No summary available.
ቀን ሚያዘያ 30/2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ጤና ጋርደዉ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ መደቅሴ ገርቢ - ወኪል ያደታ ጋረደ ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዘህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የእርሻ መሬት ጉዲይ ሆኖ የተጀመረው በጉደያ ቢላ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። የአሁንተጠሪ ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አቶ ታከለ ቁያሳ ተከሳሽ እንዱሁም የአሁን የሰበር አመልካች ጣልቃ ገብ ነበሩ።ተጠሪ አቅርበዉት የነበረዉ ክስ ይዖት፡-የስር ተከሳሽ የነበረው አቶ ታከለ ቁያስ መጠኑ 1½ ሄክታር የሆነውን ይዜታ በ2006 ዓ.ም እኔ በማላውቀው ሁኔታ ያለ ፈቃዳ ይዜብኛል። ስለዘህ ተከሳሹ በሕገ-ወጥ መንገድ የያዖብኝን ይዜታዬን እንዱለቅልኝ የሚል ነው።
የስር ተከሳሽ በሰጡት መልስ ይዜታዉን በ01/08/2004 ዓ.ም በተፃፈው ውል አቶ ጤና ጋረደው ላይ ኮንትራት ወስጄ እያረስኩ እገኛለሁ እንጂ ከሳሽ እንደሚለት አይደለም፣ ከሳሽ እኔ ኮንትራት የወሰድሁት መሬት ላይም ምስክር ሆነው በውላችን ላይ ስለነበሩ ሉጠይቁኝ አይችለም በማለት ተከራክሯል።የአሁኑ አመልካችም የስር ጣልቃ ገብ ሲሆኑ ከሳሽ ድንበሩን እና ቦታውን ጠቅሳ ክስ የመሰረተችበት ይዜታ መሬት በአከባቢያችን ባህል መሰረት በ1986 ዓ.ም እኔ ጋብቻ ስፈፅም ከሳሽ እና አባቴ አብረው በመሆን ሰጥተውኛል። ከዘያ ወዱህም ይህንን ንብረት እየተጠቀምኩበት ቆይቼ በ01/08/2004 ዓ.ም በተፃፈው ውል እስከ 2007 ዓ.ም ለ3 /ሶስት/ አመት ለተከሳሹ አከራይቻለሁ። ስለዘህ ከሳሽ የእሷ ባልሆነ ይዜታ ላይ የእሷ አስመስላ ክስ ማቅረቧ ትክክል ስላልሆነ መዛገቡ እንዱዖጋ በማለት አቤቱታ አቅርቧል። የአሁኑ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ክርክር ያስነሳው ይዜታ በወቅቱ በአካባቢያችን ባህል መሰረት ጋብቻ ስፈፅም በስጦታ መልክ ተሰጥቶኛል በማለት ያቀረበው አቤቱታ እውነት አይደለም። እኔም ሆንኩ አባቱ ይህንን ይዜታ ለጣልቃ ገብ አልሰጠንም። እስካሁን ድረስም በባላ ስም ተመዛግቦ የሚገኝ ስለሆነ የጣልቃ ገቡ አቤቱታ ውድቅ ሆኖ ከክርክር ውስጥ እንዱወጣ በማለት ተከራክሯል።
የወረዲ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃዎችን ተመልክቶ ክርክር ያስነሳው ይዜታ በፉት የከሳሿ እና የባሎ የነበረ መሆኑ ከቀረበው የሰውና የፅሁፍ ማስረጃ መረዲት ይቻላል። ተከሳሽ ደግሞ ይዜታውን ከጣልቃ ገብ በኮንትራት ወስድ ይዜታውን በተከታታይ ለሶስት አመታት ያረሰ መሆኑ፣ ይዜታው ደግሞ በ1986 ዓ.ም ጣልቃ ገቡ በሚያገባበት ወቅት በአካባቢው ባሕል መሰረት ‛ጎጆ መውጫ“ በሚል ስጦታ ተሰጥቶት ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ይዜታውን በመያዛ እንደአሰፈላጊነቱ ሲፈለግ በራሱ እያረሰ ላላ ጊዚ ደግሞ እኩል እየሰጠ የሚጠቀምበት መሆኑ ተረጋግጧል። ከሳሽ ተከሳሹ ክርክር የተነሳበትን መሬት ለሶስት አመት ማረሱን እና ጣልቃ ገቡ ደግሞ ለረጅም አመታት ይዜ መቆየቱን እያወቀች ይህንን ሁለ ጊዚ ቆይታ በአሁኑ ወቅት በ2006 ዓ.