በክርክር ተሳታፉ ያልሆነ ወገን በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ እግድ ትዔዙዛ የዔግድ ትዔዙዘን ለሰጠው ፍ/ቤት የዔግድ ይነሳ አቤቱታ ሳያቀርብ በቀጥታ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚያቀርብበት እና የዔግድ ትዔዙዘ ላይ ውሣኔ የሚያሰጥበት ስርዓት የላለ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 154፤158 123833 አቶ ለሜሳ ደገፈ እና የአዲማ ከተማ ማዖጋጃ ቤት መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. VIII 20. በክስ አቀራረብ ሥርዓት ላይ ጉድለት ያለበት መሆኑ ተረጋግጦ የተዖጋ መዛገብ ምንም አይነት ክስ እንዲልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዚ የማቋረጥ ውጤት የላለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 278 (2) (ሀ) እና (3) 123123 አቶ ተኽሉት አፈርቂ እና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሚያዘያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም 21. በአጭር ስነ ሥርዓት ክስ ላቀርብ ስለሚችልበት አግባብ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 284 124552 አቶ ምትኩ አበበ እና የከሰረውሆላንድ ካር ኃ/የተ/የግ/ማሕበር ሚያዛያ 16 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. 22. የሥር ፍ/ቤት በጭብጥነት ይዜ በአግባቡ ባጣራው ፍሬ ጉዲይ ላይ በይግባኝ ፍርደን የሚመለከተው ፍ/ቤት ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተጣራውን ፍሬ ነገር በድጋሚ እንዱጣራ ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለስ ተገቢ ስላለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.136(1)፣343(1) IX ሥነ-ሥርዓትየፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 30፣36፣224 እና 234(1)(ረ) እና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የሆሳህና ከተማ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት
No summary available.
ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓሉ መሃመድ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ ፀሃይ መንክር አመልካች/ዎች/፡- 1. ማክሲመም ኮንስትራክሽን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወኪል አንዋር አሉ ቀረቡ 2. አቶ መሉክ ዓሉ አልቀረቡም ተጠሪ-፡ የደቡብ ብሓር ብሓረሰብና ህዛቦች ክልል የሆሳዔና ከተማ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት አልቀረበም በዘህ መዛገብ አመልካችዎችና ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር፣ አንደኛ አመልካችና ተጠሪ በመዛገብ ካቀረቡት ክርክር ጋር በማጣመር በፍ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/11/4/ መሰረት በማጣመር መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ከዘህ መዛገብ ጋር በተጣመረው በሰበር መዛገብ ፣ ያቀረበው ጉዲይ በመጀመሪያ የታየው በሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤትሲሆን፣ የዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ በዘህ ክርክር ተሳታፉ ያልሆነው ህብረት ኢንሹራስ አ.ማ ተከሳሽ አንደኛ አመልካች ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል።
