በጠፊው ሰው መሞት ምክንያት መብት የሚያገኙ ሰዎች በመብታቸው መጠቀም የሚችለት መጥፊቱን የሚወስነው ፍርድ የመጨረሻ ከሆነ በኃላ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 165(1)
No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ጸጋዬ አስማማው ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- ወ/ሮ ጸሀይ አጎናፍር ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጌራ ላቀው አልቀረቡም መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ሀብት ክርክርን ይመለከታል የአሁን ተጠሪ የስር አመልካች ሆነው ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ወላጅ አባቴ ኮ/ል ላቀው ወ/ሰንበት ከቤት ወጥቶ ሳይመለስ በመቅረቱ ሚያዘያ 21 ቀን 2007ዓ.ም የመጥፊት ውሳኔ አሰጥቼ ወራሽነቴን አረጋግጫለሁ በመሆኑም የሟች አባቴን የውርስ ሀብት የውርስ አጣሪ ተሹሞ ይጣራልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል ።
ፍ/ቤቱም የውርስ አጣሪ በመሾም የሟች የውርስ ሀብት ተጣርቶ እንዱቀርብ ትእዙዛ ሰጥቷል ውርስ አጣሪው በትእዙዘ መሰረት ኮ/ል ላቀው ወ/ሰንበት ከ10/7/2007ዓ፣ም ጀምሮ ያለበት ሁኔታ ባለመታወቁ ከሚያዘያ 20/2007ዓ.ም ጀምሮ የመጥፊት ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን፣ ኮ/ል ላቀው አመልካችን ብቻ የወለደ መሆናቸውን፣ ኮ/ል ላቀው ከስር አመልካች እናት ጋር ከተለያዩ በኋላ የአሁን አመልካች ወ/ሮ ፀሀይ አጎናፍርን አግብተው መኖራቸውንና ልጅ ያለመውለዲቸውን፣ ኮ/ል ላቀው ከአሁን አመልካች ወ/ሮ ፀሀይ ጋር በባልና ሚስትነት ሲኖሩ በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 02 የቤት ቁጥር 2489 የሆነ ቤት ማፍራታቸውን ቤቱ በአሁን አመልካች እጅ የሚገኝ መሆኑን ሲያጣራ የስር አመልካች የክርክሩ ቤት በወላጅ አባታቸው እና በአሁን አመልካች በጋራ የተፈራ መሆኑን በመግለጻቸው ውርስ አጣሪው የአሁን አመልካች በጉዲዩ ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩ በሰጠው ትእዙዛ መሰረት የአሁን አመልካች የክርክሩን ቤት ከኮ/ል ላቀው ጋር በጋብቻ እያለን 70% ቢሰራም 30% ግን እሳቸው ከቤት ከወጡ በኋላ የሰራሁት የግል ንበረቴ ነው በማለት ክርክር ያቀረቡ በመሆኑ ውርስ አጣሪው ግራ ቀኙ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ትእዙዛ ቢሰጥም የስር አመልካች አቅርበው ሲያስሙ የአሁን አመልካች በተደጋጋሚ ምስክሮች እንዱያቀርቡ ታዖው ካለማቅረባቸውም በተጨማሪ ምስክር የላላቸው መሆኑን በመግለጽ ምስክሮች ያላቀረቡ ሲሆን የውርስ አጣሪው ከግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር እና የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮ የስር አመልካች የክርክሩ ቤት ወላጅ አባታቸው እና የአሁን አመልካች አብረው ባለበት ተጠናቆ የተሰራ መሆኑን ሲያስረደ የአሁን አመልካች ግን ኮ/ል ላቀው ከሄደ በኃላ ለብቻዬ የቤቱን 30 ፏርሰንት ሰርቻለሁ ቢለም አላስረደም በማለት አትቶ የክርክሩ ቤት ኮ/ል ላቀው ወ/ሰንበት እና የአሁን አመልካች ወ/ሮ ፀሀይ አጎናፍር የጋራ ንብረት ነው ስለሆነም የስር አመልካች የአባቱን ድርሻ 50% የአሁን አመልካች ድርሻቸውን 50% እኩል ይካፈለ በማለት ሪፖርት ሲያቀርብ ቤቱ የተከራየ ለመሆኑ የስር አመልካች ሲያስረደ የአሁን አመልካች አለመከራየቱን አላስረደም በማለትና እስከ አሁን የተከራየው ብር 84ሺ ነው በማለት ብር 42ሺ የስር አመልካች ድርሻ ነው በማለት ሪፖርቱ አቅርቧል ።
እዲን በተመለከተ እዲ አለኝ ብል የመጣ ስለላለ ኮ/ል ላቀው አዲ የለባቸውም በማለት ሪፖርቱ ገልጾ ሪፖርቱን ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተሰጠው ትእዙዛ መሰረት ለፍ/ቤቱ ቀርቧል። ፍርድ ቤቱም በቀረበው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዱሰጡበት በሰጠው ትእዙዛ መሰረት የስር አመልካች በውርስ አጣሪ ሪፖርቱ ላይ ያቀረቡት ቅሬታ የላለ ሲሆን ጣልቃ ገብ በሰጡት አሰተያየት የክርክሩን ቤት ከኮ/ል ላቀው ጋር ስንሰራ በየካቲት ወር 1985 ዓ.