በህገወጥ መንገድ ተይዖው በተገኙ የቁም እንስሳት ላይ አግባብ ያለው አካል በሚወስደው እርምጃ ላይ በቀጥታ ክስ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የቁም እንስሳት ግብይት አዋጅ ቁጥር 819/2006 አንቀጽ 15/5/ XVI እና 8 ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 19/4/ እና 5
No summary available.
ታኅሳስ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጰውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- የእነማይ ወረዲ ንግድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት - ዐ/ህግ አቶ ታምሩት ወርቁ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጎበዚ አሰፊ - ቀረቡ መዛገቡን መርምረን ቀጥል ያለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ ከገንዖብ ክፍያ ጋር በተያያዖ የቀረበ የፍትሒብሓር ክስ ሲሆን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ በእነማይ ወረደ ፍርድ ቤት ያቀረበው በተሸካርካሪ ተጭነው የነበሩ ስድስት የቁም እንስሶችን አመልካች የወሰደብኝ በመሆኑ እንስሶቹን እንዱመልስልኝ ወይም ግምታቸው .00/ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/ እንዱከፍለኝ በሚል ነው።
የአሁን አመልካች የቁም እንስሳት ግብይት አዋጅ ቁጥር 819/2006 ን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ 341/2007 አንቀጽ 19/4 እና 5/ መሰረት በህገወጥ መንገድ ተይዖው በተገኙ የቁም እንስሳት ላይ አግባብ ያለው አካል በሚወስደው እርምጃ ላይ ላቀርብ የሚችለው ይግባኝ መሆኑ በግልጽ የተመለከተ ስለሆነ ለወረዲው ፍርድ ቤት የቀጥታ ክስ መቅረቡ ተገቢ አይደለም።
በመሆኑም የወረዲ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጠን የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል።
ጉዲዩ የቀረበለት የወረዲ ፍርድ ቤት በተጠቀሰው አዋጅ እና ደንብ መሰረት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለኝም በማለት በመ/ቁ.0119015 በቀን 29/02/2008 ዓ/ም ብይን ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ ብይኑን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምዔራብ ጎጃም ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በመ/ቁ. 0123900 ህዲር 6 ቀን 2008 ዓ/ም ይግባኙን ሰርዝል።
የአሁኑ ተጠሪ አቤቱታ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ ችልቱም የግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 19 /4 እና 5/ ን በመተርጎም ጉዲዩ በቀጥታ ለፍርድ ቤት ላቀርብ ይችላል በማለት የሥር ፍርድ ቤቶችን ብይንም ሆነ ትዔዙዛ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አይቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 341 መሰረት መልሷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠውን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። የሰበር አቤቱታ ይዖትም በአጭሩ፡- በቁም እንስሳት ግብይት አዋጅ ቁጥር 819/2006 አንቀጽ 15 /5 እና 8/ መሰረት እንዱሁም አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 17 እና 19 መሰረት ተጠሪ በህገወጥ መንገድ እያጓጓዙቸው የተገኙ ስድስት የቁም እንስሶች ላይ በሰጠው ውሳኔ ላይ ላቀርብ የሚችለው ይግባኝ እንጂ ቀጥታ ክስ አይደለም። ስለሆነም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የወረዲ ፍርድ ቤት በመቃወሚያው ላይ የሰጠውን ብይን በመሻር የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ተሸሮ የወረዲ ፍርድ ቤት ብይን እንዱፀናልን እንጠይቃለን የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በአስተዲደር አካለ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን የይግባኝ አቤቱታ ሳይሆን ቀጥታ ክስ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል በማለት አዋጅ ቁጥር 819/2006 እና አዋጁን ተከትል የወጣ ደንብ ቁጥር 341/2007 ደንጋጌዎችን በመተርጎም የደረሰበት ድምዲሜ የህጉን ዓላማ፣ መንፈስና ይዖት በአግባቡ ያገናዖበ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል መዛገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