በዘህ መዛገብ ለተያዖው ጉዲይ ክርክር መነሻ የሆነው አንደኛ አመልካች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው የክስ ማመልከቻ ነው። አንደኛ አመልካች ተጠሪ ከሚያሰራቸው ኮንደሚኒየም ቤቶች አምስት ኮንደሚኒየም ቤቶችን በብር 1,862,626.74 /አንደ ሚሉዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሁለት ሺኅ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም/ ከሳሽ ለተከሳሽ ሰርቼ ላስረክብ ውል ተዋውያለሁ። በውላችን መሰረት፣ ከሳሽ ሶስት ኮንደሚኒየም ቤቶችን ስራ ሙለ በሙለ አጠናቅቄ አስረክቤአለሁ። ሁለት የኮንደሚኒየም ቤቶች ተከሳሽ አለባቸው የሚለውን የግንባታ ጉድለት አስተካክዬ ለማስረከብ ከሳሽ ጥያቄ ባቀርብም ተከሳሽ ባለመፈቀደ፣ በሁለቱ ቤቶች ላይ አለ የተባለውን ጉድለት ለማስተካከል የሚሆን ገንዖብ አስቀርቶ ላላውን ክፍያ እንዱከፍለኝ ብጠይቀው ተከሳሽ ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዘህ የሁለት ህንፃ የጉድለት ማስተካኪያ ወጭ በመቀነስ፣ ለሰራሁት ጠቅላላ ስራ ተከሳሽ ብር 1,018,898 /አንድ ሚሉዮን አስራ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ዖጠና ስምንት ብር/ መክፈል ሲገባው ያልከፈለኝ በመሆኑ እንዱከፍል ውሳኔ ይሰጥልኝ የሚል ይዖት ያለው ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተከሳሽነት ቀርቦ፣ ህንፃዎቹ ሲገነቡ ለህንጻዎች ግንባታ የሚያገለግለት የግንባታ ማቴሪያልች ያቀረበው ተከሳሽ ነው። በዘህ መሰረት ከሳሽ ከሰሪው ስራ ላይ ግንባታ ማቴሪያል ዋጋ ተከሳሽ ቀንሶ የማስቀረት መብት አለው። በዘህ መሰረት የአምስቱ ኮንድሚኒየም ቤቶች ጠቅላላ ዋጋ ከሳሽ በክስ ማመልከቻው ላይ የገለጸው ሲሆን፣ ከሳሽ በቅድመ ክፍያነት .90 /ሶስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ዖጠኝ መቶ ሰላሳ አራት ብር ከዖጠና ሳንቲም/ ወስዶል። ከዘህ በተጨማሪ ከሳሽ የመጀመሪያ ዘር ክፍያ ብር 157,109.07 /አንድ መቶ ሃምሳ ሰባ ሺኅ አንድ መቶ ዖጠኝ ብር ከዚሮ ሰባት ሳንቲም/ ተከፍልታል። ከሳሹ በአጠቃላይ ብር 481,043.97/አራት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አርባ ሶስት ብር ከዖጠና ሰባት ሳንቲም/ ተከፍልታል። ከሳሽ ከሰራቸው አምስት ህንፃዎች ውስጥ ሁለቱ ለሰው መኖሪያነት ሉያገለግለ እንደማይችለ በአማካሪ መሀንዱስና በአዱስ አበባ ዩንቨርስቲ የምድህስና የትምህርት ክፍል ተረጋግጧል። በመሆኑም ከሳሽ ለተከሳሽ የሚከፈለውና የሚመልሰው ሂሳብ ያለበት መሆኑን በማረጋገጥ መተማመኛ የሰጠ በመሆኑ ተከሳሽ ገንዖብ እንድከፍለው የቀረበው ክስ የህግ ድጋፍ የላለውና በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
የስር ተከሳሽ የሆነው ተጠሪ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል። የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ይዖት ከሳሽ ለህንፃዎቹ ግንባታ ከተከሳሽ የተረከበውን በቀድመው ዋጋው ብር 370,666.87 /ሶስት መቶ ሰባ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ብር ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም/ አሁን ባለው ሆሳዔና ከተማ ውስጥ ባለው የገባያ ዋጋ ብር 1,195,231.55/አንድ ሚሉዮን አንድ መቶ ዖጠና አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከሃምሳ አምስት ሳንቲም/ ለህንፃ ግንባታ ሳይሆን ለግል ጥቅሙ ያዋለ ለመሆኑ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ሉከፍል ይገባዋል። በመጀመሪያ ዘር ከተከፈለ ገንዖብ ተመላሽ ሉደርግ የሚገባው ብር 137,147 አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አርባ ሰባት ብር/ እንዱመለስና በሁለቱ የተበላሹ ህንፃዎች ሉከፍል የሚገባው መቀጫ ብር 75,808.81 /ሰባ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር ከሰማኒያ አንድ ሳንቲም በድምሩ ብር 1,590,187.37 /አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ዖጠና ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከሰላሳ ሰባት ሳንቲም/ ከሳሽና የተከሳሽ ስራ አስኪያጅ አቶ መልክ ዓሉ /ሁለተኛ አመልካች በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
