No summary available.
ሚያዛያ 16 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ምትኩ አበበ - ከጠበቃ ነቃጥበብ ገ/ሚካኤል ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- የከሰረው ሆላንድ ካር ኃ/የተ/የግ/ማሕበር - ነ/ፍጅ ፍቃደ አስፊው መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የጀመረው በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በመ/ቁ.
196585 በተሰጠው ውሣኔ እንደታየው በደቤ የመኪና ሽያጭ ውል ምክንያት መኪና እንዱረከቡ በተወሰነው መሰረት አባይ መኪናን መውሰድ ሲገባቸው ውል ከገቡለት መኪና በዋጋው የብር 66,1ዐዐ.ዐዐ ብር ልዩነት ያለውን ተከዚ መኪና በመውሰዲቸው በብልጫ የወሰደትን የመኪና ዋጋ ብር 66,1ዐዐ.ዐዐ እና ቅድሚያ ክፍያ ከፍለው የቀረባቸውን ገንዖብ ተደምሮ በጥቅለ ብር 192,1ዐዐ.ዐዐ ብር እንዱከፍለ በማለት ነሐሴ 21 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም. በአጭር ሥነ ሥርዓት ታይቶ እንዱወሰንለት ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ የቀረበውን ክስ እና ማስረጃ ከመጥሪያ ጋር ለአመልካች ተልኮላቸው የመከላከያ ማስፈቀጃ ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የስር ተከሣሽ በችልት ቀርበው እዲቸውን ያመኑ በመሆኑ እና የመከለከያ ማስፈቀጃ ቢያቀርቡም እዲቸውን እያመኑ እና እዲ እንደላለባቸው ሣይክደ ወይንም በዋጋ ልዩነት ያለውን መኪና አልወሰደኩም ወይም ደግሞ እዲውን ከፍያለሁ በማለት ሣይገልፁ ወይም በመከላከያ ማስፈቀጃቸው ጽሁፍም ላይ ሣያነሱ መ/ማስፈቀጃ ይፈቀድልኝ በማለት ብቻ ሉፈቀድ የሚገባው ሕግ በሚያዖው መሰረት ሲቀርብ እንጂ መከላከያ ማስፈቀጃ ይፈቀድልኝ በማለት አይደለም ሲል ማስፈቀጃውን ውድቅ አድርጌዋለሁ በማለት አመልካች በሰጡት የእምነት ቃል መሰረት በክሱ የተገለፀውን ገንዖብ እንዱከፍለ በአጭር ሥነ ሥርዓት የወሰነ መሆኑን ገልጾ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሣኔ እንዱሻርለት፤ አመልካች እና ክርክሩ በአጭር ስነ ሥርዓት ላታይ ስለማይገባው መከላከያ ማስፈቀጃው ተቀባይነት አግኝቶ ጉዲዩ እንዱታይለት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ግድፈት የተፈፀመበት አይደለም በሚል የይግባኝ ቅሬታውን ሰርዜታል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውም ይህው በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ ሲሆን፣ አመልካች ሚያዛያ 7 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ የስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያለሕጋዊ ምክንያት የመከላከያ ማስፈቀጃውን ውድቅ ያደረገው እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በይግባኝ ቀርቦለት የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.337 ጠቅሶ የስር ፍርድ ቤት በውሣኔው ላይ ግድፈት አልተገኘም በማለት ይግባኙን የሰረዖው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሞ ነው።
በአጭር ስነ ስርዓት እንዱታይ ክስ የቀረበው በደሀ ደንብ ነው። ተጠሪ ደሀ ልባል አይገባም።
ምክንያቱም ተጠሪ የከሰረውን የሆላንድ ካር ከብር 83 ሚሉዩን ብር በላይ ንብረት እንዱያስተዲድር ተረክቧል። በመሆኑም ዲኝነት ሣይከፍል ክስ ሉያቀርብ አይገባም።
