በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚፈጸም ጊዚያዊ ቅጥር ውል ሉከተላቸው ስለሚገባ ዶ/ር ደስአለኝ ተመስገን እና II መንግስት መስሪያ ቤት የሚደረግ የጊዚያዊ ሰራተኛ ቅጥር ውል ለፕሮጀክት ስራ ካልሆነ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515/99 አንቀጽ 22/3/፣93 የኢ.ፋ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ህዲር 18/2005 በቁጥር መ80-893/1/ የተጻፈ ደብዲቤ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር በቁጥር ሲሰመ30/መ/18/22/459 በ የተጻፈ ደብዲቤ የአዱስ አበባ ሳይንስና ቴክኖልጂ ዩኒቨርስቲ ዓ.ም
No summary available.
ታህሳስ 28 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ህትመት አሰፊ አመልካች፡- ዶ/ር ደስአለኝ ተመስገን ቀረቡ ተጠሪ፡- አዱስ አበባ ሳይንስና ቴክኖልጂ ዩኒቨርስቲ የቀረበ የለም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ለዘህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የቻለው በኢፋዳሪ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰተር አስተዲደር ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 041/2008 ቀን የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችልት አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የመንግስት ሰራተኞችን የስራ ክርክር በይግባኝ አይቶ ሉያስተናግድ የሚችለው በፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 በተሰጠው ስልጣን በአንቀጽ 2/1/ እና /3/ መሰረት አዋጅ ተፈፃሚ በሚሆንላቸው በፋዳራል መንግስት መ/ቤቶች በቋሚነት ተቀጥረው ለሚያገለግለ የመንግስት ሰራተኞች ብቻ በመሆኑ የአሁኑ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ ጋር የፈጸሙት የስራ ውል በፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አ/ቁ/ 515/99 አንቀጽ 22/3/ መሰረት ህዲር 09 ቀን 2000 ዓ/ም በወጣው የፋዳራል መንግስት ሰራተኞች /ጊዚያዊ/ ኮንትራት ቅጥር አፈፃጸም መመሪያ አንቀጽ 10 መሰረት በመሆኑ የአመልካች ቅጥር ቋሚ ሳይሆን ኮንትራት ቅጥር ስለሆነ ጊዚያዊ ሰራተኛ ጉዲይ የማየት ስልጣን የለውም በማለት በብይን መዛገቡን ዖግይቶ ይህ ብይን በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ22/10/2008 ዓ/ም በዋለው ችልት በመፅናቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን በማቅረባቸው ይህንኑ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ይህ ጉዲይ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የተጀመረ ሲሆን የአሁን አመልካች ይግባኝ ባይ፣ ተጠሪ ደግሞ መልስ ሰጪ ሁኖ ተከራክረዋል። የአሁኑ አመልካች በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አስተዲደር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ይዖቱ ሲታይም፡- ከተጠሪ መስሪያ ቤት በቁጥር ገወ 3.9/3/53/08 በቀን ጥቅምት 08 ቀን 2008 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ የተላለፈባቸውን የሥራ ስንብት ውሳኔ ያላግባብ የተሰጠ መሆኑን የሚዖርዛር ሁኖ ተጠሪ መስሪያ ቤት የሰጠው ውሳኔ በአስተዲደር ፍርድ ቤቱ ተሽሮ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዱመለሱ፣ ከየካቲት 01 ቀን 2007 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2008 ዓ/ም ያልተከፈላቸው የወር ደመወዛ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፈላቸው ይወሰን ዖንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በአስተዲደር ፍርድ ቤቱ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጎም አመልካች በዩኒቨርሲቲው ሴኔት "ሉጂስላሽን" እንደ ስነ ምግባር ጉድለት የተጠቀሱትንና የፈጸሟቸውን ግድፈቶች ያመኑ በመሆናቸውና ከስነ ምግባር ግድፈት ጋር በተገናኘ ጉዲዩ በተጠሪ አጠቃላይ ቦርድ በጉባኤ ተመርምሮ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 44(ኅ) መሰረት በቦርደ የተሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ በመሆኑ በፍርድ ቤት ላታይ የማይችል መሆኑን፣ አመልካች በተጠሪው መስሪያ ቤት ሰራተኛ ቢሆኑም በመስሪያ ቤቱ ቋሚ ሰራተኛ ለመሆን በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 