አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከተከራካሪ ወገኖች አንዲቸው በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታ ሲያቀርቡለት በስር ፍ/ቤት የታዩ ሰነድችን ወይም መታየት የነበረባቸውን ሰነድች አስቀርቦ ሳይመረምር በይግባኙ ላይ ውሳኔ፣ ፍርድ ወይም ትእዙዛ መስጠት የላለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 145/1/
No summary available.
ሕዲር 30ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች(ዎች)፡- 1. ወ/ሮ ሙለነሽ ደሬሳ 2. አቶ ዮሐንስ ይባስ ጠበቃ መስፍን እሸቱ ቀረቡ 3. ወ/ሮ ቆንጂት ይባስ 4. ወ/ሮ መቅደስ ይባስ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች በውርስ ያገኘናቸው ሁለት ቤቶች ሸራተን አዱስ ሲገነባ በልማት ምክንያት የፈረሱ በመሆኑ፣ የመንግስት አልታድ ከሚባለውድርጅት ጋር አድርጎት በነበረው ስምምነት መሰረት በፈረሱት ሁለት ቤቶች ምትክ የተሰሩትን የቤት ቁጥር 459 እና የቤት ቁጥር 530 ተከሳሾች /ተጠሪዎች/ እንዱያስረክቡ ውሳኔ ይሰጥልን በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ የበታች ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉትን በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ከሳሾች /አመልካቾች/ ለስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካቾች አንደኛ አመልካች የአቶ አብተስላሴ ወራሽ መሆኗንና ስማቸው ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ተራ ቁጥር የተገለጹት አመልካቾች የሟች ይባስ ሰዲን ወራሽ መሆናቸውን ገልጸው፤
የከሳሾችአውራሽ ሟች ይባስ ሰዲን በህይወት እያለ በወረዲ 14 ቀበላ 24 ቁጥር 382 እና ቁጥር 379 የሆነ ቤቶች አፍርተዋል። ሟች ከዘህ አለም በሞት ሲለይ 1964 ዓ/ም የሟች ወራሾች በመሆናችን ከፍርድ ቤት አረጋግጠን ሟች ያፈራቸውን ቤቶች ወርሰናል። የሟች አባታችን ሀብት የነበሩትና ከሳሾች በውርስ ያገኘናቸው ቤቶች ቦታው ሸራተን አዱስ ሆቴል ለመገንባት በመፈለጉ ምክንያት ስፍራው በአልታድ ኩባንያ በኩል ወረዲ 28 ቀበላ 04 ክልል በአሁኑ አጠራር በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ14/15 በፈረሰው ቤት ቁጥር 379 ምትክ የቤት ቁጥር 459፣ በፈረሰው የቤት ቁጥር 382 ምትክ የቤት ቁጥር 530 የሆኑት ተገንብተዋል።
ከሳሾች የውርስ ያገኛቸውን ቤቶች ተካፍለው እንዱቀርቡ በሚመለከተው አካል በተሰጣቸው ትዔዙዛ መሰረት በልማት ምክንያት የፈረሰው የቤት ቁጥር 382 የአንደኛና ሁለተኛ ከሳሾች ድርሻ መሆኑና የቤት ቁጥር 382 የሶስተኛና አራኛ ከሳሾች ድርሻ ተገልፆ የሚመለከተው አካል መዛግቦታል። በመሆኑም ከሳሾችበውርስ ባገኘናቸው ቤቶች ምትክ የተሰሩትን የቤት ቁጥር 459 እና የቤት ቁጥር 430 አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ከሶስተኛና አራተኛ ተከሳሾችተከራይተው እየኖሩባቸው በመሆኑ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ቤቶቹን ለቅቀው እንደወጡ፣ ሶስተኛና አራኛ ተከሳሾችከአንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ጋር ያደረጉትን የክራይ ውል በማቋረጥና ቤቶቹን በማስለቀቅ ለከሳሾች በድርሻችን መሰረት እንዱያስረክቡ ውሳኔ ይሰጥልን የሚል ይዖት ያለው ክስ አቅርበዋል።
ተከሳሾች የፈረሱት የቤት ቁጥር 379 እና የቤት ቁጥር 382 በአዋጅ ቁ/47/67 መሰረት የተወራሾችፍርድ ቤቱ ስልጣን የላለው መሆኑን ገልጸው ተከራክረዋል ። የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን እንደላለው ገልፆ መስከረም 1 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ትዔዙዛ ዖግቶታል። አመልካቾች በዘህ ብይን ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝን በይግባኝ መዛገብ ቁጥር 97896 ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዔዙዛ በመሻር የፋ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን መልሶለታል።