የተጠሪ ክስ ጥያቄ የቀረበው ፍርድ ባረፈበት አፈፃፀም በከፈተበትና በይግባኝ በፀና የሽያጭ ውል ጉዲይ ላይ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 284 መሰረት በአጭር ሥነ ሥርዓት ክስ ላቀርብበት ስለማይችል የተጠሪን ክስ የስር ፍርድ ቤት ተቀብል ያስተናገደው ከሕግ ውጭ ነው። በውል መሰረት በነበረ መኪና ዋጋ በተመሣሣይ የተረከበው መኪና ስለሆነ የዋጋ ልዩነት ሉጠየቅበት አይገባም በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል ተብል ይወሰንልን፣ የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ተሽሮ አመልካች ክሱን እንዱከላከል እንዱፈቀድልኝ ሲለ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ አመልካች በአጭር ስነ ስርዓት ታይቶ እንዱወሰን ለቀረበባቸው ክስ ያቀረቡት ማስፈቀጃ ማመልከቻ በሕጉ መሰረት የቀረበአይደለም በማለት ሳይቀበለው የተሰጠው ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው መልሣቸውን እንዱያቀርቡ መዛገቡ ለሰበር ችልት ላቀርብ ችሎል።
ተጠሪም ግንቦት 1ዐ ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን በመልሱ የገለፀውም ማህበሩ ጥር ዐ7 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በመ/ቁ/ 2ዐዐ8ዐ የመክሰር ውሣኔ ተሰጥቶበታል፣ አመልካችም ከማህበሩ ጋር ለተከዚ መኪና የሽያጭ ውል መዋዋላቸውን፣ ተከዚ መኪና እንዱረከቡ አልያም በግማሽ የከፈለት ገንዖብ እንዱመለስ አመልካች መክሰሳቸውን፣ በዘሁ መሰረት በመ/ቁ/ 196585 በሆነው የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች ተከዚ መኪና እንዱረከቡ እና ለማህበሩም ቀሪ ገንዖብ ብር 126,ዐዐዐ.ዐዐ እንዱከፍለ መወሰኑን፣ ነገር ግን አመልካች በውሣኔው መሰረት ገንዖቡን ያለመክፈላቸውን፣ እንዱሁም አመልካች የተዋዋለት መኪና ተከዚ ሆኖ ዋጋውም 218,ዐዐዐ.ዐዐ ሲሆን አመልካች በአፈፃፀም መዛገብ ቁ. 197933 በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍ/ብሓር ችልት ዋጋው 285,ዐዐዐ.ዐዐ የሆነውን እና ከተከዚ መኪና ልዩነት ያለውን አባይ መኪና የወሰደ ሲሆን ልዩነቱን ብር 66,1ዐዐ.ዐዐ ስለመክፈላቸው ያላረጋገጡ መሆኑን በአጠቃላይ ከአመልካች የሚፈለግ ብር 192,1ዐዐ.ዐዐ/አንድ መቶ ዖጠና ሁለት ሺህ አንድ መቶ ብር/ የሚፈለግባቸው መሆኑን ጠቅሶ ክስ መመስረቱን እና አመልካችም ቀርበው ዋጋው ልዩነት ያለውን መኪና ያለመውሰዲቸውን፣ እዲም የላለባቸው መሆኑን ሳይሆን የተከራከሩት እዲው መኖሩን አምነው ከተጠሪ የሚፈለግበት ገንዖብ ያለ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 242 መሰረት የሚፈለግባቸውን እንዱከፍለ የወሰነ ሲሆን፣ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያላነሱትን ክርክር የአባይ መኪና የወቅቱ ዋጋ 285,ዐዐዐ.ዐዐ አይደለም በማለት መከራከራቸው ተቀባይነት የላለው መሆኑን እና ችልቱም በሕግ መሰረት የፍሬ ጉዲይ ክርክር የማድረግ ሥልጣን የላለው መሆኑን ገልፆ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ እንዱፀናለት ጠይቀዋል። አመልካችም በቀደመው አቤቱታ ያቀረቡትን በመልስ መልስ በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዛገብ ተያይዝል።
No topics extracted.
