የእርሻ መሬት ይዜታን ከማስለቀቅ ጋር በተገናኘ የሚቀርብ ክስ ከእርሻ መሬት ልዩ ባህሪ አንጻር ከንብረቱ የሚገኘውን አቶ አስራት ኩምሳ እና XII ወይም ላላ ጥቅም ጭምር ከዋናው ክስ ጋር አጣምሮ ይክሰስ ልባል ስለማይችል፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216/3/፣218/ሀ/ አዋጅ ቁ. 452/1997 አንቀጽ 12 የአ/ክ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀጽ 16 ደንብ ቁ. 151/2005 አንቀጽ 18 እነ ጉደታ በዲዲ (ሁለት ሰዎች) ዓ.ም
No summary available.
ታህሳስ 7 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ አስራት ኩምሳ - ጠበቃ ረጅብ ኡስማን ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩከገጠር መሬት የተገኘ ነው የተባለን አላባ ለማስከፈል ከቀረበ ክስ ጋር ተያይዜ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች አቤቱታቸውን ለዘህ ችልት ያቀረቡት በደቡብ ምዔራብ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ04/03/2006 ዓ.ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ታይቶበመዛገብ በ30/07/2006 በፍርድ የጸናውን ውሳኔ በመሻር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች ቀደም ሲል በመሬት ይዜታው ላይ የይገባኛል ክስ ባቀረቡበት ጊዚ አሁን በመዛገብ ክስ ያቀረቡበትንም የአላባ ጥቅም አካተው መክሰስ ሲችለ ነጥለው በማስቀረት አሁን አዱስ ያቀረቡት ክስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 216 (4) እና 218 ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት የላለው ሆኖ እያለ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘህ ረገድ ከተጠሪዎቹ የቀረበውን መቃወሚያ ተቀብል መዛገቡን መዛጋት ሲገባው ወደ ፍሬ ጉዲይ ክርክሩ ገብቶ ውሳኔ መስጠቱ እና ውሳኔው በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት ማግኘቱ ተገቢነት የለውም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ በ22/02/2008 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች ሲሆኑ ክሱን ያቀረቡትም በአሁኖቹተጠሪዎች ላይ ነው።በ14/09/2005 ዓ.ም. ተዖጋጅቶ የቀረበው ክስ አጭር ይዖትም ተጠሪዎቹ የአመልካች ሕጋዊ ይዜታ የሆነውን እና አዋሳኞቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን አስር ሄክታር የሳር መሬት ምንም መብት ሳይኖራቸው በ1993 ዓ.ም.በመያዙቸው አመልካች ይዜታውን ለማስለቀቅ በቀርሳና ማሉማ ወረዲ ፍርድ ቤት የመሰረቱት ክስ ውድቅ የተደረገ ቢሆንም በይግባኝ ለደቡብ ምዔራብሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤትአቅርበው ተጠሪዎቹ ይዜታውን እንዱለቁ በመዛገብ በ08/02/2004 ዓ.ም.ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን፣ተጠሪዎቹ በይዜታው ከ1993 ዓ.ም.ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ ለአስራ ሁለት ዓመታት የተገለገለበት መሆኑን፣ከይዜታው በዓመት ግምቱ ብር አምስት ሺህ የሆነ ሳር የሚገኝ መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ ተጠሪዎቹ የ12 ዓመታትን አላባ ብር 60,000 (ስድሳ ሺህ) እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዖንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ነው።
ተጠሪዎቹ በ24/10/2005 ዓ.ም.በሰጡት መልስ አመልካች ቀደም ሲል በመሬት ይዜታው ይገባኛል ጉዲይ ክስ ባቀረቡበት ጊዚ አሁን ክስ ያቀረቡበትንም የአላባ ግምት አካተው መክሰስ ሲችለ ነጥለው በማስቀረት አሁን አዱስ ያቀረቡት ክስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 216 (3) ድንጋጌ መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል መቃወሚያ ካስቀደሙ በኃላ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተም በቀድሞው ክስ ፍርድ ያረፈበት ይዜታ አሁን በክሱ ላይየተገለጸውን መጠን የሚያህል ባለመሆኑ ክሱ የተጋነነ ነው፣በመሬቱ ላይ በግጦሽ ተሰማርተው የቆዩትም የተጠሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የላልችም አርሶ አደሮች ከብቶች ጭምር በመሆናቸው መከሰስ የሚገባን በድርሻችን መጠን ብቻ ነው፣በአላባው 12 ዓመት ሙለ ተጠቅማችኋል የተባልነውም አላግባብ ነው የሚለ እና መሰል የክርክር ነጥቦችን በማንሳት ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም አመልካቹ በይዜታው ጉዲይ አስቀድሞ ክስ ባቀረቡበት ጊዚ የሚጠይቁት አላባ የስንት ዓመት እንደሆነ ማወቅ የሚችለበት ሁኔታ ስላልነበረ ይዜታው እና ከይዜታው ላይ የሚገኘው አላባ ግምት አብሮ ሉጠየቅ የሚችል አይደለም የሚል ምክንያት ሰጥቶ መቃወሚያውን በማለፍ በፍሬ ጉዲዩ ረገድ በቀድሞው መዛገብ የቀረበውን ማስረጃ ከተመለከተ እና የአላባውን መጠን በባለሙያ ካስገመተ በኃላ አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃውን መርምሮ ተጠሪዎቹ በይዜታው ለ12 ዓመታት መጠቀማቸው በመረጋገጡ በባለሙያ በቀረበው ግምት መሰረት የ12 ዓመት አላባ ብር 49,280 (አርባ ዖጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ) ከብር 1,551.50 የዲኝነት ክፍያ ጋር ከብር 500 ወጪና ኪሳራ ጋር ለአመልካች እንዱከፍለ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በፍርድ ያጸናው ይህንኑ ውሳኔ ነው።
ጉዲዩ በመጨረሻ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በበኩለ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ የሻረው አመልካች ቀደም ሲል በመሬት ይዜታው ላይ የይገባኛል ክስ ባቀረቡበት ጊዚ አሁን ክስ ያቀረቡበትንም የአላባ ጥቅም አካተው መክሰስ ሲችለ ነጥለው በማስቀረት አላባውን በተመለከተ አዱስ ክስ ማቅረባቸው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 216 (4) እና 218 ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት ስለላለው የአላባው ክስ ከቀድሞው የይዜታ ክስ ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት ተብል ውድቅ መደረግ ነበረበት የሚል ምክንያት በመስጠት ነው።አመልካች ለዘህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ጉዲይ አመልካች ከመሬት ይለቀቅልኝ ክስ ጋር ከመሬቱ የሚገኝ አላባን አጣምሮ መጠየቅን በተመለከተ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 217 እና 218 ድንጋጌዎች ለከሳሽ ወገን አማራጭ የሚሰጡ እንጂ የሚያስገድደ አይደለም በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ ከድንጋጌዎቹ ይዖት አንጻር ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዖንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስመለስ ከሚቀርብ ክስ ጋር ከንብረቱ የሚገኝ አላባን ወይም ጥቅምን ጉዲይ አጣምሮ መክሰስን በተመለከተ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 217 እና 218 ድንጋጌዎች ፈቃጆች እንጂ አስገዲጆች አይደለም በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
አመልካች ቀደም ሲል በመሬት ይዜታው ላይ የይገባኛል ክስ ባቀረቡበት ጊዚ አሁን ክስ ያቀረቡበትንም የአላባ ጥቅም አካተው መክሰስ ሲችለ ነጥለው በማስቀረት አላባውን በተመለከተ አዱስ ክስ ማቅረባቸው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 216 (4) እና 218 ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት የክልለ ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዖብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዘሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካቹ ይዜታውን ለማስለቀቅቀደም ሲል በተጠሪዎቹ ላይ ክስ አቅርበው የነበረ እና በክርክሩም ተጠሪዎቹ መሬቱን እንዱለቁየተወሰነ መሆኑ አላከራከረም።