ጉዲዩን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመለሰው በኋላ አንደኛ ተከሳሽ /አንደኛ ተጠሪ ብቻ ቀርበው ክርክራቸውን አቅርበዋል። አንደኛ ተጠሪ 1972 ዓ/ም ጀምሮቤቱን ከመንግስት ተከራይቼ በመኖር ላይ እገኛለሁ። ተከሳሾች የቤት አበል ይወሰደ ነበር በማለትየተከራከሩ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ፣ ሶስተኛ ተጠሪና አራተኛ ተጠሪዎች ክርክሩ በሚሰማበት ቀነቀጠሮ ባለማቅረባቸው ጉዲዩ እነርሱ በላለበት እንዱታይ የስር ፍ/ቤት ብይን ሰጥቶ፣ ጉዲዩን ሁለተኛና አራተኛ ተጠሪዎች በላለበት አይቶ ውሳኔ ሰጥተዋል። የስር ፍ/ቤት የሽግግር መንግስት የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የቤት ቁጥር 379 የሶስተኛና አራተኛ ከሳሽ ድርሻ፣ የቤት ቁጥር 382 የአንደኛ አመልካች ልጅና አውራሽ የሆነው የሀብተስላሴ ይባስና የሁለተኛ ከሳሽ ድርሻ መሆኑን የመግለጽ በወቅቱ ለነበረው የክልል 14 አስተዲደር የፃፈው ደብዲቤ በማስረጃነት ከሳሾች ያቀረቡ መሆኑን ገልፆ፣እነዘህ የሰነድ ማስረጃዎች ከሳሾች ክስ ባቀረቡባቸው ቤቾችላይ መብትና ጥቅም ያላቸው መሆኑን አያረጋግጡም በማለት የስር ከሳሾች /አመልካቾች/ ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች ከዘህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዋል የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካቾች ለዘህ ሰበር ችልት መጋቢት 2 ቀን 2006 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ ስማችን ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ተራ ቁጥር የተገለጸው አመልካቾች አቶ ሀብተሰባሲ ይባስ የሟች የአቶ ይባስ ሰዳ ወራሽ መሆናችን በመዛገብ ቁጥር 221/65 በፍርድ ቤት ውሳኔ ተረጋግጧል። ሀብተስላሴ ይባስ የጠፊና አንደኛ አመልካች የሀብተስላሴ ወራሽ መሆናቸው በፍርድ ቤት አስወሰነናል። አዋጅ ቁ/ 47/67 ከመውጣቱ በፉት የአባታችን ንብረት የነበሩት ሁለት ቤቶች ባለቤትነት ለወራሾች የተላለፈልን ሲሆን፣ የውርስ ንብረቶቹን በመከፊፈል የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የባለሀብትነት ማስረጃ እንዱሰጠን፣ ቤቶቹ የከሳሾች ድርሻ መሆናቸውን በአዋጅ ቁ/ 47/1967 ስልጣን የተሰጠው የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር አጣርቶና አረጋግጦ የሰጠንን ማስረጃ የበታች ፍ/ቤቶች ውድቅ ያደረጉት ከህግ አግባብ ውጭ በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪዎች በተለያዩ ጊዚ በተናጥል ፅፈው ባቀረቡት መልስ፣ የፈረሱት ቤቶች የአመልካቾች አውራሽ ንብረት ስለመሆናቸው አመልካቾች ያቀረቡት ማስረጃ የለም። የሟች ይባስ ሰዳ ወርሶ በውርስ አጣሪ በኩል ተጣርቶ፣ ቤቶች ለአመልካቾች ያደረሱ ስለመሆናቸው አመልካቾች አላስረደም የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የፃፈው ደብዲቤ አመልካቾች የቤቶች ባለሀብት መሆናቸውን የማስረዲትና የማረጋገጥ የአስረጂነት ብቃት የለውም ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ተወርሰው መንግስት ለረዣም ጊዚ ስያስተዲድራቸውና እያከራየ ሲጠቀምባቸው የኖሩ በመሆኑ፣ ቤቶች ያልተወረሱ መሆናቸውን የማስረዲት ግዳታ ያለባቸው ከሳሾች /አመልካቾች/ በመሆናቸው አመልካቾች የማስረዲት ግዳታቸውን ስላልተወጡ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የህግ ስህተት የለበትም። አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ ቤቶችን ከሶስተኛና አራኛ ተጠሪዎች ተከራይተን እየኖርን ሲሆን፣ ከከሳሾች ጋር የሚያገናኘን ከውል ወይም ከህግ የመነጩ ግንኙነት የለንም በማለት የተከራከሩ መሆኑን ተረድተናል።
አመልካቾች የመልስ መልሳቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዘህ ሰበር ችልት የቀረቡ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን የሰበር ችልት ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት እንድችል የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመዛገብ ቁ/ 171029 አስቀርቦ መመልከቱ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ መዛገቡ እንዱቀርብ በማድረግ ተመልክቶታል። በስር ፍ/ቤት በማስረጃነት ተያይዖው ከሚገኙ የፍ/ቤት ውሳኔዎችና ላልች የሰነድ ማስረጃዎች፣ አመልካቾች በአከራካሪዎቹ ቤቶች ላይ ያላቸውን መብት ለማረጋገጥ፣ በተለያየ ጊዚ ለተለያዩ ፍርድ ቤቶች፣ ክስ ሲያቀርቡና ሲከራከሩ የቆዩ መሆኑን አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የማስረጃ ዛርዛር መግለጫ የገለጽዋቸውና በማስረጃነት ካያያዝቸው የተለያዩ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ለመረዲት ችለናል።