ም ተይዜብኛል በማለት ክስ ማቅረቧ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1149/2/ ድንጋጌ መሰረት የሕግ አግባብነት የላለው ስለሆነ ክርክር የተነሳበት ይዜታም ለረጅም ጊዚ በተለያየ ምክንያት ከከሳሿ እጅ የወጣ በመሆኑ ያቀረበችው ክስ የሕግ አግብብነት ያለው ስላልሆነ ተከሳሹን አያስጠይቅም በማለት ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ ተጠሪ የወረዲው ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለምስራቅ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ ክርክር የተነሳበት ይዜታ የአሁን ተጠሪ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የስር ፍርድ ቤት ይህንን አልፍ ክርክር የተነሳበትን መሬት ይግባኝ ባይዋ በፍ/ሕ/ቁ. 1149/2/ መጠየቅ አትችልም ብል ክሷን ውድቅ ማድረጉ ከደንብ ቁጥር 152/32 ጋር የሚቃረን ስለሆነ የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነዉ በማለት ዉሳኔዉን በመሻርክርክር ያስነሳዉ ይዜታ ለአሁን ተጠሪ ይገባል ሲል አመልካች እንዱለቅ ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ አያስቀርብም በማለት ይግባኙን ዖግቷል።አመልካች የከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የክልለ ሰበር ሰሚ የግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ውሳኔውን አፅንቷል። የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ነዉ።
አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ይዖት፡- ከከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአካባቢውን ባህልና ወግ መሰረት ሳያደርጉ በጋብቻ ላይ በጎጆ መውጫነት የሚሰጠው መሬት ሰጪው በሕይወት እያለ ወደ ራሴ ይዘርልኝ ጥያቄ መቅረብ እንደማይገባ፣ አመልካች ግን በዘሁ በተሰጠኝ ቦታ ላይ ቤት ንብረት አፍርቼ የወለድኩበት መሆኑን ሳይረደ የመሬቱ ስምም ሆነ መታወቂያው በወላጅ አባቴ ስም ስለሚገኝ ብቻ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት እና ይዜታ እንድለቅ መወሰኑ ሕግን የተከተለ አይደለም። የአሁኗ ተጠሪም ለክርክሩ መነሻ በሆነው ይዜታ ኮንትራት ውል ላይ እንደምስክር ሆና የፈረመችበት ስለመሆኗ በስር ወረዲ ፍርድ ቤት ላይ በግልፅ ተቀምጦ እያለ ከከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ያለት ችልቶች ግን ላላ ማስረጃ ሳያስቀርቡ ከ20 አመት በላይ በእጄ ይዢ የምጠቀመበት ይዜታ መሆኑ በማስጃዎቼ ተረጋግጦልኝ እያለ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ ሕግ ስህተት ስለሆነ ተሽሮ የጉደያ ቢላ ወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱፀናልኝ የሚል ነዉ።
አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች አከራካሪውን መሬት በ1986 ዓ.ም በስጦታ አግኝቶ እስካሁን እየተጠቀመበት ባለበት ሁኔታ እንዱያስረክብ መወሰኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
