የሉዛ ውል እንዱሰረዛ የሚቀርብን የዲኝነት ጥያቄን አቶ አብደልቀኒ አብደራህማን ሰኔ 27 ቀን 201 XVII መደበኛ ፍርድ ቤቶች ሉያስተናግድ የሚገባ ስለመሆኑ እና እነ አቶ ዲንኤል ወ/ኃዋሪያት(ሁለት ሰዎች) 2009 ዓ.ም. ጉሙሩክ 204 42. የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዚ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በአዱሱ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ድርጊቱ ሉያስከስስም ሆነ ሉያስቀጣ የማይችልና የተጀመረውን ክስም የማቋረጥ ህጋዊ ውጤት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 21(2)፣ የኢ.ፋ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 5/3/ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99፣ አዋጅ ቁ. 859/2006
No summary available.
ሕዲር 06 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናየት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዓ/ህግ - አልቀረበም ተጠሪ፡ ሰይፈ አበበ ንጉሴ - በላለበት ታይቶ የተወሰነ በመሆኑ አልቀረበም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የአሁኑ አመልካች ለአርሲ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ተከሳሽ (ተጠሪ) አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 በመተላለፍ የኮንትሮባንድ እቃ የጉምሩክ ስርዓት ያልተፈጸመበት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ እያለበት 21 ጀሪካን ዖይት ቀረጥና ታክስ መጠኑ በአጠቃላይ ብር 6025.45 (ስድስት ሺህ ሃያ አምስት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም) የሆነ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሽንት ቤት ክፍል ውስጥ ተከማችቶ እጅ ከፍንጅ ስለተያዖ የኮንትሮባንድ እቃ ይዜ በመገኘት ወንጀል ፈጽሞ ተከሷል የሚል ነው።
ተከሳሽ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ፍቃድ እያለኝ ከእኔ ላይ የተያዖው ስለሆነ ህጋዊ ነኝጥፊት የለብኝም በማለት ተከራክሯል። የስር ከሳሽ የአሁኑ አመልካች የሆነው ዐቃቤ ህግ ሁለት ምስክሮችን ያሰማ ሲሆን ተከሳሽም ሁለት መከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ አስመስክሯል። የጽሁፍ መከላከያ ማስረጃ በቀን 30/01/2004 ዓ/ም የተሰጠ እስከ 2007 ዓ/ም የታደሰ የምግብ ዖይት የንግድ ፈቃድ ተከሳሽ አቅርቧል።
ጉዲዩን የተመለከተው የአርሲ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን (የአሁኑ ተጠሪን) ተከላክሎል በማለት በወንጀል ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 149(2) መሰረት በነጻ እንዱሰናበት የአሁኑ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ በወንጀል ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 195(1) መሰረት በመ/ቁ.200935 በቀን 01/07/2007 ዓ/ም ዖግቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው።
የአቤቱታው ይዖት በአጭሩ፡-
የክርክሩ ሂደት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን ጉዲዩን ከስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ፤ አመልካች ካቀረበው አቤቱታ እንዱሁም አጣሪው ከያዖው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነውም በተጠሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ሸንት ቤት ውስጥ በክሱ የተጠቀሰው 21 ጀሪካን ዖይት ተይዝል። በክሱ ውስጥ የተጠቀሰ መጋዖን እየታደሰ ዖይቱ አዱስ ሸንት ቤት ውስጥ ከላልች የሱቅ እቃዎች ጋር መገኘቱን የከሳሽም ሆነ የተከሳሽ ምስክሮች በተመሳሳይ ሁኔታ መስክረዋል። ተከሳሽ (ተጠሪ) በ2004 ዓ/ም የተሰጠ የዖይት ንግድ ፍቃድ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ የታደሰውን ማቅረቡ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጧል። የአርሲ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ተከላክሎል በማለት በነጻ አሰናብቷል። በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 መሰረት ተጠሪው ከተከሰሰበት ወንጀል ሃላፉነት ነጻ ለመሆን ለእቃው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ መከፈለን የሚያስረዲ የዔቃው ጉምሩክ ዱክላራሲዮን (ሰነድ) የማቅረብ ህጋዊ ግዳታ እንዲለበት ተመልክቷል። በስር ፍርድ ቤት ለተጠሪው የዖይት ንግድ ፈቃድ አለው ከመባለ በስተቀር ዖይቱን ከማንና ከየት እንደገዙ እንዱሁም ለገዙበት ዖይት የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ መከፈለን የሚያስረዲ የእቃው ጉምሩክ ዱክለራሲዮን (ሰነድ) ተጠሪ አቅርቦ አላረጋገጠም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ተጠሪ ተከላክሎል ለማለት የሚያስችል ሆኖ አልተገኘም። ሆኖም ግን አከራካሪ ሆኖ የታየው ተጠሪ በተከሰሰበት አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 ‛ህገ ወጥ እቃዎች ይዜ ስለመገኘት“ ተብል የተደነገገው ድንጋጌ ይህን አዋጅ በተካው በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ላይ ወንጀል ሆኖ ተደንግጓል ወይስ አልተደነገገም? የሚለው ነው። የአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ላይ አልተደነገገም። በዘህ አዋጅ አንቀጽ 168 የተደነገገ ነው።
‛የኮንትሮባንድ ወንጀል“ በሚል ነው። ይህም በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ የተደነገገ ነው። በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 የተደነገገው በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ካልተደነገገ ህጋዊ መፍትሓ (legal remedy) ምንድነው?
የሚለው ምላሽ ሉያገኝ ይገባል። ይህ አዋጅ ግን ይህንን ጥያቄ የሚመልስ የህግ መርህ አይደነግግም። በዘህ ጊዚ በኢፋዱሪ ህገ መንግስት የተደነገገው መሰረታዊ መርህ እንዱሁም በወንጀል ህጉ በመርህነት የተደነገገው ተግባራዊ ላደረግ ይገባል። በልላ አነጋገር በኢፋዱሪ ህገመንግስትና በወንጀል ህግ ከተደነገገው መሰረታዊ መርህ አንጻር ታይቶ መተርጎም ይኖርበታል። በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22 የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን የኢፋዱሪ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 5 በተመሳሳይ መልኩ ደንግጎታል። በህገ መንግስቱ አንቀጽ 22(2) ድርጊቱ ከተፈጸመ በኃላ የወጣ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ከድርጊቱ በኃላ የወጣ ህግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል በማለት ተደንግጓል።
በወንጀልህግአንቀጽ 5(3) የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዚ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በዘህ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሉያስከሰሰም ሆነ ሉያስቀጣ አይችልም፤
ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ ይቋረጣል ተብል ተደንግጓል። በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ የፈጸመው ድርጊት ምንም እንኳን በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 ላይ ወንጀል ሆኖ የተደነገገ ቢሆንም በዘህ አዋጅ ምትክ በተተካው አዋጅ ቁጥር 859/2006 ወንጀል ሆኖ አልተደነገገም። ስለዘህ በኢፋዱሪ ህገመንግስት እና በወንጀል ህጉ በተደነገገው መሰረታዊ መርህ አንጻር ሲደመደም ተጠሪ ጥፊተኛ ተደርጎ ቅጣት የሚወሰንበት የህግ አግባብ የለም ብለናል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአርሲ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 44610 በቀን 22/04/2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 200935 በቀን 01/07/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ከላይ በፍርድ ሀተታው የተገለጸውን የኢፋዱሪ ህገመንግስቱንና የወንጀል ህጉን መሰረታዊ መርህ መሰረት ያደረገ ባይሆንም በውጤት ደረጃ ግን ልዩነት ስለላለው በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 195(2) (ለ) (2) መሰረት ጸንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.