የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተያያዖ ሻጭ ንብረቱን ከ3ተኛ ወገን ይዜታና ቁጥጥር ነፃ በማድረግ የማስረከብ ግዳታ እና ገዣ ከተረከበ በኃላ ንብረቱ የእኔ ነው ባይ ቢመጣ ሻጩ በዋቢነት የመቆም ግዳታ የተለያየ ግዳታ ስለመሆኑ፤ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 2875 ፣ 2274 ፣ 2880 ፣ 2881 ፣ 2882 ፣2879፣ 2888 ፣1206 ፣ 1195 ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33(2) 36(4) እና 40 (2)
No summary available.
ሕዲር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች ወ/ሮ አማረች ማሬ ጠበቃ ማስታወል ሀብታሙ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪዎች እየኖሩበት ያለውንና በ 300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት ለቅቀው እንዱያስረክቧት የመጠየቅ መብት የላትም ንብረቱን የሸጠችላትን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ከስሳ ትጠይቅ በማለት የሰጡት ውሳኔ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል ።
ከሳሽ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የመፈላም ክስ ነው ከሳሽ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀበላ 03 የቤት ቁጥር 287 የግል ሀብቴ ስለመሆኑ በክፍለ አስተዲደር የባለሀብትነትና ባለይዜታነት ማረጋገጫ ማስረጃ (ካርታ) በእጁ ይገኛል። ተከሳሾች ከቤቴ ውስጥ በጥገኝነት እንዱኖሩ ፈቅጄላቸው ሲኖሩ ቆይተዋል ። አሁን ግን ቤቴን እንዱለቁ ብጠይቃቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ቤቴን እንዱለቁና እንዱያስረክቡ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርባለች
ተጠሪዎች በተከሳሽነት ቀርበው እኛ በከሳሽ ቤት በከሳሽ ፈቃድ በጥገኝነት የምንኖር ሰዎች አይደለም ። ተከሳሾች በእጃችን አድርገን ይዖን እየኖርንበት ያለው ቤትና ይዜታ አያታችንና እናታችን ከዙሬ አርባ ዖጠኝ ዓመት ጀምሮ ይዖውት ሲኖሩበት የነበረ ቤት ነው።ተከሳሾች ከአያታችንና ከእናታችን ጋር ክስ ያቀረበበትን ቤት ይዖን ስንኖር ፣ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በአያታችን ባድ የይዜታ ቦታ ላይ በአንድ በኩል ቤት ሰርታ ስትጠቀም ቆይታ ፣ቤቱን ለአሁን ከሳሽ ሸጣለታለች ሆኖም እኛ የምንኖርበት ቤት ወ/ሮ ሂሩት አበራሽ በእጇ አድርጋ ይዙው የማታውቅና የራሱ የሆነ ይዜታና የወሰን አጥር ያለው በመሆኑ ከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ የሸጠችውም ሆነ ከሳሽ የእኛን ቤትና ይዜታ በማጠቃለል እንዳት ካርታና ፕላን እንዲወጡ የክፍለ አስተዲደር እንዳት የእኛን ቤትና ይዜታ በማጠቃለል እንዳት ካርታና ፕላን እንደሰጠ ይጠየቅልን በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የስር ፍርድ ቤት የክፍለ አስተዲደር ተገቢዉን ማጣሪያ በማድረግ መግለጫ እንዱሰጥ ትዔዙዛ የቤቱ ስመ ሀብትና ከወ/ሮ እህተ ገብረማርያም ሂሩት አበራሽ ስም ሂሩት ስም የተዙወረዉ በስር ትዔዙዛ ፊይል ቁጥር 139/84 መስከረም 25 ቀን 1985 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት እንደሆነና ከዘያ በኃላ ሂሩት አበራሽ በውልና ማስረጃ ከከሳሽ ጋር በተዋዋለችው የቤት ሽያጭ ውል 1189 ሜትር ካሬ ላይ ያረፈው ቤትና ይዜታ በከሳሽ ስም እንዱዖዋወር ተደርጎ ከሳሽ የባለሀብትነት ማስረጃ የሰጠ መሆኑን ተረጋግጧል ።
ይህንን ውሣኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ እንዱያየው አመልካች ጠይቃ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፅንቶታል።
የበታች ፍርድ ቤቶች ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ጭብጦችን አልመሰረቱም ተጠሪዎች ቤቱን በጥገኝነት ስለመያዙቸው ለቀበላ ለአስተዲደር አመልክተዋል በሻጭና በከሳሽ መካከል የተደረገው ውል ተጠሪዎችን የሚመለከት አይደለም ። አመልካች የቤቱ ሻጭ በዋቢነት እንድትቀርብላት ሣትጠራ ፣ንብረቱ ላይ ያገኛቸው የባለሀብትነት መብት ለማስከበርና ለመፊለም የሚከለክላት ህግ በላለበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ያለበት ነው በማለት አመልክታለች ።
የባለሀብትነት ካርታና ማስረጃውም በክፍለ አስተዲደር የታገደ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል ። አመልካችዎች የመልስ መልስ አቅርበዋል ።
