በትግራይ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ወራሽ የላለው መሬት በቀበላው የገጠር መሬት አስተዲደር ኮሚቴ መሬት ለላላቸው ከተሸጋሸገ በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ከመሬት ዲኝነትና ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 239/2006 አንቀጽ 14/8/ ደንብ ቁ. 85/2006 አንቀጽ 22/1//ሀ/፣21/8/
No summary available.
ታህሳስ 25 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ሀጋዘዖውደ VC በላለበት ችልት ስላስቻለ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ራኽብ ቸኮለ VC በላለበት ችልት ስላስቻለ የቀረበ የለም መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የቻለው የትግራይ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ ህዲር 23 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ 01 ገጽ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
የክርክሩ አመጣጥም የአሁን ተጠሪ ክርክሩ በጀመረበት በትግራይ ብሐራዊ ክልል ኦፍላ ወረዲ ዓዱጉል ቀበላ የመሬት ዲኝነት ከሳሽ በመሆን ለሰበር አቤቱታቸው ምክንያት የሆነውን በዓዱጉል ቀበላ ዓዱጉል በተባለው ቦታ 1ኛ በምስራቅ ሻረው በርሀ፤በምዔራብ መንገድ፤በሰሜን ጥዐማይ ካህሳይ በደቡብ ሻረው በርሀ በሚያዋስኑት መካከል የሚገኝ እና 2ኛ በምስራቅ ታደገ ግርበቱ፤በምዔራብ ጣሰው አብርሃ፤በሰሜን መንገድ፤ በደቡብ ታደገ ግርበቱ በሚያዋስኑት መካከል የሚገኝ መሬት ተጠሪ በሽግሽግ የደረሳቸውን የእርሻ ይዜታ መሬታቸውን አመልካች በኃይል ተጠቅመው የያዘባቸው በመሆኑ ለቀው እንዱያስረክቡ እንዱወሰንላቸው ያቀረቡትን ክስ መሰረት ያደረገ ነው።
አመልካችም በተከሳሽነት ቀርበው አከራካሪው መሬት የሟች አባታቸው ይዜታ መሆኑን ገልፀው በህግ አግባብ በውርስ ያገኙት በመሆኑ መሬቱ በሽግሽግ ለተጠሪ ላሰጥ አይገባም በማለት ክርክር አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የዓዱጉል ቀበላ መሬት ዲኝነትም አመልካች በክርክሩ መሬት ወራሽነት ማስረጃ ያወጡት መሬቱ ወራሽ የላለው ለመሆኑ ተረጋግጦ ለተጠሪ ከተሸጋሸገ በኋላ ነው በማለት አመልካች መሬቱን ለቀው ለተጠሪ እንዱያስረክቡ ወስኗል።
በዘህ ውሳኔ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦፍላት ወረዲ ፍርድ ቤት አቅርበው የነበሩ ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የወረዲው ፍርድ ቤትም ይግባኙ መልስ ሰጭን ያስቀርባል በማለት ሲያከራክር ቆይቶ አከራካሪው መሬት በህጋዊ ሽግሽግ ለተጠሪ የተሰጣቸው ጥር 29 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑንና አመልካች በክርክሩ መሬት የወራሽነት ማስረጃ ያወጡት ደግሞ የካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም ለመሆኑ ካረጋገጠ በኋላ አመልካች አከራካሪውን የይዜታ መሬት በውርስ አግኝቻለሁ የሚለት መሬቱ በሽግሽግ ከተሰጠ በኋላ በመሆኑ የመሬት ዲኝነት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት አፅንቶታል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው የነበሩ ቢሆንም የሥር ፍርድ ቤቶች ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም በማለት ሳይቀበል ቀርቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን ዲኝነት ለማስለወጥ ነው። መዛገቡ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርመሮ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ በመወሰኑ ተጠሪ መስከረም 09 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን አመልካችም ጥቅምት 28 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የጽሐፍ ክርክራቸውን አጠናቀዋል።
ክርክሩ በዘህ አግባብ ተጠናቋል። እኛም መዛግቡን መርምረናል። እንደመረመርነውም ለክርክር መነሻ የሆነውን መሬት አስመልክቶ ለአሁን ተጠሪ ይገባል ተብል የተወሰነው ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ምላሽ ማግኘት ያለበት መሆኑን ተገንዛበናል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር ክርክሮች ሲነሱ ምላሽ ለመስጠት የግራቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ባግባቡ በማጣራት ተገቢውን ማስረጃ መርምሮ መወሰን ይገባል። የሥር የመሬት ዲኝነትም ሆነ ወረዲ ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረጉት ግራቀኙ ወገኖች ያቀረቧቸውን ማስረጃዎች በመመልከት ነው። በዘህ ረገድ ከሥር መዛገቡ መገንዖብ እንደቻልነው አከራካሪው መሬት ለተጠሪ በሽግሽግ ከተሰጠ በኋላ አመልካች የወራሽነት ማስረጃ ያወጡ መሆናቸው፤
