አንድ ሰራተኛ በስራ ቦታ ላይ በመሞቱ ብቻ አሰሪው ለደረሰው የሞት ጉዲት ኃላፉ የሚሆንበት አግባብ የላለ ሲሆን አሰሪው ኃላፉ የሚሆነው የሞት አደጋው የደረሰው በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት መሆኑ እና የውጤት ግንኙነት መኖሩን / proscimate cause & effect relationship/ የሚያሳይ ማስረጃ መኖሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 97
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 28 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ ዊንታ ቦርጄ -የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ይርጋለም ኮንስትራክሸን ኃ.የተ.የግል ማህበር ………..የቀረበ የለም መዛገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በሐዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ19/09/08 ዓ/ም ተሰጥቶ በሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ24/12/08 ዓ/ም፣ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመ/ በ09/02/2009 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ በሥራ ላይ በሚደርስ የአካል ጉዲት የሚከፈል የካሣ ገንዖብ ጥያቄ የይርጋ ጊዚ ገደብን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በ20/08/08 ባቀረቡት ከተጠሪ ድርጅት ጋር በፈፀሙት የቅጥር ውል መሰረት ስራ ላይ እያለ በ17/06/2006 ዓ/ም በደረሰባቸው ከፉል አካል ጉዲት ምክንያት ህክምና ሲከታተለ የቆዩ ቢሆንም በጥር ወር 2008 ዓ/ም ከፍተኛ የሆነ የጤና መታወክ ያጋጠማቸው መሆኑን ጠቅሰው በአዋጁ መሰረት ዖላቂ የአካል ጉዲት ካሳ እንዱከፈላቸውና ተጠሪ ድርጅት ለአመልካች ያላግባብ ደመወዛ እየቀነሰ ሲከፍል የነበረ በመሆኑ ይኼው የተቀነሰው ደመወዛም እንዱከፈላቸው ይወሰን ዖንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ ተጠሪ ድርጅትም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንዐስ አንቀፅ 4 የተደነገገው የስድስት ወር የይርጋ ጊዚ ገደብ አልፎል በማለት መቃወሚያ አቅርቧል ።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተጠሪ ያቀረበውን መቃወሚያ በመቀበል የአካል ጉዲት ካሳ ክስ በአንድ ዓመት፣የደመወዛ ክፍያ በስድስት ወር ይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ብይን ሰጥቷል ።
አመልካች ይግባኝ ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ተቀባይነት ያጡ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልትም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ብይን የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- በ17/06/2006 ዓ/ም አመልካች ስራ ላይ እያለ የደረሰባቸው የአካል ጉዲት በህክምና ሲከታታለ ቆይተውና ተጠሪ ድርጅትም ይህንኑ አውቆ ሲያሳክማቸው ቆይቶ ጉዲቱ ተባብሶ በአመልካች አካል ላይ የደረሰው ጉዲት ዖላቂ ጉዲት መሆኑ አመልካች ያወቁት ክስ ከመቅረቡ ከሶስት ወር በፉት ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲቱ የደረሰበትን የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ/ም ለይርጋው መቆጠር መነሻ አድርገው መያዙቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዘህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦ በ ሰጠው መልስም ከአመልካች ጋር መጀመሪያ የተመሰረተው የስራ ውል በሕጉ አግባብ የተቋረጠ መሆኑን፣ አመልካች ጉዲት ደረሰብኝ የሚለት በስራ ቦታ ላይ ስለመሆኑ በተጠሪ በሕጉ አግባብ ያላሳወቁ መሆኑን፣ ተጠሪ አመልካችን በስራ ላይ ጉዲት መድረሱን አምኖ ሲያሳክማቸው የነበረበት አግባብ የላለ መሆኑንና ላልች ነጥቦችን በሰፉው ዖርዛሮ የአመልካች ክስ በይርጋ ውድቅ ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት ተከራክሯል።
የአሁኑ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ብይንና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ በይርጋ የታገደ ነው በማለት የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንዐስ አንቀፅ /1/ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የሰጡት ዲኝነት ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ጉዲዩን መርምረናል ።
