No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዘያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኸሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- ዱኖ ኮንስትራክሽን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - አልቀረበም።
መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሓር ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ለአመልካች መክፈል የሚገበው የመኪኖች ዋጋ እንደገና ተጣርቶ ሉወሰን ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ በሕግአግባብ የተሰጠ ነው ወይስ አይደለም?የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በተጠሪ ሥም፤ በአመልካች ገንዖብ፤ ተጠሪ የሚሰራውን መንገድ ለመቆጣጠር አመልካች ለቀጠራችውን ተቆጣጣሪ መሀንድሶች አገልግልት ሲሰጡ የቆዩ የሰላዲ ቁጥር 3-43969 አ.አ እና የላዲ ቁጥር 3-43997 አ.አ የሆኑ መኪኖች አመልካች ለመረከብ ያቀረበውን ክስና የዲኝነት ጥያቄ የሚመለከት ነው።
ተጠሪ ከላይ ቁጥራቸው የተገለፁትን መኪኖች የሥር ከሳሸ /አመልካች/ብር 1,185,688.16 /አንድ ሚሉዮን አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሥምንት ብር ከአስራ ስድሰት ሣንቲም/ ለተጠሪ ሰጥቶ፤ የተገዘና መኪኖቹ አመልካች ለመደባቸው ተቆጣጣሪ መሀንዱሶች አገልግልት ሲሰጡ የቆየ መሆናቸውን ገልፃ፣ ሁለቱም መኪኖች የድርጅቱን ሥራ በመምራት ላይ እያለ የተገለፀው ሙለ በሙለ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። ይህንን ዔውነታ ተከሳሽ የሚያውቀው ሲሆንአዋሽ ኢንሹራንስ /አ.ማ/ ሉያረጋግጠው የሚችለው ፍሬ ነገር ነው። ተከሳሽ መኪኖች አገልግለት የሰጡት ሶስት ዓመት ከሥምንት ወር ዱፕሪሴሽን ዋጋ ተጠቅሶ ቀሪውን ለከሳሽ ለመክፈል በፅሐፍ ጥያቄ አቅርቧል። በልላ በኩል የመኪኖቹ ዋጋ በፉት ከተገዘበት ከእጥፍ በላይ ስለጨመረ ልዩነቱን ከሳሽ ሸፍኖ አዱስ መኪኖች ገዛተው እንዲስረክበው ጥያቄ አቅርቤለታለሁ በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአመልካች የተስማማው መኪኖቹን እንደሆነና መኪኖቹ ተገልብጠው ከጥቅም ውጭ በሆኑ የአገልግልት ቅናሽ ከዋጋቸው ቅናሽ የሚደረግ ስለመሆኑ አመልካችን ተጠሪ ያልተስማሙ መሆኑን ገልፆ፣ ተጠሪ መክፈል የሚገባው መኪኖቹ በወቅቱ ገበያ የሚያወጡትን ገንዖብ መሆን አለበት። ተጠሪ የሶስት አመት ከስምንት ወር የአገልግለት ቅናሽ ከዋጋቸው ላይ ይደረግልኝ በማለት የተከራካሪ ቢሆንም፤ መኪኖቹ በአደጋ ሙለ በሙለ በመውደማቸው፣ ለመኪኖቹ የመድን ሽፊን የሰጠው የኢንሹራንስ ድርጅት፤
አመልካች ክስ ካቀረበበት ገንዖብ ያሰ ገንዖብ የከፈለው መሆኑን፤ በማስረጃ አላረጋገጠም።
