ከቅጥር ውል በመነጨ ግንኙነት የሚጠየቅ ማንኛውም ክስ በአንድ ዓመት ጊዚ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ ፣ የይርጋ ጊዚ መቆጠር የሚጀምረው በመብቱ ለመጠቀም ከሚችልበት ቀን ቀጥል ካለው ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/1/፣163/1/
No summary available.
ሐምል 19 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፦ አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- የሀረር ቢራ ፊብሪካ አክሲዮን ማህበር………………አልቀረበም ተጠሪዎች፡- 1.አቶ ዓለሙ ነጋሽ 2. አቶ ሙለቀን ከበደ 3. አቶ ተስፊዬ ማኮ 4. አቶ መለሰ ሸምታጋ 5. ወ/ሮ ጽጌ አክሉለ 6. አቶ እሸቴ በየነ 7. አቶ አገሳ ዋቅጅራ 8. አቶ ተስፊዬ ደስታ 9. አቶ ፀጋዬ ሚደቅሳ 10. አቶ አበበ አያላው 11. አቶ አብዱሳ ታደ 12. አቶ ገ/ሥላሴ ገሰሰ 13. አቶ ብርሃኑ ዖፈሩ 14. አቶ መኮንን ጌታሁን 15. አቶ ጌታቸው ለማ 16. አቶ ተሰማ ተማም 17. አቶ ይታገሱ ሳህላ 18. አቶ ገ/ማርያም በርሄ 19. አቶ ኤልያስ ይላ 20. አቶ በዚ አባትሁን 21. አቶ አስናቀ ታደሰ 22. ወ/ሮ የሹምነሽ አድነው 23. አቶ መላኩ መር 24. ወ/ሮ አልማዛ ገ/ማርያም 25. አቶ ሰንበቶ ባይሳ 26. አቶ ቡልቱማ ጉታ 27. ወ/ሮ አልማዛ ዖውዳ 28. አቶ አሰፊ መርጊያ 29. አቶ አለነ አሞኘ 30. አቶ ማስረሻ ገ/አምላክ 31. አቶ መስፍን ግርማ 32. አቶ ገበየሁ አዙለ 33. አቶ አስማማው አንተነህ 34. አቶ ገመቹ ዓለሙ 35.አቶ ባቱ ቶልሳ 36 አቶ መንግስቱ ግርማ 37. አቶ ፍቃደ ደበላ 38. አቶ ዖነበ ፍኔ 39. አቶ አበበ መዖምር 40. አቶ ኃይላ አክሉለ 41. አቶ ዖውዳ ፍንታዬ 42. አቶ አብደላ ቃሲም 43. አቶ ፍቃደ ኃይላ 44.አቶ ሲሣይ መኮንን መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ ::
ጉዲዩ፡- ከስራ ውል መቋረጥ ጋር ተያይዜ የደመወዛ ጭማሪን መሰረት ያደረገ ክርክር ነው ለዘህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የአሁን ተጠሪዎች የነበሩት የስር ከሳሾች 1ኛ. በአሁን አመልካች፣ 2ኛ. በሀረር ቢራ አክሲዮን ማህበር መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር እና 3ኛ.በሀረር ቢራ አክሲዮን ማህበር ብድር እና ቁጠባ ላይ ያቀረቡት ክስ ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በሀረሪ ክልል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱም የከሳሾችን ክስ እና የቀረበውን መቃወሚያ መርምሮ ከሳሾች በ1ኛ ተከሳሽ ላይ ያቀረቡትን ከስራ ውል መቋረጥ ጋር ተያይዜ 40 ፏርሰንት ደመወዛ ጭማሪ ተጨማሪ ክፍያ እና የኢንሹራንስ ክፍያ ክሱ የቀረበው የስራ ውላቸው ከተቋረጠ ከ6 ወር በኃላ ስለሆነ ክሱ በይርጋ ይቋረጣል። ሲል በ2ኛ እና በ3ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ በግራ ቀኙ መካከል የስራ ውል ግንኙነት የላለ ስለሆነ ጉዲዩ በግልጽ የፍትሀብሄር ክርክር በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎ ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን ተጠሪዎች በውሳኔው ቅር ተሰኝተው ለከፍተኛው ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤትም ቅሬታው መልስ ሰጪን ያስቀርባል በማለት አስቀርቦ ካከራከረ በኃላ በ2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ ላይ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት እና በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት በፍሬ ነገር አከራክሮ እንዱወስን ለስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መልሶ ልኮታል። በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልለ ህግ አግባብ የተቋቋመ የሰበር ስርአት ስለላለ ችልቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም በማለት አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ መዛገቡን ዖግቶታል።
