የአንድ ሃገር ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ብሓራዊ የዲኝነት(judicial jurisdiction) ስልጣን አለው ለማለት ሉወሰደ ስለሚገባቸው ዛርዛር እነ ማጂኮን ኮንስትራክሽን ሉትድ(ሁለት ሰዎች) እና አቶ ታትገኝ ፉጣሞ ወላቦ (አራት ሰዎች)
No summary available.
ሰኔ 27 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች- ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ ፀሃይ መንክር አመልካች- አቶ አብደልቀኒ አብደራህማን - ጠበቆች ግርማ አለሙና አሰፊ አሉ ቀረቡ ተጠሪዎች- 1ኛ. አቶ ዲንኤል ወ/ሃዋሪያት - ጠበቃ ግርማ ከበደ ቀረቡ 2ኛ. የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የይዜታ አስተዲደር ሽግግር ጊ/አገ/ፕ/ጽ/ቤት - የቀረበ የለም መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በተጠሪዎች መካከል የተደረገ የሉዛ ውል እንዱፈርስ የቀረበን የዲኝነት ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በተጠሪዎች ላይ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው።
የክሱ ይዖት፡- መንግስት በውጭ ሃገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በፈጠረው ዔድል የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተቋቁሞ በአ/አበባ ከተማ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ክልል ለማህበሩ አባላት ቤት መስሪያ ቦታ ተሰጥቷል፤ በዲሽን የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር አባል የነበሩት 1ኛ ተጠሪ ከማህበሩ ተሰናብተው በምትካቸው አመልካች በአባልነት ተተክቻለሁ፤ የአሜሪካን ድላር 5,000.00 (አምስት ሺህ) አሜሪካን ሃገር ለሚገኘው ኤምባሲ ክፍያ ፈፅሜያለሁ፤ አመልካች በማህበሩ ስለመተካቴም ማህበሩ ጥቅምት 3 ቀን 1996 ዓ.ም ለአ/አበባ መስተዲድር የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የሉዛ አፈፃፀም መምሪያ በጻፈው ደብዲቤ አሳውቋል፤ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ አመልካች በአባልነት ስለመተካቴ በዩ ኤስ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በማሳወቁና ልዩ ልዩ ቃለጉባኤዎችን በማስተላለፈ ኤምባሲው ጥቅምት 25/1996 ዓ.ም ለውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጉዲዮች ዲይሬክተር በፃፈው ደብዲቤ ገልጿል፤ ሆኖም 1ኛ ተጠሪ በማህበሩ ያለ በማስመሰል ከራሳቸው አንዲችም ገንዖብ ሳይከፍለ ከሳሽ በከፈለት የቅድሚያ ክፍያ በመጠቀም ከክፍለከተማው የመሬት ልማትና አስተዲደር መምሪያ ጋር የሉዛ ውል በመዋዋል የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ የይዜታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (ካርታ) አላግባብ ወስደዋል፤
ስለሆነም 1ኛ ተከሳሽ ከማህበሩ ያልተሰረዘ እና ቅድሚያ ክፍያ የከፈለ በማስመሰልና በማሳሳት በአዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀጽ 10(10)፣ 13(2) እና (3)፣ 14 (2)(ሐ)፣ 15(1) ድንጋጌዎች መሰረት መብት ሳይኖራቸው ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ታህሳስ 19 ቀን 1999 ዓ.ም ያደረጉት የመኖሪያ ቤት ሥራ ቦታ ሉዛ ውል እንዱፈርስ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
1ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ከሳሽ የማህበሩ አባልም ተተኪም አይደለም፤ ተከሳሽ የማህበሩ መስራች ስለሆንኩ ማህበሩ ለሉዛ አፈጻፀም መምሪያ በላከው ዛርዛር ውስጥ ስሜ በተ.ቁ 11 ተመዛግቦ ይገኛል፤ በአዋጁ መሰረት 2ኛ ተከሳሽ መሬቱን ከነካርታው አስረክቦኝ የሉዛ ውል ተፈራርመን ሥራ ጀምሬያለሁ፤ ብር 123,238.33 የሉዛ ክፍያም ከፍያለሁ፤ 1ኛ ተከሳሽ በራሱ ፈቃድና የጽሁፍ አቤቱታ ከማህበሩ የለቀቀበት ነው ተብል የቀረበው ማስረጃ ጽሁፍም ሆነ ፊርማው የኔ አይደለም፤ እኔ ስለመሰረዚ እና ከሳሽ ተተኪ ስለመሆኑ የተያዖው ቃለ ጉባኤ በተደረገበት ስብሰባ ላይ ስላልተጠራሁ አልተገኘሁም፤ በጽሁፍ ፈርሜ አባልነቴን ለቅቄያለሁ አላልኩም ስለሆነም ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። 2ኛ ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ታዜ ስላላቀረበ በፅሁፍ መልስ የማቅረብ መብቱ ታልፎል።