የክስ አቀራረብ ስርዓትን በተመለከተ በአንድ በኩል በልላ አኳኃን እንዱቀርብ ካልተፈቀደ በቀር ማናቸውም ከሳሽ ለሚያቀርበው ክስ መሰረት ላሆን የሚችል ከአንድ በላይ የሆነ ነገር ካለው ሁለንም በአንድነት አጣምሮ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ተከሳሾች ላይ የተጣመረ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 217 (1) ስር የተመለከተ ሲሆን በልላ በኩል ግን የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስመለስ ክስ የሚያቀርብ ሰው ከዘህ ዓይነቱ ክስ ጋር አጣምሮ ማቅረብ የሚችለው በድንጋጌው ስር ከፉደል ‛ሀ“ እስከ ‛ሐ“ የተመለከቱትን የክስ ምክንያቶች ብቻ ስለመሆኑ በዘሁ ሕግ በቁጥር 218 ተደንግጓል።የእነዘህ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብም የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስመለስ ክስ የሚያቀርብ ሰው ከዘሁ ንብረት የሚገኘውን ጥቅም ለማስከፈል የሚቀርበውን ክስ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለማስመለስ ከሚያቀርበው ክስ ጋር አጣምሮ ማቅረብ የሚችል መሆኑን የሚያስገነዖብ ነው።በልላ በኩል ከሳሽ ሉከስበት ሲችል ሆነ ብል በመቀነስ ባስቀረው ሀብት ምክንያት እንደገና ላላ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ እና ከሳሽ ያቀረበው ክስ በአንድ ጉዲይ ላይ የተመሰረተ ሆኖ የሚጠይቀው ዲኝነት ግን ከአንድ በላይ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሳይፈቀድለት ሉጠይቅ ይገባው ከነበረው ዲኝነት ውስጥ በከፉል ራሱ ቀንሶ ባስቀረው መብት እንደገና ሉከስበት የማይችል ስለመሆኑ በዘሁ ሕግ በቁጥር 216 (3) (4) ስር ተመልክቷል።ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብም የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስመለስ ክስ የሚያቀርብ ሰው ከንብረቱ የሚገኘውን አላባ ወይም ላላ ጥቅም ጭምር በክሱ አጣምሮ እንዱከስ በቁጥር 218 (ሀ) ስር የተመለከተው ድንጋጌ የአስገዲጅነት ባህርይ ያለው እንጂ አመልካች እንደሚለት ፈቃጅ እና ክሱን ነጣጥል የማቅረብ አማራጭን ለከሳሽ ወገን የሚተው አይደለም።በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስመለስ ከሚቀርብ ክስ ጋር ከንብረቱ የሚገኝ አላባን ወይም ጥቅምን ጉዲይ አጣምሮ መክሰስን በተመለከተ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 217 እና 218 ድንጋጌዎች ፈቃጆች እንጂ አስገዲጆች አይደለም በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር የድንጋጌዎቹን ይዖት እና ዓላማ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስቀድመው በቀረቡለት ተመሳሳይ ጉዲዮች በመዛገብ እና በላልችም መዛገቦች የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ተጠሪዎቹ አጥብቀው የሚከራከሩትአመልካቹከይዜታው የሚገኝ ነው ያለትን የአላባ ጥቅም ጥያቄ ቀደም ሲል ካቀረቡት ይዜታ የማስለቀቅ ክስ ጋር አጣምረው ማቅረብ የሚችለ ሆኖ ሳለ በዘህ አግባብ ሳያቀርቡ ቀርተው የመጀመሪያው ጉዲይ ውሳኔ ካገኘ በኃላ አላባውን በተመለከተ አዱስ ክስ ማቅረባቸው ከላይ ከተጠቀሱት የስነ ስርዓት ድንጋጌዎች ውጪ በመሆኑ በክልለ ሰበር ችልት የተሰጠው ውሳኔ ስህተት የለበትም በማለት መሆኑን የሰበር መልሳቸው ይዖት ያመለክታል።ተጠሪዎቹ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተመለከተውን የክስ አቀራረብ ስርዓት መሰረት አድርገው ያቀረቡት ክርክር በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም በልላ በኩል ግን ይህ ክርክራቸው ለክሱ ምክንያት ከሆነው ጉዲይ ልዩ ባህርይ ጋር ተገናዛቦ በአግባቡ ሉመረመር የሚገባው መሆኑን ተገንዛበናል።