አመልካቾች በአከራካሪዎች ቤቶች የአባታቸው የሟች ይባስ ሰዳ መሆናቸውን ለማስረዲት ለዘህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነውን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመዛገብ ቁ/ 171029 ከማስከፈታቸው በፉት ክስ አቅርበው በተከራከሩባቸው ላልች መዙግብት ላይ በማስረጃነት አቅርበው የያዙቸው ጠቃሚ የሰነድ ማስረጃዎች በፍ/ስ/ስ/ህግ/ቁ145/1/ መሰረት አስቀርቦ ማየትና መመርመር ያስፈልጋል። ይህም የሚሆነው አመልካቾች በቤቶች ላይ ያላቸውን መብት ለማስከበር ክርክር የጀመሩት ከሁለት አስር ዓመት በፉት መሆኑና በጉዲዩ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሲከራከሩ ረዣም ዖመን ያስቆጠረ መሆኑን፣ የአመልካቾች የሰነድ ማስረጃዎች በተለያዩ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ተያይዜ የሚገኝ መሆኑን፣ አመልካቾች በማስረጃ ዛርዛር መግለጫቸው ዖርዛረው በማስረጃነት ካያያዝቸው የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ተገልፀው እያለ፣ እነዘህን ጠቃሚ ሰነድች ያለባቸውን የፍርድ ቤት መዛገቦች በፍ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/ 145/1/ መሰረት አስቀርበው ሳያዩ፣ አመልካቾች አከራካሪዎቹ ቤቶች የሟች አባታቸው ይባስ ሰዳ ለመሆናቸው የስራና ከተማ ልማት ሚኒስተር ከፃፈዉ ደብዲቤ ዉጭ ላልች ደጋፉ ማስረጃዎች አላቀረቡም በማለት የበታች ፍርድቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ እዉነታዉን የማያንጸባርቅና ከላይ የጠቀሳቸዉን የህግ ድንጋጌዎች ያልተከተለ ሆኖ አግኝተነዋል ።
አመልካቾች ክስ ያቀረቡባቸው የቤት ቁጥር 379 እና የቤት ቁጥር 382 የሟች ይባስ ሰዳ ንብረቶች እንዱሆኑ፣ የአመልካቾች አውራሽ አዋጅ ቁጥር 47/67 ከመታወጁ በፉት መሞታቸውናአመልካቾች የሟች ወራሾች መሆናቸውን በስር ፊይል መዛገብ ቁጥር 221/65 በፍርድ ቤት ውሳኔ ያረጋገጡ መሆኑን፣ አመልካቾች ከአባታቸው በውርስ የተላለፈላቸውን ሁለት ቤቶች 1974 ዓ/ም ወራሾቹ ባደረጉት የውርስ ንብረት ክፍያ ስምምነት መሰረት፣ የቤት ቁጥር 379 የአንደኛና የሁለተኛ አመልካቾች ድርሻ መሆኑን የቤት ቁጥር 352 ደግሞ የሶስተኛ አራተኛ አመልካቾች ድርሻ መሆኑ ተረጋግጦ የተላኩለትና ይህንንም በአግባቡ መዛግቦ ያያዖ መሆኑን በመግለጽ የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የካቲት 10 ቀን 1987 ዓ/ም እና ጥቅምት 25 ቀን 1990 ዓ/ም በፃፈው ደብዲቤ የረጋገጠ መሆኑን በትዔዙዛ ባስቀረብነው በስር ፍርድ ቤት መዛገብ ውስጥ አመልካቾች ካቀረቡአቸው የሰነድ ማስረጃዎች ይዖት መረዲት ችለናል።
የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የካቲት 10 ቀን 1987 ዓ/ም እና ጥቅምት 25 ቀን 1990 ዓ/ም ለአዱስ አበባ አስተዲደር የጻፊቸው ደብዲቤዎች መሆናቸውን ገልጸው፣አመልካቾች ያቀረባቸው ሰነድች፣ የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ደብዲቤ አፃፃፍ ስርዓት ጠብቆ ለክልለ 14 መስተዲደር ጽፍና ወጭ አድርጎ የላካቸው ደብዲቤዎች መሆናቸውን ተጠሪዎች በመካድ ያቀረቡት ክርክር የለም። ሰነድቹ ሀሰተኛ ሰነድ ናቸው በማለት አልተከራከሩም። ይህም ማለት ሰነድቹ በእርግጠኝነት የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት አሰራርና የጽሁፍ ማረጋገጫ አፃፃፍ ስርዓትን ጠብቆ ለክልለ 14 መስተዲደር የፃፊቸው፣ ዔውነተኛ ደብዲቤዎች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ደብዲቤዎችን የፃፈው ባለው አሰራር መሰረት ተገቢውን ማጣራት በማድረግና አከራካሪዎቹ ቤቶች የሟች ይባስ ሰዳ ንብረቶቹ መሆናቸውን፣ የንብረቶቹ ባለቤት አዋጅ ቁጥር 47/67 ከመታወጁ በፉት ከዘህ አለም በሞት መለየቱንና አመልካቾች የሟች ወራሽ መሆናቸውን አዋጅ ቁጥር 47/67 ከመታወጁ በፉት መዛገብ ቁ/ 221/65 ማረጋገጣቸውንና አመልካቾች በውርስ ያገኘዋቸውን ቤቶች፣ በወራሾች ስምምነት 1974 ዓ/ም ተከፊፍለው ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የውርስ ንብረቶቹን የተከፊፈለበትን ሰነድ አቅርበው ሰነደ በአግባቡ ተቀምጦ የሚገኝ መሆኑን የሚገልጽ ደብዲቤዎች ናቸው።