ፍ/ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ እና መልስ ከስር ፍርድ ቤት ውሣኔ እና በአጣሪው ከተያዖው ጭብጥ አንፃር አግባብነት ካለው ድንጋጌ ጋር በማገናዖብ መርምሯል።
አመልካች ከተጠሪ ጋር የመኪና ሽያጭ ውል መኖሩ ያላከራከረ ሲሆን ግራ ቀኙም በመኪናው እርክክብ ላይ ያነሱት የተለየ ነገር የለም። በመሆኑም አመልካች ተጠሪ በአጭር ስነ ሥርዓት ያቀረቡት ክስ ደርሷቸው የመከላከያ ማስፈቀጃ ማቅረባቸውን የስር ፍርድ ቤት በውሣኔው ላይ የመዖገበ ሲሆን ያቀረቡት የመከላከያ ማስፈቀጃ ጥያቄን ማቅረባቸውን ጠቅሶ ነገር ግን ያቀረቡት የመከላከያ ማስፈቀጃ ይዖት በክሱ ላይ ያለውን ገንዖብ መልሻለሁ፣ እዲም የለብኝም በማለት ሳይሆን በቃል በችልትም ሲጠየቁ ገንዖቡ እዲቸው መሆኑን አምነው ነገር ግን ከተጠሪ የምፈልገው ገንዖብ ስላለ ነው በማለት እንዱፈቀድላቸው መጠየቃቸውን ገልጿል።
ተጠሪ ከላይ የተገለፀውን መኪና ያስረከበው በፍርድ አስገዲጅነት ሳይሆን ተከዚ መኪና እንዱያስረክብ ተወስኖ አባይ መኪና ያስረከበው ፍርድ ከተሰጠና በዋናው ጉዲይ አፈፃፀም ላይ እያለ ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት መሰረት መሆኑን የስር ፍርድ ቤት መዛገብን አስቀርበን ተመልክተናል።
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 284 መሰረት በአጭር ስነ ሥርአት የሚቀርብ ክስ ላቀርብ የሚችለው ምንም አይነት መከራከሪያ በልላኛው ወገን የማይቀርብ መሆኑ ሲረጋገጥ እና ወዱያው ሉወሰን የሚችል ሲሆን መሆኑን የሕጉ ድንጋጌ ያሳያል።
የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 284/ሀ/ በአጭር ሥነ ሥርዓት ክስ ለማቅረብም በግልጽ ውል ወይም በነገሩ አካባቢ ሁኔታ በሚመሰረት ውል ወይም በሐዋላ ወረቀት ወይም በገንዖብ አለብኝ ሰነድ ወይም በቼክ ወይም ተራ የሆነ ባለዔዲነትን የሚመለከት ውል መሆን እንዲለበት ይደነግጋል። አመልካች እና ተጠሪ በቅድሚያ የተገናኙት በውል ቢሆንም ነገር ግን አሁን የሚፈለገውን ገንዖብ ስር ከሳሽ እየጠየቀ ያለው የቀደመውን ውል ለማስፈፀመ በተደረገ ስምምነት ላይ የተጨመረው እንጂ በግልጽ ውል ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ እንዱሁም ስር ከሳሽ ባቀረበው ክስ ስር ተከሣሽ ደግሞ የምጠይቀው ገንዖብ አለኝ እያለ ያለ በመሆኑ በግራ ቀኙ መሐከል ክርክር ያለ መሆኑን ያመለክታል። ይህ ከሆነ ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 284 ከሚፈቅደው የአጭር ስነ ሥርዓት ውጭ መሆኑን የሚያሳይና የክርክሩ አመራርም በመደበኛው የሙግት ሥርዓት መመራት የሚገባው መሆኑን ተረድተናል።
በመሆኑም የቀረበውን ክስ ተከሣሽ አልካደም በማለት ብቻ ተከሣሽ የሚያቀርበውን ላልች ገንዖቡን ልከፍል አይገባም በማለት የሚያቀርባቸውን መከራከሪያ ነጥቦች በመገደብ እና የመከላከያ ማስፈቀጃውን ውድቅ በማድረግ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 231275 ሕዲር 3ዐ ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ እና ፍርድ ከዘህ በፉት በተመሳሳይ ጉዲይ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁ/ 43315 የሰጠውን አስገዲጅ ውሣኔ ካለማገናዖብ እና የቀረበውን ጉዲይ ካለመመርመር የሰጠው ውሣኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሲሆን፣ ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ በመ/ የካቲት 21 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም በዋለው ችልት በስር ፍርድ ቤት ትዔዙዛ እና ውሣኔ ላይ የተፈፀመውን የሕግ ስህተት ሳያርም የስር ፍርድ ቤት ፍርድ ጉድለት የላለበት ነው በማለት የሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ትዔዙዛ እና ፍርድ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 174388 የካቲት 21 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሕዲር 1ዐ ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በውሣኔ የዖጋውን የመ/ቁ/ 231275 በማንቀሳቀስ ጉዲዩ በመደበኛ ስነ ስርዓት እንዱገባ በማድረግ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመመልከት ተገቢ ህጋዊ ውሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
ከስር ፍርድ ቤት የቀረበው የመ/ቁ/ 231275 የሆነው መዛገብ በመጣበት አኳኋን ተመላሽ ይደረግ።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች እንዱላክ ታዝል።
መዛገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዖግቷል።