No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- 1ኛ አቶ ባንኩ ኢሩስ 2ኛ አቶ ኤሉያስ ታኒ ተጠሪ፡- አቶሳምሶን ገ/ዬሀንስ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የገጠር እርሻ መሬትን የሚመለከት ሆኖ የግራ ቀኙ ክርክር የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ በበንች ማጂ ዜን የሾኮ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኖቹ አመልካቾች ከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።የአሁኖቹ አመልካቾች ከሳሽ በመሆን በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ይዖት ባጭሩ፡- ከተከሳሽ ጋር ግንቦት 19 ቀን 2004 ዓ/ም በተፃፈ ውል በጅምርሶ ቀበላ ልዩ ስሙ ምንካታ ተብል በሚጠራው መንደር በምስራቅ የአቶ አዱሱ ገመዲ የእርሻ ማሳ፣በምእራብ የጋቸብ ወንዛ፣በስሜን የአቶ ሳሙኤል የቡና ማሳ፣በደቡብ የአቶ አዱሱ ገመዲ ይዜታ መሬት የሚያዋስነው የራሱ የሆነ ለመልማት የሚችል ይዜታ መሬት ተከሳሽ ለለማው የቡና ይዜታ 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር) ተገምቶ ገንዖቡን ለተከሳሽ ከፍለን ያልለማው ቡና ውለ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ የእኛ እና የተከሳሽ የጋራ የቡና ልማት እንዱሆን ተስማምተናል ። ለተከሳሽ ከከፈልነው ገንዖብ በተጨማሪ የለማውን ቡና ለመንከባከብ አዱስቡናለማስተከል ብር 50,000(አምሳሺህብር ) ወጪ በማድረግ አልምተናል።ለጀምሩስ ቀበላ ፅ/ቤትበቡናው ይዜታ ውስጥ ከሳሾች እንዲይገቡ በማለት ተከሳሽ ህዲር 21 ቀን 2006 ዓ/ም ፅፍያስገባ በመሆኑ እኛም ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ በይዜታው መሄድ አቁመናል።ተከሳሽ የ2006 ዓ/ም የቡና አላባ ለብቻው የተጠቀመ ስለሆነ ድርሻችን 112,666ብር ተከሳሽ እንዱከፍለንና በውለ መሰረትቡናው የጋራ ተብል እንዱወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።የአሁኑ ተጠሪ የስር ተከሳሽ በመሆን ባቀረበው መልስ ከከሳሾች ጋር በጋራ ለመስራት ውል ያደረግን ቢሆንም ይህንን መሰረት አድርገው ይዜታው የጋራ ነው ተብል ይወሰንልን ብለው ያቀረቡትጥያቄ ውለ ህግ የሚጠይቀውን መስፈርት ያላሟላ ስለሆነ የህግ መሰረት የለውም ። የ2006 ዓ/ም አላባ እንድከፍላቸው ያቀረቡት ጥያቄም በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመርያ ደረጃ የተመለከተው የሸኮ ወረዲ ፍርድ ቤት ክሱንና የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቶ አጠቃላይ ክርክሩን ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ 95,962 (ዖጠና አምስት ሺህ ዖጠን መቶ ስልሳ ሁለት ብር ) ይክፈል፤ክርክር ያስነሳውበጀምሩስ ቀበላ ልዩስሙ ሞንኪታየሚባለው ቦታ ያለው የቡና ይዜታየግራቀኙ የጋራ ይዜታ ሆኖ በጋራ እንዱጠቀሙ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዘሁ ውሳኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበውም የቀረበው ይግባኝ ሰርዜታል።የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት አቤቱታው ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ፍ/ቤቱ የቀረበው አቤቱታና የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ አጠቃላይ ክርክሩን ከመረመረ በኋላአመልካቾች በይዜታው ላይ አወጣነው የሚለትን ገንዖብ አግባብ በሆነ መንገድ ከመጠየቅ ውጪ ህገወጥና ፈራሽ በሆነ ውል መሰረት ያቀረቡት ክስ መነሻነት የስር ፍርድ ቤቶች የቡና ማሳው የጋራእንዱሆን የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል።አሁን የቀረበው ቅሬታ በዘሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአመልካቾች አቤቱታ ተመርምሮለሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸው ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ ፅሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዋች ጋር በማገናዖብ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የመጀመሪያው ጭብጥ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 12(4) መሰረት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቀርቦ ሳይታይ በቀጥታ ተቀብል