ግራቀኙ የሚያከራክራቸውን ጭብጥ ለመረዲት ችልቱ የግራቀኙን የቃል ክርክር ሰምቶ የቃል ክርክሩ ከትራንስክራይበር ማሽን ተገልብጦ ከመዛገቡ ጋር ተያይዝል ። የክፍለ አስተዲደር በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የፃፈውን መግለጫ ለማየት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዛገብ እንዱቀርብ በታዖዖው መሰረት መዛገቡ ቀርቦ ተያይዝል ።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥ በዘህ ሰበር ችልት ግራቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀ ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች በተጠሪዎች ላይ ቤቱና ይዜታው እንዱለቀቅላቸው ክስ ያቀረቡት ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና ይዜታና ከሻጭ ተረክበው የያዘትን ቤትና ይዜታ በድምሩ 1139 ካሬ ሜትር ላይ ያለትን ቤቶችና ይዜታ በብር 120,000 የካቲት 3 ቀን 1997 ጋብቻ የቤቱ ስመሀብት የተሰራልኝ በመሆኑ ተከሳሾች (ተጠሪዎች) የግል ሀብቴና ንብረቴ የሆነውን ቤትና ይዜታ ይለቀቅልኝ በማለት ነው። ተጠሪዎች የሚከራከሩበት ከሳሽ የቤትና ይዜታውን ባለቤትነት መብት በሽያጭ አስተላልፊልኛለች የምትለት አበራሽ ሂሩት እኛ የያዛነውን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዜታ ለከሳሽ በሽያጭ ለማስተላለፍ መብት የላትም ። ከሳሽ እኛን ከመጠየቋ በፉት በሽያጭ ውለ መሰረት እኛ የምንኖርበትን ቤትና 300 ካሬ ሜትር የይዜታ ቦታ ሻጭ ነፃ አድርገ እንድታስረክባትና የሽያጭ ውለን እንድትፈፅምላትና ከምትጠይቅ በስተቀር ከሳሽ የሽያጭ ውለ ሙለ በሙለ እንደተፈጸመላትና ንብረቱንም ከሻጭ እንደተረከበች አድርጋ በመቁጠር በቀጥታ እኛን ከቤት እንድንወጣ የመጠየቅና ክስ የማቅረብ መብት የላትም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ተረድተናል።
ግራቀኙ በሥር ፍርድ ቤትና በዘህ ሰበር ችልት ያቀረቡት ክርክር አመልካችና ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት የካቲት 3 ቀን 1997 ዓ.ም የተዋዋለት የቤት ሽያጭ ውል ሻጭ ሙለ ለሙለ ፈፅማለች ወይስ አልፈፀመችም ሻጭ በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታዋን ሙለ በሙለ ካልፈፀመችና ውለን በከፉል የፈፀመች መሆኑ ቢረጋገጥ ገዣዋ ሻጭ ቀሪውን ግዳታዋን እንድትፈፅምላት በሻጭ ላይ ክስ ሣታቀርብ ወይም በተከሳሽነት አጣምራ ሳትከስ የውለ ተዋዋይ ያልሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ላይ በቀጥታ ክስ በማቅረብ ትችላለች ወይስ አትችልም ?የሚለት ነጥቦች መታየት ያለባቸው ናቸው።
ከላይ ከተገለፁት ነጥቦች አንፃር ስንመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል የገባውን ግዳታ የሚፈፅምባቸው ሁለት መሰረታዊ ኃላፉነቶች አለ። የመጀመሪያው ሻጭ በሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በአንደ ወይም በልላ መልኩ ስፍራው የሚገኙ ሰዎች የተሸጠውን የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዱለቁ በማድረግ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ይዜታ ከላልች ሶስተኛ ወገኖችና ከሻጭ ቁጥጥርና ይዜታ ነፃ በማድረግ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለገዣ ማስረከብ እንደሆነ ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2875 እና ከፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2274 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ለመረዲት ይቻላል ሻጭ ከዘህ በተለየ ሁኔታ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ርዔስ መዛገብ ላይ የተመዖገበና ገዠውንም ሉያስገድደ የሚችለ የሶስተኛ ወገኖች መብት በሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ካለ ይህንኑ የሶስተኛ ወገኖች መብት ካለ ሻጭ ለገዣ ማስታወቅ ያለበት መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2880 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2881 ተደንግጓል ።