33(1) እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 210/2003 አንቀፅ 6 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተጠሪው መስሪያ ቤት ታህሳስ 16 ቀን 2005 ዓ/ም ባወጣው የቋሚ ቅጥር አፈፃፀም መስፈርቶችን አሟልተው ያልተገኙ መሆናቸውንና በተጨማሪም በየሁለት አመት በሚታደስ የኮንትራት ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኛ መሆናቸውን በመዖርዛር ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በማለት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይም ተገቢ ነው ያለውን ክርክር አቅርቧል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የሲቪል ሰርቪስ አስተዲደር ፍርድ ቤትም በተጠሪ በኩል የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር መርምሮ አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የመንግስት ሰራተኞችን የስራ ክርክር በይግባኝ አይቶ ሉያስተናግድ የሚችለው በፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 በተሰጠው ስልጣን በአንቀጽ 2/1/ እና /3/ መሰረት አዋጅ ተፈፃሚ በሚሆንባቸው በፋዳራል መንግስት መ/ቤቶች በቋሚነት ተቀጥረው ለሚያገለግለ የመንግስት ሰራተኞች ብቻ በመሆኑ የአሁኑ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ ጋር የፈጸሙት የስራ ውል በፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አ/ቁ/ 515/99 አንቀጽ 22/3/ መሰረት ህዲር 09 ቀን 2000 ዓ/ም በወጣው የፋዳራል መንግስት ሰራተኞች /ጊዚያዊ/ ኮንትራት ቅጥር አፈፃጸም መመሪያ አንቀጽ 10 መሰረት በመሆኑ የአመልካች ቅጥር ቋሚ ሳይሆን ኮንትራት ቅጥር ስለሆነ ጊዚያዊ ሰራተኛ ጉዲይ የማየት ስልጣን የለውም በማለት በብይን መዛገቡን ዖግቷል። በዘህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸው ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን ሙለ በሙለ አጽንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡-በተጠሪ መ/ቤት በሚቀጠሩበት ጊዚ ከላይ ርዔሱ ኮንትራት ቅጥር ይባል እንጂ ለብዘ ጊዚ ለተለያዩ መ/ቤቶች ተጠሪው በፃፊቸው ደብዲቤዎች አመልካች ቋሚ የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ተጠሪው ለተለያዩ መስሪያ ቤት ደብዲቤ ሲፃፍ የቆየ መሆኑን፣ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 33(1) ድንጋጌም የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቅጥር በኮንትራት የሚፈፀም መሆኑን የሚያስገንዛብ ይዖትና መንፈስ የላለው መሆኑን፣ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አግባብ ወጣ የተባለው የመንግስት ሰራተኞች የኮንትራት ቅጥር አፈፃፀም መመሪያም በጠቅላይ ሚኒስትሩ በቁጥር መ80-839/1 በተላለፈው መመሪያ መሰረት ቀሪ የሆነ እና በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ታህሳስ 16 ቀን 2005 ዓ/ም በቁጥር ሲሰሚ.30/ጠ18/22/459 ባሰራጨው ደብዲቤ መሰረት በመንግስት መስሪያ ቤቶች የጊዘያዊ ቅጥር/ኮንትራት/ ለፕሮጀክቶች ብቻ የሚፈፀም እንጂ አመልካች ለተቀጠሩበት ስራ አይነት ተፈጻሚነት የላለው መሆኑን፣ አመልካች የተቀጠሩበት የሥራ ውል በጊዚ የተገደበ ቢሆንም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተላለፈው መመሪያና ከስራው ባህርይ የተነሳ ህጋዊ ላሆን የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑን፣ ተጠሪ የአመልካችን የቋሚነት ቅጥር በመቀበል የጡረታ መዋጮ እየቆረጠ እንዱጠራቀምላቸው ሲያደርግ የቆየ መሆኑንና ላልች ነጥቦችን በመዖርዛር ቅጥሩ ቋሚ ቅጥር በመሆኑ አስተዲደር ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለው ተብል እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ቋሚ ሰራተኛ አይደለም ተብል የፏብሉክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍርድ ቤት በይግባኝ የቀረበውን ጉዲይ የማየት ስልጣን የለውም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል ጉዲዩ ለዘህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የተቻለው አመልካች በተጠሪ ተቋም የተቀጠሩት ከጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ/ም ጀምሮ በየ2/ሁለት/ አመት በሚታደስ ኮንትራት በባዮጂካል ኬሚካል ሳይንስና ቴክኖልጂ ት/ቤት ውስጥ በረዲት ፕሮፋሰር የስራ ማዔረግ በወር ብር 5443.00 እየተከፈላቸው እንዱሰሩ የተቀጠሩ በቁጥር ሰላዲ 25/6-1/05 ቀን ህዲር 19/2005 ዓ/ም