ማየቱ ስነ-ስርአታዊ ነው? ወይስ አይደለም? የሚል ሲሆን ጉዲዩ የመሬት መጠቀም መብት ይገባኛል ጥያቄ ጋር የተያያዖ በመሆኑ መታየት ያለበት በመሬት አዋጁ መሰረት ስለመሆኑ አከራካሪ አይደለም። የደቡብ ብሄር ብሓረሰቦች ሕዛቦች ክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 የክርክሮች አወሳሰን አስመልክቶ በአዋጁ አንቀፅ 12(1) እንደተደነገገው የገጠር መሬት ይዜታ መብትን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ አቤቱታ ለቀበላው የመሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ኮሚቴ ቀርቦ በተከራካሪ ወገኖች በፍቃደኝነት በተመረጡ ሽማግላዎች አማካኝነት ታይቶ በእርቅና በድርድር እንዱፈታይደረጋል።በሽማግላዎቹ እርቅና ድርድር ያልተስማማወገን ለወረዲው መደበኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዲለው በዘሁ አዋጅ አንቀፅ 12(2) ተመልክቷል።ይህ በእንዱህ እንዲለ የወረዲው መደበኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተስማማ ወገን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል ፣በዘህ ውሳኔ ያልተስማማ ወገን በተጨማሪ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ የማቅረብ መብት እንዲለው በአዋጁ አንቀፅ 12(4) ተደንግጎ እናገኛለን ። ወደያዛነው ጉዲይ ስንመለስ ከክርክሩ ይዖት ለመረዲት የተቻለውየሸኮ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ባለመስማማት ተጠሪ ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱ የስር ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ በማፅናቱ ተጠሪ በቀጥታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ መሆናቸው መዛገቡ ያመለክታል።
በመሰረቱ በገጠር የእርሻ መሬት የመጠቀም መብት፣መብቱን በዉርስ የማስተላለፍ እና መሰል መብቶች ጥበቃ ያገኙት በፋደራል መንግስት በወጣዉ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/1997 ሲሆን ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም ደግሞ ዛርዛር ሕጎች የሚወጡት በእያንዲንደ ክልል ምክር ቤት ስለመሆኑ በአዋጅ አንቀፅ 17 ስር በግልፅ ተመልክቷል ።
እንዱሁም በገጠር የእርሻ መሬት የይዜታ መብት ላይ የሚነሳው ክርክር ጉዲዩ በሚመለከታቸው ተከራካሪዎች በውይይትና በስምምነት እንዱፈታ ጥረት የሚደረግ ስለመሆኑ እና በስምምነት ሉፉታ ካልቻለ በተከራከሪ ወገኖች በተመረጡ ሽምግልና ወይንም በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር ሕግ በተደነገገው መሰረት የሚወሰን ስለመሆኑ በዘሁ አዋጅ አንቀፅ 12 ስር ተደንግጎ ይገኛል። በአዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀፅ 17 ድንጋጌ መሰረትም የደቡብብሓሮች ብሓረሰቦችክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 እና አዋጁን ለማስፈፀም ደንብ አውጥቶ በስራ ላይ ያዋለሲሆን በዘህ አዋጅ እና ደንብ በተዖረጋዉ ስርዓት መሰረት በስምምነት እና በሽምግልና እልባት ያላገኙ ጉዲዩችን በመጀመርያ ደረጃ አይቶ የመወሰን የስረ ነገር ስልጣን አስመልከክቶ የክርክሮች አወሳሰን በሚል ርእስ ስር በአዋጁ አንቀፅ 12ስር ተመልክቷል። ከገጠር የእርሻ መሬት ጋር ተያይዖዉ የሚነሱ አለመግባባቶች እና ክርክሮች በስምምነት እና በሽምግልና መፈታት ካልቻለ ክልልች በሚያወጡት ሕግ መሰረት ውሳኔ እንዲያገኙ እንደሚደረግ የሚደነግገዉ አዋጅቁጥር 456/1997 እና የደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች ክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 በክልለ ምክር ቤት የወጣው የተሻሻለውየክልለ ፍርድ ቤቶች ማቋቋምያ አዋጅ ቁጥር 43/94 ከወጣ በኃላ ነው። አዋጅ ቁጥር 43/94 የወረዲ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመሳሳይ ውሳኔ የሰጡ እንደሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆኑ ከታመነበት አቤቱታውበቀጥታ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሚቀርብ ስለመሆኑ ተመልክቷል።
