በጽሁፍ በተደረገ ውል አንደኛው ወገን ውለን ለማሻሻል ሲፈለግ ዋናው ውል በፅሁፍ እስከተደረገ ድረስ ማሻሻያውም በዙው አግባብ መሆን ያለበት ሥለመሆኑ በጽሁፍ በተደረገ ውል አንደኛው ወገን የውል ማሻሻያ ጽሁፍ ለላላኛው ወገን ሲላክልት ላላኛው ወገን ሉቀበለው እንደሚችል ሲደነግግ ውለን ለመቀበለ ግን የተለየ ስርዓት ካለማስቀመጡ በተጨማሪ በምክንያታዊ ጊዚ ውለን ያለመቀበለን እላ ኢንተርናሽናል ቢዛነስ ሀ/የተ/የግ/ማህበር እና ፊርም አፍሪካ የኢትዮ ፕሮግራም XIX ውለን እንደተቀበለ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1722፣2625
No summary available.
ታህሳስ 5 ቀን2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች:- አላ ኢንተርናሺናል ቢዛነስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርጠበቃ አቶ ደሱ ጨመዲ ቀረቡ ተጠሪ:- ፊርም አፍሪካ የኢትዮጽያ ፕሮግራም - ጠበቃ አቶ ሀይለ ቡራዩ ቀረበ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ።
ጉዲዩ ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ ሲሆን በአሁን ተጠሪ የሥርተከሳሽ ላይ ባቀረቡት ክስ ከሳሽ በደቡብ ኦሞ ዜን ሀመር ወረዲ ኩሬ ለመገንባት ተከሳሽ ደግሞ ለሥራው ቫትን ጨምሮ ብር 1‚850‚798.50 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሺህ ሰባት መቶ ዖጠና ስምንት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ለመክፈል ተስማምተን እኔ በውለ መሰረት ሰርቻለሁ ከጉድጓደየወጣውንም አፈር በውለ ላይ በተቀመጠው 30 ሜትር ርቀት ላይ 140 ሜትር በመጨመር 170 ሜትር ርቀት አጓጉዢ ደፍቻለሁ ተከሳሽ ግን በውለ መሰረት መክፈል ያለበትን ገንዖብና ተጨማሪ የአፈር ማጓጓዛ ስራ የተሰራበትን ገንዖብ ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም በመሆኑም ተከሳሽለውለ ማስፈጸሚያ በቅድሚያ የተከፈለው ቀብድ ብር 555‚239.35 /አምስት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዖጠኝ ብር ከሰላሳ አምስት ሳንቲም/ ተቀንሶ ቀሪውን ብር 1‚295‚558.95 /አንድ ሚሉዮን ሁለት መቶ ዖጠና አምስት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ከዖጠና አምስት ሳንቲም/ መክፈል ከነበረበት ጊዚ ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፈልና ተጨማሪ የአፈር ማጓጓዛና መድፊት ስራ ለሰራሁበት ቫትን ጨምሮ ብር 994‚450.00 /ዖጠኝ መቶ ዖጠና አራት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር/በድምሩ ብር 2‚290‚308.95 /ሁለት ሚሉዮን ሁለት መቶ ዖጠና ሺህ ሶስት መቶ ስምንት ብር ከዖጠናአምስት ሳንቲም/እንዱከፍለኝና ወጪና ኪሳራም የመጠየቅ መብቴ ይጠበቅልኝ የሚል ዲኝነት ጠይቀዋል ።
ተከሳሽም በወኪለ አማካኝነት በሰጠው መልስ ከከሳሽ ጋር የተባለውን ውል ፈፅመናል በውለም መሰረት ከሣሽከተከሳሽ በሚሰጠው የስራ ዛርዛር መሰረት የኩሬውን ጉድጎድ በ2.29 ሜትር ጥልቀት ለመቆፈር እና የወጣውንም አፈር በ30 ሜትር ርቀት አጓጉዜ ለመድፊት ይህንንም ሥራ በ20 ቀን ውስጥ ለማጠናቀቅ ተከሳሽ ደግሞ ብር 1‚850‚798.50 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሺህ ሰባት መቶ ዖጠና ስምንት ብር ከሃምሳ ሳንቲም / ለመክፈል ተስማምተናል ።ከሳሽግን የቆፈረው ኩሬ 2.20 ሜትር ሳይሆን 1.92 ሜትር ነው ስራውንም አጠናቆ ማረጋገጫ አቅርቦ አላስረከበም ከሳይት እንዱወጣም በተከሳሽ ትዔዙዛ አልተሰጠውም ከቁፊሮው የሚወጣውንም አፈር ከሳሽ እንዱደፊ የተስማማነው በ30 ሜትር ውስጥ ብቻ ነው ። ከስምምነታችን ውጪ ለተሰራ ስራ ልከፍል አይገባም ካሳሽ ሥራውን በውለ ላይ ከተቀመጠው በላይ በማዖግየቱ የሚጣልበት የውል ቅጣት ተቀናሽ መሆን አለበት በአጠቃላይ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብቴ ይጠበቅልኝ የሚል ነው።
