የገጠር መሬት ሕጋዊ በሆነ ሁኔታ አግባብ ባለው አካል በስጦታ የተላለፈለት ተጠቃሚ ለረጅም ጊዚ ተጠቃሚ የሆነበት መሬት መሆኑ ከተረጋገጠ መሬቱ በስጦታ ሰጪዉ ስም ተመዛግቦ መገኘቱ እና ግብር በስሙ መከፈለ ብቻ ይዜታዉ በስጦታ ዉል አልተላለፈም የሚያሰኝ ወይም በመሬቱ ላይ ያለዉን የባለይዜታነቱን መብት የማያስቀር ስላለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል ገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 2/3፤9(5) 122740 አቶ ጤና ጋርደዉ እና ወ/ሮ መደቅሴ ገርቢ ሚያዘያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም 36. የመንግስት ቤት ተከራይቶ የሚኖሩ ሰዎች የባለቤትነት እነ አቶ መክብብ ተስፊ ሚያዘያ 26 175 XV (የመፊለም ክስ) የመጠየቅ ክስ ማቅረብ የሚችለበት ህጋዊ ምክንያት ስላለመኖሩ የፍ/ሕ/ቁ. 1205 (ሁለት ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ ፀሐይ ለገሰ (ሁለት ሰዎች) ቀን 2009 ዓ.ም የዲኝነት ስልጣን 37. የአዱስ አበባ ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀደም ብል በሰጠው ፍርድ ላይ የሚቀርብለትን የፍርድ መቃወሚያ ተቀብል የመዲኘት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358፣የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ አዋጅ ቁ. 721/2004
No summary available.
ሕዲር 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች(ዎች)፡- አቶ ለገሰ ገለታ ቀርቧል ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ተጠሪዎች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ፣ አመልካች ምትክ ቦታ ሉሰጣት ይገባል በማለት፣ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ተጠሪዎች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ተቀብል የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ውሳኔ ላሰጥ ይገባል በማለት የሰጡት የሕግ ትርጉምና ውሳኔ ሕጋዊ አግባብነት ያለው መሆኑን በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው።
የጉዲዩ መነሻ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ፣ አመልካችና በዘህ ሰበር ችልት የክርክሩ ተሳታፉ ባልሆነውና በሥር ሁለተኛ የፍርድ መቃወም ተጠሪ ሆኖ ስሙ በተገለጸው የቀድሞው የቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ባንክ የከተማ ልማት ማደስ ፕሮጀክት ጽ/ቤት( በአሁኑ አጠራርየቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዲደር መምሪያ) መካከል የነበረውን የካሳና የምትክ ቦታ ክርክር ሰምቶ፣ መልስ ሰጭ ለአመልካች ምትክ ቦታ የመስጠት ግዳታ አለበት በማለት በመዛገብ ቁጥር 330/99 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ነው። ተጠሪዎች ይህ የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠውን ውሳኔ፣ ጉዲዩ የሚመለከታቸው የከተማው አስተዲደር አካላት(ተጠሪዎች) በመልሥ ሰጭነት ሳይጠሩና ክርክራቸውን ሣያቀርቡ የተሰጠና የከተማውን አስተዲደር፣ ሕዛብ መብትና ጥቅም የሚጎዲ በመሆኑ ጉዲዩ የሚመለከተን የከተማው አስተዲደር አካላት(ተጠሪዎች) ባለንበት እንደገና ታይቶ ሉወሰን ይገባል በማለት ሀምላ 6 ቀን 2007 ዓ.ም የተጻፈ የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ፣ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 በመጥቀስ ለከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አቅርበዋል።
የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጠሪዎችን ፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ከመረመረ በኋላ ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው የሚላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመጥቀስ፣ ተጠሪዎች የፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 በመጥቀስ ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ተቀብል ለማስተናገድና ቀደም ብል የሰጠውን ፍርደ እንደገና ለማየት የሚያስችለው የህግ መሰረትና ሥልጣን የላለው መሆኑን ገልጾ፣ ተጠሪዎች ያቀረቡትን መቃወሚያ አይቶ ውሳኔ ለመስጠት ሥልጣን የለኝም በማለት የጉ/መዛገብ ቁጥር 330/99 ሀምላ 