ማንኛውም ወገን የይርጋው ጊዚ ካለፈ በኋላ የይርጋ ጊዚን እንደመቃወሚያ አድርጎ ለማንሳት ያለውን መብት ሉተው የሚችል ስለመሆኑ፣ ዳኞች በገዙ ስልጣናቸው የይርጋውንም ደንብ መከላከያ ለመጥቀስ የማይችለ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 165/5/፤ የፍ/ሕ/ቁ. 1856/2/
No summary available.
ሐምል 27 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር -የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ወልደሰንበት ዲዱ -ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ‛ን“ መሰረት አድርጎ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዘህ ችልት ያቀረበው በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ15/07/2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ16/09/2009 ዓ.ም የተሻሻለው እና በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ በ28/09/2009 ዓ.ም በትዔዙዛ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ወረዲ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበረው የአሁኑ አመልካች ላይ በ28/02/2009 ዓ.ም አዖጋጅተው ባቀረቡት ክስ በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ ከ01/02/1974 ዓ.ም ጀምሮ በመካኒክነት የስራ መደብ ላይ በመጨረሻ ብር 5,198 (አምስት ሺህ አንድ መቶ ዖጠና ስምንት) ወርኃዊ ደመወዛ እያገኙ ሲሰሩ ቆይተው ስራቸውን በ09/03/2008 ዓ.ም በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁ መሆኑን፣አመልካች የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱፈጽም እና የመልቀቂያ /የመሸኛ/ ደብዲቤ እንዱሰጣቸው ተጠሪው በ09/03/2008 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የጠየቁ ቢሆንም አመልካች ዙሬ ነገ እያለ አቆይቶ በ25/08/2008 ዓ.ም የሰጣቸው መሆኑን የሚገልፅ ሆኖ፡-
የ63 ቀናት የዓመት ዔረፍት ክፍያ ብር 10,915.80፣ 3. በ2007 ዓ.ም. ለሰራተኞች የተከፈለ ቦነስ የአንድ ወር ተኩል ደመወዛ ብር 7,797 እና 4. በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 38 መሰረት ክፍያ የዖገየበት የሶስት ወር ደመወዛ ብር 15,594 በድምሩ ብር 96,682.80 (ዖጠና ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሁለት ከሰማንያ ሳንቲም) አመልካች ድርጅት ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍላቸው እንዱሁም አስፈላጊውን ፍርማሉቲ በማሟላት የስራ ልምዲቸውን እና የክሉራንስ ደብዲቤ ለጡረታና ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ እንዱያስተላልፍላቸው ይወሰን ዖንድ ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩለ በ22/03/2009 ዓ.ም በሰጠው መልስ ክሱ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162 (4) መሰረት በስድስት ወር ይርጋ የሚታገድ ነው የሚል የመጀመሪያ መቃወሚያ ካስቀደመ በኃላ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ ክሱ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን፣የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ በተደራቢነት የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት የላለው መሆኑን፣የአመልካቹ ንብረት በዔዲ የሚፈለግባቸው መሆኑን፣ዔዲ ካለባቸው ደግሞ የስራ ልምድ ማስረጃ ከመስጠት ውጪ አመልካቹ የመልቀቂያ ደብዲቤ ለመስጠት የማይገደድ መሆኑን፣የዓመት ዔረፍታቸውን በወቅቱ መጠቀም ሲገባቸው ያልተጠቀሙ መሆኑን፣ዔዲ እያለባቸው እና የሚከፈላቸው ክፍያ በላለበት ሁኔታ ክፍያ የዖገየበት መቀጫ መጠየቃቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጾ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሮአል።
ፍርድ ቤቱም የይርጋ መቃወሚያውን በ17/04/2009 ዓ.ም በብይን ካለፈ እና በፍሬ ጉዲዩ ረገድ ክሱን እና የተጠሪውን ምስክሮች ከሰማ በኃላ የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ፡-