ተጠሪ መልስ ባለማቅረባቸዉ መልስ የመስጠት መብታቸዉ ታልፍ ጥቅምት 07 ቀን 2009 ዓ.ም ዉሳኔ ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በላለበት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱነሳላቸዉ ተጠሪ አቤቱታ አቅርበዉ ተቀባይነት በማግኘቱ ዉሳኔዉ ተነስቶ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
ተጠሪ ለአቤቱታዉ የሰጡት መልስ ይዖት፡- አመልካች ክርክር ያስነሳዉን መሬት አንዳ በሕጋዊ መንገድ ተሰጥቶኛል እያለ፤ አንዳ ደግሞ ስጦታዉ ተፈጻሚ የሚሆነዉ የአካባቢዉን ባሕል መሰረት በማድረግ ነዉ በማለት የሚያነሳዉ ነጥብ የሕግ ድጋፍ የለዉም።ተጠሪ ዉል አለማድረጓን ከሥር ጀምራ የተከራከረች ሲሆን የወረዲዉ መሬት እና የአከባቢዉ ጥበቃ ጽ/ቤት በጻፈዉ ደብዲቤ ይዜታዉ በተጠሪ ባለቤት ስም እንዲለ እንጂ በስጦታ ስለመተላለፈ የቀረበ ማስረጃ የለም የሚል ሆኖ እያለ አመልካች ዉል ለመኖሩ ተረጋግጦልኛል የሚለዉ ተቀባይነት የለዉም።
አመልካች በ1986 ዓ.ም ሲያገባ ሁለት ሄክታር መሬት ተሰጥቶት ነበር ቢባል እንኳ አንድም ቀን ተጠቅሞበት እንደማያዉቅ ተረጋግጧል። ተጠሪ መሬቱን ይዙ እስከ አሁን ግብር እየከፈለች ስትጠቀምበት እንደነበረ እና አመልካች ደግሞ የገጠር መሬት ትቶ ቢላቲ ከተማ ይኖር እንደነበረ በመ/ ላይ በቀረበዉ ማስረጃ ተረጋግጧል። ስለሆነም የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ተደርጎ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ዉሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነዉ። አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን ከስር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዖዉ ጭብጥ ጋር በማገናዖብ መርምረናል። እንደመረመርነዉም የአሁኑ አመልካች ያቀረባቸው ሁለት የሰው ምስክሮች ክርክር የተነሳበትን ይዜታ እንደሚያውቁ፣ በ1986 ዓ.ም ጣልቃ ገቡ ሲያገባ በአካባቢው ባሕል መሰረት ለጎጆ መውጫ ተጠሪ ከባሎ ጋር ክርክር ያስነሳዉን ይዜታ ለአመልካች መስጠታቸውን እና ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ይዜታዉን አመልካቹ ይዜ አንዲንዳ በራሱ እያረሰ እየተጠቀመ፣ አንዲንድ ጊዚ ደግሞ የእኩል ሰጥቶ የሚጠቀምበት መሆኑን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ለሶስት አመት ኮንትራት ለስር ተከሳሹ መስጠቱን እንደሚያውቁና ይዜታው ከ20 አመት በላይ በአመልካች እጅ የሚገኝ መሆኑን እንደመሰከሩ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ ያረጋግጣል። ከዘህ በተጨማሪ በአካባቢው ባህል መሰረትአመልካቹ ክርክር የተነሳበት ይዜታ መስጠቱን የሚገልፅ መጋቢት 12 ቀን 1986 ዓ.ም የተፃፈ የስጦታ ውል ቀርቧል። ላላዉ በአመልካች እና በስር ተከሳሽ መካከል በተደረገዉ የኪራይ ዉል ተጠሪ በምስክርነት መፈረሟና በስር ፍ/ቤት በተደረገዉ ክርክር ይህንኑ በግልጽ ክዲ አለመከራከሯ መሬቱ ለአመልካች በስጦታ የተሰጠ መሆኑን በተጨማሪነት የሚያረጋግጥ ነዉ። የተጠሪ ምስክሮችም ቢሆኑ የስር ተከሳሽ መሬቱን በምን መልክ መያዘን ባያዉቁም ለ3 ተከታታይ ዓመት ይዜ እያረሰ ይጠቀምበት መሆኑን መመስከራቸዉ ሲታይ ተጠሪ በመሬቱ መጠቀም ካቆሙ ረጅም ጊዚ ያለፈዉና የአመልካችን ክርክር የሚያጠናክር መሆኑን መገንዖብ ይቻላል።
