በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም ህግ መሰረት ግጭትና አለመግባባትን በመጀመሪያ በአስታራቂ ሽማግላዎች እንዱፈቱ የሚደነገጉት ድንጋጌዎች አርሶ አደር ከአርሶ አደር በሚያደርገው የሚፈጠርን አለመግባባትን ለመፍታት እንጂ በህግ ወለድ እና በአንድ አርሶ አደር ሰዎች መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት ጭምር የሚያካትት ሥላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀፅ 16
No summary available.
ሕዲር 9 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተክሉት ይመስል ቀነዓ ቂጠታ ክፍለጽዮን ማሞ ሰናይት አድነው አመልካች፡- የወንጂ ሸዋ ስኳር ፊብሪካ ተጠሪ፡- አቶ ባጫ አለሙ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የመሬት ይዜታ ክርክር በተመለከተ በሽማግላዎች ታይቶ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ/ም ውሳኔ ከሰጡበት በኋላ በአዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 16 ንዐስ አንቀጽ 1/መ/ እና /ሰ/ በተደነገገው የሰላሳ ቀናት የይርጋ የጊዚ ገደብ ካለፈ በኋላ ሚያዘያ 30 ቀን 2005 ዓ/ም ክስ ያቀረበ በመሆኑ፣ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሰጡት ብይን አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ለአዲማ ልዩዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው የክስ ማመልከቻ ነው። ከሳሽ/አመልካች/ ከምስራቅ ሸዋ ዜን ከተማ ልማት ጽ/ቤት በህጋዊ ካርታ ተረክቦና የሸንኮራ አገዲ አልምቶ ከሚጠቀምበት የይዜታ መሬት ተከሳሽ /ተጠሪ/ ስፊቱና መጠኑ እንደዘሁም አዋሳኝ ምልክቱ በክስ ማመልከቻው የተገለጸውን ሸንኮራ አገዲ ተክልና የይዜታ መሬት ከሀምላ 1 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ በመያዛ ሁከት እየፈጠረብኝ ስለሆነ ሁከቱ እንዱወገድ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ ጉዲዩ በሽማግላዎች ታይቶ ውሳኔ ከተሰጠውና ውሳኔው በቀበላው አስተዲደር ከተመዖገበ በኋላ በህጉ የተመለከተው የሰላሳ ቀናት የይርጋ ጊዚ ካለፈው ያቀረበ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል መቃወሚያ አቅርቧል። የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል ብይን ሰጥቷል። አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካች በዘህ ሰበር ችልት ሰኔ 25 ቀን 2006 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የሸንኮራ ተክልና የመሬት ይዜታ ክርክር በጅምሩ በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 16 መሰረት ለአስማሚ ሽማግላ የሚቅረብ አይደለም። ጉዲይ ስለ ዔርቅ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች የሚያሟላ አይደለም። ይህ በሆነበት ሁኔታ አስታራቂ ሽማግላዎቹ ውሳኔ በሰጡ በሰላሳ ቀናት ክስ ያላቀረብክ ስለሆነ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ መስከረም 1 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ መልስ፣ አመልካች ጉዲዩ በሽማግላ እንዱታይለት ከጠየቀ በኋላ የቀበላው አስተዲደር ሽማግላዎች መድቦ ጉዲዩ ታይቶ ከተወሰነ በኋላ በስልሳ ቀን ውስጥ ክሱን ያላቀረበ በመሆኑ ለዘህ ሰበር ችልት የቀረበው ቅሬታ የህግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው፣ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 16 ግጭትና አለመግባባት በመጀመሪያ በአስታራቂ ሽማግላዎች እንደፉቱ የሚደነግጉ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ዓላማ በሁለትና ከዘያ በላይ በሆኑ አርሶ አደሮች መካከል በእርሻ መሬት ይዜታ ምክንያት የሚነሳ አለመግባባት፣ ጉዲዩን በቅርብ አይተውና ተመልክተው፣ወደ ሙግት ሳይገባ በሽማግላዎች የሚፈቱበትን ስርዓት ለመዖርጋትና አርሶ አደሩ በመሬት ይዜታ ግጭት ምክንያት ለምርት ስራ የሚያውለውን ጊዚ በፍርድ ቤት ክርክር እንዲያሳልፍ ለማድረግ ነው። የዘህ አዋጅ ድንጋጌ የፋዳራል መንግስት ካወጣው አዋጅ ቁጥር 456/97 ድንጋጌዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም ያለባቸው መሆኑ የሚያከራክር ነጥብ ሆኖ አላገኘነውም።
የክልለ ም/ቤት ያወጣው የአዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 16 ድንጋጌዎች በፋዳራል ወይም በክልል ደረጃ የተመዖገበና ህጋዊ እውቅና ያገኘ ህግ ወለድ ሰው ከአንድ አርሶ አደር ጋር በመሬት ድንበር ወይም ይዜታ ጥያቄ ምክንያት በሚፈጥር አለመግባባት የሚያገለግል እንዲልሆነ በአዋጅ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ዓላማ ለመረዲት ይቻላል። ከዘህ አንፃር ሲታይ የአሁን አመልካች በህጋዊ ካርታ ተረክቦ ለስኳር ምርት ካለማው ልማትና ሸንኮራ አገዲ ተክል ተጠሪ እንዱለቅለት ክስ ለማቅረብ፣ ጉዲዩ በመጀመሪያ በሽማግላዎች የማሳየት ኃላፉነት ቅድመ ሁኔታ የለበትም። ይርጋውም ጊዚ የሚቆጠረው በቀበላ አስተዲደር የተመደቡ አስታራቂ ሽማግላዎች ውሳኔ ከሰጡበት ጊዚ ጅምሮ ሳይሆን ተጠሪ የሸንኮራ እርሻውን በሀይል ይዝል ከተባለበት ሀምላ 1 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ መሆን አለበት። ከዘህ አንፃር ሲታይ አመልካች ክስ ያቀረበው ተጠሪ በይዜታው ላይ ሁከት ከፈጠረበት ጀምሮ በህግ የተደነገገው የይርጋ የጊዚ ገደብ ከማለፍ በፉት ማለትም ሀምላ 25 ቀን 2005 ዓ/ም በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች አግባብነት የላለውን የኦሮሚያ ክልል አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 16 ንዐስ አንቀፅ 1/1/ ጠቅሰው የአመልካች ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሰኔ 11 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሯል።
አመልካች ይዜታውን ለማስከበር ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ አልሆነም በማለት ወስነናል።
የአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ የሚያቀርቡትን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/ 341/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዘህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.