ፍ/ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የጊዚ መራዖሙን ከሳሽ በአካባቢው የአየር ንብረት ችግር ምክንያት የሥራው መጠናቀቂያ ጊዚ ለ15 ቀን እንዱራዖም ህዲር 4 /2005 ዓ.ም ለተከሳሽ የፃፈው ደብዲቤ ቀርቧል።ሆኖም ግን ተከሳሽ መልስ ያልሰጠ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1684 እና 1722 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ለላላው ወገን በጽሁፍ የሚያቀርበው የውል ማሻሻያ ሀሳብ ላላኛው ወገን ምክንያታዊ በሆነጊዚ ውስጥ መልስ ያልሰጠ ከሆነ በዛምታ ውለን መቀበል መሆኑ መረዲት የሚቻል በመሆኑ ከሳሽ በፅሁፍ ላቀረበው የውል ማሻሻያ ተከሳሽ ዛም ማለቱ ውለ በ15 ቀን መራዖሙን የሚያስከትል በመሆኑ ተከሳሽ የጠየቀውን ሥራው ለዖገየበት የሚከፈል ቅጣት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ነገር ግን ውለ የቁፊሮ ጉድጎድ ጥልቀት 2.20 ሜትር ሲሆን ከሳሽ የቆፈረው 1.92 ሜትር በመሆኑ 0.28 ሜትር ጉድለት ስላለ የዘህ ጉድለት የገንዖብ መጠን 111‚840.90 /አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ስምንት መቶ አርባ ብር ከዖጠና ሳንቲም/ እና የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ ብር 555‚239.35 /አምስት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዖጠኝ ከሰላሳ አምስት ሳንቲም/ ተቀንሶ ቀሪው ብር1‚054‚069.45 /አንድ ሚሉዮን ሃምሳ አራት ሺህ ስልሳ ዖጠኝ ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም/ቫትን ጨምሮ ተከሳሽለተከሳሽ ይክፈለው በማለት ሲወስን ወለደን በተመለከተ ለውለ በአግባቡ ላለመፈፀምየተከሳሽ በአግባቡ የውል ግዳታውን ያለመወጣት አስተዋፅኦ አድርጓል በማለት የወለድ ይከፈለኝ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ሲወስን የተጨማሪ ስራን ማለትም በግራ ቀኙ ውል ላይ የተቀመጠውን አፈሩን በ30 ሜትር ርቀት አጓጉዜ ለመድፊት ሲሆን ከሳሽ በ170 ሜትር ርቀት ነው አጓጉዢ የደፊሁት ለዘህም የውል ማሻሻያ በፅሁፍ አድርጌ ለተከሳሽ ሰጥቻለሁ ሲል ተከሳሽም ይኸው የውል ማሻሻያ በፅሁፍ የደረሰው ለመሆኑ ካለመካደም በተጨማሪ በ23/5/2005 ዓ.ም ከፃፈው ደብዲቤ መረዲት ተችሎል።በተጨማሪም ይህንን የውል ማሻሻያ ሀሳብ አልቀበልም በማለት መቃወሙን ተከሳሽ አልገለፀም ወይም አላስረዲም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1684,1722,2625 መሰረት የማሻሻያውን ውልተከሳሽ ሳይቃወም ዛም ማለቱ ውለን መቀበለን ያሳያል።ዋጋውን በተመለከተ በዋናው ውል ከነበረው ለሜትር ኪዩብ 25 ብር ወደ 75 ብር ከፍ ብሎል ቢልም በውል ማሻሻያው ላይ አልተገለፀም በማለት ውለ ላይ በተቀመጠው ዋጋ መሰረት የተጨማሪው 140 ሜትር ርቀት ብር 994‚450.00 /ዖጠኝ መቶ ዖጠና አራት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር/ ተከሳሽለከሳሽ ሉከፍል ይገባል በማለት በአጠቃላይዋናውን ገንዖብ ብር1‚054‚069.45 /አንድ ሚሉዮን ሃምሳ አራት ሺህ ስልሳ ዖጠኝ ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም/ ፍርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ህጋዊ ወለድጋር ተከሳሽለከሳሽእንዱከፍል ሲወሰን የተጨማሪ ስራን በተመለከተ ብር994‚450.00 /ዖጠኝ መቶ ዖጠና አራት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር/ ቫትን ጨምሮ ተከሳሽለከሳሽ ይክፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታውን ለፋደራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን የፋደራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቅሬታው መልስ ሰጪን ያስጠራል በማለት መልስ ሰጪን አስጠርቶ ካከራከረ በኋላ ዋናው ውል ላይ የተጠየቀው ዲኝነት ላይ በተሰጠው ውሳኔ የቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ በማፅናት ሲወስን፤ ተሰራ የተባለውን ተጨማሪ ስራን በተመለከተ አፈሩን ወስድ ለመድፊት