አመልካች ለዘህ ለፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታን ያቀረበው በዘሁ ላይ ነው። የአመልካች ድርጅት ነ/ፈጅ ጥር 3 ቀን 2009 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ ክሱ በይርጋ ይታገድ ይገባው እንደነበር እና የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይርጋ ክርክሩን ውድቅ ለማድረግ የሰጠው ምክንያት መሰረታዊ የሕግ ትርጉም ስሕተት የተፈፀመበት ስለመሆኑ በማብራራት የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱታረም አመልክተዋል። የሰበር አጣሪው አቤቱታውን ከመረመረ በኋላ የአመልካች ድርጅት ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ የታለፈበትን አግባብ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። የተጠሪዎች ወኪል ሚያዛያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም የጽሐፍ መልስ ያቀረቡ ሲሆን አመልካች የመልስ መልስ ለመስጠት ያለመፈለጉን በመግለጽ ያላቀረበ ስለሆነ የመልስ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የግራ ቀኙ ክርክር እና የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም የተያዖውን ጭብጥ ከሕጉ አንፃር አገናዛበን መርምረናል። ከፍ ሲል በዛርዛር እንደተመለከተው በአመልካች እና ተጠሪዎች መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው ግንቦት 3 ቀን 2005 ዓ.ም መሆኑ እና ክስ የቀረበው መጋቢት 17 ቀን 2006 ዓ.ም መሆኑ አከራካሪ አይደለም።በተጠሪዎች በኩል የቀረበው ክስ የሥራ ውላችን ሲቋረጥ በስምምነት ከስራ ለሚለቅ ሰራተኛ ከተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የደመወዘን 100 ፏርሰንት ለመክፈል አሰሪው ስምምነት አድርጎ የተከፈለን ቢሆንም የስራ ውላችን ከተቋረጠ በኃላ ታህሳስ ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ በስምምነት ከስራ ለሚለቅ ሰራተኛ ከተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የደመወዘን 140ፏርሰንት ለመክፈል አሰሪው ስምምነት ላይ መድረሱን በመግለጽ ሉከፈለን የሚገባ የደመወዛ ጭማሪ 40 ፏርሰንት እና የኢንሹራንስ ክፍያ እንዱከፈለን ይወሰንልን የሚል ነው።
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162 ልዩ ልዩ የመብት ጥያቄዎችን አስመልክቶ ክሱ መቅረብ ያለበትን የጊዚ ገደብ ወስኗል።
የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ ለማድረግ የሰጠው ምክንያት የሥራ ውል ከተቋረጠበት ከግንቦት 3 ቀን 2005 ዓ.ም ክስ እስከቀረበበት መጋቢት 17 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዚ ሲሰላ ስድስት ወር ያለፈው መሆኑን በመግለጽ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162(4)ን በመጥቀስ ሲሆን የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ክርክሩ በይርጋ አይታገድም በማለት ውሳኔ የሰጠው የደመወዛ 40 ፏርሰንት ጭማሪ እና የኢንሹራንስ ክፍያ የይርጋ ጊዚ በአዋጁ አንቀጽ 162(1) መሰረት በ1 አመት ይርጋ የሚቋረጥ መሆኑን እና የተጠሪዎች ክስም የቀረበው የስራ ውለ ከተቋረጠ አንድ አመት ሳይሞላው ነው በማለት መሆኑን ከስር መዛገብ መረዲት ተችሎል።
የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162(4)ን ስንመለከት የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሰራተኛውም ሆነ በአሰሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ የስራ ውለ በተቋረጠ በ6 ወር ጊዚ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጎ ይገኛል። የተጠሪዎችን የክስ ይዖት ስንመለከት ደግሞ የስራ ውላችን ግንቦት 3/2005 ከተቋረጠ በኃላ ታህሳስ ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለሚወጡ ሰራተኞች አመልካች ለመክፈል የተስማማው የደመወዛ ጭማሪ ለኛም ሉከፈለን ይገባል የሚል ነው። ተጠሪዎች ክስ ያቀረቡበት መብት ተቋቁሟል የሚለት የስራ ውላቸው ከተቋረጠ ከ7ወር በኃላ አመልካች ከስራ ለሚለቁ ሰራተኞች የደመወዛ ጭማሪ አድርጓል በሚል መሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው። ይህ መሆኑ ከተረጋገጠ የተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት የተቋቋመ የመብት ጥያቄ ላሆን የሚችልበት ምክንያት የለም። ስለሆነም የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪዎች መብት ከስራ ውል መቋረጥ የመነጨ ነው በማለት ድምዲሜ ላይ ደርሶ የአዋጁን አንቀፅ 162(4)ን በመጥቀስ ክርክሩ በ6 ወር ይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠው ውሳኔ ሕጋዊና ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ይልቁንም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአዋጁ አንቀጽ 162(1) መሰረት ከቅጥር ውል በመነጨ ግንኙነት የሚጠየቅ ማንኛውም ክስ በ1 አመት ጊዚ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን በመጥቀስ እና የተጠሪዎች የስራ ውል ከተቋረጠበት ክስ እስከቀረበበት ድረስ ያለው ጊዚ ሲታሰብ 1አመት የማይሞላው መሆኑን በመግለጽ የተጠሪዎች ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት ድምዲሜ ላይ ደርሶ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ አዋጁ ለይርጋ አቆጣጠር በምክንያትነት የደነገገውን መስፈርት መሰረት ያደረገ በመሆኑ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
