አንደን የፍትሒብሓር ክስ ባንድ ወይም ካንድ በበለጡ ፍርድ ቤቶች ዖንድ ለማቅረብ የሚቻል ሲሆን የክሱ ማመልከቻ በቀደምትነት የቀረበለት ፍርድ ቤት ብቻ የዲኝነት ሥልጣን እንዲለው ተቆጥሮ ለክርክሩ ውሳኔ ላሰጥ የሚችል ሥለመሆኑ አንድን ሰው በመወከል በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመሟገት በህጉ የተቀመጠውን የዛምድና ደረጃ ወይም በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ የውክልና ወ/ሮ አልማዛ እምሩ እና ወ/ሮ አይጠገብ ቀሬ X የሚያስፈልግ ስለመሆኑየፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 7(2)፣32፣57፣58 እና 63
No summary available.
ሰኔ 20ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጰውልስ አርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዛ እምሩ - ተወካይ አቶ ኢማሙ እብራሂም ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አይጠገብ ቀሬ- አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዮ ፍርድ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ መነሻ የባልና ሚስት ንብረት ክርክርን መሰረት ያደረገ ነው። የአሁኗ ተጠሪ በተወካያቸው በኩል በጋምቤላ ክልል መንግሥት ሥር ለሚገኘው ለማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀን 16/10/2007 ዓ/ም ጽፈው ያቀረቡት ክስ የሟች አቶ ደምሴ ጋሻው የመጀመሪያ ሚስት መሆናቸውን፣ አመልካች /የሥር ተከሳሽ/ ሁለተኛ ሚስት ነኝ በማለት የእሳቸውን የሚስትነት ድርሻ ንብረት እና የሟች ልጅ የውርስ ድርሻ ንብረቱን ለብቻቸው ይዖው የሚጠቀሙ በመሆኑ የተጠሪ የሚስትነት እንዱሁም የሟች ልጅ የውርስ ንብረት ድርሻ ይገባኛል የሚል ነው።
የአሁኗ አመልካች /የሥር ተከሳሽ/ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚዎችን ያቀረቡ ሲሆን ይዖታቸውም፡-
የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኗ ተጠሪ በመቃወሚያዎቹ ላይ መልስ እንዱሰጡ ካደረገ በኃላ የአመልካችን መቃወሚያዎችን በብይን ውድቅ አድርጎ በማለፍ የፍሬ ነገር ክርክሩን ከሰማ በኃላ የግራ ቀኙን የሰው ምስክሮችን ቃል ሰምቶ ውሳኔ ሰጥቷል።
ይህን ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ለጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙን ተቀብል የግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል። ቀጥልም የሰበር አቤቱታ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም አቤቱታውን ተቀብል ክርክራቸውን ከሰማ በኃላ የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን በአቤቱታቸውም በመጀመሪያ ደረጃ መሰረት የሚያደርጉት የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአመልካች በኩል የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን በብይን ያለፈው ያለአግባብ ሆኖ እያለ ቀጥል ያለት ፍርድ ቤቶችም ይህንን ሳያርሙ ማለፊቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ካለ በኃላ በፍሬ ነገርም ረገድ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽሞዋል የሚለዋቸውን ዛርዛር የቅሬታ ነጥቦችን አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታውን አጣሪው መርምሮ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ያደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ህዲር 29 ቀን 2009 ዓ/ም በነበረው ቀጠሮ መልሳቸውን ያላቀረቡት መጥሪያ ስላልደረሳቸው መሆኑን ገልጸው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዱሰጣቸው በጠየቁት መሰረት መልስ በተለዋጭ ቀጠሮ ቀን እንዱያቀርቡ ተፈቀደላቸው ሳያቀርቡ በመቅረታቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን ወደ ፍሬ ነገሩ ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ብቻ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን መርምረናል። በዘሁ መሰረት፡-
አመልካች አስቀድመው ክስ ለሻካ ዜን ክፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል ወይስ አላቀረቡም? ክስ በቅድሚያ ለሸካ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ከሆነ መቃወሚያቸው በሥር ፍርድ ቤት መታለፈ ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 7 አንፃር እንዳት ይታያል?