ም ከባንክ ብድር የወሰድን መሆኑን የሚገልጽ እና ኮ/ል ላቀው ከሄደ በኃላ ለመክፈል ተቸግሬ ባንኩ ማስጠንቀቂያ የሰጠበትን እና ኮ/ል ላቀውም የጻፈትንም ደብዲቤ አቅርቤያለሁ በተጨማሪም ኮ/ል ላቀው ከሄደ በኃላ ለቤቱ ጠቅላላ ዋጋ 30 ፏርሰንት የሚሆን ወጪ አድርጌያለሁኝ በማለት ሰነድች ያያያዛኩኝ ስለሆነ ቤቱን የሰራንበት የጋራ እዲ ያለብን መሆኑ እና በግል የሰራሁት 30 ፏርሰንት የግላ ልባል ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከውርስ አጣሪው ሪፖርት ጋር መርምሮ የአሁን አመልካች ያቀረቡትን 2 ቅሬታ መሰረት በማድረግ 1ኛ.ለክርክሩ ቤት ከባንክ ተወሰደ የተባለውን ብድር አስመልክቶ የአሁን አመልካች ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ማለትም አመልካች እና ባለቤታቸው ኮ/ል ላቀው በየካቲት ወር 1983 ዓ.ም ከቤቶች እና ገንዖብ ቁጠባ በጋራ ለቤት መስሪያ በማለት ገንዖብ የወሰደ መሆኑን፣ ኮ/ል ላቀው በግንቦት ወር 1983 ከሀገር ወጥተው በ1985ዓ.ም ለአሁን አመልካች የጻፈት ደብዲቤ ቤቱ ተሰርቶ ያልተጠናቀቀ መሆኑን ያሳያል።
በማለት አትቶ ምንም እንኳን የስር አመልካች ኮ/ል ላቀው ከቤት ሲወጡ ቤቱ ተሰርቶ አልቆ ነበር በማለት ቢከራከሩም የአሁን አመልካች ማስረጃ ኮ/ል ላቀው ከቤት ሲወጡ ቤቱ ተጠናቆ ያላለቀ መሆኑን በተሻለ አስረድተዋል በማለት አትቶ ቤቱ ተሰርቶ የተጠናቀቀው ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላ ነው በማለት አመልካች ለቤቱ ማሰሪያ ያወጡትን ወጪ የሚያሳዩ ሰነድች ያቀረቡ ስለሆነ ይህ ገነዖብ ከነወለደ የአሁን አመልካች እና የአሁን ተጠሪ የጋራ እዲ ነው በማለት ሲወስን የአሁን አመልካች ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላ የተሰራው ቤት የግል ንብረቴ ይባልልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ ምንም እንኳን ኮ/ል ላቀው ከቤት የወጡት በ1983 ዓ.ም ቢሆንም ከዘሁ ጊዚ ጀምሮ እስከ መጋቢት 22/2002 ዓ.ም ድረስ ከአሁን አመልካች ጋር በደብዲቤ ይገናኙ የነበረ መሆኑን አመልካች ካቀረቧቸው የሰነድ ማስረጃዎች መረጋገጥ መቻለን ገልጾ አመልካች እና ኮ/ል ላቀው በዘህ ጊዚ ውስጥ ሁለ አብረው ባይኖሩም በጋብቻ የነበሩ ባል እና ሚስት ነበሩ በማለት አትቶ በጋብቻ ጊዚ የተፈራ ሀብት በሙለ የባል እና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው በማለት የክርክሩ ቤት የአመልካች እና የባለቤታቸው የኮ/ል ላቀው ነው።
ስለሆነም የአሁን ተጠሪ የአባታቸውን ድርሻ አመልካች የራሳቸውን ድርሻ የቤቱን ግምት እኩል ይካፈለ በማለት የውርስ አጣሪውን ሪፖርት በማሻሻል ውሳኔ ሰጥቷል።
በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች ለስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለዘህ ሰበር ችልት የቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የቀረበውን የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ከቀረበው ክርክር እና ማስረጃ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን መርምረነዋል። እንደመረመርነውም የአሁን አመልካች ዋና ቅሬታ የተጠሪ አቤቱታ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ እያለ ይህ ታልፍ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚል እና የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩ በይርጋ አይታገድም በማለት ውሳኔ የሰጠው እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያጸነው የአሁን ተጠሪ ክርክሩን ያቀረቡት በ6/9/2007ዓ.ም ሲሆን የአባታቸውን የመጥፊት ውሳኔ በፍርድ ቤት ያሳወጁት በ21/8/2007 ዓ.ም በመሆኑ ክርክሩ በይርጋ አይታገድም በማለት ነው።
በፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 165(1)ላይ በጠፊው ሰው መሞት ምክንያት መብት የሚያገኙ ሰዎች በመብታቸው መጠቀም የሚችለት መጥፊቱን የሚወስነው ፍርድ የመጨረሻ ከሆነ በኃላ እንደሆነ ተደንግጓል። የአሁን ተጠሪ ክርክሩን ያቀረቡት በ6/9/2007ዓ.ም ሲሆን የአባታቸውን የመጥፊት ውሳኔ በፍርድ ቤት ያሳወጁት በ21/8/2007 ዓ.ም መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው።