አዋጅ ቁጥር 47/67 የማስፈጸም ኃላፉነትና ስልጣን የተሰጠው የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 15 ተደንግጓል። ይህ በህግ ስልጣን የተሰጠው የመንግስት መስሪያ ቤት በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በየደረጃው ያዋቀራቸውን አደረጃጀቶች በመጠቀም ተገቢውን ማጣራት በማድረግ፣ የቤት ቁጥር 379 እና የቤት ቁጥር 382 የአመልካቾች አውራሽ ሟች ይባስ ሰዳ እንደሆኑ በማረጋጥ የፃፈው ደብዲቤ፣ አከራካሪዎቹ ቤቶች የሟች ይባስ ሰዳ ስለመሆናቸው የሚያስረዲ ብቃት ያለው ማስረጃ ሆኖ እያለ ደብዲቤዎቹን የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት አሰራር ስርዓትን ተከትል የፕሮቶኮል ቁጥር፣ ቀን፣ የባለስልጣን ፊርማና የሚኒስቴር መስሪያ ቤት የራስጌና የግርጌ ማህተም በማረጋገጥ ውጭ አድርጎ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የፃፎቸው መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ፣ ደብዲቤዎቹ ውስጥ በግልጽ የቤት ቁጥር 379 የአንደኛና ሁለተኛ አመልካች ድርሻ፣ የቤት ቁጥር 382 የሶስተኛና የአራኛ አመልካቾች ድርሻ መሆኑን በግልጽ በሰፈራበት ሁኔታ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች በህግ ቤቶቹ በትርፍነት የተወረሱ መሆን አለመሆናቸውን፣ ቤቶቹ በመጀመሪያ የማን ሀብት እንደነበሩ የማጣራትና የንብረቱ ባለሀብት የሆኑት ወራሾች መብት ከአዋጅ ቁጥር 47/67 አንፃር የማጣራትና ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ያለው የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የፃፈው እውነተኛ ደብዲቤ፣ የአስረጂነት ብቃት፣ ተአማኝነትና ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር በአዋጅ ቁ/ 47/67 በተሰጠው ስልጣን የሚወሰናቸው ውሳኔዎች ውጤት አልባ የሚያደርግና ህግን ያልተከተለ የማስረጃ አመዙዖን በመሆኑ የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
የስርና ከተማ ልማት ሚኒስቴር አዋጅ ቁጥር 47/67 የማስፈጸም፣ በአዋጅ መሰረት አንድ ቤት በትርፍነት ሉወረስ የሚገባው መሆኑን ወይም አለመሆኑን የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ያለው ከፍተኛ አስተዲደራዊ አካል ነው። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአዱስ አበባ አስተዲደር /ክልል 14 መስተዲደር/ እና በእሱ ስር የተደራጀ ላልች የመንግስት አካላት አዋጅ ቁጥር 47/67 በማስፈጸም ሂደት የሰጡት ውሳኔ አዋጁን መሰረት ያደረገ መሆኑን መርምሮ የማሻሻል፤ የመለወጥ ወይም የመሻር አስተዲደራዊ ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተሰጠው የመንግስት አካል ነው። ላልች የከተማው አስተዲደር አስፈፃሚ አካላት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አጣርቶ ለሚሰጠው ውሳኔ የሚከበርና የማስፈጸም ህጋዊ ግዳታና ኃላፉነት ያለባቸው መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 47/67 በግልጽ ተደንግጓል። ከዘህ አንፃር ስንመለከተው የስራና ከተማ ልማትሚኒስቴር የካቲት 10 ቀን 1987 ዓ/ም እና ጥቅምት 25 ቀን 1990 በፃፈው ደብዲቤ የወሰናቸውን ውሳኔዎች የማክበርና የማስፈጸም ግዳታ በህግ የተጣለባቸው 3ኛ ተጠሪና አራኛ ተጠሪ፣ የሚኒስተሩ ውሳኔ ውድቅ እንዱያረግ ለበታች ፍርድ ቤቶች ጽፈው ያቀረቡት ክርክር፣ በህግ የተጣለባቸውን አስተዲደራዊ ኃላፉነት ያልተወጡ መሆኑን የሚያሳይና የህግ መሰረት የላለው ክርክር ነው። በወቅቱ በነበሩ የህግ ማዔቀፍች የሚኒስቴር መ/ቤቱ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር፣ የክፍለ ከተማውንና የሶስተኛና አራተኛ ተጠሪዎች ትርፍ ቤትን በተመለከተ የሰጡትን ውሳኔ የመሻር፣ የመለወጥ ወይም የመሻሻል ከፍተኛ የሆነ የአስፈጻሚነትና አስተዲዲራዊ ስልጣን ያለው ሲሆን፣ የከተማው አስተዲደር፣ ክፍለ ከተማውም ሆነ ለሶስኛና አራተኛ ተጠሪዎች የሚኒስቴር መስሪ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ አፈፃጸም የማስተጓጎል፣ የማጓተት፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውሳኔ ህጋዊ ውጤት እንዲይኖረው የሚያደርጉ ተግባራትን የፈጸም፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ውሳኔ የመሻር ወይም የመለወጥ አስተዲደራዊ ስልጣን አልነበራቸውም። በመሆኑም ሁለተኛ ተጠሪና አራተኛ ተጠሪ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውሳኔ ተፈፃሚ መሆን የለበትም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ምንም