የአመልካች ተወካይ በውክልና ክስ ለማቅረብ ይችላለ ወይስ አይችለም? የሚለ ጭብጮች ተይዖዋል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡የአሁኗ ተጠሪ የሟች ባለቤታቸው ንብረት በአሁኗ አመልካች እጅ ስለሚገኝ የልጃቸውና የእርሳቸው ድርሻ እንዱወሰንላቸው ክስ በጋምቤላ ክልል ሥር በሚገኘው በጎዲሬ ወረዲ ፍርድ ቤት መሥርተው የሥረ ነገር ሥልጣን ክርክር በመነሳቱ ምክንያት ክስ የማቅረብመብት ያለው ወገን ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ ያቅርብ ተብል መዛገቡ ተዖግቷል። የወረዲ ፍርድ ቤት ብይንም በየደረጃ ላለት ፍርድ ቤቶች ቀርቦ ፀንቷል።
ከዘህ በኃላ የአሁኗ አመልካች ለሸካ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችልት በቀን 09/10/2007 ዓ/ም የተጻፈ ክስ በአሁኗ ተጠሪ ላይ አቅርበው የክስ መጥሪያ ደርሶዋቸው በቀን 13/10/2007 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርበው የቃል ክርክር እንደተደረገና ከዘህ በኃላ የቀረበ ክስ መሆኑን በመጥቀስ አመልካች መቃወሚያ አቅርበው ተከራክረዋል። የአሁኗ ተጠሪም የአመልካችን መቃወሚያ ክደው አልተከራከሩም።
የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ በቀደምትነት የቀረበው ሸካ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው?
ወይስ በማጃንግ ብሓረሰብ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው? የሚል ጭብጥ ይዜ ቀደም ሲል በጎዲሬ ወረዲ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ሲከራከሩ ቆይተው በ26/6/2007 ዓ/ም በዋለው ችልት በተሰጠው ውሳኔ የአሁኗ ተከሳሽ /አመልካች/ ቅር በመሰኘት በከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርክር ላይ የቆዩ ከመሆኑ ባለፈ ተከሳሽ /የአሁኗ አመልካች/ ያነሱትን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በቀደምትነት ክስ የቀረበው በማጃንግ ብሓረሰብ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ግራ ቀኙ ወደ ፍሬ ነገር ገብተው ክርክራቸውን እንዱቀጥለ ሲል በፍ/መ/ቁ. 02223 በቀን 27/11/ 2007 ዓ/ም ብይን እና በቀን 4/2/2008 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል።
የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለ ክስ ቀደምትነት መሰረት ያደረገው በጎዲሬ ወረዲ ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስ ነው። ከላይ እንደተመለከተው የአሁኗ ተጠሪ በዘህ ወረዲ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ በሚሉዮኖች የሚቆጠር ገንዖብ ነው ተብል በሥረ ነገር ሥልጣን ምክንያት የተዖጋ ነው። በዘህ ብይን ላይ የመክሰስ መብት ያለው ሰው ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ ለማቅረብ እንደሚችል ተቀምጧል። ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ንብረት በጋምቤላ ክልል እና በደቡብ ብሓር ብሓረሰቦች ህዛቦች ክልል ሥር ባለት ዜኖች ውስጥ የሚገኝ በመሆኑና የግራ ቀኙም የተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ስለሆኑ አመልካች በሚኖሩበት ክልል በሚገኘው ሸካ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ለዘህ ክስ ተጠሪ ቀርበው መልስ ሰጥተዋል። የቃል ክርክርም አድርገዋል። ይህ ከሆነ በኃላ ለማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላላ ክስ የአሁኗ ተጠሪ ማቅረባቸውን ከሥር ፍርድ ቤት ብይን ተመልክተናል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ክርክር የሚመራበትን ሥርዓት በግልጽ ያስቀምጣል። የሥነ ሥርዓት ህጉም ዓላማ ክርክር ቀልጣፈ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ተገማች እና ተደራሽ እንዱሆን ማድረግ ነው። የተያዖውን ጉዲይ በተመለከተ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ እንዱቀርብ ብይን ከተሰጠ በኃላ በቅድሚያ የቀረበው ለሸካ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 7 /1/ ሥር አንድ የፍትሐብሕር ክስ መታየት የሚገባው በአንድ የፍትሐብሕር ፍርድ ቤት ብቻ እንደሆነ በመርህ ደረጃ ይደነግጋል። በንዐስ አንቀጽ 2 ላይ አንደን የፍትሐብሕር ክስ ባንድ ወይም ካንድ በበለጡ ፍርድ ቤቶች ዖንድ ለማቅረብ የሚቻል ሲሆን የክሱ ማመልከቻ በቀደምትነት የቀረበለት ፍርድ ቤት ብቻ የዲኝነት ሥልጣን እንዲለው ተቆጥሮ ለክርክሩ ውሳኔ ላሰጥ ይችላል በማለት ተቀምጧል። አሁን ለተያዖው ጉዲይ አግባብነት ያለው የተጠቀሰው ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 7/2/ ሲሆን ይህም ከላይ ከተመለከተው ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ዓላማ አንጻር ላታይ የሚገባ ነው። የማጀንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወረዲ ፍርድ ቤት ቀርቦ በሥረ ነገር ሥልጣን ምክንያት የተዖጋውን ጉዲዩ በይግባኝ ቀደም ሲል አይቶ የዖጋ ሆኖ እያለ አዱስ ክስ ሲቀርብለት መጀመሪያ በሥልጣን ምክንያት በይግባኝ ታይቶ የታለፈውን ግምት ውስጥ በማስገባት የአመልካችን መቃወሚያ ውድቅ ማድረጉ ሲታይ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 7 /2/ ድንጋጌን የጣሰ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም በዘህ ረገድ የተሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የሙጉት ተከፊይ ሆነው ለመከራከር የሚችለ ሰዎችን