No summary available.
ሚያዘያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ አይሸሹም መለሰ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ተኽሉት አፈወርቂ - አልቀረበም ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን - የመቀላ ቅርንጫፍ አልቀረበም መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
አመልካች ተጠሪ መኪናዬን አላግባብ ቁጥጥር ስር በማዋል ጉዲት አድርሶብኛል በማለት ግንቦት 29 ቀን 2004 ዓ.ም የተጻፈ ክስ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ፣ በቀረበው ክስ ውስጥ ያሰፈረው ፍሬ ነገር ዔውነት ስለመሆኑ የአመልካች ጠበቃ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
92 መሰረት ለማረጋገጥ እንደማይቻልና አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 92 መሰረት የክሱን እውነተኛነት ቀርቦ ያረጋግጥልን በማለት በመቃወሙ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጅምሩ በሬጅስትራር በኩል ቴክኒካል መስፈርቶች የተሟለ መሆኑ ተረጋግጦ ያልቀረበ መዛገብ ነው በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዛገቡን ዖግቶታል።
ከዘህ በኋላ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረብኩት ክስ የተጋነነ ስለሆነ አስተካክዬ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ይፈቀድልኝ በማለት ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ/ም አመልክቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም አመልካች ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ ለማቅረብ እንደሚችለ በመግለጽ ትዔዙዛ ሰጥቷል። አመልካች ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም ለመቀላ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ ተጠሪ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ቴክኒካል ሁኔታዎችን ባለማሟላቱ የተዖጋ በመሆኑ ይርጋ ሉያቋርጥ አይችልም። ስለዘህ ክሱ በይርጋ ይቋረጣል በማለት ያቀረበውን መቃወሚያ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማለፈ፣ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የወሰነ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ያለ ፍርድ ቤቱ ፈቃድ ክሱን ያቋረጠ በመሆኑ፤ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦት በነበረው ክስ ይርጋ አይቋረጥም። ስለዘህ መኪናዋ ከተለቀቀችበት ጊዚ ጀምሮ ሲታሰብ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ብይን ሰጥቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንን በመቃወም ሲሆን ተጠሪም በጽሁፍ መልስ ሰጥቷል አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተገለጸው ሲሆን፣ በእኛ በኩል እንዲየነው አመልካች ተጠሪ መኪናዬን ከህግ አግባብ ውጭ በመያዛ፣ ጉዲት ስላደረሰብኝ ካሳ ይክፈለኝ በማለት በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዛገብ ግንቦት 24 ቀን 2004 ዓ.ም አቅርቦት የነበረው ክስ በፍታሐ ብሓር ሥነ- ሥርዓት ህግ ቁጥር 92 መሰረት ዔውነት መሆኑ ተረጋግጦ ያልቀረበ መሆኑን በመግለጽ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሱን ውድቅ በማድረግ መዛገቡን የዖጋው መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች በህጉ የተገለጸው ቴክኒካል መስፈርት አያሟላም ተብል የተዖጋበት መዛገብ እንዱንቀሳቀስለት ያመለከተው ፍርድ ቤቱ አልተሟላም ያለውን መስፈርት ለማሟላት ሳይሆን፣ በቀረበው ክስ የተገለጸው የገንዖብ መጠን የተጋነነ በመሆኑ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሳችንን እንድናቀርብ በማለት እንደሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይዖት ተረድተናል።
ይህም አመልካች በተጠሪ ላይ በመዛገብ ግንቦት 24 ቀን 2004 ዓ.ም አቅርቦት የነበረው ክስ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 278 ንዐስ አንቀጽ 2(ሀ) በተደነገገው መሰረት የአመልካች ክስ በፍ/ስ/ስ/ህግቁጥር በተደነገገው መሰረት ዔውነት ስለመሆኑ ተረጋግጦ በከሳሽ (አመልካች) ባለመቅረቡ ምክንያት ውድቅ ያደረገው መሆኑንና አመልካች ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም ባቀረበው ማመልከቻ፣ በክሱ ውስጥ ተጠሪ (ተከሳሽ) እንዱከፍል የተጠየቀው ገንዖብ ዔውነትነት የላለውና የተጋነነ መሆኑን የሚገልጽ በመሆኑ ከሳሽ ክሱን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 92 መሰረት ዔውነት መሆኑን በማረጋገጥ ክሱ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለማስቀጠል እንደማይችል መሆኑን በማረጋገጥ ክሱን ስልጣን ላለው ፍርድቤት ለማቅረብ እንዱችል ጥያቄ ያቀረበበት ነው።
ይህም አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.ር92 መሰረት ዔውነት መሆኑን በማረጋገጥ ያቀረበው ክስ የላለና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህ ቴክኒካል ሁኔታ ካልተሟላ ጉዲዩን ልመለከተው አልችልም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.ር 278 ንዐስ አንቀጽ 2 (ሀ) መዛገቡ እንዱዖጋ የሰጠውን ትዔዙዛ ለማስለወጥ የሚያስችል በቂ ምክንያት በማቅረብ ክሱ እንዱቀጥል ያላደረገ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ስለሆነም አመልካች በመዛገብ ግንቦት 24 ቀን ያቀረበው ክስ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.92 የተደነገገውን አስገዲጅ መስፈርት የማያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዛገብ እንዱዖጋ የሰጠው ትዔዙዛ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምንም አይነት ክስ እንዲላቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዚ የማቋረጥ ውጤት የላለው መሆኑን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.278 ንዐስ አንቀጽ 2(ሀ) እና ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች ይዖትና ይህ ሰበር ችልት ስለድንጋጌዎቹ ዓላማ ተግባራዊ አፈጻጸምና ህጋዊ ውጤት በሰበር መዛገብ ከሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ለመረዲት ይቻላል።
ከዘህ አንጻር ሲታይ አመልካች መኪናዋ እንድትለቀቅ በፍርድ ከተወሰነበት የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ለመቀላ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ እስካቀረበበት ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ። መብቱን ለማስከበር ህጋዊና ቴክኒካዊ መስፈርቶችን ያሟላ ክስ አቅርቦ እንደማያውቅ ተቆጥሮ የይርጋው ጊዚ መሰላት ያለበት በመሆኑ አመልካች የፍታሐ ብሓር ህግ ቁጥር 2143 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገው የሁለት ዓመት የይርጋ የጊዚ ገደብ ካለፈ ከአስር ወራት በኋላ ክሱን ለመቀላ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ ከላይ የተጠቀሱትን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
No topics extracted.