አይነት የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሁበት መሆኑን ለማረጋገጥ በክፍለ አስተዲደር የተመዖገበና ተረጋግጦ የተሰጠ የባለሀብነት ካርታና ፕላንና ማስረጃ የሚያስፈልግ መሆኑ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1195 ተደንግጓል። መርሁ ይህ ሆኖ አንድ ሰው በጉልበቱ፣ በገንዖቡና በዔውቀቱ ያፈራው የማይንቀሳቀስ ሀብት ባለሀብት ስለመሆኑ በክፍለ አስተዲደር የተሰጠ የባለሀብትነት ማስረጃ የላለው ሰው፣ የንብረቱ ባለሀብት መሆኑን ላልች የሰነድና የሰው ማስረጃዎችንበማቅረብ ለማስረዲት የሚችል ስለመሆኑ ይህ ሰበር ችልት በሰበር መዛገብ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። ከዘህ አንፃር ሲታይ የአመልካቾች አባት ሟች ይባስ ሰዳ፣ የአከራካሪዎች ቤቶች ባለሀብት እንደሆነና አመልካቾች የውርስ ድርሻ ስለሆኑ ቤቶች የማያስረዲ የሰነድ ማስረጃ አመልካቾች ለበታች ፍ/ቤቶች አቅርበው እያለ፣ ቤቶች የአባታችሁ ስለመሆናቸው የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ያላቀረባችሁ በመሆኑ፣ ክስ የማቅረብ መብትና ጥቅም የላችሁም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከላይ የገለጽነውን የሰበር ችልት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያልተከተለና የአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ2/1/ ድንጋጌ የሚጥስ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሰጠው ውሳኔና የፃፈው ደብዲቤ የአዋጅ ቁ/ 47/67 እና የላልች አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ መሆኑን መርምረናል። የአመልካቾች አባት አቶ ይባስ ሰዳ ከዘህ አለም በሞት የተለዩት በ1964 ዓ/ም መሆኑ ተረጋግጧል ይህም ማለት በሟች /የአንድ ሰው/ ሀብት የነበሩት ሁለት ቤቶች ሟች በሞት ከተለዩበት ጊዚ ጀምሮ የሟች ወራሾች ሀብት የባለመብትነት መብታቸው ሉተላለፍላቸው የሚችል መሆኑን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 826 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። ይህም የሟች ይባስ ሰዳ ሁለት ቤቶች፣ አዋጅ ቁጥር 47/67 ከመታወጁ በፉት የሟች አምስት ወራሾች ንብረት ሆኖ በኢትዮጲያ የውርስ አወራረስ ስርዓት መሰረት ከሟች ወደ ወራሾቹ የሚተላለፍ መሆኑን ያሳያል። በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰው ትርፍ ቤትና የከተማ ቦታ ነው። ሆኖም አዋጅ ቁጥር 47/67 በሚታወጅበት ወቅት አምስት የሚሆኑት የሟች ይባስ ሰዳ ልጆችን ወራሾች የአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀጽ 5 በሚደነግገው መሰረት የነበራቸው ትርፍ ቤት ሳይሆን፣ ለአምስቱ ወራሾች ከነቤተሰባቸው ለመኖሪያነት የማይበቁ ከአባታቸው በውርስ ያገኛቸው አከራካሪዎቹ ቤቶች ናቸው። ይህም በመሆኑ የሟች ሰራተኞች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1079 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በስምምነት ሁለቱን ቤቶች ተካፍለው፣የባለሀብትነት ማስረጃ ለሚሰጠው የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ጥያቄያቸውንና ማስረጃዎችን አቅርበው እያለ ቤቶች በልማት ምክንያት የፈረሱ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰጠው ውሳኔና የፃፈው ደብዲቤ አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁጥር 47/67 እና የውርስ ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ መሆኑን ያሳያል። ከላይ በዛርዛር በገለጽናቸው ምክንያቶች ተጠሪዎች አመልካቾች በውርስ አግኝተዋቸው በነበሩ የቤት ቁጥር 375 እና 382 ምትክ የተሰሩትን የቤት ቁጥር 459 እና የቤት ቁጥር 375 እና 382 ምትክ የተሰሩትን የቤት ቁ/ 459 እና የቤት ቁ/530 ለአመልካቾች እንዱያስረክቡ መወሰን ሲገባቸው፣የአመልካቾቹን ክስ ውድቅ በማድረግ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ የካቲት 10 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ጥር 22 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካቾች ክስ ያቀረቡባቸውና በልማት ምክንያት የፈረሱት በወረዲ 14 ቀበላ 24 ይገኙ የነበሩት የቤት ቁጥር 382 እና የቤት ቁጥር 379 የሆኑት ቤቶች አመልካቾች ከሟች አባታቸው አቶ ይባስ ሰዳ በውርስ ያገኟቸውና በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት በትርፍነት ያልተወረሱ የግል ሀብታቸው ናቸው በማለት ወስነናል።