በተመለከት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ በሁለተኛ መጽሐፍ አንቀጽ 32 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ሥር ዛርዛር ድንጋጌዎችን አስቀምጧል። እነዘህን ተከራካሪዎችን ወክለው ለመከራከር የሚችለ ሰዎችንም በተመለከተ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 57 እና ተከታዮቹ አንቀጾች ሥር ዛርዛር ድንጋጌዎችን ደንግጓል። አሁን በተያዖው ጉዲይ ተጠሪን ወክለው በሥር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት የተጠሪ ወኪል አንቀጽ 58 ወይም 63 ‘ን’ ድንጋጌ የሚያሟለ ናቸው ወይስ አይደለም? የሚለውን መመልከት ተገቢ ይሆናል። አመልካች የተጠሪ ወኪል ከእነዘህ ሁለቱ ድንጋጌዎች አንደንም የማያሟለ በመሆናቸው ሉከራከሩ አይችለም በማለት በሥር ፍርድ ቤት ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል። የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዘህ መቃወሚያ ምንም ብይን ሳይሰጥ በዛምታ እንዲለፈ ከሰጠው ብይን ላይ ተመልክተናል።
አንድ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ለቀረበለት መቃወሚያ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 245 /2/ መሰረት ተገቢውን ብይን መስጠት እንዲለበት በግልጽ ተደንግጓል። ከዘህ ጋር በተያያዖ ተከራካሪ ወገኖች የሚያቀርቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ብይን ሳይሰጥ በማለፍ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የላለው ስለመሆኑ ይህ ችልት በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን በአግባቡ ሳይመለከተውና ለቀረበለት መቃወሚያ ብይን ሳይሰጥ በዛምታ ማለፈ ሲታይ ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የተጠሪ ተወካይ ክስ አቅርበው ለመከራከር እንዱችለ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 58 ድንጋጌን የማያሟለ እንዲልሆነ የተጠሪ ተወካይ ለማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ካቀረቡትና በብይኑ ላይ ከሰፈረው ለመመልከት ችለናል። በተጨማሪ የፍትሐብሕር ሥነ ህግ ቁጥር 63 ድንጋጌንም የሚያሟለ እንዲልሆነ በሥር ፍርድ ቤት ከተደረገው ክርክር ለመገንዖብ ተችሎል። በዘሁ መሰረት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 58 ወይም 63 ድንጋጌን የማያሟለትን የተጠሪን ወኪል የሥር ፍርድ ቤት እንዱከራከሩ ማድረጉ ድንጋጌዎቹን የጣሰ ሆኖ ተገኝቷል። ከዘህ በተጨማሪ አንድን ሰው በመወከል በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመሟገት በህጉ የተቀመጠውን የዛምድና ደረጃ ወይም በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ የውክልና ስልጣን የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ይህ ችልት በ
የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉምን፣እንዱሁም በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ስለዋናዎቹ ባለጉዲዮች በመሆን ላልች ሰዎች በተሟጋችነት ሉቀርቡ ስለሚችለበት ስርዓት፣ በህጉ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልቶ አለመገኘት የሚያስከትለው ህጋዊ ውጤትን በተመለከተ በ
ሥር የተሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያላገናዖ ሆኖ አግኝተነዋል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሚሰጠው ውሳኔ በማንኛውም ደረጃ በሚገኙት ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዲጅነት እንዲለው አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 /1/ ይደነግጋል።
በአጠቃላይ የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከላይ የተመለከቱትን መሰረታዊ ነገሮችን በአግባቡ ሳያጤን የሰጠው ብይን እንዱሁም ቀጥል ያለት የበላይ ፍርድ ቤት ችልቶችም ይህን ሳያርሙ ማለፊቸው ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የማጃንግ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ በቀን 27/11/2007 ዓ/ም የሰጠው ብይን እና በቀን 4/2/2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ፣ የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ.01850/08 በቀን 11/04/2008 ዓ/ም እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በፍ/ሰ/ቁ. 00500/08 በቀን 16/09/2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 348 /1/መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በቀን 09/10/2007 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ መሰረት የተጀመረውን ክርክር በተጀመረው መዛገብ ላይ በመቀጠል የሸካ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክሩን ተመልክቶ የመሰለውን ውሳኔ እንዱሰጥ ተብል ተወስኗል ።
ከላይ በሁለተኛ ጭብጥ በፍርድ ሀተታ ላይ በተገለጸው መሰረት ቀደም ሲል ለተጠሪ ወኪል በመሆን የተከራከሩት አቶ ሞገስ አለምነህ ጉዲዩን ለመከራከር አይችለም ብለናል።
የዘህን ችልት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይላክላቸው።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.