ነገር ግን አዋጅ ቁጥር 377/1996 "ን" መሰረት አድርገው የሚቀርቡ ክሶችን የይርጋ ጊዚ አቆጣጠር በተመለከተ በአዋጁ በተለየ አኳኃን ካልተገለጸ በቀር የይርጋ ጊዚ መቆጠር የሚጀምረው መብትን ለመጠቀም ከሚቻልበት ቀን ቀጥል ካለው ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 163(1) ስር የተደነገገ ከመሆኑ በተጨማሪ የፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
የስር ሁለቱም ፍርድ ቤቶች ማለትም መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ክርክሩ በይርጋ የሚታገደው ክሱ በ6ወር ጊዚ ውስጥ ባለመቅረቡ ነው በማለት እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ክሱ በይርጋ የማይታገደው በ1 አመት ጊዚ ውስጥ የቀረበ ስለሆነ ነው በማለት የይርጋ ጊዚውን በማስላት መደምደሚያ ላይ የደረሱት የስንበት ደብዲቤው ለተጠሪዎች ተሰጥቷል ከተባለበት ከ03/09/2005 ዓ.ም ጀምሮ በመቁጠር ስለመሆኑ የውሳኔው ይዖት ያመለክታል።ይሁን እንጂ ለተጠሪዎች የስንብት ደብዲቤው በ03/09/2005ዓ.ም የተሰጣቸው ቢሆንም ተጠሪዎች ለክሳቸው መሰረት ያደረጉት ታህሳስ ወር 2006ዓ.ም ጀምሮ በስምምነት ከስራ ለሚለቅ ሰራተኛ ከተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የደመወዘን 140 ፏርሰንት ለመክፈል አሰሪው ስምምነት ላይ መድረሱን እና በዘህ መሰረት ክፍያ መፈጸሙን በመግለጽ መሆኑን ተጠሪዎች በስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ካቀረቡት ክስ ይዖትም ሆነ ከግራ ቀኙ ክርክር መረዲት የተቻለ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የስንብት ደብዲቤው ለተጠሪዎች ተሰጥቷል ተብል በተጠሪዎች የተገለጸውን ግንቦት 03 ቀን 2005 ዓ.ም ለይርጋ ጊዚው አቆጣጠር የመነሻ ቀን አድርገው መውሰዲቸው ይልቁንም ተጠሪዎች ከስራ የተሰናበቱት በ3/9/2005 ጀምሮ ቢሆንም ተጠሪዎች ሉከፈለን ይገባል በማለት ክስ ያቀረቡት ታህሳስ 6 ቀን 2006 ዓ.ም የተደረገ የደመወዛ ጭማሪን መሰረት ያደረገ መሆኑን ከግራ ቀኙ ክርክር መገንዖብ የተቻለ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 163(1) በተመለከተው መሰረት ለይርጋ ጊዚው አቆጣጠር የመነሻ ቀን ተደርጎ መወሰድ የሚገባው በስምምነት ከስራ ለሚለቁ ሰራተኞች ደመወዛ ጭማሪው ክፍያ 140 ፏርሰንት እንዱሆን ከተወሰነበት ከታህሳስ 6 ቀን 2006 መሆኑን ተገንዛበናል። ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት መጋቢት 17 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዚ ሲቆጠር ደግሞ አንድ(1)አመት የማይሞላው በመሆኑ ተጠሪዎች ያቀረቡት የክፍያ ጥያቄ በአዋጁ አንቀጽ 162(1) መሰረት በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
ሲጠቃለል የሀረሪ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክር በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠውን ውሳኔ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሻር ክርክሩ በይርጋ አይታገድም በማለት እና የፍሬ ነገር ክርክሩን አከራክሮ እና አጣርቶ እንዱወስን ለስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱመለስ የሰጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የሀረሪ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ9/12/2006ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሀረሪ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 12532 በ18/8/2008ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1)መሰረት ጸንቷል።
የተጠሪዎች የክፍያ ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162(4) መሰረት በይርጋ የሚታገድ አይደለም ብለናል።
የዘህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። ይፃፍ።
የውሳኔው ግልብጭ በየደረጃው ለሚገኙ የስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖግቷልወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.