የተጨማሪ እሴት ታክስ የፋዳራል ታክስ በመሆኑና የክልል የገቢዎች ቢሮዎች ታክሱን የሚያስተዲድሩት በዉክልና ስልጣናቸዉ በመሆኑ ምንም እንኳ ታክሱ የተወሰነዉ በክልለ የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቢሆንም የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ይግባኝ ማቅረብ የሚገባዉ ስልጣን ላለዉ የፋዳራል ፍ/ቤት ወይም የዉክልና ስልጣን ላለዉ የክልል ፍ/ቤት ሥለመሆኑአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 28(2) እና አንቀጽ 30፣አንቀጽ 43(3)፣ 112
No summary available.
ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ መቻልደጉ ሰሙር ጠበቃ አብደርሃማን ሰይድ ቀረቡ ተጠሪ፡- የሚዙን አማን ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የአሁን አመልካች ተጠሪው ከ2000 እስከ 2005 ዓ.ም ባለዉ የግብር ዖመን በኦዱት ምርመራ ዉጤት ላይ በመመስረት የገቢ ግብር፣ አስተዲደራዊ መቀጫና ወለድን ጨምሮ ብር 2,779,095.30 ሲወስን የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ አስተዲደራዊ መቀጫና ወለድ ደግሞ ብር 1,972,184.97 በመወሰን ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ የግብር ማስታወቂያ ደብዲቤዎች አሳዉቋል። አመልካች በዉሳኔዉ ቅር ተሰኝቶ ባቀረበዉ ይግባኝ መነሻነት የሚዙን አማን ከተማ አስተዲደር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ አመልካች ፍሬ ግብር እና ፍሬ ታክስ ሙለ በሙለ እንዱከፍል ሆኖ ከወለድ 25% ከፍል 75% እንዱነሳለት እንዱሁም አስተዲደራዊ መቀጮ ሙለ በሙለ እንዱነሳለት በመሻሻል ወስኗል።
በዘህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ግራቀኙ ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የቤንች ማጂ ዜን የቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ ወለድ 75% እና አስተዲደራዊ መቀጮ ሙለ በሙለ ይነሳ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ሕግን መሰረት ያላደረገ ነዉ በማለት ሲሽር ፍሬ ግብርና ፍሬ ታክሱን በተመለከተ በአግባቡ ሳይጣራ ሙለ በሙለ ይክፈል መባለ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮት ግብር ይግባኝ ሰሚዉ ጉባኤ እንደገና አጣርቶ እንዱወስን ጉዲዩን በመመለስ ወስኗል።
በዘህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ የአሁኑ ተጠሪ ባቀረበዉ ይግባኝ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ መርምሮ የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍሬ ግብር እና የፍሬ ታክስ እንደገና ተጣርቶ እንዱወሰን ለጉባኤዉ መመለሱም ሆነ ጉባኤዉ አስቀድሞ በሰጠዉ ዉሳኔ ወለድ 75% እና አስተዲደራዊ መቀጮ ሙለ በሙለ እንዱነሳ መወሰኑ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት በመሻር ወስኗል። ይህን ዉሳኔ በመቃወም የአሁን አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 285/94 መሰረት የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ ጉዲዩን ለማየት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን የለዉም በማለት መዛገቡን በትዔዙዛ ዖግቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉን ትዔዙዛ እና በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነዉ።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዖት፡- ጉዲዩ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክርክር ያለበት ስለሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 285/94 መሰረት የፋዳራል ጉዲይ ነዉ በማለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የደረሰበት ድምዲሜ ሕግን መሰረት ያደረገ አይደለም። ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 3 እና 2(3) ድንጋጌ አንጻር ጉዲዩ በፋዳራል ፍ/ቤቶች የወል ዲኝነት ስልጣን ሥር ይወድቃል ተብል ሉተረጎም አይገባም። አዋጁ በመላ አገሪቱ ተፈጻሚነት ያለዉ አዋጅ በመሆኑ፣ አዋጁን መሰረት አድርገዉ ክልልች የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግን የሚያስከብሩና ታክሱን የሚሰበስቡ በመሆኑ በአዋጁ ላይ ለሚነሳ ክርክር በክልል ፍ/ቤቶች የመጨረሻ ዉሳኔ ሰጪ አካል የሆነዉ የሰበር ችልት ስልጣን የለዉም መባለ የአዋጁን አላማ ያልተከተለ ነዉ። በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 43(4) መሰረት የይግባኝ አቀራረብ እና የግብር ይግባኝ ጉባኤ ስልጣንና ተግባር በተመለከተ የገቢ ግብር አዋጅ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተደነገገ በመሆኑና አግባብነት ያለዉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 56/95 የክልል አዋጅ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለዉ። በመሆኑም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን እንዲያይ የሚከለክል ግልጽ ድንጋጌ በላለበት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት መዛጋቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ጉዲዩን አይቶ እንዱወስን ሉመለስለት ይገባል።