ሕግ አውጪው የአዋጅ ቁጥር 43/94 ምእራፍ ሶስት ‛የፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን“ በሚለው ርእስ ስር የተመለከተው ድንጋጌ መኖሩን እያወቀ ከገጠር የእርሻ መሬት ጋር ተያይዖው የሚነሱት አለመግባባቶች እና ክርክሮች በስምምነት እና በሽምግልና መፈታት ካልቻለ በሚያወጡት ሕግ መሰረት ውሳኔ እንዱያገኙ በአዋጅ ቁጥር 456/1997 መደንገጉና በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 12(4) የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ያልተስማማ ወገን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጨማሪ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል መደንገጉ ከእርሻ መሬት ጋር ተያይዖው የሚነሱት ክርክሮች ካላቸው ልዩ ባህርይ አንጻር ከላልች ጉዲዬች በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ የይግባኝ መብት መስጠቱ እና ከገጠር መሬት የይዜታ ክርክር አንፃር ቁጥር 456/1997 ልዩ ሕግ መሆኑን ከአጠቃላይ የሕግ አወጣጥ ስርዓት መርህ መገንዖብ ይቻላል ።ይህም ከገጠር የእርሻ መሬት ይዜታ ጋር ተያይዜ ለሚነሳው ክርክር በመሬት አዋጁ መሰረት ሉመራ የሚገባው ነው ብለናል።
ከላይ በዛርዛር በተመለከተው መሰረት አቤቱታው የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 12(5) መሰረት በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ይኖራል ተብል ከታሰበ የማየት ስልጣን እንዲለው ተመልክቷል።በዘህ ጉዲይ መታየት ያለበት መሰረታዊ የክርክር ነጥብ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ትዔዙዛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ መሰረት አለው ወይስ የለውም? የሚል ነው።
በመሰረቱ አንድ ጉዲይ ለሰበር ሰሚ ችልት ብቁ ሁኖ ላታይ የሚችለው ጉዲዩ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ስለመሆኑ በቅድሚያ ሲረጋገጥ ነው። በኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3) (ሀ) ፣ በክልለ ህገ መንግስት አንቀፅ 75 (2(ሐ)) እና የክልለ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም በወጣው የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 43/1994 አንቀጽ 5(3) ድንጋጌ በግልጽ እንደተመለከተው አንድ ጉዲይ ለሰበር ሰሚ ችልት ብቁ የሚሆነው አቤቱታ የቀረበበት ጉዲይ የመጨረሻ ውሳኔ (Final court decision) ያገኘ መሆን ያለመሆኑን በቅድሚያ መረጋገጥ ያለበት መሰረታዊ ነጥብ ስለመሆኑ የድንጋጌዎቹ ይዖትና መንፈስ ያስገነዘቡናል። በመሆኑም ሰበር ሰሚ ችልት የመጨረሻ ፍርድ ባላገኙ ጉዲዮች ውሳኔ የመስጠት ስልጣንና ኃላፉነት ያልተሰጠው መሆኑን መረዲት ይቻላል።
በልላ አገላለጽ ለሰበር ብቁ ያልሆኑ የመጨረሻ ፍርድ ያላገኙ ጉዲዮች በሰበር ሰሚ ችልት ሉስተናገደ የሚችለበት ስርዓት አይኖርም።
ስለሆነም በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 12(4) የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ያልተስማማ ወገን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጨማሪ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል እንዱሁም በዘሁ አዋጅ አንቀፅ 12(5) እንደተደነገገው በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ይኖራል ተብል ከታሰበ ሰበር ሰሚ ችልቱ የማየት ስልጣን እንዲለው በግልፅ ተደንግጓል። በያዛነው ጉዲይ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያልደረሰና የመጨረሻ ፍርድ ያላገኘ ስለሆነ ፣ ሰበር ሰሚ ችለቱ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት አለመሆኑን ተገንዛቦ ስልጣንን በተመለከተ ከተከራክሪ ወገኖች የቀረበለት ተቃውሞ ባይኖርም በፍትሃብሓር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 9(1)እና 231(1) (ለ) እንደተመለከተው በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ቀርቦ ሉስተናገድ በሚችል ደረጃ የመጨረሻ ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ለዘህ ችልት ብቁ አይደለም ስልጣን የለኝም በማለት መመለስ ና ማረም ሲገባው ተቀብል በማስተናገደም ሆነ ውሳኔ መስጠቱየህግ ድጋፍ የለውም ብለናል።
ሲጠቃለል የቀረበው ጉዲይ የገጠር መሬት አዋጅ ልዩ ከመሆኑና ገጠር መሬትን መሰረት በማድረግ ለሚነሱ ክርክሮች አወሳሰን፣ በአዋጁ አንቀፅ 12 የተደነገገውን ድንጋጌመሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም አቤቱታ የቀረበበት ውሰኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.