ጉዲዩ በዘህ መልኩ የቀረበለት የከተማ አስተዲደሩ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ እንዱሁም የማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ እና ላልች ሰነድችን ከማህበሩ አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በ1ኛ ተከሳሽ ምትክ አመልካች አባል እንዱሆኑ የወሰነ መሆኑ ታውቆ አስፈላጊው ፍርማሉቲ እንዱፈፀም ለሉዛ አፈጻፀም መምሪያ ከጻፈው ደብዲቤ ባለፈ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የተሰጠ ውሳኔ እና ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ የፀደቀ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ የለም፤ 1ኛ ተከሳሽ በማህበሩ አልቀጥልም ሲለ ገልጸዋል ተብል በተያዖው ቃለ ጉባኤ ላይ ያለው ፊርማ ስለተካደ በፍረንሲክ ተመርምሮ ፊርማው የ1ኛ ተከሳሽ አለመሆኑ ተረጋግጧል፤ ስለሆነም በተከሳሾች መካከል የተፈፀመው የሉዛ ውል እንዱፈርስ ሲለ ከሳሽ ያቀረቡት አቤቱታ ወድቅ ላሆን ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ላይ ቅሬታቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሥር ፍርድ ቤቶች ባሳለፈት ውሳኔ ተፈጸመ የሚለትን የህግ ስህተት በመዖርዖር ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ማመልከቻው ተመርምሮ አመልካች የሉዛ ውለ እንዱሰረዛ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ከማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንጻር ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ከፍሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን ለሰበር ችልቱ በተያዖው ጭብጥ መሰረት ፍሬ ጉዲዩ ከመታየቱ በፉት አመልካች ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ የከተማው ፍርድ ቤቶች አከራክረው ለመወሰን የሥረ ነገር ሥልጣን ያላቸው መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት በመያዛ መመርመሩ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
ተሻሽል የወጣው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 የከተማው ፍርድ ቤቶች ስለሚኖራቸው የዲኝነት ሥልጣን የሚደነግግ ሲሆን በተጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1(ሀ) እና (መ) ሥር የከተማውን መሪ ፕላን አፈጻፀም የሚመለከቱ የይዜታ ባለመብትነት፤ የፈቃድ አሰጣጥ ወይም የቦታ አጠቃቀምን በተመለከተ የሚነሱ ጉዲዮች፤
እንዱሁም የከተማው አስተዲደር አስፈፃሚ አካላት (ተቋማት) የሚገቧቸውን አስተዲደራዊ ውልች በተመለከተ የሚነሱ ጉዲዩችን በተመለከተ የፍትሃብሄር የዲኝነት ስልጣን እንዲላቸው ተመልክቷል።
በተያዖው ጉዲይ አመልካች ያቀረቡት ክስ 1ኛ ተጠሪ ከማህበሩ ያልተሰረዘ እና ቅድሚያ ክፍያ የከፈለ በማስመሰልና በማሳሳት በአዋጅ ቁጥር 147/1991 መሰረት መብት ሳይኖራቸው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት የመኖሪያ ቤት ሥራ ቦታ ሉዛ ውል እንዱፈርስ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ይህ ክስ ተጠሪዎች ያደረጉትን ውል መሰረት ያደረገ ቢሆንም ክሱ የከተማውን መሪ ፕላን አፈጻፀም የሚመለከት የይዜታ ባለመብትነት፤ ከፈቃድ አሰጣጥ ወይም የቦታ አጠቃቀም ጋር ያልተያያዖ ሲሆን አስተዲደራዊ ውል ልባል የሚችል አይደለም። ስለሆነም ጉዲዩ በከተማው ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ሥር የሚወድቅ ሆኖ አላገኘነውም። የሉዛ ውል እንዱሰረዛ የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄን በተመለከተ በመደበኛ ፍርድ ቤት ላታይ የማይገባው መሆኑን የሚደነግግ በግልጽ የተመለከተ ህግም የለም። ይኸው ሰበር ሰሚ ችልት ከዘህ በፉት በሰ/መ/ እና ላልችም መዙግብት የሰጠው ውሳኔም ይህን የሚያሳይ ነው።
ስለሆነም የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች የማህበራት አዋጅ ከሚሰጠው መብት ጋር በማያያዛ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የተደረገው የሉዛ ውል እንዱፈርስ ያቀረቡትን ክስ ተቀብል በማከራከር ውሳኔ የሰጠው ጉዲዩን ተቀብል ለመዲኘት በህግ ባልተሰጠው የዲኝነት ስልጣን በመሆኑ፤ ጉዲዩን በይግባኝ እና በሰበር የተመለከቱ ፍርድ ቤቶችም ይህን ሳያርሙ ማለፊቸው የህግ ስህተት በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም ይገባል ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይግባኝ ሰሚው ችልት በመ/ቁ 2335 መጋቢት 11/2007 ዓ.ም ያሳለፈው ትዔዙዛ፤ እንዱሁም የከተማው ሰበር ችልት በመ/ ነሃሴ 8/2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
ጉምሩክ
No topics extracted.