16 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው ብይን ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪዎች የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት፣ ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 358ና ተከታይ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ለመቀበልና የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ውሳኔ መስጠት ስልጣን አለው በማለት የይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሰጠውን ብይን በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል።ይግባኝ ሰሚው ችልት የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጠሪዎችን የፍርድ መቃወሚያ በመቀበልና የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሶ ልኮለታል።
አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የከተማው የሰበር ችልት የአመልካችን ሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች ለዘህ ሰበር ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ፣የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ጉዲዩን መጀመሪያ አይቶ ውሳኔ የሰጠው ተጠሪነቱ ለአንደኛ ተጠሪ ሆነው የቀድሞው የቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ባንክ ከተማ ልማት ማደስ ፕሮጀክት ጽ/ቤት( በአሁኑ አጠራር የቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዲደር መምሪያ) በሁለተኛው ተጠሪ በኩል ተወክል ያለውን ክርክርና ማስረጃ ካቀረበ በኋላ ነው። ስለዘህ ተጠሪዎች ጉባኤው ቀደም ብል ውሳኔ የሰጠው የሚመለከታቸው የከተማው አስተዲደር አካላት(ተጠሪዎች) በመልሥ ሰጭነት ሳይጠሩና ክርክራቸውን ሣያቀርቡ የተሰጠ ነው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተገቢነት የላለውና የህግ መሰረት የላለው ነው። ጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ተጠሪዎችን መብትና ጥቅም የሚጎዲ ባለመሆኑና በአጠቃላይ ተጠሪዎች ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ፣የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ተጠሪዎች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ተቀብል እንዱያይ የሰጡት ብይን በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት መልስ በጉዲዩ ተከራካሪ መሆን የነበረብን እኛ ነን። ጉባኤው እኛን በመልስ ሰጭነት ሣይጠራ የሰጠው ውሳኔ የከተማው አስተዲደርና ሕዛብ ጥቅም የሚጎዲ ነው። ተጠሪዎች በዘህ አይነት ሁኔታ የተሰጠን ፍርድ በመቃወም የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ማቅረብ እንደምንችል የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰበር መዛገብ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ፣ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በዘህ ሰበር ችልት ግራ ቀኙ ያቀረቡት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ፣ ቀደም ብል በሰጠው ውሳኔ ላይ በፍ/ሥ/ሥ ሕግ ቁጥር 358ና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የሚቀርብለትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው፣ ቀደም ብል የሰጠውን ፍርድ እንደገና እንዱመረምር በላልች የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ተቀብል የማየት፣ ክርክር የመስማትና መርምሮ የመወሰን ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ፣ በልማት ከይዜታቸው ለሚነሱና ንብረታቸውን ለሚያነሱ ሰዎች የካሣ ክፍያና ምትክ ቦታ ጥያቄና አቤቱታ ላይ አስተዲደራዊ ውሳኔ የመሥጠት ኃላፉነት ያለበትና በከተማ ቦታ በሉዛ ስለመያዛ ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 272/1994 እና ይህንን አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት ሥልጣን የተሰጠው የከተማው አስተዲደር "አግባብ ያለው አካል" ፣ ስለ ምትክ ቦታ ጥያቄውና ስለ ካሳ ክፍያ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኙ ሰዎች የሚቀርቡትን የይግባኝ ቅሬታ ተቀብልና የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶና አጣርቶ ውሳኔ የመስጠት በሕግ የዲኝነት ሥልጣን የተሰጠው አካል ነው።