ሁለተኛ ተጠሪ በተከሳሽ ላይ ያቀረብኩት ክስ ስላለ እኔን ተከሳሽነት ከሳሽነት ባቀረበው ክስ ገንዖብ በአንድነትና በነጠላ ያቀረበው ክስ ስነ ስርዓታዊ አይደለም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቅርቧል። የተከሳሽ ከሳሽ የከሳሽ ተከሳሽና አቶ መልክ ዓሉ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለት በተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ያቀረበው ገንዖብ የህግ መሰረት የላለው ነው።
ከሳሽ ከተከሳሽ የሚጠይቀው ቀሪ ሑሳብ ያለበት ሆኖ እያለ፣ እንደገና ገንዖብ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ያቀረበው ክስ የህግ ድጋፍ የላለውና በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ከሳሽ /አንደኛ አመልካችና/ ተከሳሽ /ተጠሪ/ የአምስቱን ህንፃዎች እርክክብ ሲፈጽሙ፣ ከሳሽ በተከሳሽ የሚከፍለው ብር 406,446.49 /አራት መቶ ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ ስድስት ብር ከአርባ ዖጠኝ ሳንቲም/ ያለበት መሆኑን በመግለጽ የዔዲ መተማመኛ ፈርሞና በመሀተም አረጋግጦ ሰጥቷል። ይህም ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ያቀረበው የክፍያ ጥያቄ ተገቢነት የላለው መሆኑን ስለሚያረጋግጥ፣ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጌዋለሁ። በአንፃር ተከሳሽ በተከሳሽ ከሳሽነት ከጠየቀው ገንዖብ ውስጥ ብር 406,446.49 /አራት መቶ ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ ስድስት ብር ከአርባ ዖጠኝ ሳንቲም/ እና የመቀጫ ገንዖብ ብር 257,808.81 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር ከሰማኒያ አንድ ሳንቲም በድምሩ ብር 664,255.30 /ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ብር ከሰላሳ ሳንቲም/ ከሳሽና አቶ መለክ ዓሉ በአንድነትና በነጠላ ለተከሳሽ ይክፈለ በማለት በመዛገብ ግንቦት 7 ቀን 2006 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካችዎች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ሰኔ 25 ቀን 2006 ዓ/ም በሰጠው ትዔዙዛ የአመልካችዎችን በፍ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/ 337 መሰረት ሰርዜታል።
በሰበር መዛገብ መነሻ የሆነውን ክስ ለሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ተጠሪ ነው። ተጠሪ ለሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ባቀረበው ክስ ከአንደኛ አመልካች አምስት የኮንድሚኒየም ቤቶች ሰርቶ የማስረከብ ከከሳሽ ጋር የህንፃ ስራ ውል ሲዋዋል ተከሳሽ ህብረት ኢንሹራንስ /አ.ማ/ እስከ ብር 182,262.64 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከስልሳ አራት ሳንቲም/ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሰጥቷል። የስራ ተቋራጩ ስራውን በተሟላ ሁኔታ ያላስረከበ በመሆኑ ተከሳሽ ዋስትና የሰጠበትን ገንዖብ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተከሳሽ የነበረው ህብረት ኢንሹራንስ /አ.ማ/ ክስ ያቀረበበትን የዋስትና ገንዖብ የማይከፍልበትን ምክንያት ዖርዛሮ ተከራክሯል። አንደኛ አመልካች ጣልቃ ገብቶ፣ በህንጻዎቹ ግንባታ ላይ ጉድለት የላለ በመሆኑ የከሳሽ ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። የሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የስራ ተቋራጭ /ጣልቃ ገብ/ ከሰራቸው አምስት ህንጻዎች ውስጥ ሁለቱ ህንጻዎች ጉድለት ያለባቸው መሆኑ ተረጋግጧል። ስለዘህ ተከሳሽ ዋስትና የሰጠበትን ብር 182,262.24 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከሃያ አራት ሳንቲም / ለከሳሽ ሉከፍል ይገባል በማለት በመዛገብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል። አንደኛ አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዛቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዛገብ ህዲር 12 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትእዙዛ የአመልካችን የይግባኝ ቅሬታ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዜታል።
