No summary available.
ሐምል 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ አሰግድ ጋሻው እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ሞገስ ወ/መላክ - አልቀረበም ተጠሪ፡- የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ - አልቀረቡም መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው።መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመ/ቁ ጡ/ይ/1/1/155/2008 በቀን 28/07/2008 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 15/09/2008 ዓ.ም በማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው ።
ጉዲዩ የኮንትራት ሥራ አገልግልት ጊዚ ለጡረታ መብት አያያዛን የሚመለከት ነው ። አመልካች ለመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አዱስ አበባ ሪጅን /በተጠሪ/ ባቀረቡት አቤቱታ ከ11/06/68 እስከ 25/03/73 በቀድሞ ግብርና ሚኒስቴር ፣ከ12/01/84 እስከ 30/01/92 በአዱስ አበባ መስተዲደር የፕሮጀክት ፅ/ቤት ከ02/02/92 እስከ 07/11/2000 አዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የህብረት ሥራ ማህበራት ማደራጀትና ማስፊፉያ ቢሮ ለ21 ዓመት ከ8 ወር ከ9 ቀን ያገለገለ በመሆኑ የጡረታ አበል ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበውን ከ02/02/92 እስከ 30/10/92 ያለውን አገልግልት ውድቅ በማድረግ እንዱሁም ከሰኔ 01/1995 ዓ.ም በፉት ያለው የኮንትራት አገልግልት ጊዚ አግባብ ባለው አካል ያልተፈቀደ በመሆኑ ለጡረታ አይታሰብም በማለት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የአመልካች አገልግልት ከ21 ዓመት በላይ ቢሆንም በኮንትራት ተቀጥሮ በሰሩባቸው ጊዚያት የጡረታ መዋጮ ተቀንሶ ገቢ ያለመሆኑ በጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 መሰረት በኮንትራት የተፈፀሙት አገልግልት እንዱያዛ ከሚመለከተው ክፍል የተፈቀደበት ማስረጃ ያልቀረበ በመሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ኤጀንሲ የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው በማለት አጽንቷል ።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም መልስ ሰጪን ሳይጠራ የአመልካችን የይግባኝ ቅሬታ ባለመቀበል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አሰናብቶታል ።
የአመልካች የሰበር አቤቱታም የቀረበው ይህንን በመቃወም ሲሆን ይዖቱም የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 11/4/መ በቋሚነት በተቀጠረበት የመንግስት መ/ቤት በጊዚያዊነት በተከታታይ አገልግልት የሰጠበት ጊዚ ለጡረታ አገልግልት የሚቆጠር መሆኑን የሚደነግግ በመሆኑና በልላ አግባብ ባለው አካል ማስወሰን የሚጠይቅ አይደለም ፣ ከሆነም የጡረታ ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ነው፣ በኮንትራት ተቀጥሮ በስራሁበት ጊዚ የሚከፈለው የጡረታ መዋጮን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 11/6/መ/ ሆነ በአዋጅ ቁጥር714/2003 አንቀጽ 17/5/ መሰረት የኮንትራት ወይም ጊዚያዊ አገልግልት ለመያዛ እንደቅድመ ሁኔታ ሰራተኛው የራሱንና የአሰሪውን የጡረታ መዋጮ ድርሻ ጨምሮ ራሱ ባቀረበ ጊዚ የሚከፍለው እንጂ በአገልግልት ጊዚ አይደለም ፣በዘህ መሰረት ለመክፈል አመልክቻለሁ ።
ስለሆነም የተፈፀመው ስህተት ታርሞ የኮንስትራት ጊዚው ታስቦ አበል ይወሰንልኝ የሚል ነው ።የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በቋሚነት ከመቀጠራቸው በፉት በመንግስት መ/ቤት በኮንትራት የሰሩበት ጊዚ አገልግልት ለጡረታ አይታሰብም መባለን በአዋጅ 714/2003 አንቀፅ 17/3 /ሰ/ መሰረት ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዜ በሰጠው መልስ አመልካች ለጡረታ አገልግልት ሉያዛልኝ ይገባል ያለት ከ12/01/1984- 30/01/1992 በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፕሮጀክት ጽ/ቤት በጊዚያዊነት የፈፀሙት ሲሆን ይህም በአዋጅ 345/05 እና 714/03 ከመውጣታቸው በፉት በመሆኑ የአመልካች ጥያቄ ተፈጻሚነት የለውም ፣ ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፉት የነበረውም 209/55 ሲሆን የኮንትራት አገልግልት ለጡረታ አይታሰብም፣ አመልካች ተጠሪ በኮንትራት በሰራሁበት ጊዚ የጡረታ መዋጮ ተቀንሶ ገቢ አልተደረገም ያለትም የጡረታ መዋጮ የሚሰበሰበውም ሆነ የጡረታ ተጠቃሚነት ባለመብት የሚረጋገጠው ቋሚ ለሆነ የመንግስት ሰራተኛ ነው ። ስለሆነም በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመ ባለመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ይደረግልን ብሎል ። የአመልካች የመልስ መልስም ቀርቧል ።