ግራ ቀኙ በ30 ሜትር የተስማሙ ሲሆን ይግባኝ ባይ ይህ ውል ቢኖርም በ30 ሜትር ርቀት ለመድፊት ቦታው ምቹ ባለመሆኑ በ170 ሜትር ርቀት ላይ ደፍቻለሁ ይህንንም ለፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አሳውቄበዘሁ እንድቀጥል በተሰጠኝ ትእዙዛመሰረት ነው በማለትየገለፀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው ውል የፅሁፍ እስከሆነ ድረስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1722 መሰረት የውል ማሻሻያም ሲደረግ በፅሁፍ መደረግ ነበረበት በጽሁፍ ባለመደረጉ ምክንያት ለማሻሻያ ውል የተጠየቀው የዲኝነት ገንዖብ መጠን ሉከፈል የሚገባ አይደለም በማለት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ወስኗል።
በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን የሰበር አቤቱታ አቅራቢ ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታውን ያቀረበ ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልቱም ቅሬታውን ከስር መዛገብ ጋር መርምሮ ተጨማሪውን ሥራ በተመለከተ በግራቀኙ መሀከል የተደረገ ውል የለም በሚል መነሻነት የተጨማሪ ስራ ክፍያ ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍል አይገባም በማለት የተወሰነበትን አግባብነት ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ያስችል ዖንድ ተጠሪ ቀርቦ መልስ ይስጥበት ብሎል።
ተጠሪም የሰበር አጣሪው ችልት ከያዖው ጭብጥ አንፃር የሰጠው መልስ በውለ ከተመለከተው አፈር መድፉያ ቦታ ማለትም 30 ሜትር ወደ 170 ሜትር በመጨመር መደፊቱ ከተሰጠው የስራ ትእዙዛ ውጪ ነው።በመሆኑም ተጠሪ ተጠያቂ የሚሆንበት ምክንያት የለም ። በተጨማሪም ከውል ውጪ የሆነ ግዳታን ለማካተት አንደኛው ወገን ደብዲቤ መፃፍ ብቻውን ላላኛው ወገን ተዋዋይ እንደተስማማ አያስቆጥረውም በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1682 ሥር ተደንግጓል በመሆኑም የተጨማሪ ስራ ክፍያን አስመልክቶ የሥር ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ይፅናልኝ ብሎል።
እኛም የቀረበውን የሰበር አቤቱታ በሰበር ችልት ከተያዖው ጭብጥ አንፃር መርምረነዋል።እንደመረመርነውም ለሰበር ከቀረበው አቤቱታ ውስጥ የተጨማሪ ስራ ክፍያ ሉከፈል ይገባል በማለት በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ በሥር ጠቅላይ ፍ/ቤት መሻሩ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በተመለከተ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ሉከፍል ይገባል በማለት የወሰነው የማሻሻያው ውል በፅሁፍ ተደርጎ ለተጠሪ እንዱደርስ መደረጉንና ተጠሪም ሳይቃወም ዛም ማለቱን ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተረጋግጧል በሚልና በፅሁፍ በተደረገ ውል ላይ አንደኛው ወገን ውለን ማሻሻል ሲያስፈልገው በፅሁፍ ላላኛው ወገን ሉያሳውቀው እንደሚገባ ላላኛው ወገን የማይስማማበት ከሆነ ተቃውሞውን መግለፅ አለበት ነገር ግን በበቂ ምክንያታዊ ጊዚ የማሻሻያ ውል በፅሁፍ የደረሰው ተዋዋይ መልስ ሳይሰጥ ዛም ቢል በፍ/ብ/ሕ/ቁ1684፣1722 እና 2625ን በመጥቀስ የማሻሻያ ውልን እንደተቀበለ ይቆጠራል በሚል ሲሆን የስር ጠ/ፍ/ቤት ይህንን ውሳኔ የሻረው በግራ ቀኙ መሀከል የተፈፀመው የመጀመሪያ ውል በፅሁፍ እስከተደረገ ጊዚ ድረስ ማሻሻያው ውልም በፅሁፍ መደረግ እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1722 ሥር ተደንግጎ እያለአመልካች ተጨማሪ ስራ ሰርቻለሁ ያለው በፕሮጀክቱ ስራ አሰኪያጅ በተሰጠኝ ትእዙዛ ነው ማለቱ የስራ ትእዙዜቹ በፅሁፍ ባልተሰጠበት ሁኔታ የተሻሻለ ውል አለ ለማለትአይቻልም በሚል ነው።