አመልካቹ የመጀመሪያውን ክስ ያቀረቡት ይዜታውን ለማስለቀቅ ነው።በገጠር የእርሻ መሬት የይዜታ መብት ላይ የሚነሳው ክርክር ጉዲዩ በሚመለከታቸው ተከራካሪዎች በውይይትና በስምምነት እንዱፈታ ጥረት የሚደረግ ስለመሆኑ እና በስምምነት ሉፈታ ካልቻል በተከራካሪ ወገኖች በተመረጠ ሽምግልና ወይንም በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር ሕግ በተደነገገው መሰረት የሚወሰን ስለመሆኑ በፋዳራል መንግስት በወጣው የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀጽ 12 ስር ተደንግጎ ይገኛል።በልላ በኩል ከእርሻ መሬት ይዜታ ጋር ተያይዖው የሚነሱ ክርክሮች በወረዲ ፍርድ ቤት ቀርበው ከመታየታቸው በፉት በስምምነት እና ቀጥልም በሽምግልና መታየት የሚገባቸው ስለመሆኑ የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 16 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 18 ተመልክቷል።
ከላይ በተጠቀሱት አዋጆች እና ደንብ ድንጋጌዎች መሰረት ለፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፉት በስምምነት እና ቀጥልም በሽምግልና እንዱታይ የሚደረገው ጉዲይ የእርሻ ይዜታ ክርክር እንጂ ከእርሻ ይዜታው የሚገኘው ጥቅም ወይም አላባ ጭምር አይደለም።እንዱህ ከሆነ ደግሞ ከሳሽ የሆነ ወገን አላባውን የሚመለከተውን ክስ ይዜታውን ለማስለቀቅ ከሚያቀርበው ክስ ጋር አጣምሮ ሉያቀርብ የሚችልበት አግባብ አይኖርም።ከእርሻ መሬት የሚገኘውን ጥቅም አስመልክቶ በሚቀርቡ ክሶች ጉዲይ ተጠሪዎቹ ጠቅሰው የሚከራከሩባቸው የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 218 (ሀ) እና 216 (3) ድንጋጌዎች መተርጎም የሚገባቸው የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀምን አስመልክቶ ከወጡ ሕጎች ዓላማ እና መንፈስ ጋር ተገናዛበው ነው።ቀደም ሲል በቀረበለት ተመሳሳይ ጉዲይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ በ18/07/2007 ዓ.ም. የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉምም በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2 (1) መሰረት በዘህ መዛገብ ለቀረበው ጉዲይ አስገዲጅነት ያለው መሆኑን ተገንዛበናል።በመሆኑም አመልካቹ ቀደም ሲል በሳር መሬት ይዜታው ላይ የይገባኛል ክስ ባቀረቡበት ጊዚ አሁን ክስ ያቀረቡበትንም የአላባ ጥቅም አካተው መክሰስ ሲችለ ነጥለው በማስቀረት አሁን አዱስ ያቀረቡት ክስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 216 (4) እና 218 ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት የክልለ ሰበር ችልት የደረሰበት መደምደሚያ እና ይንንኑ መደምደሚያ መሰረት አድርጎ የሰጠው ውሳኔ የጉዲዩን ልዩ ባህርይ፣ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ሕጎች እና ቀደም ሲል በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያላገናዖበ በመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባው ሆኖ አልተገኘም።በልላ በኩል የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔውን የሰጠው ተጠሪዎቹ ያቀረቡትን መቃወሚያ መሰረት በማድረግ በመሆኑ እና የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን መርምሮ የመጨረሻ ፍርድ ያላሰረፈበት በመሆኑ በዘህ ረገድ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዖንድ ጉዲዩ ወደ ክልለ ሰበር ችልት ሉመለስ የሚገባው መሆኑን ተገንዛበናል።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ በ22/02/2008 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዖንድ ጉዲዩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341 (1) ለኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት እንዱመለስ ወስነናል።ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዖንድ የውሳኔው ግልባጭ ይላክለት።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ አመልካቾቹ የራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዛገቡ ተዖግቷል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