አመልካቾች በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1079/1/ መሰረት በስምምነት ተካፍለው ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ባስመዖገቡት መሰረት፣ አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካች የውርስ ድርሻ በሆነው የቤት ቁጥር 382 ምትክ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 14/15 አልታድ የተባለውን ድርጅት የሰራውን የቤት ቁር 530 ተጠሪዎች ለአንደኛና ሁለተኛ አመልካቾች ያስረክቡ በማለት ወስነናል።
የሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የውርስ ድርሻ በሆነው በቤት ቁጥር 459 ተጠሪዎች ለሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ያስረክቡ በማለት ወስነናል።
በዘህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
መ/ተ የሰ/መ/ቁ/ 123833 መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም ዳኞች---- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ አይሸሹም መለሰ ፀሐይ መንክር አመልካች---------- አቶ ለሜሳ ደገፈ ቀረቡ ተጠሪ--------------- የአዲማ ከተማ ማዖጋጃ ቤት ነ/ፈጅ ቅድስት ቤክሲሳ ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የእግድ ትዔዙዛን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በኦሮሚያ ክልል ወረዲ ፍርድ ቤት ነው፣ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሣሽ ሲሆኑ እነ ቡኔ በዲኔ / 4 ሰዎች/ ተከሳሾች ነበሩ።
ለእግደ መሰጠት ምክንያት የሆነው የቤት ክርክር ሲሆን የስር ወረዲ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 154 መሰረት በቃለ መሐላ ተደግፍ በአሁን አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ በአዲማ ከተማ ቀበላ ዐ5 የቤት ቁጥር 369 የሆነውን ቤት እንዱታገድ በመጠየቁ ምክንያት በመ/ቁ/ 9ዐ352 ሰኔ 29 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም. በዋለው ችልት ቤቱ እና በቤቱ ውስጥ ያለው ንብረት ጭምር ላላ ትዔዙዛ እስኪሰጥ ድረስ ለ3ኛ ወገን ተላልፍ እንዲይሰጥ ሲል የእግድ ትዔዙዛ ፍ/ቤቱ ሰጥቷል።
ይህን የእግድ ትዔዙዛ በመቃወም የአሁን ተጠሪ ይግባኝ ብል ለክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም በመ/ቁ/ 21371 ሐምል ዐ2 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤትን እግድ ትዔዙዛ እንዲይፈፀም ሲል እግድ ሰጥቷል።
አመልካች የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዔዙዛ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አስቀርቦ መርምሮ በስር ፍርድ ቤት ክርክር የተነሳው በአመልካች እና ላልች 4 ሰዎች መሐከል ሲሆን ተጠሪ የሆነው / አስተዲደሩ/ ግን በክርክር ተካፊይ ያልሆነ፣ ወይም በሕግ መሰረት ወደ ክርክሩ የገባ ሳይሆን ተከሶ መልስ ሳይሰጥ እግድ እንዱነሳ አቤቱታ የማቅረብ መብት ሳይኖረው፣ እንዱሁም የተሰጠው እግድ ጊዚያዊ ሆኖ እያለ የወረዲው ፍርድ ቤት የእግድ ትዔዙዛ ስህተት የላለበት ሆኖ እያለ በመሻር እንዲይፈፀም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ትዔዙዛ መሻር ያለበት ነው በማለት የወረዲው ፍርድ ቤትን ትዔዙዛ በማፅናት በመ/ቁ/ 226292 ሐምል 23 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም. በዋለው ችልት ውሣኔ ሰጥቷል።