አመልካች በሰበር መዛገብ የሆሳዔና ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም ታህሳስ 8 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ አመልካች ከተጠሪ የምጠይቀው ቀሪ ክፍያ ያለኝ መሆኔን ገልጬ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቤአለሁ። የተሰሩት ቤቶች ጉድለት አለባቸው ወይም የለባቸውም የሚለው ጭብጥ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ታይቶ ከመወሰኑ በፉት፣ የሀዱያ ዜን የሕንጻው ግንባታ ጉድለት ያለበት ነው በማለት ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ከሕብረት ኢንሹራንስ /አ.ማ/ የተያዖው ገንዖብ ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የሚል የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል።
ተጠሪ አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን የአንደኛ አመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚልበትን ምክንያት በመዖርዖር መልስ ሰጥቷል። ጉዲዩ ለዘህ ሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዖው ጭብጥ የሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አንደኛ አመልካች የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8 በመጥቀስ ያቀረበው መቃወሚያ የማለፊቸው አግባብነት በሰበር አጣርቶ ለመወሰን የሚል ነው። ጉዲዩ በሰበር መዛገብ /በዘህ መዛገብ የቀረበው አቤቱታ ያስቀርባል የሚባል ቢሆን ለመጠባበቅ በሚል ከመጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ቀነ ቀጠሮ ሲለወጥ ቆይቶ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም በመዛገብ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ግራቀኙ ያደረጉት ክርክር ከዘህ መዛገብ ጋር ተጣምሮ እንዱታይ ትእዙዛ የተሰጠበት በመሆኑ ከዘህ መዛገብ ጋር ተጣምሮ ታይቷል።
በዘህ መዛገብ ማለትም በሰበር መዛገብ አመልካችዎች ሐምል 2 ቀን 2006 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት፣ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካችዎች በጋራ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ሁለተኛ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ የለም። ተጠሪ ክስ ያላቀረበበት ሁለተኛ አመልካችን በመጨመር ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከሕግ አግባብ ውጭ ተቀብለው የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሳኔ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባዋል። የህንጻዎቹ ጊዚዊ እርክብክብ ሲፈጸም ሁለቱ የኮንድሚኒየም ቤቶች ሙለ ለሙለ እንዱፈርሱ አንደኛ አመልካች እንደተስማማ፣ አንደኛ አመልካች ለተጠሪ ብር 406,446.59 /አራት መቶ ስድስት ሺ አራት መቶ አርባ ስድስት ብር ከሃምሳ ዖጠኝ ሳንቲም/ እንዲለበት የዔዲ መተማመኛ ፈርሞ ሰጥቷል የተባለው ሰው ይህንን ለማድረግ የውክልና ስልጣን የላለው መሆኑን ገልጸን ተከራክረን እያለን የስር ፍ/ቤት ፣ ለጉዲዩ የማይመለከተው ሰው የፈረመውን ፊርማ ሰነድ መሰረት በማድረግ የአንደኛ አመልካች ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግና