ተከራካሪ ወገኖች ባላነሱት የመከራከሪያ ነጥብ ወይም የግራ ቀኙ ወገኖች ባልተለያዩበት ጉዲይ እንዱጣራ በማድረግ ውሳኔ መስጠት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 241፣242
No summary available.
ሕዲር 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኸሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የሳስኮ ኢንደስትሪያል ንግድና ትራንስፖርት ድርጅት፡ጠበቃ አቶ አብደላ አሉ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢፋዱሪ ትምህርት ሚኒስቴር፡- ነ/ፈጅ አማረች መለስ ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ።
ጉዲዩ የስር ከሳሽ የአሁን አመልካች በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዲ ምድብ ችልት ያቀረቡት ክስ ከተከሳሽ ጋር ውል የፈፀምን ሲሆን ይኸውም የመስታዋት ማጓጓዛ ስምምነት ሆኖ ለሆሳዔና ዩንቨርስቲ 400 ኩንታል መስተዋት የአንደ ዋጋ 69.00 /ስልሳ ዖጠኝ ብር/ በቀጥላላ 27,600.00 /ሃያ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ብር/ ለደብረታቦር ዩኒቨርስቲ 400 ኩንታል መስተዋት የአንደ ዋጋ በብር 114.00 /አንድ መቶ አስራ አራት ብር/ በቀጥላላ 45,600 /አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ብር/ ለቡሬ ሆራ ዩኒቨርስቲ 400 ኩንታል መስተዋት በብር 114.00 /አንድ መቶ አስራ አራት ብር/ በጠቅላላ 45,600 /አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ብር/ ከላይ የተጠቀሰው ሰራዎች በጠቅላላው ድምር 118,800.00 /አንድ መቶ አስራ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ የሚያወጣ ስራ ሰርቼ ተከሳሽ ሉከፍለኝ ሲገባ ያልከፈለኝ ስለሆነ እርክክቡ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ፣ ወጪና ኪሳራ ጋር ይወሰንልኝ የሚል ዲኝነት በመጠየቃቸው ነው።
ተከሳሽ በወኪለ አማካኝነት በሰጠው መልሰ የመጀመሪያ ደረጃ መቃመሚያ ከሳሽ ችልታ የለውም በሚል መከራከሪያ አቅርቦ በተጨማሪም ይህ ቢታለፍ ብለው ተከሳቭ መሰሪያ ቤት አስተዲደር መ/ቤት በመሆኑ ከከሳሽጋር የሚደረግ ውል በጽሁፍ መሆን ሲገባው በጽሁፍ የተደረገ ውል የለንም ስለሆነም ከሳሽ ክስ ማቅረብ አይችልም ይችላል እንኳን ቢባል ከሳሽ ለአስሩ ዩኒቨርስቲዎች መስተዋቱን ለማቅረብ ጨረታ አሸንፍ ለሶስት ዩኒቨርስቲ ብቻ በማቅረብ ክፍያ መጠየቅ አይችልም ከሳሽ ካጓጓዖው መስተዋት ውስጥም በከፉል የተሰበረ በመሆኑ ይኸው ተቀንሶ እንዱከፈለው ሲባል ከሳሽ ያልተስማማ በመሆኑ ውለን ያፈረሰ በመሆኑ ከክሱ በነፃ ልሰናበት ይገባል ብሎል።
ፍ/ቤቱም በተከሳሽ በኩል የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ ካከራከረ በኃላ በከሳሽና በተከሳሽ በኩል የተፈፀመው ዉል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3131-3132 ድረስ በተገለፀው መሰረት ከአስተዲደር መስሪያ ቤት ጋር የተፈፀመ ውል ሲሆን ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1724 መሰረት በጽሁፍ ላደረግ ሲገባው ባለመደረጉ ውለ በህጉ መሰረት የተቀመጠው የአጻጻፍ ስርአትን ያሟላ አይደለም በማለትና ይህ ደግሞ በ1720/1/ መሰረት ከረቂቅ የዖለለ ውጤት የለውም በማለት ክሱን ውደቅ በማድረግ ሲወሰን የአሁን አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ቅሬታው በይግቦኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤት መዛገቡን መርምሮ ቅሬታው መልስ ሰጪን እያስጠራም በማለት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዜታል።
ለሰበር የቀረበው አቤቱታ በአመልካችና በተጠሪ መሀከል የተፈፀመ ውል የጨረታ ሆኖ እያለ የአስተዲደር ውል ነው ተብል በጽሁፍ ላደረግ ሲገባ በጽሁፍ አልተደረገም ተብል የተሰጠው ውሳኔ ውለ የአስተዲደር ቢሆን እንኳን በፍ/ብ/ህ/ቁ 3141-3117 ድረስ የተደረገ ህጋዊ ውል ሆኖ እያለ በስር ፍ/ቤቶች ክሱ ውድቅ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታልና ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