የሻጭ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ከሶስተኛ ወገን ይዜታና ቁጥጥር ነፃ በማድረግ የማስረከብ ግዳታ ገዣ ለሻጭ ከሚሰጠው የመነቀል ዋስትና ግዳታ የተለየ ነው ። ሻጭ በንብረቱ ላይ ያስፈሩና በንብረቱ መዛገብ የተመዖገበ መብት የላላቸውን ሰዎች የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እንዱለቁ በማድረግ ለሻጭ የማስረከብ ግዳታ የማይንቀሳቀስ ንብረት ውል በመፈፀም ሂደት ገዣ ሻጭ ሉያከናውነው የሚገባ የመጀመሪያ ግዳታ ሲሆን በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2882 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ሻጭ ለገዣ የሸጠለት የማይንቀሳቀስ ንብረት የማይነቀል ስለመሆኑ የሚሰጠው ዋስትና ገዣ የገዙውን የተረከበውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ከላልች ሰዎች ቁጥጥር ነፃ ሆኖ ከተረከበ በኃላ ንብረቱ የእኔ ነው ባይ ቢመጣ ሻጭ በዋቢነት ሉቆምለት የሚገባ መሆኑን የሚያመለክቱ ድንጋጌዎች ናቸው።
የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ንብረቱን ከላልች ሰዎች ቁጥጥር ይዜታ ሥር ነፃ አድርጎ በማጓጓዛ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2875 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2274 መሰረት የማስረከብ ግዳታ ያለበት ከመሆኑ በተጨማሪ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ለማስተላለፍ የሚችለ አስፈላጊ ሰነድች ለገዠ የማስረከብና የማይንቀሳቀሰ ዉን ንብረት የማይነካ የባለሀብትነት መብት ለገዣ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነ ተግባራትን የመፈጸም ግዳታ መሆኑ በፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 2875 በፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2879 ንኡስ አንቀጽ 1 እና የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2281 ድንጋጌዎችን በጣምራ በማየት ለመረዲት ይቻላል።
ከላይ በዛርዛር ካየናቸው የህግ ድንጋጌዎች አንጻር ሲታይ 1139 ካሬ ሜትር የይዜታ ቦታ ላይ ያረፈውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሙለ በሙለ ለአመልካች የሸጠችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት፣በሽያጭ ውለ መሰረት የማይንቀሳቀስውን ንብረትና ይዜታውን ከላልች ሰዎች ቁጥጥርና ይዜታ ስር በማስለቀቅ የማይንቀሳቀስ ንብረትና ይዜታውን በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 2875 በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 2274 እና በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 2888 መሰረት ለገዣ(ለአመልካች)የመፈጸም ግዳታውን የተወጣችው ሙለ በሙለ ሳይሆን በከፉል ነው።ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዜታ.ከተጠሪዎች አውራሽ ንብረቱን ገዙሁ ከምትልበት 1984 ዓ.ም ጀምሮ ተረክበውና በእጇ አድርጋው የማይታወቅ መሆኑና፣ቤቱን ለአመልካች ከሸጠችላት በኋላ ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና ይዜታ፣ ተጠሪዎች በህግ አግባብ እንዱለቁ በማድረግ ለአመልካች ያላስረከበችበት አመልካችም በሽያጭ ውለ የተገለጸውን ቤትና ይዜታ ሙለ በሙለ ሳይሆን፣ሻጭ(አበራሽ ሂሩት)ይዙው የነበረውን ቤትና ይዜታ ብቻ ከሻጭ የተረከበች መሆኑን ተረድተናል።
ገዣ ሻጭ በሽያጭ ውለ የገለጸችውን የማይንቀሳቀስ ንብረትና ይዜታ፣ ተጠሪዎች የሚኖሩበት ቤትና ይዜታ ሳይጨምር በሻጭ እጅና ይዜታ ስር ያለውን ቤትና ይዜታ የተረከበች ቢሆንም፣ሻጭ የሰጠቻትን ሰነድ በመጠቀም በሽያጭ ውለ ላይ የተመለከተውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለመብት መሆኗን የሚሳይ ማስረጃ ከክፍለ አስተዲደር ተሰጥቷታል።ይህም ገዣዋ(አመልካች)ከላልች ሰዎች ይዜታና ቁጥጥር እንደዘሁም የመብት ጥያቄ ነጻ ሆኖ ከሽያጭ ያልተረከበችውን ተጠሪዎች የሚኖሩበት ቤትና ይዜታ ባለመብት መሆኗን የሚያረጋግጥ የባለህብትነት ማስረጃ የተሰጣት መሆኑን ያሳያል።አመልካች የቤቱ ባለሃብትነት መብት በሽያጭ ውል ከወ/ሮ አበራሽ ሂሩት የተላለፈላት መሆኑን የሚያሳይ የሽያጭ ውል ሰነድና በሽያጭ ውለ መሰረት በማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብትነት የተዙወረላት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ በማያያዛ በፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1206 መሰረት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም አላት።ነገር ግን አመልካች ባቀረበችው የክስ መነሻ አከራካሪ ሆኖ የተገኘው ጭብጥ፤(ሀ) ቤቱን ንብረቴ ነው ካለ ለአመልካች የሸጠችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት አከራካሪውንና ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና ይዜታ ባለሃብትነት መብት ለአመልካች የማስተላለፍ እርግጠኛ የሆነ የባለሀብትነት መብት በንብረቱ ላይ አላት ወይስ የላትም?