የተጠሪን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በመቀበል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካችዎች የመቀጫ ገንዖብ እንዱከፍል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ ታህሳስ 16 ቀን 2007 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። ተጠሪ 2ኛ አመልካች የአንደኛ አመልካች ስራ አስኪያጅ በመሆኑና አንደኛ አመልካች ለፈጸመው ጉድለትና ጥፊት በንግድ ሕጉ መሰረት ሃላፉነት ስላለበት፣ በአንድነትና በነጠላ ተጠያቂ እንዱሆን መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል። የውክልና ስልጣን በተመለከተ አዱስ ያቀረበ የፍሬ ጉዲይ ክርክር ነው ከዘያም በኋላ አንደኛ አመልካች ያደረጋቸው መጻጻፍች ስላለ የአመልካችዎች ክርክር ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። በግራቀኙ በኩል የሁለቱም የሰበር መዙግብት ማለትም በዘህ መዛገብና በሰበር መዛገብ ግራቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ በአጭሩ የተገለጸው ሲሆን በትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ ይረዲን ዖንድ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የመዛገብ ቀርቦ ከመዛገቡ ጋር እንዱያያዛ ተደርጓል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሁለቱ የሰበር መዙግብት ግራቀኙ ያቀረቡት የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር በተጠሪ ላይ ክስ ያቀረበው አንደኛው አመልካች ነው። ተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሲያቀርብ፣ በተጠሪ ላይ ክስ ያላቀረበውን ሁለተኛውን አመልካች በተከሳሽ ተከሳሽነት በመጨመር ክስ የቀረበ መሆኑን ተገንዛበናል። የከሳሽ ተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሉያቀርብ የሚችለው በከሳሽ ላይ እንደሆነና፣ ተከሳሽ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሢያቀርብ በፍታብሓር ስነ-ስርዓት ሕግ ቁጥር 224 የተገለጸውን ስርዓት መከተል ያለበት መሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ. 234 ንዐስ አንቀጽ 1/ረ/ ተደንግጓል። ከዘህ በተጨማሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተከሳሹ ሲያቀርብ የፍርድ ቤቱ ስልጣን እንዳት እንደሚወሰን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 30 ተደንግጓል። ተጠሪ በከሳሽነት ያልተሳተፈ ሶስተኛ ወገን /ሁለተኛ አመልካች/ ከአንደኛ አመልካች ጋር አጣምሮ ክስ ለማቅረብ ከፈለገ፣ በፍታብሓር ስነ-ስርዓት ሕግ ቁጥር 36 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት አንደኛ አመልካችንና ሁለተኛ አመልካችን አጣምሮ በአዱስ መዛገብ በመክሰስ መዛገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ. 11/1/ አንደኛ አመልካች ካቀረበው ክስ ጋር ተጣምሮ እንዱታይለት ከሚያመለክት በስተቀር፣ በተጠሪ ላይ ክስ ያላቀረበውን ሁለተኛ አመልካችን በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውስጥ ስሙን መዛግቦና ጨምሮ ማቅረቡ፣ ከላይ የተጠቀሱትን የሕግ ድንጋጌዎች ያልተከተለ ሆኖ እያለ፣ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ በሕግ ከተደነገገው ስርዓት ውጭ ሁለተኛው አመልካች ላይ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተቀብለው ውሳኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ሁለተኛ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው መስከረም 21 ቀን 2004 ዓ.