አንድ አሰሪ የቀጠረውን ሰራተኛ በሙከራ ጊዚ አጥጋቢ ውጤት አላሳየህም በማለት የሥራ ውለን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ መብት የሚኖረው በህጉ አግባብ የተደረገ የሙከራ ታደሰ እንጆሪ ሆቴልና ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና III ስምምነት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 11/1/ /2/ እና /3/ ወ/ሪት ለላ ዖሪሁን
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 18 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- ታደሰ እንጆሪ ሆቴልና ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ.የተ.የግል ማህበር -ነ/ፈጅ ይሁንልኝ ቡልቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሪት ለላ ዖሪሁን - አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ በሐዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ ለሪቬኒ ሂሳብ ስራ መደብ በቋሚነት ተቀጥረው ከአርባ አምስት ቀናት በላይ በስራ ላይ ከቆዩ በኋላ አመልካች ድርጅት ከህግ ውጪ የሥራ ውላቸውን ያቋረጠባቸው መሆኑን ገልጸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈሎቸው ይወሰንላቸው ዖንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪን የሙከራ ጊዚ ሲጠናቀቅ ያሰናበታቸው በመሆኑ እርምጃው ሕጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዘህ መልኩ የቀረበለትም የሐዋሳ ከተማ መ/ደ/ፍ/ቤትም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተደረገ በተባለው የስራ ቅጥር ውል ላይ ያለው የተጠሪ ፊርማ የተባለው በተጠሪ በመካደ ምክንያት በባለሙያ እንዱመረመር አድርጎ ውጤቱ እንዱቀርብ በማድረግና የግራ ቀኙን ምስክሮችን በመስማት ፍሬ ነገሩን ከአጣራ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የቅጥር ውል ያቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍል በማለት የክፍያዎችን አይነትና መጠናቸውን ለይቶ ወስኗል። በዘህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ የተቀጠሩት ለሙከራ ጊዚ ሁኖ የሙከራ ጊዚ ሲጠናቀቅ እንዱሰናበቱ መደረጉ ከሕግ ውጪ አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮታል። በዘህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ችልቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በ26/09/2008 ዓ/ም የተደረገው የቅጥር ውል ተጠሪ ለሙከራ ጊዚ የተቀጠሩ ስለመሆኑ የሚያሳይ አለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪ ለሙከራ እንደተቀጠሩ ተቆጥሮ የአርባ አምስት ቀን ጊዚ ሲያልፍ የሥራ ውለ መቋረጡ ተገቢ ነው ተብል በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለትና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11(3) ድንጋጌን በዋቢነት ጠቅሶ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ አፅንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- ተጠሪ የአርባ አምስት ቀን ጊዚ ከአለፊቸው በኋላ መሰናበታቸው በሕጉ አግባብ ሁኖ እያለ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በዘህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን በበኩላችንም ጉዲዩን መርምረናል። በዘህም መሰረት በጉዲዩ ላይ ምላሽ የሚያሻውም የጉዲዩ መሰረታዊ ጭብጥ አመልካች ተጠሪን ከሥራ ማሰናበቱ በሕጉ አግባብ ነው? ወይንስ አይደለም? የሚለው ነው።
በግራ ቀኙ መካከል የቅጥር ውል የተደረገው ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ/ም ስለመሆኑና በዘህ የቅጥር ስምምነት ላይ ቅጥሩ የሙከራ ጊዚ ያለው ስለመሆኑ የተስማሙበት አግባብ የላለ መሆኑን ተጠሪ ጠቅሰው የሚከራከሩ ሲሆን አመልካች በበኩለ ቅጥሩ በ01/10/2008 ዓ/ም ተደርጎ ስንብቱ በአርባ ሶስተኛው ቀን በ13/11/2008 ዓ/ም የተደረገ ስለመሆኑና በዘህ ጊዚ ደግሞ አሰሪው ሰራተኛውን በማናቸውም ምክንያት ማሰናበት እንደሚችል ሕጉ መብት የሰጠው መሆኑን ገልጾ ተከራክሮ የሥር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ መካከል የቅጥር ውለ የተደረገበትን ጊዚና በ01/10/2008 ዓ/ም ተደረገ በተባለው ሰነድ ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪ መሆን ያለመሆኑ ላይ ክርክር በመነሳቱ ምክንያት ፊርማው እንዱመረመር አድርጎ በሰነደ ላይ ያለው ፊርማ ከተጠሪ ፊርማ ጋር የማይመሳሰል መሆኑን በባለሙያ ተረጋግጦ ያቀረበለት ከመሆኑም በላይ የግራ ቀኙን ምስክሮችን ሰምቶ የተጠሪ ማስረጃዎች ክብደት ሉሰጣቸው የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የአመልካች