ለተወሰነ ጊዚ የተቀጠረን ሰራተኛ የሥራ ውለ የሚቋረጥበት ጊዚ ሲደርስ አሰሪው ማሰናበት የሚችል ሲሆን ስንብቱ ከህግ ውጪ ነው ሉያሰኝ የማይችል ሲሆን በዘህ አግባብ የተሰናበተን ሰራተኛ የሥራ ሥንብት ክፍያ ሉያገኝ ይገባል የማያስብል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24/1/፣ አንቀጽ 30/1/
No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የላሉበላ ማር ሙዛየም - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ማሬ በዙ - የቀረበ የለም መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በአማራ ብ/ክ/መ/ የሰሜን ወል ዜን አስተዲደር ላስታ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተከሳሽ የነበረ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ነበረች። የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ መሰረታዊ ይዖት በአመልካች ድርጅት ከመስከረም 2004 ዓ.ም ጀምሮ በቀን ብር 45.00 /አርባ አምስት / እየተከፈላት እየሰራች እያለ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም ያለአግባብ ከስራ ስላሰናበተኝ የስንብት ክፍያ፤ የካሳ ክፍያ፤
የማስጠንቀቂያ ጊዚ ክፍያ፤ የህዛብ በዓላት፤ የዓመት ዔረፍት፤ የትርፍ ሰዓት ክፍያዎች በጠቅላላ ብር 24,020.60 /ሃያ አራት ሺህ ሃያ ብር ከስልሳ ሳንቲም/ እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን አመልካችም በተከሳሽነት ቀርቦ በሰጠው መልስ ተጠሪ የቀን ሰራተኛ ስለሆነች በአሰሪና ሰራተኛ ህግ ልትዲኝ አይገባም፤ የህዛብ በዓላትና የትርፍ ሰዓት ክፍያ ክስ ከከሰሰችበት ወደኋላ እስከ ስድስት ወር ድረስ ያለውን ብቻ እንጂ መጠየቅ የምትችለው ካዙ በፉት ያለው በይርጋ ቀሪ ስለሚሆን ልትጠይቅ አይገባም፤የዓመት ዔረፍት ከ2 ዓመት በላይ ያለው በይርጋ ይታገዲል በማለት የመጀመሪያ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ጉዲዩ አስመልክቶ የሰጠው መልስ ደግሞ ተጠሪ ከስራ የተሰናበተችው ስራው እየቀነሰ ስለሆነ ተቀንሳ ነው፤ የኮንስትራክሽን ድርጅት የሆነ አሰሪ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 30 እና በሰበር መዛገብ መሰረት የስራ መጠን በቀነሰ ጊዚ ሰራተኞች ለማሰናበት የማስጠንቀቂያና ላልች የቅነሳ ስርዓቶችን እንዱከተል የማይጠበቅበት በመሆኑ ተጠሪ የካሳ ክፍያ፤ ያለማስጠንቀቂያና የአገልግልት ክፍያ ልታገኝ አይገባም፤የአመት እረፍት ይከፈላታል ከተባለ የሁለት ዓመት ብቻ ነው ሉከፈላት የሚገባው ሲል የመከላከያ መልሱን አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዖነ በኋላ ተጠሪ ከስራ የተሰናበተችው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 29 እና 30 በተደነገገው መሰረት በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት የማስጠንቀቂያ ጊዚ ክፍያ፤ የካሳ ክፍያ አመልካች ሉከፍል አይገባም፤ የሁለት ዓመት እረፍት ክፍያ ብር 1,485.00 /አንድ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አምስት ብር/፤ የህዛብ በዓል የአንድ ቀን ብር 90.00 /ዖጠና ብር/ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል፤ ስራው ሙለ በሙለ ሳያልቅ ስራው እየቀነሰ በመምጣቱ ምክንያት ከስራ የተቀነሰ ሰራተኛ በአዋጁ አንቀጽ 39/1/ሐ/ መሰረት የስራ ስንብት ክፍያ ማግኘት ያለበት ስለሆነ አመልካች ለተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዱከፍል ሲል ወስኗል።
የአሁን አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሰሜን ወል ዜን መስተዲድር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337 መሰረት ይግባኙ በትእዙዛ ሰርዜታል። በመቀጠል አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን ያቀረበ ቢሆንም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም በማለት አቤቱታው በትእዙዛ ሰርዜታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የካቲት 17 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዖርዛሮ አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዖዖው መሰረት ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዖው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። እንደመረመርነው የስራ ስንብት ክፍያ ይከፈል ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከመዛገቡ መገንዖብ የተቻለው የአሁን ተጠሪ ከስራ እንዱሰናበት የተደረገው በአመልካች ድርጅት የተያዖው የህንፃ ስራ ፕሮጀክት