤቱን በአግባቡ ተደራድረው ይሸጣለ ተብል ስለማይገመት ነው።
በመሰረቱ አንድ ውል በህግ ፉት የጸና ህጋዊ ተቀባይነት ወይም (ውጤት) እንዱኖረው ውል ለማቋቋም ከሚያስችለ መስፈርቶች አንደ የችልታ መስፈርት ሲሟላ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1678(ሀ) ስር ተመልክቷል። አንድ ውል በህጉ አግባብ ተፈፅመዋል ለማለት የሚቻለው ግራቀኙ ፍፁም በሆነ አኳሃን የተስማሙ እና ፍቃዲቸው የሰጡ መሆኑን ሲረጋገጥ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1680(1) ተደንግጓል ።በተዋዋይ ወገኖች የተደረገው ውል የፈቃድ ጉድለት ያለበት መሆኑ ሲረጋገጥ የተደረገውን ውል እንዱፈርስ ዲኝነት መጠየቅ እንደሚቻል በፍ/ብ/ህ/ቁ 1696 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የተደነገገ ጉዲይ ነው። የፍቃድ ጉድለት ከሚገለፅባቸው ነገሮች አንደ ከተዋዋይ ወገኖች በአንደ ውልን ለማፍረስ የሚያስችል ጉዲት መኖሩ ማሳየት ሲቻል ነው።
በፍ/ብ/ህ/ቁ 1710 ንኡስ አንቀፅ 2 እንደተመለከተው‛…የተጎጂው ፈቃድ የተገኘው ችግሩን የመንፈስ ቀላልነቱን መጃጀቱን በእድሜ መግፊቱን ወይም በንግድ ግልፅ የሆነ የልማድ እውቀት የላለው መሆኑን በመደገፍ እንደሆነ እና በህሉናም ግፍ መስል ሲታይ ውለን ማፍረስ ይቻላል ። በማለት የተደነገገው መሆኑ ተገንዛበናል። ከላይ እንደተመለከተው የስር መጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት ይሁን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ቸልት ተጠሪን በችልት በማስቀረብ ቃለ መጠይቅ ስለማድረጋቸው እና በተደረገው ማጣራትም ተጠሪ በእድሜ መግፊት /መጃጀት/ ምክንያት የህጋዊ ተግባራት ውጤት (juridical acts) በአግባቡ ማመዙዖን የማይችለ መሆኑን ማረጋገጫቸውን የሚያመለክት ነው።
በተዋዋይ ወገኖች የሚደረገው ውል ተወዲዲሪ መብትና ግዳታ የሚያቋቋም በሆነ ጊዚ የግራቀኙ መብት እና ግዳታ በተቻለ መጠን ፍትሐዊ ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ መሆኑ ከአጠቃላይ የውል መርሆዎች የምንገነዖበው ነው። በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ በእድሜ በመግፊት ወይም በመጃጀታቸው ሳቢያ ከአመልካች ጋር ያደረጉት ውል የገበያ ሁኔታበአግባቡ አጥንተው ተደራድረው የገበያ ዋጋውንምን ያህል እንደሆነ ለይተው ታዋውሎል ማለት የሚቻል አይደለም።
የአሁኑ ተጠሪ ዔድሜያቸው ከ90 አመት በላይ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። የስር ፍ/ቤት በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተደረገው ውል እንዱፈርስ የወሰኑት የተጠሪ የጤና ሁኔታ መሰረት በማድረግ ሳይሆን በእድሜው መግፊት ወይም(በመጃጀት) ምክንያት ማህበራዊ ግንኝነታቸው የተገደበ በንግድ ግልፅ የሆነ ልማድ ወይም እውቀት የላላቸው ስለመሆኑ በማረጋገጥ ነው። በህጉ አግባብ የተደረገ ውልች ህጋዊ ውጤት ሉኖራቸው እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ግልፅ ቢሆንም በፍቃድ ጉድለት የተገኘ ውል ግን የተዋዋይ ወገን ጥቅም በሚጎዲ መልኩ የሚጸናበት የህግ ምክንያት አይኖርም በተያዖው ጉዲይ የአሁኑ ተጠሪ በዔድሜ የገፈ ከመሆናቸው አንፃር አረጋውያን የህግ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የህብረተሰብ ክፍልች አንደ በመሆናቸው ከአመልካች ጋር ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ህጋዊ ውጤቱ በጥንቃቄ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው። የአሁኗ ተጠሪ ከአመልካች ጋር እኩል የመደራደር አቅም እና ችልታ የነበራቸው መሆኑን ባልተረጋገጠበት የተደረገው የሽያጭ ውል መብታቸው የነካ አይደለም የሚያስብል አይደለም። በዘህ ሁለ ምክንያት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዱሁም የክልለ የጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር ከ/ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር የሽያጭ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ ህጉ በአግባቡ ተፈፃሚ አድርገዋል ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀማቸውን የሚያሳይ ሆኖ አልተገኘም።በዘህም የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርገን ተከታዩን ወስነናል።
የደ/ብ/ብ/ህ/ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ በ29/08/2007 ዓ/ም በዋለው ችልት የሀድያ ዜን ከ/ፍ/ቤት በመ/ በ08/05/2007 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በመሻር የተሰጠውን ውሳኔ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በ28/09/2007 ዓ/ም የተሰጠው ትእዙዛ ፀንቷል።
የዘህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ የስር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
በዘህ ፍ/ቤት
No topics extracted.