ከላይ በተጠቀሱት አዋጆች የከተማ ቦታ እንዱለቅ የውሳኔ ማስታወቂያ የደረሰውና በአስተዲደራዊ ውሳኔው መብቴን ነክቶብኛል የሚል ሰው ለከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ይግባኝ ቅሬታ ከማቅረቡ በፉት አግባብ ላለው የአስተዲደር አካል በሰባት ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ አለበት።የከተማ ቦታ እንዱለቅ የተሰጠውን ውሳኔ ማስታወቂያ በመቃወም አቤቱታ የቀረበለት አግባብ ያለው አስተዲደሩ አካል በጽሁፍ ውሳኔ መስጠት እንዲለበት በአዋጆቹ ተደንግጓል። የአስተዲደሩ አካል በአቤቱታው ላይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በውሳኔው ቅር ያለው ሰው ፣ለይግባኝ ሰሚ ጉባኤው የይግባኝ ቅሬታውን ስለሚቀርብበት ሁኔታ፣ የአዋጅ ቁጥር272/1994 በአንቀጽ 16 እና አንቀጽ17 በዛርዛር ባስቀመጣቸው ድንጋጌዎችና በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በአንቀጽ 26፣ አንቀጽ 27ና በአንቀጽ 28 ድንጋጌዎች ተደንግጎ ይገኛል ።
ከላይ በገለጽናቸውና ላልች አግባብነት ባላቸው የህግ ድንጋጌዎች ለከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተሰጠው ሥልጣንና ኃላፉነት፣የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በከተማ ቦታ ማስለቀቅ፣ሂደት የሚቀርቡ የምትክ ቦታና የካሳ ጥያቄ ጉዲዮች ላይ የሚመለከተው አስተዲደር አካል በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ሰው የሚያቀርበውን የይግባኝ ቅሬታ፣ የመቀበል፣ የይግባኝ ባዩንና የመልስ ሰጭ ክርክር የመቀበል፣ ማስረጃ በትዔዙዛ ማስቀረብና አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውሳኔ የመሰጠት ሥልጣንን የሚያካትት ነው። ይህ የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሥልጣን፣በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ንዐስ አንቀጽ1፣በአዋጅ ቁጥር 272/1994 እና ይህንን አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት የተሰጠ የዲኝነት ሥልጣን ነው።
የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤና በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ንዐስ አንቀጽ1 ከላይ በገለጽናቸው የህግ ማዔቀፍች የዲኝነት ሥልጣን የተሰጠው አካል መሆኑ የራሱ የሆነ መገለጫ፣ ባህሪና ሕጋዊ ውጤት አለው።የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በህግ የዲኝነት ሥልጣን የተሰጠው አካል መሆኑ፣ በዲኝነት ሥልጣኑ አይቶ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በሕግ አግባብ በልላ ዲኝነትሥልጣን ባለው አካል ታይተው ካልተሻሩ ወይም ካልተለወጡ በስተቀር አስገዲጅነትና ተፈጻሚነት ያላቸው ውሳኔዎች ናቸው።የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በህግ በተሰጠው የዲኝነት ሥልጣኑ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በአስተዲደሩ ክፍል ውሳኔ የሚሻሻለ፣ የሚለወጡ ወይም የሚሻሩ አይደለም።
የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በህግ በተሰጠው የዲኝነት ሥልጣኑ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በፍርድ ቤት የተሰጠ ፍርድና ውሳኔ ልዩ ባህሪና ሕጋዊ ውጤት ያላቸው ናቸው። ይህም ማለት የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በህግ በተሰጠው የዲኝነት ሥልጣኑ የሚወስናቸው ውሳኔዎች የሚሻሻለት፣ የሚለወጡትወይም የሚሻሩት በሁለት መሰረታዊ መንገድና ሥርዓትና አሰራር ነው። የመጀመሪያው የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ውሳኔ፣በህግ በተደነገገው ሥርዓት መሰረት ታይቶ የሚጸናበት፣የሚሻሻልበት፣ በሚለወጥበትና የሚሻርበት ሥርዓት የይግባኝ ሰሚ ጉባኤውን ውሳኔ በይግባኝና በሰበር ሥርዓት አይተው ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ታይቶ እንዱወሰን የሚደረግበት አሰራር ነው። ይህ አሰራር የፍርድ ቤቶችን አደረጃጀትና የይግባኝና የሰበር ሥረ ነገር ስልጣን መሰረት በማድረግ የይግባኝ ጉባኤው ውሳኔ የሚታይበት የሕግ ሥርዓት የተዖረጋለትና፣ በልምድ በዲበረ የዲኝነት አሰራር የሚደገፍ ነው።