ተጠሪ ለአመልካች አቤቱታ በቀን 01/11/2008 ዓ/ም የተጻፈ መልስ ሰጥቷል። የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ እንደቀረበው ሲሆን ጉዲዩን ከሥር ፍርድ ቤቶች ብይን፣ ትዔዙዛ እና ውሳኔ እንዱሁም በዘህ ችልት ከተደረገው ክርክርና አጣሪ ከያዖው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። የግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው የስልጣን ጥያቄ መሰረት ያደረገው የአዋጅ ቁጥር 819/2006 አንቀጽ 15 /5 እና 8/ እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣ ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 19 /4 እና 5/ ነው። አግባብ ያለው አካል በአዋጁ አንቀጽ 15/5/ ማንኛውም የቁም እንስሳት ግብይት ተሳታፉ የግብይት ሂደቱን የሚያዙባ አሳሳች ድርጊት ፈጽሞ ሲገኝ ተገቢውን አስተዲዲራዊ እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን እንዲለው ሲደነግግ፣ የአንቀጹ ንዐስ አንቀጽ 8 ደግሞ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዘ ወይም ግብይት ሲፈጸምባቸው የተገኙ የቁም እንስሳትን የመያዛ፣ የቁም እንስሳቱን እንደ አግባቡ በመጀመሪያ ወይም በሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት ማዔከል አቅርቦ በጨረታ በመሸጥ ገንዖቡን በዛግ የባንክ ሂሳብ እንዱቀመጥ የማድረግ፣ በዘህ አዋጅ አንቀጽ 17 መሰረት እንዱወረስ ሲወሰንም ለመንግሥት ገቢ እንዱሆን የማድረግ ሥልጣን የተሰጠው እንደሆነ ይደነግጋል። እነዘህ ድንጋጌዎች አግባብ ያለው አካል ሉወስድባቸው የሚችልባቸውን አስተዲዲራዊ እርምጃ የሚገልጹ ናቸው። አግባብ ያለው አካል ማነው? ለሚለው ጥያቄ አዋጁ በአንቀጽ 2 (24) "አግባብ ያለው አካል"እንደአግባቡ ሚኒስቴሩ ወይም የንግድ ፈቃድ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠው የክልል አካል ነው በማለት ይተረጉማል።
እርምጃዎቹ ሲወሰደ ክስ ለማን እንደሚቀርብ ግን አዋጁ አይገልጸም። ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 19/4/ የአስተዲደር አካለ እርምጃ ሲወስድ ክስ ለማን እንደሚቀርብ ይደነግጋል። ይኸውም "ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ይችላል" የሚለው ነው። ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የትኛው ነው? የሚለውን ደንቡ በግልጽ ባያስቀምጥም ሥልጣን በሥረ ነገር ወይም በገንዖብ መጠን ሉወሰን ይችላል። በልላ አነጋገር ክስ አቅራቢ የሚጠይቀው የዲኝነት ዓይነት ወይም የገንዖብ መጠን የፍርድ ቤቱን ሥልጣን ይወስናል ማለት ነው። በዘህ በዲኝነቱ መጠን ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ ይቀርባል ማለት ነው። ይህም የሚያመለክተው ክስ የሚቀርበው ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሳይሆን ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ነው ። ይህም ወረዲ ፍርድ ቤት ወይም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ላሆን ይችላል። ክስና ይግባኝ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። በዘህ ንዐስ አንቀጽ መሰረት የህግ አውጪው ሀሳብ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ቀጥታ ክስ ላቀርብ እንደሚችል መደንገጉን ነው። የእንግሉዖኛው ትርጉምም ቢሆን " May institute case in a court of law having jurisdiction within 30 day after the decision is passed or after laps of period specified for decision" የሚለው ከላይ የገለጽነውን ያረጋግጣል። ይህ ቢሆንም የአንቀጹ ንዐስ አንቀጽ 5 ደግሞ "ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤት" በማለት የሚገልጽ ሲሆን ይህ በንዐስ አንጽ 4 ላይ ከተደነገገው ጋር ይቃረናል።ሆኖም ግን ከእንግሉዖኛው ትርጉም ሲታይ የህግ አውጪው ሀሳብ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ እንዱቀርብ መሆኑን ነው። እነዘህን ሁለቱን ንዐስ አንቀጾች ህግ አውጪው ከሰበው ግብ አንጻር መተርጎም የፍርድ ቤት ድርሻ ነው።
በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እነዘህን ሁኔታዎችን በማጤን የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በቀን 17/09/2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
የዘህን ችልት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በቀን 23/10/2008 ዓ/ም የተሰጠው የእግድ ትዔዙዛ ተነስቷል። ለሚመለከተው አካል ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረስ።
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።