ም የተደረገው የጊዚዊ እርክብክብ ቅጽ ላይ አንደኛ አመልካች ለተጠሪ የሚመልሰው ብር 406,446.49 /አራት መቶ ስድስት ሺ አራት መቶ አርባ ስድስት ብር ከዚሮ አርባ ዖጠኝ ሳንቲም/ እዲ ያለበት መሆኑን ያሚገልጽ ሰነድ ነው ። አመልካች ይህ በጊዚዊ እርክብክብ ቅጹ ላይ የተገለጸው የሑሳብ ስላት ትክክል አለመሆኑን በመግለጽ አንደኛ አመልካች ሙለ በሙለ ሰርቶ ለስራ ከባቻው ሶስት ህንጻዎች መክፈል የሚገባውን ክፍያ ያልከፈለ መሆኑን፣ በመግልጽ የተከራከር ሲሆን ይህንኑ በተመለከተ ያስረደልኛል የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች በማስረጃነት ያቀረበ መሆኑን፣ አንደኛ አመልካችና ተጠሪ በቃል በጽሁፍ ካደረጉት ክርክር ተረድተናል። ይህንንም ክርክር መነሻ በማድረግ የተለያዩ የሙያ አስተያየቶች ከተለያዩ መስራያ ቤቶች የተሰጡ መሆኑን ተረድተናል። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ መስከረም 22 ቀን 2004 ዓ/ም በተዋለው ጊዚዊ የእርክብክብ ቅጽ ላይ ያስፈሩትን የሑሳብ ስላቶ በማስረጃነት የሚጠቀም ከሆነ፣ የጊዚዊ የእርክብክብ ቅጽ ላይ የሰፈሩ ፍሬ ነገሮች አገልግልት የሚስጡት ሙለ እርክብክብ እስኪፈጸምና የመጨረሻው ሑሳብ ተሰርቶ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ብቻ ነው ወይስ አይደለም? ጊዚዊ እርክብክብ ቅጹ ላይ የተገለጸው የሑሳብ ስላት በስራ ተቋራጩና በአስሪው መካከል የሚፈለገውን ክፍያና ሑሳብ ለማስረዲት የሚችላ ሰነድ ነው ከተባለ፣ የዔዲው መታማመኛ የተፈርመው አመልካችን ወክል የዔዲ መተማመኛ የመፈርም ስልጣን ባለው ሰው ነው ወይስ አይደለም? የሚለትን ነጥቦች በጭብጥነት ይዜ ማጣራት ነበረበት። በዘህ ቅጽ ላይ የፈረመው ሰው ማንነቱ ያልተገለጸ ወይም ስሙን ያልተጻፈ ሲሆን ተጠሪ ጊዚዊ እርክብክብ ቅጹ የተፈርመው በአንደኛ አመልካች ስራ እስኪያጅ ነው የሚል ክርክር በስር ፍርድ ቤትና ለዘህ ሰበር ችልት በቀረበው ክርክር አላቀረበም።
ሰነደ አመልካች ስራ አስኪያጅ በወከለው ሰው የተፈርመ ነው የሚል ክርክር ቀርቧል።
የአንደኛ አመልካች ስራ አስከያጅ ወርቅነህ አብዩ ህዲር 24 ቀን 2003 የሰጡት የውክልና ሰነድ ተወካዩ በኩንባያው ስም የዔዲ መተማመኛ እንዱፈርም ስልጣን የማይሰጠው መሆኑን በትዔዙዛ ከቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዛገብ ለመረዲት ችለናል። ኩባንያውን ወክል የዔዲ መተማመኛ ለመፈርም የውክልና ስልጣን በላለው ሰው የተፈረው የዔዲ መተማመኛ ሰነድ መነሻ የስር ፍርድ ቤት አንደኛ አመልካች ያቀረበውን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ ማድርጉና በተጠሪን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተቀብል ውሳኔ መስጠቱ ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በዘህ ምክንያት የስር ፍርድ ቤት የፍታብሓር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 136(1) መሰረት ባለሙያዎችን በመመደብ፤
(ሀ) አንደኛ አመልካች በውለ መሰረት ሰርቶ ላስረከባቸው ሶስት የኮንደሚኒየም ህንጻዎች ግንባታ ተጠሪ መክፈል የሚገባው ጠቅላላ ክፍያና አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች መመለስ የሚገባው የግንባታ የማቴሪያል ዋጋ ምን ያህል ነው።
(ለ) ጉድለት አለባቸው የተባለት ሁለት ህንጻዎች ላይ ያለ ሁለም ኮለኖችና የመሬት ውስጥ ስራዎች ሙለ በሙለ ፈራሽ ይሆናለ አይሆኑም? አንደኛ አመልካች ከመሬት በታችና መሰረቱን ለማውጣት ለሁለቱ ህንጻዎች የሰራው ስራ ግምትና፣ ህንጻዎቹን በመስራት የወሰደው የማቴሪያል ግምት ምን ያህል እንደሆነ ተመዛኖ እንዱመጣ በማድረግና፣ ሁለቱ ህንጻዎች ላይ ለታየው ጉድለት ተጠሪ ሉጠይቅ የሚችለው የጉዲት ካሳ ነው ወይስ የመቀጫ ገንዖብ የሚለውን፣ በማመዙዖን የአንደኛ አመልካችን ክስና የተጠሪን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ መወሰን ሲገባው መስከረም 22 ቀን 2004 ዓ/ም በተምላው የጊዚዊ ዔርክብክብ ቅጽ ላይ ብቻ በመመስረት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዘህ አንጻር ተጠሪ ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የሰጠውን የኢንሹራንስ ድርጅት በሰጠው የዋስትና ግዳታ መሰረት እንድፈጽምለት በሀዱያ ዜን ክስ ያቀረበው ዋስትና ቦንድ የሰጠውን ድርጅት ዋስትና የገባቢትን ገንዖብ እንዱከፍል ለመጠየቅ በመሆኑ አንደኛ አመልካች የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 8 በመጥቀስ ያቀረበውን መቃወሚያ የበታች ፍርድ ቤቶች ማለፊቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
