አንድ ግብር ከፊይ የሂሳብ መዛገብ እና ሰነድ ካልያዖ ወይም በማናቸውም ምክንያት የሂሳብ መዛገቡን እና ሰነደን የግብር አስገቢው ባለስልጣን ያልተቀበለው እንደሆነ ወይም ግብር ከፊዩ በሕጉ በተወሰነው ጊዚ ውስጥ ገቢውን ያላስታወቀ እንደሆነ ግብር አስገቢው ባለስልጣን የግብሩን ልክ በግምት ሉወስን አቶ ተክላ ፈረጃ ጋዱሳ እና የኢ/ያ ገ/ጉ/ ባለስልጣን የመርካቶ ቁ.1 XVIII ስለመሆኑ፡የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 69
No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ተክላ ፈረጃ ጋዱሳ ጠበቃ ሳሙኤል ኤፍሬም ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢ/ያ ገ/ ጉ/ ባለስልጣን የመርካቶ ቁ.1መካከለኛ ግብር ከፊዬች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አልቀረቡም መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የንግድ ሥራ ግብር ክፍያን በሚመለከት የአሁን አመልካች ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ያቀረቡትን ጥያቄ የሚመለከት ነው።አመልካች ለግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ያቀረቡት ቅሬታ ይዖት በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመጋዖን ማከራየት ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆኑን፤በ2006 ዓ/ም ግብር ዖመን ገቢውን በመዛገብ በመያዛ እና በማሳወቅ የሂሳብ መዛገብ አቅርቤ እያለ ሳያጣራ ከግብር/ ታክስ አወሳሰን ስርአት ውጪ ከተያዖብህ ያነሰ አመታዊ ሽያጭ ነው ያሳየኸው በሚል ብቻ ውድቅ በማድረግ የወሰነበትን የቀን ገቢ ግምቱን ሳይገልፅልኝ ታክሱን በግምት በወሰንኩት ልትከፍል ይገባል በማለት ወስኗል ። ገቢየን የማሰበስበው በተጠሪ በታወቀና ራሱ አዜ ባስገዙኝ በሂሳብ መመዛገብያ ማሽን ሆኖ ባለበት እንዱሁም መብራት ሲጠፊ እና በተለያየ ምክንያት የማይሰራ ቢሆን እንኳን ለተጠሪ በማሳወቅ ራሱ በፈቀደልኝና ባወቀው ደረሰኝ የሰበሰብኩትን ገቢየን መዛገብ በመያዛ አሳውቄ እያለሁ ይህን ሁለ እወነታ በማለፍ ድርጅቱን በግንባር አይቶ የገመተበትን ጊዚ ሳይገልፅ የወሰነው ከአወሳሰን ስርአት ውጭ ነው ። በልላ በኩል የቀን ገቢያቸው ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) መሆኑ አምነው ፈርመዋል በማለት የገለፀው እኔ በወቅቱ በቦታው አልነበርኩም የነበረው ልጄ አስፈራርተውና ተቆጥተው ያስፈረሙት መሆኑ ገልፆልኛል ። ስለሆነም የምስራበት መጋዖን እጅግ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ጉባኤው በአካል የስራ እንቅስቃሴውን ተመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው ተጠሪው አላግባብ የጠየቃቸውን ክፍያ ጉባኤው ውድቅ እንዱያደርግላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪው ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው በሰጠው መልስ የአመልካች ለ2006 ዓ/ም የግብር ዖመን ያቀረቡትን የሂሳብ መዛገብ መርካቶ መሃል ካላቸው መጋዖን ማከራየት ስራ ጋር ሲነፃፀር በጣም ዛቅተኛና ሉቀራረብ የማይችል ከመሆኑም በላይ ግብር ከፊዩ እራሳቸው ከሰጡት የቀን ገቢ መረጃ እንኳን በጣም የራቀ መረጃ ስላቀረቡ ተጠሪ በህግ መሰረት እና ባለው መረጃ መሰረት በማድረግ መወሰኑ ተገቢ ነው ። የአመልካች መጋዖን ያለበት የስራ ቦታ ከፍተኛ የገበያ ቦታ መሃል መርካቶ ኬኔዱ ህንፃ አጠገብ ሰፉ እቃ የማስቀመጥ አገልግልት ፈላጊና ተጠቃሚ ያለበት ላይ በመሆኑ የቦታው ስፊትም 65 ካ.ሜ.