ጉዲዩን አንደመረመርነው ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዚ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንዐስ አንቀፅ 1 ስር የተደነገገው የአንድ አመት የይርጋ ጊዚ ገደብ ነው።አሁን አከራካሪ የሆነው ይህ የጊዚ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው መቼ ነው? የሚለው ነው። ይህንኑ ለመመለስ አመልካች በክሳቸው ላይ የጠቀሷቸውን መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችንና ተጠሪም ለእነዘህ ፍሬ ነገሮች ያቀረባቸውን የክርክር ነጥቦችን መመልከቱ ተገቢነት ይኖረዋል።
አመልካች በክሳቸው ላይ የጠቀሱት መሰረታዊ ነጥብ ከተጠሪ ጋር በመሰረቱት የስራ ውል አግባብ በስራ ላይ እያለ የአካል ጉዲት የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም ደርሶባቸው ሕክምና ሲከታታለ ቆይተው ጉዲቱ ዖላቂ መሆኑን ጥር ወር 2008 ዓ.ም አካባቢ አውቀው ተጠሪ ላይ ለዘሁ ለዖላቂ የአካል ሚያዘያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም ክስ የመሰረቱ መሆኑን ሲሆን ተጠሪ ጉዲት ካሳ እንዱከፍል አጥብቆ የሚከራከረው ደግሞ በ2006 ዓ.ም ከአመልካች ጋር የነበረው የስራ ውል በሕግ አግባብ የተቋረጠ መሆኑ በፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተረጋገጠ መሆኑን፣ በዘህ ጊዚ ደረሰ የተባለው ጉዲትም በተጠሪ በሕጉ አግባብ ያልታወቀና በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ነው ልባል የማይችል መሆኑንና አመልካች ህክምና እንዱያገኙ ሲያደርግ የቆየውም ድርጅቱ በአመልካች ላይ የደረሰውን የአካል ጉዲት በስራ ላይ የደረሰ መሆኑን በማመን ሳይሆን የድርጅቱ ባለቤት በግላቸው በሰብአዊነት ያደረጉት ተግባር መሆኑን በመዖርዖር ነው።ይሁን እንጂ በ2006 ዓ/ም በአመልካች ላይ ደረሰ የተባለው የአካል ጉዲት በሕጉ አግባብ በስራ ላይ የደረሰ መሆን ያለመሆኑ፣ ተጠሪ ለህክምናው ሲያወጣው የነበረ ወጪ መኖርያ ለመኖሩና ጥር 2008 ዓ.ም በአመልካች የታወቀው የዖላቂ አካል ጉዲት በ2006 ዓ.ም በደረሰባቸው አደጋ የመጣ መሆን ያለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ በግራ ቀኙ ማስረጃ የሚታዩ ነጥቦች ከመሆናቸው ውጪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ሉነሱ የሚችለ ነጥቦች አይደለም። ስለሆነም የአመልካች ክስ አመሰራረት ከተጠሪ ጋር የፀና የስራ ውል እያለ በ2006 ዓ.ም በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት የመጣው ዖላቂ ያልሆነ የአካል ጉዲት በሕክምና ቢከታተለም ለውጥ ሳያሳይ ቀርቶ ወደ ዖላቂ የአካል ጉዲት መሸጋገሩን የሚገልጽና ይህ ስለመሆኑ የታወቀው ደግሞ በጥር ወር 2008 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑን የሚያሳይ እና ተጠሪም በዘህ ረገድ ግልጽ ማስተባበያ ክርክር ባለቀረበበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች የይርጋ ጊዚው መቆጠር ያለበት ከ17/06/2006 ዓ.ም ጀምሮ ነው በማለት የያዘት መነሻ የአመልካችን ክስ ይዖት ያላገናዖበ ሆኖ ተገኝቷል። ለይርጋው ጊዚ መነሻ መሆን ያለበት ጥር ወር 2006 ዓ/ም ነው ከተባለ ደግሞ አመልካቹ ክስ ያቀረቡት በ20/08/2008 ዓ.ም በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162(1) ስር ያለው የአንድ አመት ጊዚ አላለፈም። በዘህም ምክንያት አመልካች ያቀረቡት የአካል ጉዲት ካሳ በይርጋ የታገደ ነው ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በሐዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ19/09/08 ዓ.ም ተሰጥቶ በሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ24/12/08 ዓ.ም፣ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት በመ/ በ09/02/2009 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የአካል ጉዲት ካሳን በተመለከተ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የታገደ ነው ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሸሯል። አመልካች በደመወዛ ላይ ያቀረቡት ክስ በይርጋ ውድቅ መደረጉ አልተነካም።
በአመልካች የአካል ጉዲት ካሳ ላይ የቀረበውን የግራ ቀኙን ክርክር የሐዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በመቀጠል ጉዲዩን በሚገባ አጣርቶ ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።
በዘህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭ ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፈርማ አለበት ።
ቅ/ሀ ፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ
No topics extracted.