በልላ በኩል የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የወረዲዉ ፍ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ ለመሻር የሰጠዉ ምክንያት የእርሻዉ መሬት እስካሁን በተጠሪ ባለቤት ስም ተመዛግቦ የሚገኝ እና ግብር የሚከፈልበት መሆኑን ነዉ። ነገር ግን ክርክር ያስነሳዉ መሬት በ1986 ዓ.ም አመልካች ሲያገባ ለጎጆ መዉጫ ተብል እስከተሰጠዉና በተግባር በይዜታዉ ስር አድርጎ በራሱም ሆነ እያከራዬ ከ20 ዓመት በላይ እየተጠቀመበት የሚገኝ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በአባቱ ስም መሆኑና ግብር መከፈለ ብቻ በመሬቱ ላይ ያለዉን የባለይዜታነቱን መብት አያስቀርበትም።
በመሰረቱ የኦሮሚያ ክልል ገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 2/3/ ሕጋዊ የመሬት ይዜታ ማለት ሕጋዊ በሆነ ሁኔታ አግባብ ባለው አካል ለተጠቃሚዎች የተሰጠ መሬት፣ ወይም በውርስ ወይም በስጦታ የተገኘ መሬት ማለት ነው በማለት ሲደነግግ፤
የአዋጁ አንቀጽ 9(5) ደግሞ ባለይዜታዉ በመሬት ይዜታው የመጠቀም መብቱን በዘያ መሬት ገቢ ለሚተዲደሩ ወይም ላላ ገቢ ለላላቸው የቤተሰብ አባላት ወይም መሬት ለላላቸው ልጆቹ በስጦታ ማስተላለፍ እንደሚችል ይደነግጋል። በዘህ ድንጋጌ መሰረት ተጠሪና ባለቤታቸው ለአሁኑ አመልካች ክርክር የተነሳበትን ይዜታ በስጦታ አስተላልፈዉ ተጠቃሚ አድርገዉታል። አመልካች ከ20 ዓመት በላይ ተጠቃሚ የሆነበት መሬት መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ መሬቱ በስጦታ ሰጪዉ ስም እስከአሁን ተመዛግቦ መገኘቱ እና ግብር በስሙ መከፈለ ብቻ ይዜታዉ በስጦታ ዉል አልተላለፈም የሚያሰኝ አይሆንም።
ሲጠቃለል አመልካች ክርክር የተነሳበትን መሬት በሕጋዊ መንገድ አግኝተው ከ20 /ሃያ/ አመት በላይ በእጃቸው ይዖው በራሳቸዉም ሆነ አከራይተዉ ሲጠቀሙበት የቆዩ መሆናቸው በሚገባ ተረጋግጦ እያለ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ይዜታውን ለተጠሪ እንዱመልሱ በማለት ዉሳኔ መስጠቱ የአመልካችን ከይዜታዉ ያለመፈናቀል ሕገ-መንግስታዊ መብት የሚጥስ ሆኖ እያለየክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ሆነ ሰበር ሰሚ ይህን ተቀብለው በማጽናት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በምስራቅ ወለጋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 18 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ፤በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 20 ቀን 2007 ዓ.ም በተሰጠ ዉሳኔእናበኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ ታሕሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም በተሰጠ ትዔዙዛ የጸናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የጉደያ ቢላ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ታሕሳስ 02 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ክርክር ያስነሳዉ የእርሻ መሬት አመልካች ለተጠሪ ለማስረከብ አይገደድም ተብል ተወስኗል።
አፈጻጸሙ ለጊዚዉ ታግድ እንዱቆይ
No topics extracted.