በመሰረቱ በፅሁፍ የተደረጉ ውልች አንደኛው ወገን ውለን ለማሻሻል ሲፈልግ ዋናው ውል በተፈፀመበት አይነት ማለትም ዋናው ውል በፅሁፍ እስከተደረገ ድረስ በፅሁፍ ላደረግ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1722 ሥር ተደንግጎ ይገኛል ወደተያዖው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የተጨማሪ ስራ ውልን ለማድረግ የፅሁፍ ውል ለተጠሪ መስጠቱን ተጠሪም ያምናል።ነገር ግን የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የተጨማሪ ስራ ትእዙዛ ለመስጠት ስልጣን የለውም ከሚለው ስንነሳ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2625 ሥር እንደተመለከተው በፅሁፍ በተደረገ ውል ላይ አንደኛው ወገን የውል ማሻሻያ ፅሁፍ ለላላኛው ወገን ሲልክለት ላላኛው ወገን ሉቀበለው እንደሚችል ሲደነግግ ውለን ለመቀበለ ግን የተለየ ስርአት ካለማስቀመጡ በተጨማሪ በምክንያታዊ ጊዚ ውለን ያለመቀበለን ካላስታወቀ ውለን እንደተቀበለ እንደሚቆጠር ደንግጓል።በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ ፅ/ቤት በፅሁፍ የተደረገው ውል ማሻሻያ ሲደርሰው በቂ በተባለ ጊዚ አይሆንም የሚልበትን ምክንያት መግለፅ ይጠበቅበታል ነገር ግን በቂ በሆነ ጊዚ ውል ሉሻሻል የማይችልበትን ምክንያት ካለመግለፁም በተጨማሪ በፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በተሻሻለው ውል መሰረት ይፈፅም በማለት የቃል ትዔዙዛ መስጠቱን ተጠሪ ፅ/ቤት ከማመኑም በተጨማሪ ተጨማሪ ስራው አልተሰራም በማለት ያቀረበው ክርክር የለም።ፕሮጀክት ስራ አስኪያጁ ትእዙዛ መስጠት አይችልም ካለ የማሻሻያው ውል በደረሰው ጊዚ ተቃውሞ ማቅረብ ሲገባው አላቀረበም።ፕሮጀክት ስራ አስኪያጁ ተጨማሪ ትእዙዛ ባይሰጥም እንኳን የተጠሪ የፅሁፍ ማሻሻያ ውል ሲደርሰው ዛም ማለት ተጨማሪ ውለን እንደተቀበለው ያስቆጥራል። በአመልካች በኩል ሲታይ ደግሞ ላቀረበው ተጨማሪ ማሻሻያ ውል የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ እንዱቀጥል ካዖዖው ውለ ለመሻሻለ ምንም ተጨማሪ ማረጋገጫ አስፈላጊ አይሆንም ከዘህ ሁለ መነሻ ሲደረግ የተሻሻለ ውል አለ በተሻሻለው ውል መሰረት አመልካች ሉሰራ ይችላልና ስራውን ሰርቶታል መስራቱም ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
አመልካች ተጨማሪ ስራውን መስራቱ እስከተረጋገጠና የሰራውም በህግ አግባብ እስከሆነ ድረስ ለሰራው ስራ ክፍያ የማይፈጸምበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ከዘህ ሁለ ስንነሳ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጨማሪ ስራውን ክፍያ ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍል ይገባል በማለት ሲወስን የስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጨማሪ ስራ ክፍያን ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍል አይገባም በማለት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ ቁ.109882 በቀን 26/02/2008 ዓ.ም አመልካች ለተጠሪለተጨማሪስራ ክፍያ ብር 994.750.00(ዖጠኝ መቶ ዖጠና አራት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) ሉከፍል ይገባልበማለት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በቀን 28/4/2007 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ /ሥ/ሥ/ህግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ቁ.130572 በቀን 28/4/2007 ዓ.ም አመልካች ለተጠሪብር 994.750.00(ዖጠኝ መቶ ዖጠና አራት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር)ለተጨማሪ ስራ ሉከፍል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ /ሥ/ሥ/ህግ ቁ.
348(1) መሰረት ጸንቷል።
348(1) መሰረት ጸንቷል።
ት እ ዙ ዛ የውሳኔው ግልባጭ በየደረጃው ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ በውሳኔ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይተላለፍ።
No topics extracted.