የሥራ ስንብት እርምጃ ሕገ ወጥ ነው በማለት መወሰኑን፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ደግሞ ስንብቱ በሕጉ በተመለከተው የሙከራ ጊዚ ውስጥ የተከናወነ በመሆኑ ህጋዊ ነው በማለት የወሰነ ቢሆንም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በግራ ቀኙ መካከል የሙከራ ጊዚ እንዱኖር የተደረገ ስምምነት በላለበት ሁኔታ አመልካች ተጠሪን ከአርባ አምስተኛው ቀን በፉት አሰናብቼአለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ሉያገኝ የሚችልበት አግባብ የለም በማለት የወሰነ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት ተገንዛበናል።
አንድ ሰራተኛ ሉመደብበት ለታቀደው ቦታ ተስማሚ መሆኑና አለመሆኑን ለመመዖን ለሙከራ ጊዚ ሉቀጥር እንደሚችል፤ይህ የግራ ቀኙ ስምምነትም በጽሐፍ መደረግ እንዲለበት፤ የሙከራ ጊዚውም ከ45 ተከታታይ ቀናት መብለጥ እንደላለበት ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11(1) ፣(2) እና (3) አጠቃላይ ይዖትና መንፈስ የምንገነዖበው ነው። የሙከራ ጊዚ ቅጥር ሲፈፀም ሰራተኛው በግልጽ ሉያውቀው የሚገባው ጉዲይ ሲሆን የሙከራ ጊዚ እንዱኖር ስምምነት ከተደረሰም ስምምነቱ በጽሐፍ ሁኖ በሁለት ምስክሮች መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ ሕጉ ያሳያል። በዘህ አግባብ የተደረገ የሙከራ ጊዚ ስምምነት መኖሩ ከተረጋገጠ አሰሪው ሰራተኛውን ለተቀጠረበት የሥራ መደብ ተስማሚ አለመሆኑን ካመነበት የቅጥር ውለን ያለምንም ማስጠንቀቂያ የማቋረጥ መብት ሕጉ የሰጠው ጉዲይ ነው። በመሆኑም አሰሪው ይህንኑ በሕጉ የተቀመጠውን መብቱን ሉጠቀም የሚችለው አሰሪው ሰራተኛውን ለሙከራ ጊዚ ለመቅጠር ወስኖ ሰራተኛውም ይህንኑ በግልጽ አውቆትና ተገንዛቦት በፅሐፍ ያሰፈሩት ስምምነት መኖሩ ከተረጋገጠ ብቻ ነው።
ወደ ተያዖው ጉዲይ ስንመጣ አመልካች ተጠሪን በ43ኛው ቀን ያሰናበታቸው ስለመሆኑ ቢረጋገጥም ለሙከራ ጊዚ የቀጠራቸው ስለመሆኑና በዘህ ረገድም ተጠሪ የሚያውቁት ውል መኖሩን ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዖን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች አላረጋገጡም። ይልቁንም አመልካች አለኝ የሚለውና የተጠሪ ፊርማ ተቀምጦበታል በተባለው ሰነድ ላይ ያለው ፊርማ በባለሙያ እንዱመረመር ተደርጎ ፊርማው የተጠሪ ያለመሆኑና አመልካች ያቀረበው ይኼው ሰነድ ከላልች የተጠሪ ማስረጃዎች ጋር ሲመዖን የማስረጃነት ክብደት ሉሰጠው የማይገባ መሆኑ መረጋገጡን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። ስለሆነም አመልካች ተጠሪ ለሙከራ የተቀጠሩ በመሆኑ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የማቋረጥ መብት አለኝ በማለት የሚያቀርበው ክርክር በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 11(3) ስር የተቀመጠውን ድንጋጌ ሙለ ይዖትና መንፈስ ያላገናዖበ ሁኖ አግኝተናል። ተጠሪ ያለማስጠንቀቂያ ሉያሰናብት የሚያስችል ጥፊት የፈፀሙ ስለመሆኑ አመልካች ገልጾ የሚያቀርበው ክርክርም ስንብቱ የሙከራ ጊዚ ውስጥ የተከናወነ ነው በማለት ከሚያቀርበውና ሕጋዊ ካልሆነው ክርክሩ ጋር አብሮ የማይሄድና በተገቢው ማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዖን ስልጣን ያለው የወረዲው ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ጉዲይ መሆኑን ተገንዛበናል። በአጠቃላይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ስንብቱ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 11(3) ድንጋጌን ያላገናዖበ መሆኑን በመጥቀስ የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሐዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ማፅናቱ የሚነቀፍበትን የሕግ አግባብ ስለላለ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
በሐዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ/ በ29/02/2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ03/08/2009 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበረውን የሥራ ውል ያቋረጠው ከሕግ አግባብ ውጪ ነው ተብል ብር 16,522.00 (አስራ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሁለት ብር) አመልካች ለተጠሪ እንዱኪፍል ተብል በተወሰነው ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህትት የለም ብለናል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
ት ዔ ዙ ዛ በ19/08/2009 ዓ/ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ ብለናል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፈርማ አለበት ።
ቅ/ሀ
No topics extracted.