የአሁን ተጠሪም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በሰበር ታይቶ እንዱታረምለት አቤቱታ በማቅረቡ መነሻነት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 231128 ታህሳስ 18 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችልት ጉዲዩን መርምሮ ክርክር ያስነሳው የመንግሥት ቤት በአዲማ ከተማ መስተዲድር የሚተዲደር መሆኑን ፣ በከተማ ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት ቤቶችን የማስተዲደር፣ የመቆጣጠር እና የማከራየት የከተማ መስተዲድሩ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የከተማ መስተዲድር በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 158 መሰረት አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው። ስለዘህ የስር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዘህ ሁኔታ ሳያየው የአዲማ ከተማ መስተዲድር ክርክሩ ውስጥ ሳይኖር የእግድ ይነሳልኝ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም ብል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለው ሆኖ በመገኘቱ በሙለ ድምጽ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የወረዲ ፍርድ ቤቱ የሰጡትን ውሣኔ በመሻር የምስራቅ ሸዋ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማጽናት ወስኗል።
አመልካች የሰበር ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን ፍርድ በመቃወም በ15/6/2ዐዐ8 ዓ.ም.የተፃፈ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሲሰጥ የሕግ ስህተት ፈጽሟል የሚለበትን ነጥቦች በመዖርዖር በሰበር ታይቶ እንዱታረምላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።
በአቤቱታው ከዖረዖሩት በአጭሩ፡- በስር ፍርድ ቤት እግድ እንዱሰጥልኝ ጠይቄ ፍ/ቤቱ እግደን የሰጠልኝ ሲሆን፣ የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ተከሣሽ ያልነበረ፣ ወይም በሕግ አግባብ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ሳይገባ፣ ወይም ለወረዲው ፍርድ ቤት እግደ እንዱነሳ አቤቱታ ሳያቀርብ የእግድ ትዔዙዘን በከፍተኛ ፍርድ ቤት አሽሯል።
እግደን ያነሳው ፍርድ ቤት የፍትሕ ስርአቱን ጥያቄ ውስጥ በሚጥል መልኩ አቤቱታ ሲቀርብለት መጥሪያ ሳይልክልኝ በጉዲዩ ላይ ምንም አይነት መልስ ሳልሰጥ ሕገመንግስታዊ መብቴን ተጠቅሜ ክርክር ሳላደርግበት የአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዔዙዛ የሻረበት ትዔዙዛ እንዱደርሰኝ አድርጓል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ጊዚያዊ እግደ እንዱቆይ ማድረጉ የማስተዲደር እና የመቆጣጠር መብቱን በምንም መልኩ የሚነፍግ አይደለም።
በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ እና የአዲማ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለተፈፀመበት ይታረምልኝ በማለት ሰፉ አቤቱታ አቅርበዋል።
አቤቱታው የቀረበለት የሰበር አጣሪም ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ በስር ተከራካሪ ባልነበረበት በሥር ፍ/ቤት በተሰጠ የእግድ ትዔዙዛ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ እግድ የተነሳበትን አግባብ የሕግ መሰረት ያለው መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል መዛገቡ ለሰበር ችልት ይቅረብ በማለቱ ላቀርብ ችሎል።
አጣሪው ከያዖው ጭብጥ አኳያ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ መጥሪያ ተልኮለት በ19/1/ዐ9 የተፃፈ መልስ አቅርቧል። ከመልሱም በአጭሩ እንደተመለከትነው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ውሣኔ የተፈፀመ ስህተት የለም፣ ምክንያቱም አንድ አቤቱታ አቅራቢ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 154 የተሰጠውን እግድ እንዱነሳለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 158 መሰረት እግደን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ የሚችለው ከሳሽ ወይም ተከሣሽ ነው የሚል የሕግ ድንጋጌ የለም። የአሁን ተጠሪ በክርክሩ ተካፊይ ሳይሆን የተሰጠውን እግድ እንዱነሳለት የመጠየቅ የሕግ አግባብ የለውም የሚለው ጥያቄ በሕግ ድንጋጌው ስር የሚወድቅ አይደለም። በመሆኑም ሰበር ሰሚ ችልቱ የሚነቀፍ ውሣኔ ስላልሰጠ ይፅናልን። አመልካች ቤቱን ያገኘሁት ከተለያዩ አካላት ድጋፍ ደብዲቤ ተጽፍልኝ ነው ይበል እንጂ ማስረጃ ግን የለውም፣ ተጠሪ ባልተከሰበሰበት እና በማያውቀው ጉዲይ ንብረቱ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት መታገደ አግባብ አይደለም በማለት በመልሱ ከገለፀው ውስጥ ለጉዲዩ አግባብ ነው ያልነውን መዛግበናል።