ሁለተኛው የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደማንኛውም በህግ የዲኝነት ሥልጣን እንደተሰጠው ፍርድ ሰጭ ተቋም፣ ራሱን ውሳኔ በድጋሜ አይቶና አጣርቶ ሉወስን በሚችልባቸው የህግ ሥርዓቶች ማለትም በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ አንቀጽ 74፣አንቀጽ 78፣አንቀጽ 358ና ተከታይ ድንጋጌዎችና በአንቀጽ 6 በተደነገጉት ሥርዓቶች ጉዲዩ እንደገና በማየት፣ የሚመለከታቸውን ባለጉዲዮች ክርክርና ማስረጃ በመስማት የራሱን ውሳኔ በህግ በተደነገገው ሥርዓት መሰረት እንደገና አይቶ በማጽናት፣ በማሻሻል፣ በመለወጥና በመሻር ውሳኔ የሚሰጥበትን አሰራርና ሥርዓት በመከተልና ተግባራዊ በማድረግ ነው።
ይህም የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የዲኝነት ነክ ሥልጣን ነጻነት፣ ተጠያቂነት ማስከበሪያና የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው በዲኝነት ሥልጣኑ አከራክሮ ሲወስን የፈጸማቸው የዲኝነት አካሄድ፣ የስነ ሥርዓትና የፍርድ ስህተት በራሱ እንደገና ታይቶ ከሚታረምበት መሰረታዊ የዲኝነት የስራ አካሄድና የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው በህግ ከተሰጠው የዲኝነት ስልጣን መሰረታዊ ተቋማዊ ባህሪው የሚመነጭ ነው። ከዘህ አንጻር በህግ በተደነገገው ሥርዓት መሰረትየከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀደም ብል የሰጠው ውሳኔ በድጋሜ አይቶ ውሳኔ እንዱሰጥ የሚቀርብለትን አቤቱታ በመቀበልና መርምሮ ውሳኔ መስጠት ከተፈጥሯዊ ተቋማዊ የዲኝነት ነክ ሥልጣኑ የሚመነጭ ሥልጣን ይኖረዋል።
ከላይ በዛርዛር ከገለጽናቸው ሕገ መንግስቱና ላልች የህግ ድንጋጌዎች ይዖትና ዓላማአንጻርበከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀደም ብል በሰጠው ፍርድ ላይ በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ አንቀጽ 358ና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የሚቀርብለትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ተቀብል የማየት፤ ተከራካሪ በመሆንየሚቀርቡ ሰዎች የሚያቀርቡትን ክርክር የመስማት አጣርቶ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣኑ የሚመነጨው፣ለይግባኝ ሰሚ ጉባኤው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ንዐስ አንቀጽ1፣አዋጅ ቁጥር272/1994 እና ይህንን አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር721/2004 መሰረት ከተሰጠው የዲኝነት ነክ ሥልጣኑ የሚመነጭ ነው።
ይህም የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው የዲኝነት ሥልጣኑ ዋና ባህሪና መገለጫ፣የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ውሳኔ መስጠት ነጻነት፣ የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ውሳኔ አስገዲጅነት፣ ተፈጻሚነት ተጠያቂነት ማስከበሪያ መንገድ ነው። የአሰራር ሥርዓቱ የይግባኝ ሰሚ ጉባኤው በዲኝነት ሥልጣኑ አከራክሮ ሲወስን የፈጸማቸው የዲኝነት አካሄድ፣ የስነ ሥርዓትና የፍርድ ስህተት በራሱ እንደገና አይቶ የሚታረምበት አሰራር ነው። ከዘህ አንጻር ሲታይ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ አንቀጽ 358 ና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ተጠሪዎች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ የመቀበልና መርምሮ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን፣ ከላይ የተገለጹትን ሕግ ድንጋጌዎች ይዖት፣ መሰረታዊ ዓላማ፣ ተግባራዊ ተፈጻሚነትና ህጋዊ ውጤት ያላገናዖበ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑምየአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ሰሚ ችልትና የከተማው አስተዲደር የሰበር ችልት፣ የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጠሪዎችን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አይቼ የመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠውን ብይን በመሻር፣ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ተጠሪዎች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ በመቀበል መርምሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ አንቀጽ 341(1) መሰረት መመለሳቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
No topics extracted.