የሆነ ትንሽ ሱቅ ተከይተው የሚሰሩ ባለሱቆች ሱቆቻቸውን ለማሳያ ብቻ እየተገለገለ እቃዎቻቸውን በማስቀመጥ የሚጠቀሙበት ነው እራሳቸው ጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ/ም ለቀን ገቢ ገማቾች በሰጡት መረጃ ላይ በቀን 1,000 (አንድ ሺህ ብር) አገኛለሁ ያለትን በመውሰድ ቢታይ እንኳን የአመት ሽያጭ ብር 365,000 (ሶስት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) ነው። ምንም ገቢ አላገኘሁም ቢለ እንኳን ያመኑዋቸው አራት ወራት ቢሰላ የሚመጣው ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሆኖ ሳለ ባቀረቡት ሂሳብ መዛገብ ላይ አገኘሁ ያለት ሽያጭ ብር 89,100 (ሰማንያ ዖጠኝ ሺህ አንድ መቶ) ሲሆን በዘህም በቀን 244.11(ሁለት መቶ አርባ አራት ብር ከአስራ አንድ ሳንቲም) በመሆኑ የአመልካች የሂሳብ መዛገብ እምነት ስላጣንበት ውድቅ አድርገነዋል ። የቀን ገቢ ግምቱ የተከናወነው በድብቅ ሳይሆን ገማች ኮሚቴ ድርጅታቸው ድረስ በመሄድ ይግባኝ ባይ በሰጡት መረጃ መሰረት በማድረግ የንግድ ቤቱ አያያዛና የመጋዖኑ ስፊት፣እቃ የመያዛ አቅም ና የአካባቢውን ሁኔታ በዘሁ ተግባር የተሰማሩ ብዘ ነጋዳዎች ውሱን መሆናቸው በማየጥ አመልካች በሰጡት በቀን ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ላይ የተወሰነ በመጨመር ብር 1,400 (አንድ ሺህ አራት መቶ ብር) በማድረግ የተገመተ መሆኑን በመጥቀስ አቤቱታቸው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ አመልካች ከቀን ገቢ ግምት ግማሽ በታች በሆነ መልኩ በሂሳብ መዛገብ ያቀረቡትና ያሳወቁት ገቢ በበቂ እና አሳማኝ ምክንያቶች የተደገፈ ሆኖ ስላላገኘነው መልስ ሰጪ በ2006 ዓ/ም ግብር ዖመን የቀን ገቢ ግምት ብር 1,400 (አንድ ሺህ አራት መቶ) ብር በመያዛ ግብርና ታክስ የወሰነበት አግባብ የሚነቀፍ አይደለም በማለት አፅንቶታል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግራቀኙን አከራክሮ ውሳኔውን አጽንቶታል።በመቀጠል አመልካች ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታ ያቀረቡ ቢሆንም መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጓል።የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡-አመልካች የ2005 ዓ/ም የግብር ዖመን በተመሳሳይ ባሰራሁት የሂሳብ መዛገብ በባለሞያ ሂሳብ መዛገብ ተሰርቶ የቀረበውን ይህንኑ በህጉ በተጣለበት ግዳታ ሳይመረምር የ2006 ዓ/ም የግብር ዖመን በተመለከተ በባለሞያ ሂሳብ መዛገብ ተሰርቶ የቀረበውን ተጠሪው መስሪያ ቤት በሂሳብ መዛገብ የቀረበውን አመታዊ ሽያጭ ከቀን ገቢ ግምት ያነሰ ነው፣ በሚል ምክንያት አልቀበልም ብል በቀን ገቢ ግምት መወሰኑ ከአዋጂ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 69 እና ከ64 ጀምሮ ካለት ድንጋጌዎች የወጣ በሆነ ሁኔታ በራሱ ግምት እንድከፍል መወሰኑ ያለአግባብ ነው። በመሆኑም ለግብር ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ያቀረብኩት አቤቱታ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዘህ ችልት መታየት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ግራ ቀኙ በጽሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው ። ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዖብ መርምሮታል ። በዘህ ችልት ምላሽ ማግኘት የሚገባው ነጥብም ተጠሪው ባቀረበው ግምት መሰረት አመልካች እንዱከፍለ የተወሰነው የግብር መጠን በአግባቡ ነው ?ወይስ አይደለም?