አመልካችም ለቀረበው መልስ የመልስ መልሳቸውን አቤቱታቸውን በሚያጠናክር መልኩ አቅርበው ተያይዝል።
እኛም የቀረበውን ጉዲይ በአጣሪው ከተያዖው ጭብጥ አንፃር ከስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ከአመልካች አቤቱታ እና መልስ ፣ የመልስ መልስ እና አግባብነት ካለቸው የሕጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረናል።
ከላይ እንደተመለከትነው ጉዲዩ በስር ፍርድ ቤት እግድ ከመሰጠት ጋር ተያይዜ የተነሳ ክርክር ሲሆን፣ የስር ፍርድ ቤት ክርክር ያስነሳውን ቤት እግድ የሰጠው በስር ከሳሽ በአሁን አመልካች ጠያቂነት ነው። በዘህ ጉዲይ ተከሣሽ የነበረው ላላ ሰው እንደነበረ እና ተጠሪ ግን በክርክሩ ተካፊይ እንዲልሆነ ተጠሪም ያመነው እና በስር ፍርድ ቤቶችም ሲገለፅ የመጣ ነገር በመሆኑ አያከራክርም። የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 4ዐ፣ 41፣ 42፣ 358፣ 418 በተደነገገው ሥርዓት ተጠሪ ወደ ክርክሩ ውስጥ ተሳታፉ መሆኑም አልተመለከተም። ክርክር ያስነሳው ቤት ግን የአስተዲደሩ /ተጠሪ የሚያስተዲድረው / ነው የተባለ በመሆኑ ተጠሪው በሚያስተዲድረው ቤት ላይ ሁለት ወገኖች ክርክር አንስተው ጉዲዩ በፍርድ ቤት የተያዖ በመሆኑ አመልካች እግድ በቤቱ ላይ እንዱሰጥበት ጠይቀው እግደን የወረዲ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል።
እግድ የተሰጠው በክርክሩ ውስጥ ተሳታፉ ባልሆነው ተጠሪ በሚያስተዲድረው ቤት ላይ በመሆኑ ተጠሪ ይህ ጉዲይ አይመለከተውም ምንም ጥያቄ የማንሳት መብት የለውም ለማለት የሚቻል አይሆንም። ቁም ነገሩ ግን አንድ በንብረቴ ላይ እኔ ሳላውቀው ትዔዙዛ ተሰጥቶብኛል የሚል ወገን ፍርድ ቤቱ እኔን ሳያሳትፍ ያልተገባ ትዔዙዛ ሰጥቶብኛል በማለት አሁን በዘህ መዛገብ የተሰጠው እግድ አይነት ትዔዙዛ በተሰጠ ጊዚ አቤቱታ የማቅረብ መብት ያለው መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 158 በግልጽ ተደንግጓል።
አቤቱታውንም ተቀብል የማስተናገድ እና የተሰጠው የማገጃ ትዔዙዛ በቀረበው አቤቱታ መሰረት ሉያሻሽል ፣ሉያነሳ፣ ሉሰርዛ የሚችለውም እግደን የሰጠው ፍርድ ቤት ሲሆን፣ የቀረበውን አቤቱታ እግደን የሰጠው ፍርድ ቤት ሳይቀበል ውድቅ ያደረገ እንደሆነ ይግባኝ የሚባልበት ከሚሆን በቀር በክርክር ተሳታፉ ያልሆነ ወገን በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ እግድ ትዔዙዛ በቀጥታ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚያቀርብበት እና ትዔዙዘ ላይ ውሣኔ የሚያሰጥበት ስርዓት ግን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ ውስጥ የተደነገገ አይደለም።
የእግድ ትዔዙዘ ጠቀሜታው ለጊዚው የተሰጠ በመሆኑም ይህ እግድ ሳይነሳ መቅረቱ በአመልካች ላይ የሚያስከትለው ችግር ካለ እግደን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቦ በስር ፍርድ ቤት ቀርቦ አቤቱታም አቅርቦ የስር ፍርድ ቤቱ በቀረበው አቤቱታ ላይ የሰጠው የተለየ ትዔዙዛ ስለመኖሩ የስር ፍርድ ቤቱ ትዔዙዛ ግልባጭ አያመለክትም። አመልካችም እግድ የተሰጠው አላግባብ ነው የሚል አቤቱታውን በስር ፍርድ ቤት አቅርቦ ትዔዙዛ ባላሰጠበት ሁኔታ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በክርክር ተሣታፉ ባልሆነበት ጉዲይ በቀጥታ ይግባኝ በማቅረብ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ማሻሩ ፣ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ሥነ ሥርዓታዊ መስመሩን ጠብቆ የቀረበ ይግባኝ መሆን ያለመሆኑን ሳያረጋግጥ እና በስር ፍርድ ቤት ታይቶና ትዔዙዛ የተሰጠበት መሆን ያለመሆኑን ሳይመረምር በመዛገቡ ላይ ከሣሽ ወይም ተከሣሽ ወይም ጣልቃ ገብ ያልሆነ ወገን ይግባኝ ቅሬታ ሲቀርብለት ተቀብል የስር ፍርድ ቤትን ትዔዙዛ መሻሩ ፣ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የፈፀመውን ስህተት ማረም ሲገባው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የይግባኝና የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 231128 ታሕሳስ 18 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ፀንቷል። ።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረስ መዛገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.