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተለገፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን ለሰበር ችልት መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዖው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምረነዋል ። እንደመረመርነው አመልካች በኮንትራት የፈፀሙት አገልግልት ለጡረታ አይታሰብም የተባለው ነጥብ ከህጉ ጋር በማገናዖብ በቅድሚያ መታየት ያለበት ነው ።
አዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 11/4/ /ሰ/ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ አዋጁ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በቋሚነት በተቀጠረበት መ/ቤት በጊዚያዊነት /በኮንትራት/ በተከታታይ አገልግልት የሰጠበት ጊዚ ለጡረታ ተግባር ይታሰብለታል ሲል በተመሳሳይ መልኩ አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 17/3/ /ሰ/ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በቋሚነት በተቀጠረበት መ/ቤት በጊዚያዊነት ሳያቋርጥ በተከታታይ አገልግልት የሰጠበት ጊዚ ለጡረታ ተግባር እንደሚያዛለት ይደነግጋል ።
አመልካች በኮንትራት አገልግልት ከሰኔ 1 ቀን 1995 ዓ.ም በፉት የሰጠባቸው ደግሞ ከ12/01/84 እስከ 30/01/92 ዓ.ም በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፕሮጀክት ጽ/ቤት እና ከ02/02/92 እስከ 30/10/92 ድረስ ያለት ጊዚያት መሆኑን ከክርክሩ መገንዖብ ይቻላል። አመልካች እነዘህንየኮንትራት /ጊዚያዊ/ ሥራ አገልግልት የሰጠው በዘያው በቋሚነት ተቀጥሮ በሚሰራበት መ/ቤት አይደለም፣ እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር345/1995 አንቀጽ 11/6 /መ/ ሆነ በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 17/5/ መሰረት የኮንትራት ወይም ጊዚያዊ አገልግልት ለመያዛ እንደቅድመ ሁኔታ ሰራተኛው የራሱንና የአሰሪውን የጡረታ መዋጮ ድርሻ ጨምሮ ራሱ ቀርቦ ስለመክፈለ አልተረጋገጠም። በልላ በኩልም የአመልካች የኮንትራት /ጊዚያዊ/ የስራ አገልግልት ጊዚ የተፈፀሙት አዋጅ ቁጥር 345/1995 ሆነ አዋጅ ቁጥር 714/2003 በስራ ላይ በነበሩበት ጊዚ አይደለም ። እንደዘህ በሚሆን ጊዚ ደግሞ ተፈጻሚነት የሚኖረውን አዋጅ በተመለከተ በሰበር መ/፣50591 በተሰጠው ትርጉም መሰረት አዋጅ ቁጥር 345/1995 ከመውጣቱ በፉት የተፈጠሩ ህጋዊ ሁኔታዎች ተፈጻሚ የሚሆነው አዋጅ ቁጥር 209/55 ነው ።
በዘህ አዋጅ መሰረት ደግሞ የኮንትራት አገልግልት ለጡረታ አይታሰብም ።
በልላ በኩልም በአዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 17/5/ በኮንትራት /በጊዚያዊነት/ የተሰጠ አገልግልት ለጡረታ ተግባር የሚያዖው በአዋጅ ቁጥር 345/1995 በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ቋሚ ሰራተኛ ለሆነና በአዋጅ ቁጥር 907/2007 በፀደቀ ቀን ሥራ ላይ ለሚገኝ ሰራተኛ መሆኑን ያስገነዛባለ ።
በአጠቃላይ የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ አመልካች በጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 መሰረት ቀደም ሲል በኮንትራት የፈፀሙት አገልግልት ለጡረታ ሉያዛ አይገባም በማለት የሰራተኛና ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ውሳኔ ያፀናው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። በዘህ መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዓ በቁጥር ጡ/ይ/1/1/155/2008 በቀን 28/07/2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በ15/09/2008 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል ።
አመልካችና ተጠሪ በዘህ ችልት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል ።
No topics extracted.