ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክሶች ወይም ይግባኞች መጣመር በነበረባቸው ሰዓት ሣይጣመሩ ቢቀሩና የግራ ቀኙን የተለያየ መብት በሚያጎናፅፍ ሁኔታ ቢወሰን እነዘህን ውሳኔዎች ተጣጥሞ እንዱፈፀሙ ማድረግ ተገቢ ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.11
No summary available.
ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- በደቡብ ወል ዜን የለገሂዲ ወረዲ ገንዖብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ዓ/ሕግ አበበ ሙለ ቀርበዋል ተጠሪ፡- ሰለሞን አባይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ቀረበ የለም መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የግንባታ ዉልን መነሻ ክፍያ ለመጠየቅ የቀረበዉን ክስ የሚመለከት ክርክር ሲሆን፣ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.97192 በ5/9/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት የአሁን አመልካች የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲ ዩአመጣጥ ሲታይ በደቡብ ወል መስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ፣የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፣ የለገሂዲ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዲዉ 012 ቀበላ የሸክፍ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለማሰራት ያወጣዉን ጨረታ ከሳሽ አሸንፍ በ12/10/2002 ዓ.ም ዉል የተዋዋልን ሲሆን፣ በዘህ ዉል መሰረት ሥራዉን አጠናቅቄ ጊዚያዊ ርክክብ ተደረጓል፤ ነገር ግን ተከሳሽ ቀሪ ክፍያ ብር 86,944.26 ስላልከፈለኝ ይህን ገንዖብ ለዖገየበት ጊዚ መቀጫ 1% ጋር እንዱከፍለን፣ እንዱሁም በዘህ ምክንያት የደረሰብኝ ኪሳራ ብር 52,324 ስለሆነ በአጠቃላይ ብር 380,383.53 እንዱከፍለን በማለት ከሷል። ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ይህን ዉል ማድረጋችን የማይካድ ቢሆንም ከሳሽ የቀረበዉ ክፍያ ብር 63,791.63 ብቻ ነዉ፤ እንዱሁም ከሳሽ የግንባታዉን ሥራ በጥራት ሳይሰራ ክፍያ የተፈጸመ መሆኑን የኦዱት ሪፖርት ያረጋገጠ ስለሆነ ብር 58,659.20 እንዱካካስልኝ በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በማጣራት በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ ለከሳሽ ያልከፈለዉን ክፍያ ብር 86,949.26 ሉከፍል ይገባል የዘህ ገንዖብ ክፍያ ለዖገየበት 1% መቀጫ እንዱከፍል፣ ከሳሽ ያጣዉን ጥቅም በተመለከተ ተከሳሽ ብር 1,683.00 ለከሳሽ እንዱከፍለዉ፣ ተከሳሽ ከሳሹ ሥራዉን በጥራት ስላልሰራ ብር 58,659.20 እንዱመልስልን በማለት የጠየቀዉን በተመለከተ ተቀባይነት የለዉም ከሳሽ ይህን ገንዖብ ለተከሳሽ ሉመልስ አይገባም፤ ተከሳሽ የጠበቃ አበል በተወሰነ ገንዖብ ልክ 10% እና ወለድ ዉሳኔ ከተሰጠበት እስከሚከፈልበት በማለት ወስኗል። የሥር ተከሳሽ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት በመ.ቁ.9121 ብር 58,659 እንደተወሰነለት በመግለጽ ይግባኙን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ የመቀጫ ክፍያ 1% ክስ እስከቀረበበት እንዱከፈል ጠይቆ እያለ ዉሳኔ እስከተሰጠበት የተባለዉ ያልተጠየቀ ዲኝነት ስለሆነ ተገቢ አይደለም፤ ወለድን በተመለከተ ክስ ከቀረበበት ጀምሮ እስከ ዉሳኔ ድረስ ባለዉ ጊዚ ተከሳሽ በተወሰነዉ ገንዖብ ልክ 9% ተከሳሽ ለከሳሽ ሉከፍል ይገባል በማለት የሥር ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የሥር ተከሳሽ አሁንም ይህን ዉሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ችልቱ ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ5/9/2007 ዓ.ም የተጻፈ አምስት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታዉም ይዖት በአጭሩ፡--የአሁን ተጠሪ ቀሪ ክፍያ እንዱፈጸምለት በመ.ቁ.5402 ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ አመልካች ደግሞ ተጠሪ የሰራዉ የግንባታ ሥራ ጥራት ጉድለት ስላለበት ለማስተካከል ግንባታዉን ለማስተካከል ብር 58,659.00 ወጪ ያደረገ ስለሆነ ይህን ገንዖብ እንዱከፍለን በመ.