በሰበር አጣሪው ችልት ተጠሪ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤት መስተዋት የማቅረብ ማጓጓዛ ጨረታ አውጥቶ አመልካች ተወዲድሮ አሸንፍ ለሶስት ዩኒቨርስቲዎች ያቀረበ መሆኑ ባልተካደበት ያጓጓዖበት ዋጋ ሲጠየቅ ውላችን በጽሁፍ አልተደረገምና ሉከሰኝ አይገባም ተብል በቀረበ ክርክር መነሻነት ክሱ ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ለማጣራት ተጠሪ ይጠራ በማለቱ ተጠሪ መስሪያ ቤት በሰጠው መልስ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተገቢና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ስለሆነ ሉፀና ይገባል ካለ በኃላ አመልካች ድርጅት በውለ መሰረት ለአስር ዩኒቨርስትዎች ያላቀረቡ ስለሆነ ልንከፍል አይገባም ብለዋል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 3132/2/ ስር እንደተመለከተው ውለ ከህግ አገልግልት ስራ ጋር የተያያዖና ለስራውም አፈፃፀም የተዋዋዩን ስራ ተካፊይነት ሳያቋርጥ የሚጠይቅ በሆነ ጊዚ ውለ የአስተዲደር መ/ቤት ውል እንደሆነ ይደነግግና በፍ/ብ/ህ/ቁ 3131/1/ ስር እንደተመለከተው መንግስት ወይም ላልች የአስተዲደር ሰራተኞች የሚዋዋሎቸው ውልች ስለውልቹ በጠቅላላና ስለ ልዩ ልዩ ውልች የተሰጡት የዘህ ውል ድንጋጌዎች በጠቅላላው እንደሚፀናላቸው ይደነግጋል።
ስለ ውልች በጠቅላላው በተፃፈው የፍ/ብ/ህ/ቁ 1724 ስርም እንደተመለከተው ከአስተዲደር መ/ቤት ጋር የሚደረጉ ውልች በጽሁፍ ሉደረጉ እንደሚገባ ይደነግግና በፍ/ብ/ህ/ቁ 1720 ስር እንደተመለከተው ውልን ለማቋቋም በጽሁፍ እንዱደረጉ የታዖዘ ውልች በጽሁፍ ካልተደረጉ እንደ ረቂቅ እንደሚቆጠሩ ይደነግጋል።
በልላ በኩል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 242 ስር እንደተደነገገው ማናቸውም ተከራካሪ ወገን በመከላከያ መልሱ ወይም በማናቸውም ላላ መንገድ የተከሰሰበትን ነገር በሙለ ወይም በከፉል የሚያምን መሆኑን የገለፀ እንደሆነ ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ የእምነት ቃለን የሰጠ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በታመነው ነገር ላይ ብቻ ፍርድ መሰጠት እንዲለበት ይገልጻል።
ይህ ማለት ለአንድ ለቀረበ ክርክር የተሰጠው መልስ የታመነ እስከሆነ ድረስ ፍ/ቤቱ በታመነው መሰረት ውሳኔ ላሰጥ እንደሚገባና ወደ ማስረጃ የሚገባው በክስ አይነት ካልታመነ ብቻ እንደሆነ የተደነገገ ነው። ስለሆነም ወደተያዖው ጉዲይ ስንመለስ ውለ በጽሁፍ ነው ወይስ በቃል የውለ ይዖት ምን ነበር እየተባለ የሚጣራው በክሱ መሰረት ካልታመነ ነው። በቀረበው ክርክር የስር ተከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ ለቀረበበት ክስ የሰጠው መልስ የእምነት መሆኑ ከክርክሩ መረዲት ይቻላል። ይህ እስከሆነ ድረስ ፍርድ ቤቱ ከቀረበው ክስ እና መልስ አንጻር ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል።
ከዘህ መነሻ ሲደረግ የስር ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን ከሰማ በኃላ ውለ ከአስተዲደር መ/ቤት ጋር የተፈፀመ በመሆኑ በጽሁፍ መደረግ ሲገባው አልተደረገም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሲሰጥ ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የስር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ማረም ሲገባው አልፍ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ በማጽናት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በቀን 21/2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የስር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ በማጽናት በመዛገብ በቀን 26/4/2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በስር ክሳቸው ለሶስት ዩኒቨርስቲዎች መስታወቶችን አጓጉዢአለሁ ሲለ ተጠሪም ለሶስት ዩኒቨርሰቲዎች አመልካች ያቀረበ ቢሆንም ካቀረባቸው መስታውቶች ዉስጥ የተሰባበሩ መስተዋቶች መኖራቸውን በገለፀው መሰረት አመልካች በሶስት ዩኒቨርስቲዎች ለእያንዲንደ ዩኒቨርስቲ ምን ያህል ኩንታል መስታወት እንዲጓጓዘ የአንደ ኩንታል ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ አመልካች ካጓጓዖው ውስጥ ምን ያህለ እንደተሰበረ በግራ ቀኙ ውል መሰረት ለተጠሪ ሉከፈላቸው የሚገባ ክፍያ አለ ወይስ የለም የሚከፈላቸው ከሆነስ ሉከፈላቸው የሚገባው የገንዖብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ በማስረጃ ተጣርቶ ይወሰን ዖንድ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 341/1/ መሰረት ልከናል።
ለዘሁ ፍ/ቤት ክርክር የተደረገ ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሰቸውን ይቻለ።
ት ዔ ዙ ዛ የውሳኔው ግልባጭ በየደረጃው ለሚገኙ የስር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ በውሳኔ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.