ከዘህ በተጨማሪ የመኪኖቹ ግምት እንዱሰራ ትእዙዛሰጥቸ የሰላዲ ቁጥር 3-43969 አ.አ ብር 780,000 /ሰባት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር/የሚያወጣ እንደነበርና የሰላዲ ቁጥር 3-43997 ብር 820,000 / ሥምንት መቶ ሃያ ሺህ ብር/ያወጣ እንደበር ቢርቢስ ገዛሙ የንብረት ጉዲት ገማች ሪፖርት አቅርቦልኛል። ይህም አመልካች ተጠሪ እንዱከፍለው የጠየቀው 348/አንድ ሚሉዮን አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ስድሰት መቶ ሰማኒያ ሶስት በር ከርባ ሥምንት ሣንቲም/ መኪኖቹ በወቅቱ ከሚያወጡት ዋጋ በታች በመሆኑ ይህንን ገንዖብ ክስ ከቀረበበት ጊዚ ጀምሮ ከሚታሰብ፤ ከዖጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዘህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ፤ በአንድ በኩል መኪኖቹ በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት በመወደማቸው ይግባኝ ባዩ /ተጠሪ/ የመድን ሽፊን ከሰጠው የኢንሹራንስ ድርጅት አመልካች የመልሰ ሰጭ እንዱቀበል ማድረግ ሲገባው ራሱ ተቀብል ወስኗል ካለ በኋላ፤ በልላ በኩል ባለሙያው የመኪኖቹ ዋጋ እየጨመረ እንደሚሂድ ታሳቢ በማድረግና የመኪኖቹን የአገልግልት እርጅና ቀናሽ ታሳቢ ሣያደርግ ግምቱን ሰርቶ ማቅረቡ ስህተት ያለበት ነው በማለት የመኪኖቹ ዋጋበልላ ገለልተኛ ባለሙያ ተሰርቶ እንዱቀርብ በማድረግ፣ የሥር ፍርድ ቤት ይግባኝ ባይ ለመልስ ሰጭ ሉከፍል የሚገባውን የገንዖብ መጠን ውሣኔ ይሰጥበት በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሶልኮለታል።
አመልካች ውሣኔ ያረፈበት ገንዖብ ባለሙያ ገምቶ ካቀረበው ያነሰ ሆኖ እያለና፤ የመኪኖች ዋጋ የእርጅና ተቀንሶ ተጠሪ የሚከፍል ስለመሆኑ አመልካችና ተጠሪ በተዋዋለት ውለ ላይ ባልተገለፀበትና ባልተስማማንበት ሁኔታ፤ የባለሙያ ግምት ውድቅ ለማድረግ ወደ ምክንያት ሣይኖረው ይግባኝ ሰሚው ችልት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ መሻሩና ወደ ሥር ፍርድ ቤት ላላ የባለሙያ ግምት እንዱያሰራ ጉዲዩ መልሶ መላኩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ ተፈልጎ ሉገኝ ያልቻለ መሆኑን አመልካች የቃለመሀላ ማመልከቻ በማቅረቡ ህዲር 15 ቀን 2009 ዓ.ም በታተመው አዱስ ዖመን ጋዚጣ ጥሪ ተደርጎለት ባለመቅረቡ፣ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካች የቀረበው የሰበር አቤቱታ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪ መኪኖቹን እንዱመልስለት መኪኖቹን መመለስ የማይችል ከሆነ መኪኖቹን ለመግዙት የሰጠውን ገንዖብ እንዱከፍል የዲኝነት ጥያቄ አቅርቧል። ተጠሪ መኪኖቹ በአደጋ የወደም ለመሆኑ መኪኖቹን በአካል ላስረክበው አልችልም። ተመሣሣይ ይዖት ያላቸው መኪኖች ገዛቸ ለአመልካች ለመተካት፤ የመኪኖቹ ዋጋ ከእጥፍ በላይ ያደገ ስለሆነ፣ ቀሪውን ዋጋ ከሳሽ አመልካች ችል ገዛቸ እንድተካለት ጥያቄ አቅርቤያለሁ። የመኪኖቹ የእርጅናና የአገልግልት ዋጋ ቅናሽ ተደርጎልኝ የመኪኖቹን ዋጋ ልክፈል የሚል መከራከሪያ አቅርቧል። ይህ የተጠሪ ክርክር በጉዲት ካሣ ምክንያት የወደሙት መኪኖች፣በአደጋው ምክንያት ከጥቅምውጭ በሆኑበት ወቅት መኪኖቹ ከተገቡበት ዔጥፍ የሆነ የገበያ ዋጋ የነበራቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ መከራከሪያ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ መኪኖቹ በአደጋው ሙለ በሙለ ወደመው ከአገልግልት ውጭ በመሆናቸው ምክንያት፣ ተጠሪ ለመኪኖቹ የመድን ሽፊን ከሰጠው የኢንሹራንስ ድርጅት፣ የመኪኖቹ የሚከፈለውን የመድን ገንዖብ የተቀበለ መሆኑተረጋግጧል። ለመኪኖቹ የመድን ሽፊን የሰጠው ድርጅት መኪኖቹ ሶሰት ዓመት ከስምንት ወር አገልግልት ከሰጡ በኋላ በአደጋ ምክንያት ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው ምክንያት ለተጠሪ የከፈለው ገንዖብ፣ አመልካች ተጠሪ እንዱከፍለው በክሱ ከጠየቀው ገንዖብ ያነሰ መሆኑን በማንሣት ተጠሪ ያቀረበው ክርክር የለም። በአንፃሩ ተጠሪ የኢንሹራንስ ድርጅቱ ለመኪኖቹ የከፈለው ምን ያህል እንደሆነ ለሥር ፍርድ ቤትም ሆነ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ባቀረበው ክርክር አልገለፀም። ተጠሪ የኢንሹራንስ ድርጅቱ ለመኪኖቹ የከፈለው አመልካች በክሱ ከጠየቀው ገንዖብ በታች መሆኑን እስካላስረዲና በተቃራኒው ከኢንሹራንስ ድርጅቱ የተከፈለውን ገንዖብ ለመግለፅ ፈቃደኛ ካልሆነ፡ ተጠሪ መኪኖቹ ላይ በደረሰው አደጋ ከኢንሹራንስ ድርጅቱ የተከፈለው ገንዖብ አመልካች በክሱ ከጠየቀው ገንዖብ ያልተናነሰ ወይም ከዘህ በላይ ነው የሚለውን የህሉና ግምት ለመያዛ የሚያስችል ነው።
ሶስት ዓመት ከስምንት ወራት ካላገለገለ በኋላ የመገልበጥ አደጋ ደርሶቦቸው ከአገልግልት ውጭ የሆኑት መኪኖች፣ በወቅቱ የነበራቸው የገበያ ዋጋና፣የቅሪት ዋጋቸው ምን ያህል እንደሆነ የሥር ፍርድ ቤት ገለልተኛ ባለሙያ መድቦ አሰርቷል። የተመደበው ባለሙያ የመኪኖቹን ዋጋ የገመተው መኪኖቹ ከፊብሪካ ተመርተው እንደመጡ አዱስ መኪኖች በማድረግ ሣይሆን መኪኖቹ ሶስት ዓመት ከሥምንት ወራትአገልግለው በሚኖራቸው ይዜታ፣ መኪኖቹ ሶስት ዓመት ከሥምንት ወር አገልግልት ሰጥተው የሚያወጡትን ዋጋመሰረት በማድረግ እንደሆነ ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔና አመልካችካቀረበው ክርክር ተረድተናል።
ከዘህ በተጨማሪ ገለልተኛ የንብረት ገማች የሆነው ባለሙያ ያቀረበውን የመኪኖች ዋጋ ግምት ተጠሪ የላላ የባለሙያ ግምት ወይም የተሻለ ዔውቀትናክህልት ያለው ባለሙያ የሙያ ምስክርነት እንዱሰጥ በማድረግ አላስተባበለም። ከዘህ አንፃር ሲታይ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ባለሙያው መኪኖቹ የሰጡትን አገልግልት ከግንዙቤ ውስጥ ሣያስገባ የመኪኖቹን ግምት ሰርቶ እንዲቀረበ አድርጎ በመውሰድ ጉዲዩ እንደና በባለሙያ ይገመት በማለት የሰጠው ውሣኔ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 136/1/ እና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ዓላማ ያላገናዖበና የሥር ፍርድ ቤት በጭብጥነት ይዜ ያላጣራው ምንም አይነት ፍሬ ጉዲይ ሣይኖረው ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተጣራውን ፍሬ ነገር በድጋሚ እንዱያጣራ የሰጠውና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ውሣኔ ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሓር ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በድምፅ ብልጫ ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ የሰጠው ውሣኔ በድምፅ ብልጫ ፀንቷል።
በዘህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.