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ ያሻሻለው የቦነስ ክፍያው ከስራ ውል መቋረጥ ጋር ግንኙነት የላለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ ነው በሚል ምክንያት በዘህ ረገድ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ብቻ በመሻር ሲሆን አመልካች ለዘህ ችልት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪው የስራ ውላቸውን በፈቃዲቸው ያቋረጡት በ09/03/2008 ዓ.ም. ሆኖ ክስ ያቀረቡት ደግሞ በ28/02/2009 ዓ.ም መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162 እና 164 ድንጋጌዎች አንጻር ተጠሪው ባለበት ለማጣራት እንዱቻል ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዖው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዘህም መሰረት የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቹ ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ያደረጉት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162 (4) የተመለከተው የስድስት ወር የይርጋ ጊዚ መቆጠር መጀመር የሚገባው አመልካች እንደሚከራከረው ተጠሪው ስራቸውን በፈቃዲቸው ከለቀቁበት 09/03/2008 ዓ.ም ጀምሮ ሳይሆን አመልካች የመሸኛ ደብዲቤ ለተጠሪ ከሰጠበት ከ25/08/2008 ዓ.ም ጀምሮ ነው፣ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ሲቆጠር ደግሞ ክሱ እስከቀረበበት 28/02/2009 ዓ.ም ድረስ ስድስት ወር አላለፈውም በማለት መሆኑን የመዛገቡ ግልባጭ ያመለክታል።በይርጋ ረገድ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ይህ ብይን ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? ወደሚለው ጥያቄ ከመገባቱ በፉት በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠው የይርጋ ብይን ረገድ አመልካቹ በሰበር አቤቱታው ላይ ያቀረበው የቅሬታ ነጥብ መኖር አለመኖሩን በቅድሚያ ማጤኑ ተገቢ ሆኖ ተገኝቶአል።አመልካች በ01/10/2009 ዓ.ም አዖጋጅቶ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ላይ የይርጋ መቃወሚያ አቅርቦ እንደነበረ እና ነገር ግን ውድቅ እንደተደረገበት የክርክሩን ሂደት እና የጉዲዩን አመጣጥ ለማሳየት ያህል ከመጥቀሱ ውጪ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ቅሬታውን በገለጸበት እና የዘህን ሰበር ችልት ዲኝነት በጠየቀበት የሰበር አቤቱታው ክፍል ላይ በስር ፍርድ ቤቶች በይርጋ ረገድ የተሰጠው ብይን እና ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለመሆኑ የገለጸው ነገር አለመኖሩን እና የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በይርጋ ምክንያት እንዱሻርለት ያቀረበው የዲኝነት ጥያቄ አለመኖሩን የሰበር አቤቱታው በግልጽ ያመለክታል።ተጠሪው በሰበር መልሳቸው ላይ በዘህ ረገድ ባቀረቡት የክርክር ነጥብ ረገድም አመልካቹ በመልስ መልሱ ላይ የሰጠው ማስተባበያ የለም።ማንኛውም ወገን የይርጋው ጊዚ ካለፈ በኃላ የይርጋ ጊዚን እንደመቃወሚያ አድርጎ ለማንሳት ያለውን መብት ሉተው የሚችል ስለመሆኑ በአዋጁ በአንቀጽ 165 የመጀመሪያ ዐረፍተ ነገር ላይ የተመለከተ ሲሆን ዳኞች በገዙ ስልጣናቸው የይርጋውን ደንብ መከላከያ ለመጥቀስ የማይችለ ስለመሆኑም ከአዋጁ አንቀጽ 162/5/ እና ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1856 (2) ድንጋጌ ይዖትና መንፈስ የምንገነዖበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካቹ በሰበር አቤቱታው ላይ የቅሬታ ነጥብ አድርጎ ባላቀረበበት ሁኔታ የይርጋ ጉዲይ በክርክር ጭብጥነት መያዘ ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
አመልካቹ የሰበር አቤቱታ ያቀረበበት ዓቢይ ነጥብ ተጠሪው የጡረታ መብት ተጠቃሚ ሆነው ሳለ የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት የተወሰነላቸው አላግባብ ነው የሚል ሲሆን ተጠሪው ስራቸውን እንደለቀቁ ወዱያውኑ የጡረታ አበል ተጠቃሚ አለመሆናቸው በስር ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ መሆኑን የመዛገቡ ግልባጭ የሚያመለክት በመሆኑ በዘህ ረገድ በአመልካቹ የቀረበው ክርክርም የመዛገቡን ግልባጭ መሰረት ያደረገ አይደለም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የተሻሻለው እና በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ በ28/09/2009 ዓ.ም. በትዔዙዛ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት በውጤት ደረጃ ፀንቷል።
በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዛገብ የተያዖው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዘህ መዛገብ በ01/10/2009 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዔዙዛ ተነስቷል።ይጻፍ፡
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ አመልካች የራሱን ይቻል።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.