አንደኛ አመልካች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ሲያቀርብ ከሰራቸው አምስት ህንጻዎች ውስጥ ሁለቱ ጉድለት ያለባቸው መሆኑንና የሁለቱን ጉድለት ለማስተካከል የሚያስፈልገውን ገንዖብ ገምት አቅርቧል። የአንደኛ አመልካች የስራ አፈጻጸም ዋስትና የሰጠው ህብረት ኢንሹራንስ (አ.ማ) ለተጠሪ እንዱከፍል የተወሰነበት ብር 186,262.62 /አንድ መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከስልሳ ሁለት ሳንቲም/ የአንደኛ አመልካች የተጠሪ ሑሳብ ተሰርቶ አንደኛ አመልካች ለተጠሪ የሚከፍለው ዔዲ ካለ፣ ከአንደኛ አመልካች ዔዲ ላይ ሉቀነስ የሚገባው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በዘህ ፍርድ ተራ ቁጥር 11 የተያዘትን ጭብጦች ካጣራ በኋላ ሉከተለው የሚገባ የክርክር አመራር ነው። ከዘህ ውጭ የሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአንደኛ አመልካች የስራ አፈጻጸም ዋስትና ቦንድ በሰጠው የኢንሹራንስ ድርጅት ላይ ያቀረበውን ክስ ተቀበለው የሰጡት ውሳኔ የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 8 ድንጋጌን የማይጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ከላይ በዛርዛር በገለጽናቸው ምክንያቶች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ አመልካች ያቀረበውን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግና የተጠሪን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በመቀበል የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ግንቦት 7 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ሰኔ 25 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ትዔዙዛ ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘህ ፍርድ በተራ ቁጥር 11 የተያዘትን ጭብጦች በገለልተኛ ባለሙያዎች ተጣርተው እንዱቀርቡለት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 136(1) መሰረት ትዔዙዛ በመስጠትና ዔውነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለ ማስረጃዎችን በማስቀረብ ወይም ምስክሮችን በመስማት የአንደኛ አመልካች ክስና የተጠሪን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ ላቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ላይ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልስን ልከንለታል።
ሁለተኛ አመልካች ላይ ተጠሪ ያቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ፣ በህጉ ከተደነገገው ስርዓት ውጭ የቀረ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስነናል።
የሀዱያ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የደቡብ ብሓርብሓረስቦችና ህዛቦች ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ ህዲር 12 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአንደኛ አመልካችንና ተጠሪ አከራክሮ ውሳኔ ሲሰጥ፣ ለአንደኛ አመልካች የስራ አፈጻጸም ዋስትና የሰጠው ህብረት ኢንሹራንስ (አ.ማ) ለተጠሪ እንዱከፍል በፍርድ የተወሰነበትን ገንዖብ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሂሳብ ስላቱ እንዱሰራ በማድረግ ውሳኔ ላሰጥበት ይገባዋል በማለት ወስነናል።
በዘህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለራሳቸው ይቻለ።
የዘህ ውሳኔ ግልባጭ ከሰበር መዛገብ ጋር ይያያዛ መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.