የሉዛ ውል ሉቋረጥ ወይም ሉፈርስ ስለሚችልባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች የሉዛ አዋጅ ቁ. 272/94 አንቀጽ 15/1/
No summary available.
ታህሳስ 25 ቀን 2005 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጰውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- የጎንደር ከተማ አስተዲደር አገልግልት ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ወ/ሮአይናዱስ አሰጋህኝ ቀርባለች ተጠሪ፡- እስማኤል አህመድ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር-ጠበቃ አቶ ወንድሜነህ ዲኛው ቀረበ መዛገቡ ተመርምሮ ቀጥል ያለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው የጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በቀን 09/08/2006 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን ተጠሪ ይግባኝ ለጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ያቀረበውን አከራክሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር በመ/ በቀን 25/10/2006 ዓ/ም ሲወስን፣ የአሁን አመልካች ውሳኔውን ለማስለወጥ ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ ለሰበር ሰሚ ችልት የሚያስቀርብ ሆኖ አልተገኘም በማለት የሰበር አጣሪ በሰ/አ/መ/ ታህሳስ 8 ቀን 2007 ዓ/ም መዛገቡን በመዛጋቱ ነው።
የአሁን ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበረ። የክሱ ይዖትም፡- ተጠሪ በጎንደር ከተማ ቀበላ 06 ክልል የቤት ቁጥር 18፣19፣20 እና 22 ያለትን የመንግስት ቤቶች ተከራይቶ ለበርካታ ዓመታት ሲገለገል መቆየቱን፡ ቤቶቹን በመንግሥት ፖሉሲ መሰረት በሉዛ ገዛቶ ለማልማት እንደሚፈልግ ለተከሳሽ ጽ/ቤት ጥያቄ ማቅረቡን፣ ጥያቄውን ጽ/ቤቱ ለኪቢአድ አቅርቦ መ/ቤቱም ጥያቄያውን ተቀብል በባለሙያ ተገምቶ እንዱቀርብ ማድረጉን፣ግምቱ ለኪቢአድ እንዱከፈል ተከሳሽ ጽ/ቤት በቁጥር 1762/765/2001 በቀን 7/9/2001 ዓ/ም በጻፈለት ደብዲቤ መሰረት ብር 292.235.35 (ሁለት መቶ ዖጠና ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ከሰላሳ አምስት ሳንቲም) ገቢ አድረጎ ቅድመ ክፍያ ብር 89.614.80 (ሰማኒያ ዖጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አስራ አራት ብር ከሰማኒያ ሳንቲም) ለተከሳሽ /ለአመልካች/ ጽ/ቤት ገቢ ማድረጉን፣ የሉዛ ውል ፈርሞ 746.79 /ሰባት መቶ አርባ ስድስት ከሰባ ዖጠኝ/ ካ.ሜትር በካርታ ቁጥር 7339/02 በሆነው የሉዛ ይዜታ ቦታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መሰጠቱን፣ ወደ ግንባታ ለመግባት የግንባታ ፈቃድ ተጠይቆ ሉሰጠው ስላልቻለ ለሥራና ከተማ ልማት ቢሮ በቀረበው አቤቱታ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮው በሰጠው የተስተካከለ ሳይት ፕላንና ትዔዙዙዊ ደብዲቤ መሰረት በህግ አስገዲጅነት የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቶት ወደ ግንባታ እንዱገባ እንዱወሰን ሲል ጠይቋል።
አሁን አመልካች (የሥር ተከሳሽ) ክሱ ደርሶት በድርድር እንጨርሳለን ብል ከሄደ በኃላ በቀጠሮ ቀን ባለመቅረቡ መልስም ባለመስጠቱ ክርክሩ በላለበት ቀጥል እያለ በመቅረቡ በቀን 4/6/2003 ዓ/ም በዋለው ችልት ግራ ቀኙ የቃል ክርክር ማድረጋቸውን፣ አመልካች /ተከሳሽ/ በቃል ክርክሩ ወቅት ለከሳሽ /ለተጠሪ/ የተሰጠው ካርታ የተሰረዖ መሆኑን በቀን 18/5/2003 ዓ/ም በተጻፈ ዲብዲቤ ትዔዙዛ የተሰጠ መሆኑን፣ ለከሳሽ /ለተጠሪ/ በቀን 25/5/2003 ዓ/ም ካርታው የተሰረዖ መሆኑን የተገለጸለት ስለሆነ በተሰረዖ ካርታ መብት አለኝ ብል ክስ ሉመሰርት አይገባም በማለት በቀረበው መቃወሚያ መሰረት መቃወሚያው ተመርምሮ ብይን ተሰጥቶ ነበር።
የአሁን ተጠሪ /የሥር ከሳሽም/ በብይኑ ላይ ቅር በመሰኘት እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ተከራክሮ ስለጸናበት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ ችልቱም የግራ ቀኙን አከራክሮ በ
በቀን 22/01/2006 ዓ/ም በዋለው ችልት የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር የሥር ፍርድ ቤት ወደ ክርክሩ በመግባት ጉዲዩን ከሚከተለት ነጥቦች አንጻር አጣርቶ እንዱወስን ፡-
ከፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠው ትዔዙዛ መሰረት መዛገቡ ተንቀሳቅሶ የግራ ቀኙ በጉዲዩ ላይ ክርክራቸውን አድርገዋል። የጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የከሳሽ ከርታ የተሰረዖው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ፣ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎቻቸውን መርምሮ በውሳኔው ላይ የሚከተለትን ነጥቦችን ካነሳ በኃላ ፍርደን የደመደመ ሲሆን እነዘህም ነጥቦች፡-
በወቅቱ ሥራ ላይ የነበረው የሉዛ አዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 15 ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ የሚያስረዲው የሉዛ ይዜታ መቋረጥና የካሳ አከፊፈል በተመለከተ ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 6/94 አንቀጽ 4 (4) ደግሞ የከተማ ቦታን በሉዛ ስለ መፍቀድ ሲሆን፣ በማናቸውም አግባብ በሉዛ የሚሰጥ የከተማ ቦታ ለውል ገቢው ለማስረከብ ዛግጁ የሆነ መሆን ይኖርበታል ሲል ይደነግጋል።
እንዱሁም የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3180 ላይ የተቀመጠው ተዋዋይ ጥፊት ባይኖርበትም የአስተዲደር መ/ቤት ውለን ሉያፈርስ ይችላል። ይህም ውለ ለህዛባዊ አገልግልት የሚጠቅም ሳይሆን ሲቀር ወይም ለፍላጎቱ የማይስማማ ሆኖ ሲገኝ ነው በሚል አስቀምጧል።
በተጨማሪም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
በቀን 14/02/2000 ዓ/ም በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1195 መሰረት በአስተዲደር አካለ የተሰጠው የይዜታ ማረጋገጫ ማስረጃ ከተሰረዖ፣ የይዜታ ማረጋገጫ ማስረጃ ባለቤትነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይኖረው ለክርክር መነሻ በሆኑ ቤቶች ላይ መብት እንዲለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳያቀርብ ክስ ማቅረብ በህግ ተቀባይነት የለውም ሲል የሰጠው ውሳኔ ያስረዲል።
ስለዘህ እነዘህ ድንጋጌዎች ሲታዩ በሥር ከሳሽ /በአሁን ተጠሪ/ እና በሥር ተከሳሽ/ በአሁን አመልካች/ መካከል የተደረገው የሉዛ ውል የተሰረዖው በአግባቡ ነው ሲል ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ይግባኝ ለጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ የግራ ቀኙን አከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ በሉዛ ውለ መሰረት የመጠቀም መብት አለው፣ የሉዛ ውለ ሉሰረዛ አይገባም፣ ተጠሪ ዲኝነት የጠየቀውን የግንባታ ፍቃድ አመልካች ይስጥ በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች ይህን ውሳኔ ቅር በመሰኘት አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን የሰበር አጣሪ ቅሬታው ለሰበር ችልት የሚያስቀርብ ሆኖ አልተገኘም ሲል መዛገቡን ዖግቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ የሰጠውን ትዔዙዛ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 13/05/2007 ዓ/ም የተጻፈ ዛርዛር ቅሬታ ነጥቦችን አቅርቧል።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ሐምል 24 ቀን 2007 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ እንደተመዖገው ሲሆን ጉዲዩን ከሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ፣ በዘህ ችልት ከተደረገው ክርክር እንዱሁም አጣሪው ያስቀርባል ሲል ከያዖው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነውም ይህ ጉዲይ ቀደም ሲል እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ቀርቦ የነበረና ድጋሚ ታይቶና ተጣርቶ እንዱወሰን የሚጣሩ ነጥቦች ተይዖው የተመለሰ ነው። ጉዲዩ ወደ ሥር ፍርድ ቤት ከተመለሰ በኃላ የግራ ቀኙ ክርክር ማድረጋቸውን፣ የጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኙ የቀረቡለትን የሰነድ ማስረጃዎችን የተመለከተ መሆኑን፤ የተነሱትን ፍሬ ነገሮችን ከሉዛ አዋጅ ቁጥር 272/94፣ ከደንብ ቁጥር 6/94፣ አግባብነት ካለው የፍትሐብሕር ህግ ድንጋጌ እና በግራ ቀኙ መካከል ከተደረገው የሉዛ ውል አንጻር ተመልክቶ ውሳኔ የሰጠ መሆኑን የውሳኔ ግልባጭ ያስረዲል። ይህ ውሳኔ ግን የሉዛ አዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 15/1/ ድንጋጌን ያገናዖበ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ሉጤን ይገባል።