ለተጠሪ አከራካሪው መሬት በተሰጠበት ወቅትም ተቃዋሚ ካለ እንዱቀርብ ጥሪ ተደርጎ እንደነበርና አመልካች በወቅቱ ሳይቀርቡ ቆይተው መሬቱ ለተጠሪ ከተሰጠ በኋላ ወራሽ መሆናቸውን አረጋግጠው ማስረጃ ማቅረባቸውን በማረጋገጥ የሥር ፍርድ ቤቶች አከራካሪው መሬት ለአመልካች የማይገባ ስለመሆኑ ወስነዋል።
በትግራይ ብሓራዊ ክልል የገጠር መሬት አስተዲዲር አዋጅ ቁጥር 239/2006 አንቀጽ 14(8) እንዱሁም ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 85/2006 አንቀጽ 22(1)(ሀ) ሥር እንደተመለከተው ወራሽ የላለው መሬት በቀበላው የገጠር መሬት አስተዲደር ኮሚቴ መሬት ለላላቸው ይሸጋሸጋል በማለት ደንግጓል። በዘሁ ደንብ አንቀጽ 21(8) ሥር እንደተመለከተው ከሽግሽግ በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ከመሬት ዲኝነትና ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ ተቀባይነት እንደላለው ደንግጓል። የእነዘህ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ የሚያስረዲው አንድ የገጠር መሬት ባለይዜታ የሞተ እንደሆነ መሬቱ ያለወራሽ ስለመቅረቱ ተገቢ ማጣራት በማድረግ እውነትም ወራሽ የላለው ሆኖ የተገኘ እንደሆነ መሬት ለላላቸው የቀበላ ነዋሪዎች በሽግሽግ ላሰጥ የሚገባ መሆኑን፤ መሬቱን ከማሸጋሸጉ በፉት የቀበላ ገጠር መሬት አስተዲደር ኮሚቴው መሬቱ ወራሽ ያለው እንደሆነ ተገቢ ማጣራት ማድረግ ያለበት ሆኖ በዘህ ሂደት አልፍ የተሸጋሸገ መሬት ይመለስልኝ የሚል አቤቱታ በመርህ ደረጃ ተቀባይነት የላለው መሆኑን በልዩ ሁኔታ በመሬት ዲኝነት አካል ወይም በፍርድ ቤት ከተወሰነ ተቀባይነት ሉኖረው እንደሚችል የሚያስረዲ ነው።
ስለሆነም አንዳ ወራሽ የለውም ተብል በሽግሽግ የተሰጠ መሬት በመሬት ዲኝነት ውሳኔ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ አርፍበት ወራሽ የሆነ ሰው ከመጣ አቤቱታ ቀርቦበት በሽግሽግ ያገኘው ሰው ሉለቅ እንደሚችል የትግራይ ብሓራዊ ክልል የገጠር መሬት አስተዲዲር አዋጅ ቁጥር 239/2006ን ለማስፈፀም ከወጣው ደንብ ቁጥር 85/2006 አንቀጽ 22(1)(ሀ) ድንጋጌ መገንዖብ የሚቻል ነው።
አመልካች አሁን በያዘት የወራሽነት ማስረጃ መነሻነት በመሬት ዲኝነት ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ በአከራካሪው መሬት ላይ ወራሽ ሉሆኑ የሚችለ ከሆነ መሬቱ አንዳ ለተጠሪ በሽግሽግ ተሰጥቷል ተብል መብታቸውን መንፈግ ከክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር ህግ ዓላማና መንፈስም አንፃር ሲታይ ተቀባይነት ያለው አይደለም። የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች በክርክሩ መሬት የወራሽነት ማስረጃ ማውጣታቸውን ግንዙቤ ከወሰደ በኋላ የወራሽነት ማስረጃ በፍርድ ቤት የተሰጣቸው ቢሆንም መሬቱ ከተሸጋሸገ በኋላ የቀረበ የወራሽነት ማስረጃ ውሳኔ ተቀባይነት የለውም ማለታቸው የክልለን የገጠር መሬት አስተዲደር ህግ ድንጋጌዎች ያላገናዖበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የያዘት የወራሽነት ማስረጃ ለማስረጃነት የሚያገለግል በመሆኑ ተጠሪ ጋር ክርክር ላደረግበት የሚገባውና ሉስተባበልም የሚችል ነው። ከዘህ አንፃር በጉዲዩ ላይ ተጠሪ የሚያቀርቡት ክርክርና ማስረጃ አመልካች ካቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ ጋር ተገናዛቦ ሉመረመር የሚገባው ነው። ይሁን እንጂ በጉዲዩ ላይ ዲኝነት የሰጡት የሥር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በዘህ አግባብ ተመልክተው ያስተናገደት ሳይሆን አመልካች የወራሽነት ማስረጃ ያቀረቡት መሬቱ ከተሸጋሸገ በኋላ ነው በሚል ምክንያት ብቻ አመልካች አከራካሪውን መሬት መውረስ የሚገባቸው ወይም የማይገባቸው ስለመሆኑ ሳያጣሩ መሬቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ መወሰናቸውን ከመዛገቡ ተገንዛበናል። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
በዓዱጉል ቀበላ የመሬት ዲኝነት አካል ተወስኖ በኦፍላ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዛገብ /07 መስከረም 06 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት እንዱሁም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ ህዲር 23 ቀን 2008 ዓ.ም ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በመሆኑም አመልካች የያዘት የወራሽነት ማስረጃ በክርክሩ መሬት ላይ የሚሰጣቸው መብት ምን እንደሆነ ተጠሪው አመልካች ባቀረቡት የውርስ ማስረጃ ላይ ያላቸው ክርክርና ማስረጃ እንዱያቀርቡ በማድርግ ከግራቀኙ ክርክርና ማስረጃ አንፃር ጉዲዩን ካጣራ በኋላ አከራካሪው መሬት ለአመልካች በውርስ ይገባቸዋል ወይስ አይገባቸውም?
በሚለው ጭብጥ ላይ ተገቢውን እንዱወስን የዘህ ችልት ውሳኔ ቅጅ ለዓዱጉል ቀበላ መሬት ዲኝነት ይተላለፍ ብለናል።
መዛገቡን ዖግተናል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.