ስራው እየተጠናቀቀ በመሄደ ነው። የስራ ውል ሉቋረጥ የሚችልባቸው መንገድች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 23 ስር ተመልክቷል። አንደኛው መንገድ በአሰሪው አነሳሽነት የሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ እንደሁኔታው በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስጠንቀቂያ ላደረግ የሚችል ሆኖ የምክንያቶቹ ዛርዛር እና አፈፃፀሙ ከአንቀፅ 26 እስከ 30 ተደንግገው ይገኛለ። በተጨማሪም በሕብረት ስምምነት ያለማስጠንቀቂያ ውለን ለማቋረጥ የሚያበቃ ምክንያት ተደርጎ የተወሰደ ጉዲይም በአሰሪው አነሳሽነት ያለማስጠንቀቂያ ውለን ሉያቋረጥ የሚችል መሆኑ በአንቀጽ 27/1/ተ/ ተደንግጎ ይገኛል። ስለዘህ በአዋጁ በተደነገጉ ምክንያቶችና ሁኔታዎች የሚፈፀም የስራ ውል ማቋረጥ ህጋዊ የስራ ማቋረጥ ሲሆን ከነዘህ ውጭ የሚደረጉ የስራ ውል ማቋረጥ ህገወጥ መሆኑን ከአንቀጽ 42 ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል።
ለአንድ ኮንስትራክሽን ስራ የተቀጠረ ሰራተኛ የኮንስትራክሽኑ ስራ ሲያልቅ ወይ ሲጠናቀቅ በወሳኝ ደረጃ የሚገኝ ሆኖ እያለ አሰሪ የስራ ውለ ማቋረጥ እንደሚችል እርምጃው ከህግ ውጭ ነው የሚያሰኝ ህጋዊ ምክንያት የለውም። በኮንስትራክሽን የሚሰሩ ስራዎች በባህሪያቸው በተወሰነ ጊዚ የሚያልቅ መሆኑ ግልጽ ነው። ተጠሪ የተሰማራችው የግንባታ ፕሮጀክት መሆኑ በግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የሚያከራክር አይደለም። በፕሮጀክት የተያዖው ስራ ሲጠናቀቅ አሰሪው ሰራተኞች ይዜ የሚቆይበት ሁኔታ ሉኖር አይችልም። በመሆኑም የግንባታ ስራው በሂደት እየተጠናቀቀ ሲሄድ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 30 መሰረት ስንብቱ መፈጸሙ በአጠቃላይ የፕሮጀክት ስራ እንደመሆኑ መጠን ተጠሪ የምትሰራው ስራ እየተጠናቀቀ በመሄደ አመልካች የወሰደው እርምጃ በህጋዊ መንገድ መሆኑን የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። የአመልካች ጥያቄ በዘህ ሁኔታ ከስራ የተሰናበት ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈለው አይገባም የሚል ነው። የግንባታ ስራው ባለበት ጊዚ የሚሰሩ ስራው ሲገባደድ ወይም ሲጠናቀቅ የስራ ውላቸው የሚቋረጥ ሰራተኞች ናቸው። ለእንደዘህ አይነት የስራ ውል የተቀጠሩ ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 24 ንዐስ 1 መሰረት ለተወሰነ ጊዚ የተቀጠሩ ሰራተኞች እንደሆኑ የሰበር ችልቱ ከዘህ በፉት በመዛገብ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ለተወሰነ ጊዚ የተቀጠረ ሰራተኛ የስራ ውለ የሚቋረጥበት ጊዚ ሲደርስ ከስራ ማሰናበት እንደሚቻል ከአዋጁ አንቀፅ 24 ንዐስ አንቀፅ 1 ለመረዲት ይቻላል።
ስለሆነም አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 24 ንዐስ አንቀፅ 1 እና አንቀፅ 30 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መሆኑ ከተረጋገጠ ለተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ የሚከፍልበት ምክንያት የለም። በተመሳሳይ ጉዲይ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ እና በላልች በርካታ መዙግብት በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) መሰረት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበተው በአግባቡ ነው ካለ በኋላ አመልካች ለተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ እንዱከፍል የሰጡት ውሣኔ ክፍል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በላስታ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/9 ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በሰሜን ወል መስተዲድር ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 8 ቀን 2009 ዓ/ም እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 0316070 በትእዙዛ ያፀኑት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረትተሻሽለዋል።
የስራ ስንብት ክፍያ ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር /አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የሁለት ዓመት እረፍት ክፍያ ብር 1,485.00/ አንድ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አምስት ብር/ እና የህዛብ በዓል የአንድ ቀን ብር 90.00/ዖጠና ብር/ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተሰጠ ውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.