በቀድሞው የሉዛ አዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 15/1/ ሥር የሉዛ ውል ሉቋረጥ እና ሉፈርስ የሚችልባቸው ምክንያቶች በሉዛ የተያዖው ቦታ በተሰጠው ጊዚ ውስጥ ጥቅም ላይ ሳያውለው ሲቀር፣ ቦታው ለህዛብ ጥቅም ተብል ለላላ አገልግልት ሲፈለግ እና የሉዛ ዖመኑ ሲያልቅ እንደሆነ በግልጽ ተደንግጓል። በዘህ ድንጋጌ ሥር የሉዛ ውል እንዱፈርስ ለማድረግ በድንጋጌው ሥር ከተቀመጡት ከሶስቱ መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ በውል ተቀባዩ በኩል ሳይፈጸም የቀረ ስለመኖሩ ውለ እንዱፈርስ የሚጠይቀው ወገን የማስረዲት ሸክም ይኖርበታል። በተያዖው ጉዲይ የአሁን አመልካች የሉዛ ውለ ተሰርዝል ከማለት ውጭ በሉዛ አዋጁ አንቀጽ 15/1/ ከተደነገጉት ውስጥ በተጠሪ በኩል ሉፈጸሙ የሚገባቸው ነገሮች ሳይፈጸሙ ስለመቅረታቸው ወይም ክርክር የተነሳበት ቦታ ለህዛብ ጥቅም ስለመፈለጉ በፍጹም አላስረዲም። የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት በዘህ ህግ አግባብ መሰረት በአግባቡ ሳይመረምር የይዜታ ማረጋገጫ ካርታው መሰረዘ እና ግንባታ ፈቃድ መከልከለ ተገቢ ነው በሚል ውሳኔ መስጠቱ ተገቢነት የለውም።
አመልካችም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ሲል የሚከራከረው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። እንዱሁም አመልካች የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በፍትሐብሕር ህግ ስለ አስተዲደር መ/ቤት ውልች የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን በአግባቡ ሳይመለከት የሉዛ አዋጁን ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ አግባብነት የለውም በማለት ለዘህ ችልት ያቀረበው ቅሬታ ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም። ምክንያቱም የሉዛ አዋጅ ቁጥር 272/94 እየታየ ላለው ጉዲይ እጅጉን አግባብነት ያለውና ልዩ ህግ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህን አዋጅ አንቀጽ 15/1 እና ደንቡን አያይዜ ከመተርጎሙም ባሻገር የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3181 የተረጎመበትም መንገድ ሲታይ የሚነቀፍ አይደለም።
በአጠቃላይ የጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ከላቸው ህጎች አንጻር ተመልክቶ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር የሉዛ ውለ ሉፈርስ አይገባም፣ የተጠሪ መብት ሉጠበቅ ይገባል፣አመልካችም የግንባታ ፍቃድ ለተጠሪ እንዱሰጥ ሲል የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ህጋዊ ምክንያት ያለው ሆኖ አልተገኘም። የክልለ ሰበር ሰሚ አጣሪም የአመልካችን የሰበር አቤቱታውን መሰረዘ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ትዔዙዛ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። ሲጠቃለልም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ጎንደር ከተማ አስተዲደር የከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 25/10/2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/አ/መ/ቁ. 42200 ታህሳስ 8 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 15/1/ ሥር የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን ተጠሪ ስለመጣሱ ባለማሰረዲቱ እንዱሁም ክርክር የተነሳበት ቦታ ለህዛብ ጥቅም ተፈልጎ ስለመሆኑ ባለማረጋገጡ ምክንያት የሉዛ ውለ ሉፈርስ አይገባም ብለናል።
አመልካች ተጠሪ ዲኝነት የጠየቀውን የግንባታ ፍቃድ የጎንደር ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት ላሰጥ ይገባል ብለናል።
የዘህን ችልት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይላክ፡፤
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.