(ለ)ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት የተጠሪዎች የሚኖርበትን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዜታ ጨምራ የባለሀብትነትን ማስረጃና ካርታ የሰራችው በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም?አመልካችስ 1139 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትና ባለይዜታ መሆኗን የሚያረጋግጥ የባለህብትነት ማስረጃና ካርታ የተሰጣት በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም?(ሐ)ተጠሪዎች እየኖሩበት ያለውን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዜታ ቦታ ለአመልካች የመልቀቅና የማስረከብ ግዳታ አለባቸው ወይስ የለባቸውም?የሚለት ለአመልካች 1139 ካሬ ሜትር የይዜታ ቦታ ላይ ያለውን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሽያጭ ውል አስተላልፊለች የተባለችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በክርክሩ ተሳታፉ ስትሆን ውሳኔ ላሰጥባቸው የሚችለ ጭብጦች አይደለም።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች የቤቱ ሻጭ የሆነችውን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ከሚከሰሱ በስተቀር በቀጥታ ተጠሪዎች ቤቱን እንዱለቁለት ክስ ማቅረብ አትችልም በማለት የሰጠው ውሳኔ ሻጭ በሽያጭ ያስተላለፈው ንብረት ላይ ያለውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ገዣው ከውል የመነጨ መብት ያለው መሆኑን ያላገናዖበና የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1195 የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1206 እና የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33(2) ድንጋጌዎች ያላገናዖበ በመሆኑ ስህተት ያለበት ነው።ነገር ግን የበታች ፍርድ ቤቶች ቤቱን ለአመልካች የሰጠችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በክርክሩ ተከሳሽ መሆን አለባት በማለት የደረሱበት ድምዲሜ የፍትሃብሄር ህግ አንቀጽ 2875፣ አንቀጽ 2274፣አንቀጽ 2888 እና የፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 40 ንዐስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በጉዲዩ ተከሳሽ መሆን አለባት በማለት የደረሱበት መደምደሚያ በውጤት ደረጃ የሚነቅፍ ሆኖ አላገኘነውም።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የቤቱን ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት መክሰስ አለባት ካለ በኋላ፣ይህ ውሳኔአቸው የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት ሳይመዛን ተጠሪዎችን ከክስ ማሰናበታቸው አግባብነት ያላቸውን የስነ-ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም አመልካች ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በሽያጭ ውለ መሰረት ተጠሪዎች የያዘትን ቤት አስለቅቀው ታስረክበኝ የሚል ክስ ስታቀርብ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ በማናቸውም ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን በተከሳሽነት አጣምራ መክሰስ እንዲለባት የፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 36 ንዐስ አንቀጽ 4 አስገዲጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል።ይህም አመልካች ሻጭዋን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩትን በምትከስበት ጉዲይ ተጠሪዎች የግድ በተከሳሽነት እንዱሳተፈ ማድረግ የሚገባ መሆኑ በህግ የተደነገገ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ዲኝነት ከፍላ ያቀረበችውን ክስ የቤቱ ሻጭ በጉዲዩ የመጀመሪያ ተከሳሽ መሆን አለባት በሚል ምክንያት ዖግቶ አመልካችን ከሚያሰናብት፣በጉዲዩ የቤቱ ሻጭ በክርክሩ በተከሳሽነት ተሳታፉ እንድትሆን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 40 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ትዔዙዛ መስጠት በዘህ ፍርድ አንቀጽ ተራ ቁጥር 13 በተመለከቱና በላልች ጭብጦች ላይ አመልካች (የቤቱ ገዣ)፣ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ሻጭና በአከራካሪውን ቤትና ይዜታ ይዖው የሚኖሩት ተጠሪዎች የሚያቀርቡትን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ መወሰን ሲገባው፣አመልካች ተጠሪዎችን የመክሰስ መብት የላትም በማለት መዛገቡን መዛጋቱና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ማጽናቱ ከላይ በዛርዛር የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎችና የዲኝነት አካሄድ ስርዓት ያልተከተለና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዛገብ የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዛገብ መጋቢት 2 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በተከሳሽነት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 40 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በመጨመር፣በዘህ ፍርድ በተራ ቁጥር 13 የተመለከቱትንና ላልች አከራካሪ ጭብጦች ላይ ግራ ቀኙ የሚያቀርቡትን ክርክርና ማስረጃ በማሰማትና ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መልሰን ልከንለታል።
በዘህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.