በመሆኑም ከዘህ ጊዚ ጀምሮ በመብታቸው መጠቀም የሚችለ መሆኑ በህጉ የተመለከተ ሲሆን የመጥፊት ውሳኔ አሰጥተው የውርስ ሀብት ያቀረቡበት ጊዚ ሲቆጠር በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ክርክሩ በይርጋ የሚታገድ ባለመሆኑ ይርጋን አስመልክቶ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ላላውን ክርክር በተመለከተ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የውርስ አጣሪውን ሪፖርት ምክንያት በማሻሻል በውጤት ደረጃ ያጸናው ውሳኔ እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ያጸነው ውርስ አጣሪው ኮ/ል ላቀው ከቤት ሲወጡ ቤቱ ተጠናቅቆ የነበረ መሆኑን የስር አመልካች በሰው ማስረጃ አስረድተዋል ስለሆነም የአሁን አመልካች ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላ የሰሩት ተጨማሪ ስራ ለመኖሩ ያላስረደ በመሆኑ የግል የሚባልላቸው መብት የለም በማለት ሲሆን፤
የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይህንን ክርክር አስመልክቶ ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላ ቤቱ ያልተጠናቀቀ መሆኑን እራሳቸው በጻፈት ደብዲቤ ተረጋግጧል በማለት ነው።
ነገር ግን ኮ/ል ላቀው ከቤት የወጡት በ1983 መሆኑ ክርክር ያልተነሳበት ጉዲይ ቢሆንም እስከ 2002 መጋቢት ወር ድረስ በደብዲቤ ከአሁን አመልካች ጋር ይገናኙ የነበረ መሆኑን አመልካች ካቀረቧቸው ማስረጃዎች ማረጋገጥ የተቻለ ስለሆነ ምንም እንኳን አመልካች ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላ የሰሩት ተጨማሪ ቤት መኖሩን በመግለጽ የግላቸው እንዱባልላቸው የጠየቁ ቢሆንም በዘህ ግንኙነት የተፈራ ንብረት የባል እና ሚስቱ የጋራ ንብረት ነው በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን በስር ከተደረገው ክርክር እና ማስረጃ መረዲት ተችሎል።
በመሰረቱ በፋደራለ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 63(1) ላይ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን እስካላስረዲ ድረስ የተጋቢዎች ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ ቢመዖገብም የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት እንደሆነ እንደሚገመት ተደንግጓል። የአመልካች ክርክር በቤቱ ላይ ተጨማሪ ስራ የተሰራው ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላ ነው በማለት ቢከራከሩም እስከ 2002 መጋቢት ወር ድረስ ይጻጻፈት የነበረውን ደብዲቤ አመልካች በማቅረብ ያስረደ መሆናቸውን ከመረጋገጡም በተጨማሪ ኮ/ል ላቀው በ1983 ከቤት ወጥተው የመጥፊት ውሳኔ በፍርድ ቤት የተሰጠው ሚያዖያ 21 ቀን 2008ዓ.ም በመሆኑ የአመልካች እና የኮ/ል/ላቀው ጋብቻ እና ግንኙነት በኮ/ል ላቀው ከቤት መውጣት ያልተቋረጠ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በመሆኑም በጋብቻ ጊዚ የተፈራ ንብረት የባል እና ሚስቱ የጋራ ንብረት ሆኖ እንደሚገመት በህጉ የተደነገገ እና የግል ልባል የሚችለው የግላ ነው የሚለው ተጋቢ የግለ መሆኑን በማስረዲት እንደሆነ በህጉ ተደንግጎ ይገኛል። የአሁን አመልካች ኮ/ል ላቀው ከሄደ በኃላ የተሰራ በመሆኑ የግል ንብረቴ ነው ከማለት በስተቀር በግል ገንዖቤ ሰርቻለሁ በማለት ያነሱት መከራከሪያ የላለ በመሆኑ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የውርስ አጣሪውን ሪፖርት ምክንያት በማሻሻል በውጤት ደረጃ ኮ/ል ላቀው ከቤት ከወጡ በኃላም ተሰራ የተባለው ቤት የባል እና ሚስት የጋራ ንብረት ነው በማለት ውሳኔ መስጠቱ እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ውሳኔ በማጽናት መወሰኑ ህግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
.የስር የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በቀን 6/8/2008ዓ.ም የውርስ አጣሪውን ሪፖርት በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ እና ይህንን ውሳኔ በማጽናት የስር የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሀምላ 8 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በየደረጃው ለሚገኙ የስር ፍርድ ቤቶች የውሳኔው ግልባጭ ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.