ቁ.9121 ክስ አቅርበናል፣ የሥር ፍ/ቤት እንዱጣመር በማድረግ አጣርቶ ዉሳኔ መስጠት ሲገባዉ ይህን ሳያድርግ ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም። የሥር ፍ/ቤት በመ.ቁ.9121 ተጠሪ ለአመልካች ብር 58,659 እንዱከፍለን ዉሳኔ ተሰጥቶ እያለ ይህ ዉሳኔ ጸንቶ እያለ ለአመልካች ገንዖብ እንድንከፍል ዉሳኔ መስጠቱ ጉዲዩን በአግባቡ አለማጣራቱን ያመለክታል። ስለዘህ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣በመ.ቁ.9121 በተሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ የግንባታ ሥራዉን በጥራት ስላልሰራ ብር 58,659.00 ለአመልካች እንዱከፍል ተወስኖ እያለ፣ በመ.ቁ.5402 ደግሞ አመልካች ለተጠሪ ቀሪ ክፍያ ብር 86,944.26 እና ክፍያ ለዖገየበት የመቀጫ እና የወለድ ገንዖብ እንዱከፍለዉ የመወሰኑን እና የሁለቱ ፊይልች በአንድ ላይ ተጣምሮ ያለመወሰን ያስከተለዉን የሥነ ሥርዓት ጉድለት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.11 አንፃር ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጣሪ መልስ እንዱያቀርብ በታዖዖዉ መሰረት በ4/4/2008 ዓ.ም የተጻፈ ሁለት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡--የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ በአግባቡ ስለሆነ የቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር ሰቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን ተጠሪ የግንባታ ዉልን መነሻ በማድረግ ቀሪ ክፍያ እንዱከፈለዉ አመልካች ላይ ክስ አቅርቦ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በመ.ቁ.5402 ላይ አመልካች ለተጠሪ ብር 86,944.26 እና የዘህን ገንዖብ 1% መቀጫ ተሰልቶ እንዱከፍል፣ ወለድ ዉሳኔ ከተሰጠበት ገንዖቡ እስከሚከፈል ድረስ እና የጠበቃ አበል በተወሰነ ገንዖብ ልክ 10% እንዱከፍል ወስኗል፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሉከፈል የሚገባ የመቀጫ ገንዖብ እና የወለድ መጠን ላይ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል፣ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህን ዉሳኔ ማጽናቱን የቀረበዉ የዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። በልላ በኩል አመልካች በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ የሰራዉ የግንባታ ሥራ ጥራት ስላልነበረዉ ይህን ጉድለት ለማስተካከል ብር 58,659.20 ወጪ ስላደረግን ይህን ገንዖብ እንዱከፍለን በማለት በመ.ቁ.9121 ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ የሰራዉ ሥራ ጥራት የላለዉ መሆኑን በማረጋገጥ ተጠሪ ይህን ጉድለት እንዱያስተካክል ወይም በክሱ የተመለከተዉን ብር 58,659.20 ለአመልካች እንዱከፍል ወስኗል። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር የሥር ፍ/ቤቶች እነዘህ መዛገቦች አጣምረዉ ዉሳኔ መስጠት ሲገባቸዉ ይህን ሳያደርጉ ዉሳኔ መስጠታቸዉ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክሯል። የአሁን ተጠሪም ባቀረበዉ ክርክር እነዘህ ሁለት ዉሳኔዎች መሰጠቱን ክድ የተከራክረ ነገር የለም። ይህ ችልት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ እንደተመለከተዉ በዘህ ጉዲይ ሁለት መዛገቦች መከፈታቸዉን የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ባያመለክትም፣ አመልካች ይህ ገንዖብ እንዱካካስለት የጠየቀ መሆኑን ያሳያል፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች በዘህ ጉዲይ በሁለት መዙግብት ዉሳኔ እንደተሰጠበት ግልጾ የተከራከረ ቢሆንም በዘህ ጉዲይ ላይ ተገቢ ዉሳኔ ሳይሰጡበት አልፈውታል። ከዘህ መገንዖብ እንደሚቻለዉ ግራ ቀኛቸዉ በየፉናቸዉ የየራሳቸዉን ክስ አቅርበዉ መዛገብ አስከፍቶ ዉሳኔ ያገኙ መሆናቸዉን ያመለክታል።