የዜኑ ክፍተኛ ፍ/ቤት ስለ አዲሪ ቡና መረጃ ከዜኑ ግብይት መምሪያ አስቀርቦ ከመረመረ በኃላ ጉባኤዉ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 56/95 አንቀጽ 116(1/ሐ) ላይ የተመለከተዉን ማስረጃን አስቀርቦ የማጣራት ሥራዉን አለመስራቱን አረጋግጦ ዉሳኔዉን በመሻር እንደገና በማስረጃ አጣርቶ ዉሳኔ እንዱሰጥ መልሷል። ይህን ማድረጉ በሕግ ጉዲይ ላይ የተሰጠ ዉሳኔ አይደለም የሚያስብል ባለመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛ ፍ/ቤትን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። እንዱሁም የከፍተኛዉን ፍ/ቤት ዉሳኔ ከሻረ በኃላ ጉዲዩን ወደ ጉባኤዉ መመለስ ሲገባዉ በዛምታ በማለፈና በተዖዋዋሪ መንገድ የተጠሪን ዉሳኔ ማጽናቱ የሕግ ስህተት ነዉ። አመልካች ያቀረብኩት የሂሳብ መዛገብ ዉድቅ መደረጉም ስህተት ነዉ።
ባቀረብኩት ሑሳብ መዛገብ ብቻ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ልከፍል ይገባል የሚል ክርክር ባላቀረብኩበት አግባብነት የላላቸዉ ምክንያቶች አንስቶ በመተቸት እና አከራካሪዉን ጭብጥ ባለመረዲት የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዉሳኔ ተሽሮ የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ መሆኑን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ገልጾታል። ይህ ከሆነ ደግሞ የክልለ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን በይግባኝ የማየት ስልጣን አለዉ ወይ? የሚለዉንና ይህን ተከትል የሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ለማጣራት ሲባል ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት መጥሪያዉ ለክልለ ገቢዎች ባለስልጣን ተብል እንዱቀየር አቤቱታ ቢያቀርብም ተቀባይነት በማጣቱ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመከተዉን የሚመስል ሲሆን አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በመገናዖብ መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነዉ ተጠሪ ከ2002 እስከ 2005 ዓ.ም ያለዉ የንግድ እንቅስቃሴ ኦዱት ከተደረገ በኃላ የገቢ ግብር፣ አስተዲደራዊ መቀጮና ወለድ እንዱሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ አስተዲደራዊ መቀጮና ወለድ ጨምሮ የወሰነበት ሲሆን አመልካች ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ይግባኝ አቅርቦ ፍሬ ግብሩን፣ ፍሬ ታክስ እና 25% ወለድ እንዱከፍል ሲወስን 75% ወለድ እና አስተዲደራዊ መቀጮ እንዱነሳለት ወስኗል። በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ዉሳኔ ባለመስማማት ግራቀኙ ለዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን በከፉል ወለድ እና አስተዲደራዊ መቀጮ ሙለ በሙለ እንዱነሳ መወሰኑ ስህተት መሆኑን ቢገልጽም ፍሬ ግብሩና ታክሱ በአግባቡ ሳይጣራ የተወሰነ ነዉ በማለት ዉሳኔዉን ሽሮት እንደገና ተጣርቶ እንዱወሰን ወደ ጉባኤዉ መልሶታል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍሬ ነገር ክርክሩ በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና እንዱጣራ የሰጠዉ ዉሳኔ የሕግ ስህተትን ከማረም ስልጣን ዉጪ ነዉ ሲል ሽሮት የተጠሪን ዉሳኔ በተዖዋዋሪ መንገድ አጽንቶታል።
አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ጉዲዩን የተመለከተዉ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 285/94 መሰረት የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ በክልል ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲይ በመሆኑ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት መዛገቡን ዖግቶታል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ የፋዳራል በመሆኑ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም ማለቱ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም የሚለዉን ጭብጥ ለመመለስ አግባብነት ያላቸዉን የሕግ ድንጋጌዎች እንመልከት።
በመሰረቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የፋዳራል መንግስት የታክስ ስልጣን ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 28(2) እና አንቀጽ 30 መሰረት ታክሱን የመሰብሰብና የማስተዲደር ስልጣን ለፋዳራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተሰጠ መሆኑ በግልጽ ተመልክቷል። የክልል የገቢዎች ባለስልጣን ቢሮዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰበስቡት ታክሱን የማስተዲደር የራሳቸዉ ስልጣን ኖሯቸዉ ሳይሆን ታክሱን ለማስተዲደር ካለዉ አመቺነት የተነሳ ስልጣን ባለዉ አካል በተሰጣቸዉ ዉክልና ነዉ። የክልለ ገቢዎች ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስን በዉክልና ማስተዲደሩ ብቻ ጉዲዩን የክልል ጉዲይ ሉያደርገዉ አይችልም። ከዘህ በተጨማሪ የአዋጁ አንቀጽ 43(3) በግልጽ እንደሚደነግገዉ በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ዉሳኔ ላይ የሚቀርበዉ ይግባኝ የሚስተናገደዉ በገቢ ግብር አዋጁ መሰረት መሆኑ ተመልክቷል። የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 112 ደግሞ በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ዉሳኔ ላይ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል ወገን ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል ተመልክቷል። ስለሆነም የተጨማሪ እሴት ታክስ የፋዳራል ታክስ በመሆኑና የክልል የገቢዎች ቢሮዎች ታክሱን የሚያስተዲድሩት በዉክልና ስልጣናቸዉ በመሆኑ ምንም እንኳ ታክሱ የተወሰነዉ በክልለ የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቢሆንም የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ይግባኝ ማቅረብ የሚገባዉ ስልጣን ላለዉ የፋዳራል ፍ/ቤት ወይም የዉክልና ስልጣን ላለዉ የክልል ፍ/ቤት መሆን ይኖርበታል። ከዘህ አንጻር ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም ማለቱ የሚነቀፍ አይሆንም።
በልላ በኩል ምንም እንኳ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም ማለቱ ተገቢ ቢሆንም ቀጥል የሚነሳዉ ጥያቄ የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን ተመልክተዉ ዉሳኔ የሰጡበት ስልጣን ኖሯቸዉ ነዉ? ወይስ አይደለም የሚለዉ ነዉ። ጉዲዩ ከላይ እንደተገለጸዉ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 11፣ በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 43(4) እና በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 112 መሰረት ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል ወገን ይግባኝ ሉያቀርብ የሚችለዉ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነዉ።
በተያዖዉ ጉዲይ የስር ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ዓይተዉ የወሰኑት የፋዳራል ጉዲይ መሆኑን ተገንዛበዉ ባላቸዉ የዉክልና ስልጣን ተጠቅመዉ ሳይሆን የክልል ጉዲይ ነዉ በሚል ነዉ። ከዘህ መገንዖብ የሚቻለዉ የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን የማየት የስረ-ነገር ስልጣን ሳይኖራቸዉ ጉዲዩን ተመልክተዉ መወሰናቸዉን ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍ/ቤቶች የስረ-ነገር ስልጣን ሳይኖራቸዉ ስልጣን አለን በሚል በተሳሳተ ግንዙቤ የሰጡትን ዉሳኔ የማረም ኃለፉነት እያለበት ዉሳኔውን ሳይሽር በዛምታ ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
ሲጠቃለል የተጨማሪ እሴት ታክስ ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ ጉዲይ በመሆኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የስረ-ነገር ክርክሩን ተመልክቶ የመወሰን ስልጣን የለኝም ማለቱ ተገቢ ቢሆንም የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩ የፋዳራል መሆኑን ሳይገነዖቡና ስልጣን ሳይኖራቸዉ የሰጡትን ዉሳኔ መሻር ሲገባዉ በዛምታ ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የቤንች ማጂ ዜን የቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 15 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔም ሆነ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ የስረ-ነገር ስልጣን ሳይኖራቸዉ የሰጧቸዉ ዉሳኔዎች በመሆናቸዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ጥር 26 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ ተሻሽሎል።
የተጨማሪ እሴት ታክስ ጉዲይ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች የስረ-ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ ጉዲይ በመሆኑ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ነዉ ተብሎል።
የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስረ-ነገር ስልጣን ሳይኖራቸዉ የሰጧቸዉ ዉሳኔዎች የተሻሩ በመሆናቸዉ ይህ ዉሳኔ ግራቀኙን በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ዉሳኔ ላይ ስልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት ይግባኝ ከማቅረብ አይከለክልም ተብል ተወስኗል።
መዛገቡ ተዖግቷል ይመለስ።
No topics extracted.