በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ስጦታው በተደረገበት የእርሻ መሬት ላይ በቤተሰብነት የተመዖገበ አባልን ያገለለ መሆኑ ከታወቀ ይኸው ሰነድ በህግ ተቀባይነት የማይኖረው ስለመሆኑ ህጉን ያልጠበቀ የገጠር መሬት ይዜታ በኑዙዚ ወይም በስጦታ ተላልፎል የሚለው ወገን መብቱን ለማስጠበቅ በሁለት ዓመት መጠየቅ ነበረበት ልባል የሚችል ስላለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2441፣ አዋጅ ቁጥር 456/97 የአ/ብ/ክ/መ/የመ/አስ/አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/98 አንቀጽ 16/3 ፣ ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/2
No summary available.
ሰኔ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ አዙል አይናለም -ተወካይ ጌትነት ተረፈ ተጠሪ፡- 1ኛ፣ አቶ ምህረት በላይ -ቀረቡ 2ኛ. የቡሬ ዖ/ወ/አከ/ጥ/መ/አስ/አጠ/ፅ/ቤት -አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የእርሻ መሬት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩም የተጀመረው በአ/ብ/ክ/መንግስት የቡሬ ወረዲ ፍ/ቤት ነው ። በዘያ ደረጃ አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች ነበሩ ። አመልካች በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አቤቱታ፡- ከሳሽ የፈፀምኩት የስጦታ ውል መንፈስ ልልነት እና አቅመደካማ በመሆኔ የፈፀምኩት ስለሆነ የስጦታ ውለ ሉፈርስ ይገባል በማለት ዲኝነት ጠይቋል።1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ በመሆን ባቀረበው መልስ ከሳሽ ያቀረበው ስጦታ ይፍረስልኝ ጥያቂ ይርጋ ጊዚው ያለፈው ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል በማለት የተከራከረ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በበኩለ ከሳሽ የፈፀመው ስጦታ ውል በህግ መሰረት የተደረገ ስለሆነ የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዲው ፍርድ ቤትም በስር ተከሳሾች የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወምያ መሰረት በማድረግ ስጦታው ተደረገ ከተባለው ጊዚ ጀምሮ በሁለት አመት ውስጥ የይረሰዛልኝ ጥያቄ ስላልቀረበበት ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2441 መሰረት በይርጋ የታገደ ነው በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። በዘህ ብይን የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። እንዱሁም የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር አቅርቦም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብል ተሰርዜበታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ብይን በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- በተጠሪዎች የቀረበው መቃወምያ የፍትሃብሄር ህጉን በመጥቀስ ሲሆን ይህ ክርክር ግን የሚዲኘው በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 133/98 ፣እና ደንብና መመሪያ እንጂ በፍትሃብሄር ህጉ መሰረት ባለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ሉሻር ይገባል የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለዘህ ችልት ቀርቦ እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው የፅሁፍ ክርክራቸው ተለዋውጠዋል።
የጉዲዮ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ጭብጥ የአመልካች ክስ በይርጋ የታገደ ነው ተብል ውድቅ መደረጉ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ ተገኝቷል። ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረቱት የፈፀምኩት የስጦታ ውል መንፈስ ልልነት እና አቅመ ደካማ በመሆኔ የፈፀምኩት ስለሆነ ስጦታው ሉሰረዛ ይገባል በማለት መሆኑን፣ ተጠሪ ደግሞ ጉዲዩ በሁለት አመት ይርጋ የሚዖጋ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው የበታች ፍርድ ቤቶችም የተጠሪን የመቃወሚያ ነጥብ በመያዛ ክሱን በይርጋ ውድቅ ያደረጉ መሆኑን ነው።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 16/3 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም ባወጣው ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/2 እንደተደነገገው የአሁኑ ተጠሪ ዋጋ ያለው የስጦታ ማስረጃ አቅርበናል እንኳ ቢባል ስጦታው በተደረገበት የእርሻ መሬት ላይ በቤተሰብነት የተመዖገበ አባልን ያገለለ መሆኑ ከታወቀ ይኸው ሰነድ በህግ ተቀባይነት የማይኖረው መሆኑን መገንዖብ ይቻላል።
በደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/2/ በተመለከተው መስፈርት መሰረት መሬት ያዟ በሞተበት ወቅት የእራሱ የሆነ ቤተሰብ እያለው ባደረገው ስጦታ ቤተሰቡን የሚነቅል ሆኖ በመገኘቱ የተነሣ ስጦታ በህግ ፉት ተቀባይነት የላለው ሆኖ በተገኘ ጊዚ የእርሻ መሬት ለማን እና እንዳት በውርሱ ሉተላለፍ እንደሚገባ በዘሁ ደንብ አንቀጽ 11/7/ ስር ከፉደል /ሀ/ እስከ /መ/ የተቀመጠውን ቅደምተከተል በመጠበቅ እንደሆነ ተደንግጓል።
የስር ፍርድ ቤቶች ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2441 ድንጋጌ መሰረት በሁለት አመት ይርጋ የሚታገድ መሆኑን የሰጡት ውሳኔ አግባብነት ተመልክተናል። ጉዲዩ የገጠር እርሻ መሬት ስጦታን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩ የሚገዙው ልዩ በሆኑት የገጠር መሬት አስተዲደር ሕጎች ነው። በዘህ ረገድ ተፈጻሚነት ያላቸው ሕጎች በፋዳራለ መንግስት የወጣው አዋጅ ቁጥር 456/97፣በክልለ ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 133/98 እና ደንብ ቁጥር 51/99 እንዱሁም ይህንኑ ተከትል በክልለ የወጣው መመሪያ ናቸው። እነዘህ ሕጎች አንድ የገጠር እርሻ መሬት የሚተላለፍባቸውን መንገድች የሚያሳዩ ሲሆን ከእነዘህ መንገድች መካከል በውርስና በስጦታ ይዜታው የሚተላለፍበትን አግባብ የሚመለከቱ ይገኙበታል። የገጠር እርሻ መሬት በውርስና በስጦታ ሲተላለፍም በሕጎቹ የተቀመጡ ክልከላዎችና እነዘህ ክልከላዎች ሳይከበሩ የሚደረግ ኑዙዚ መኖሩ ሲረጋገጥ የይዜታ መብቱ የሚተላለፍላቸው ወገኖች ቅደም ተከተል መኖሩን የደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11(2) እና (7) ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል።
ስለሆነም በሕጉ ክልከላ የተደረገባቸው የይዜታ ማስተላለፍ ሁኔታዎች ያለ ሲሆን ሕጉን ያልጠበቀ የገጠር መሬት ይዜታ በኑዙዚ ወይም በስጦታ ተላልፎል የሚለው ወገን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2441 አግባብ በሁለት አመት መጠየቅ ነበረበት ልባል የሚችል ያለመሆኑን ከልዩ ሕጎቹ ድንጋጌዎች ይዖት እና መሰረታዊ አላማ የምንረዲው ሁኖ አግኝተናል። የሁለት አመት ይርጋ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው ከተባለ ደግሞ ከአመልካቾች እድሜና ላልች ሕጋዊ ምክንያቶች ጋር ተያይዜ በመታየት እልባት የሚያገኘው ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካች በእድሜ የገፈ መሆናቸውን የክርክሩ ሂደት ስለሚያሳይ እና ይህም ጉዲዩ በልላ የይርጋ ዖመን የሚቋረጥ መሆን ያለመሆኑ ላይ ክርክር ሉያስነሳ የማይገባ ሁኖ ስለአገኘው አግባብነት ያለውን የይርጋ ዖመን ከወዱሁ መለየቱ ተገቢ ሁኖ አልተገኘም። ስለሆነም ክሱ በይርጋ የሚታገድ ሁኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የክስ ይዖት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2441 ድንጋጌ ይዖት፣መንፈስና ዓላማ ጋር በአግባቡ ሳያገናዛቡናያለ ቦታው ጠቅሰው የአመልካች ክስ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ብይን ሁኖ አግኝተናል።በዘህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በቡሬ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 20 ቀን 2008 ዓ/ም ተሰጥቶ በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-65729 ህዲር 27 ቀን 2008 ዓ/ም እንዱሁም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ታህሳስ 14 ቀን 2008 ዓ/ም በትዔዙዛ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች ክስ በይርጋ የታገደ አይደለም ብለናል።
የቡሬ ወረዲ ፍርድ ቤት ክርክሩን በመ/ በሆነው ቀጥልና በስነ ስርዓቱ ሕጉ መሰረት በመምራት ተገቢውን ይወሰን በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይፃፍ።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።