በመሰረቱ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክሶች ወይም ይግባኞች በሚቀርቡብት ጊዚ በሕጉ የተመለከተዉ መስፈርት ተሟልቶ እንደሆነ ተጣምሮ መታየት እንዲለባቸዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.11 ያስገናዛባል። በዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክሶች ወይም ይግባኞች በአንድ ፍ/ቤት ቀርበዉ በመሰማት ላይ በሚገኙበት ጊዚና ተከራካሪዎቹም ወገኖች ባንድ ዖንግ የተመደቡ ሲሆኑ የቀረበዉም የሕግ ክርክር ወይም የነገር ጭብጥ ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ሲሆን ከባለጉዲዮቹ አንደኛዉ ወገን ባመለከተ ጊዚ ወይም ፍ/ቤቱ ተገቢነቱን የገመተ እንደሆነ ክሶቹ ተጣምረዉ በአንድነት እንዱታዩ አስፈላጊዉን ትዔዙዛ ለመስጠት ይቻላል። በማለት ደንግጓታል። ከዘህ ድንጋጌ ይዖትና ዓላማ መገንዖብ እንደሚቻለዉ እነዘህ ክሶች ወይም ይግባኞች መጣመራቸዉ ተከራካሪ ወገኖችን ተገቢ ካልሆነ ወጪ ለማስቀረትና ጊዚያቸዉን ለመቆጠብ ሲባል፣ እንዱሁም በጉዲዩ ላይ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ተመሳሳይ እና የማይጣረስ ወይም የማይጋጭ እንዱሆን ለማስቻል መሆኑን ያመለክታል። በዘህ አግባብ አሁን ወደ ተያዖዉ ጉዲይ ስንመለስ የግራ ቀኛቸዉ ክርክር አንድ የግንባታ ዉልን መነሻ ያደረገ በመሆኑ፣ ከግንባታ ሥራዉ ጋር በተያያዖ ተጠሪ ቀሪ ክፍያ እና ላልች ክፍያዎችን የጠየቀ መሆኑን፣ አመልካች ደግሞ የግንባታዉ ሥራ በጥራት ስላልተሰራ አመልካች ይህን ጉድለት ለማስተካከል ያወጣዉን ወጪ ተጠሪ በማለት የጠየቀ በመሆኑ፣ የሥር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ11 በሚደነግገዉ አግባብ መዛገቦቹን በማጣመር ዉሳኔ ቢሰጡ ኖሮ አሁን የተፈጠረዉ ሁለት ዉሳኔዎች ባልተወሰነ ነበር። አሁን ግን በዘህ ጉዲይ በሁለት መዛገቦች ሁለት ዉሳኔዎች እንዲለ ችልቱ ተገንዖቦታል። በአንድ ጉዲዩ ግራ ቀኛቸዉ ባለመብት የሆኑበት ሁለት ዉሳኔዎች እንዲለ ያመለክታል። የሥር ፍ/ቤቶች እነዘህን መዛገቦች አጣምሮ ዉሳኔ ባይሰጡም፣ እነዘህ ዉሳኔዎች ተጣጥሞ እንዱፈጸሙ ካልተደረገ ለአፈጻጸምአስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥሩ እንደሚሆኑ ግልጽ ነዉ። ስለሆነም ግራ ቀኛቸዉ የየራሳቸዉን ክስ አቅርበዉ የፍርድ ባለመብት እስከሆኑ ድረስ ዉሳኔዎቹ ተጣጥሞ ሉፈጸሙ ይገባል ብለናል።
በዘህ መሰረት ሲታይ የአሁን አመልካች ለተጠሪ ብር 86,944.26 ከመቀጫ እና ከወለድ እንዱሁም ከጠበቃ እና ከላልች ወጪዎች ጋር እንዱከፍል የተወሰነ ሲሆን፣ ተጠሪ ደግሞ ብር 58,659.20 ለአመልካች እንዱከፍል የተወሰነ መሆኑን ማየት ይቻላል። አሁን ተጠሪ ከአመልካች ጋር ባደረገዉ ክርክር ሥራዉን በጥራት እንዲልሰራ ተረጋግጦ ይህን ለማስተካከል አመልካች ያጣዉን ወጪ እንዱተካ በተወሰነበት ሁኔታ የአሁን አመልካች ለተጠሪ የመቀጫ ገንዖብ፣ የጠበቃ አበል እና ላልች ክፍያዎችን የሚከፍልበት አግባብ ሉኖር አይችልም። ስለሆነም የአሁን አመልካች የገንዖብ መቀጫ፣ የጠበቃ አበል እና ላልች ወጪዎችን ለተጠሪ ለመክፈል ኃላፉነት የለበትም ብለናል። በልላ በኩል የአሁን አመልካች ለተጠሪ ሉከፍለዉ የሚገባዉ የገንዖብ መጠን ተቀንሶለት ብር 27,840.06 /ሀያ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ከዚሮ ስድስት ሳንቲም/ እና የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ከሰጠበት ከ17/6/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዲይ በዘህ አግባብ አይተዉ ሁለቱን መዛገቦች አጣምረዉ ዉሳኔ መስጠት ሲገባቸዉ የአሁን አመልካች በፍርድ መብት ባገኘበት ይህን ዉሳኔ ባለመቀበል ለተጠሪ ገንዖብ እንዱከፍል የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የደቡብ ወል ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.5402 በ17/6/2006 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማሻሻል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.01- 02009 ታህሳስ 8 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.97192 በ5/9/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆነ ተሻሽሎል።
የአሁን አመልካች ብር 27,840.06 /ሀያ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ከዚሮ ስድስት ሳንቲም/ እና የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ከሰጠበት ከ17/6/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ብለናል።
የአሁን አመልካች በግንባታ ዉለ መሰረት የገንዖብ መቀጫ፣ የጠበቃ አበል እና ላልች ወጪዎችን ለተጠሪ ሉከፍል አይገባም ብለናል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉ ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.