የሚለው ጭብጥ ሆኖ አግኝተነዋል ። የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 69 ግብር ከፊዩ የሂሳብ መዛገብ እና ሰነድ ካልያዖ ወይም በማናቸውም ምክንያት የሂሳብ መዛገቡን እና ሰነደን የግብር አስገቢው ባለስልጣን ያልተቀበለው እንደሆነ ወይም ግብር ከፊዩ በሕጉ በተወሰነው ጊዚ ውስጥ ገቢውን ያላስታወቀ እንደሆነ ግብር አስገቢው ባለስልጣን የግብሩን ልክ በግምት ሉወስን እንደሚችል ይደነግጋል።በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ በአመልካች ላይ የቀን ገቢ ግምትን መሰረት የግብር ማስታወቂያ የሰጣቸው አመልካች የ2006 ዓ/ም የግብር ዖመን በተመለከተ በባለሞያ ሂሳብ መዛገብ ተሰርቶ የቀረበ ቢሆንም ተጠሪው መስሪያ ቤት በሂሳብ መዛገብ የቀረበውን አመታዊ ሽጭ ከቀን ገቢ ግምት ያነሰ ነው በሚል ምክንያት አልተቀበላቸውም። አመልካች ከዘህ በፉት ራሳቸው ባሳወቁት የቀን ገቢ ግምት ብር1,000 (አንድ ሺህ ብር) ነው በማለት የገለፁ ሲሆን በሂሳብ መዛገባቸው ያሳወቁት አመታዊ ገቢ ብር 89,100 (ሰማንያ ዖጠኝ ሺህ አንድ መቶ) መሆኑን በዘሁ መሰረትም በዘህም በቀን 244.11(ሁለት መቶ አርባ አራት ብር ከአስራ አንድ ሳንቲም) በመሆኑ ፣አመልካች የአመት ገቢያቸው ከግማሽ በታች ያሳወቁ በመሆናቸው ተረጋግጦ ያቀረቡት የሂሳብ መዛገብ ውድቅ የተደረገ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ ይቻላል።
አመልካች ሂሳብ መዛገብ ነበረኝ በባለሞያም አሰርቼ ያቀረብኩት ትክክለኛ ገቢየ ነው በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም አመልካች ከሚሰሩበት መጋዖን ስፊት እንዱሁም መጋዖኑ ለእቃ ማከማቻነት በጣም አስፈካጊ በሆነ ቦታ ላይ በመሆኑ ያቀረቡት የቀን ገቢ እምነት የማይጣልበት ስለመሆኑ ፍሬ ነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዖን ሥልጣን ባለው የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ተረጋግጧል ። በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 112 መሰረት ለዘህ የሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሕግ ስሕተትን የማረም ሥልጣን እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዖን ሥልጣን የለውም ። ስለሆነም በአመልካች ላይ የተጣለው የግብር መጠን በሕጉ መሰረት መሆኑን ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዖን ሥልጣን ባለው የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እና በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ለዘህ ችልት ያቀቡት አቤቱታ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም ።
በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመ.ቁጥር 033/08 ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ/ም ተሰጥቶ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ. ሃምላ 27 ቀን 2008 ዓ/ም እንዱሁም በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. መስከረም 10 ቀን 2009 ዓ/ም በትዔዙዛ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.