ለአመልካቹ የተፃፈው ደብዲቤ ይዖቱ የሚያስረዲ መሆኑን፣ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በ12/02/2005 ዓ/ም በተደረገው የቅጥር ውል በአንቀጽ 4 የውለ ጊዚ ከጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ጊዚ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን፣ በአንቀጽ 8 ውለ የውለን ጊዚ ማብቂያ ተከትል በጽሁፍ የሚታደስ መሆኑን፣ በአንቀጽ 9/1/ ዩኒቨርስቲው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ማስጠንቀቂያ ውለን በማንኛውም በቂ ምክንያት የመሰረዛ መብት ያለው መሆኑን፣ በዘህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 4/መ/ የውለ ጊዚ ሲያበቃ ውለ የሚቋረጥ መሆኑን፣ ለውለ ተፈፃሚነት ያላቸው ህጎችና የስልጣን ወሰን በኢትዮጲያ ህግ መሰረት የሚስተናገድ መሆኑን በመካከላቸው አለመግባባት በሚፈጠሩበት ጊዚ የኢትዮጲያ ፍርድ ቤት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በአንቀጽ 11 ስር በግልጽ መደንገጉን ነው። የአስተደዲር ፍርድ ቤት አመልካች ቋሚ አይደለም በማለት ይግባኛቸውን ሳይቀበል የቀረውም ሆነ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህንኑ የአስተዲደር ፍርድ ቤትን ብይን ያጸናው የቅጥር ውለ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በተስማሙት መሰረት አስገዲጅነት እንዲለው፣ በዘህም ምክንያት ውለ ከመነሻውም ቢሆን በተጠሪ መ/ቤት በተሰጠው ውሳኔ ቅሬታውን መቅረብ ያለበት ለአስተዲደር ፍ/ቤት ሳይሆን ለመደበኛ ፍ/ቤት መሆኑን እንደሚያስረዲ፣ አመልካች ቅጥሩ ጊዚያዊ ሳይሆን ቋሚ ቅጥር ነው ሲለ ለሚያነሱት ክርክር በማስረጃነት የሚጠቅሷቸውና ተጠሪ መ/ቤት ለተለያዩ ተቋማት የጻፎቸው ደብዲቤዎችም በራሪ ደብዲቤዎች ከመሆናቸው ውጪ በ12/02/2005 ዓ/ም የተፈጸመ ውል ወደ ቋሚነት የተሸጋገረ መሆኑን የሚያስረዲ ውል አመልካች አላቀረቡም የሚለ ምክንያቶችን በማስፈር መሆኑን እንዱሁም የተጠሪ መስሪያ ቤት አመልካችን ሲያሰናብት በቦርደ ውሳኔ መሰረት የሆኑት ምክንያቶች ከስነ ምግባር ግድፈቶች ጋር የተያያዘ እንጂ ቅጥሩ በሁለት አመት የጊዚ ገደብ በመወሰኑ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የማያሳይ መሆኑን ተገንዛበናል።
በመሰረቱ የቅጥር ውል አለ ወይስ የለም? ከሚለው ነጥብ ጋር በተያያዖ የቅጥር ውል አፈፃፀምንና የቅጥር ውል አሰራረዛን አስመልክቶ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የቅጥር ዓይነት በሁለት ዓመት ጊዚ የተገደበ ስለመሆኑ ግራ ቀኙን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ይህ ክርክር ያሰነሳው የቅጥር ዓይነት በጊዚ የተገደበ እንደመሆኑ መጠን የአዋጅ ቁጥር 515/99 የተፈፃሚነት ወሰንን ለመለየት እንዱረዲ በአንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር ‛የመንግስት ሰራተኛ“ ማለት በፋደራል መንግስት መ/ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራን ሰራተኛ ብቻ የሚመለከት በመሆኑና የአዋጁም ተፈፃሚነት ይኸው ቋሚ የመንግስት ሰራተኛ በዘሁ አንቀጽ 2(3) ሥር ከተመለከተው የመንግስት መ/ቤት ጋር በሚያደርጉት ክርክር ላይ የተወሰነ ነው በሚል የተቀመጠውን የአዋጅ ትርጓሜ መነሻ በማድረግ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ትርጉም በዘህ ደረጃ የሚነቀፍ አይደለም። ሆኖም የሚያከራክራቸውን የቅጥር ሁኔታ በጊዚ መገደቡን ተመልክቶ የአሁን አመልካች የኮንትራት ሰራተኛ ነው ከሚል መደምደሚያ ላይ ከደረሰ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 2(2) ‛ጊዘያዊ ሰራተኛ“ ማለት በመንግስት መ/ቤት ውስጥ የዖላቂነት ባህሪ በላለው ሥራ ወይም ሁኔታዎች ሲያስገድደ በቋሚ የሥራ መደብ ላይ በጊዘያዊነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው የሚል ትርጓሜ በማስቀመጥ አዋጁ በእነዘህ ጊዚያዊ ሰራተኞች ላይ ተፈፃሚ ላሆን እንደማይችል በአንቀጽ 2(1) የተመለከተውን የአዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን በሚያጠናክር ሁኔታ ከተደነገገና ይህንኑም ይበልጥ ግልፅ በማድረግ በአንቀጽ 3 ላይ የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰንን በመንግስት መ/ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ በሚሰራ የመንግስት ሰራተኛ ላይ ብቻ እንደሆነ ካስቀመጠ በኋላ ጊዘያዊ ሰራተኞች በዘህ አዋጅ ሉካተቱ የማይችለ መሆኑን በመደንገግ ሳይገደብ በአዋጁ አንቀጽ 22 ሥር በአዋጅ የሚገዙ የመንግስት መ/ቤት ከቋሚ የመንግስት ሰራተኛ ባሻገር ጊዚያዊ ሰራተኛን መቅጠር የሚችልበትን ሁኔታ በንዐስ ቁጥር 1 ለይቶ ከደነገገ በኋላ በዘህ አኳኋን በመንግስት መ/ቤት የሚቀጠሩ ጊዚያዊ ሰራተኞች አቀጣጠር ስለሚኖራቸው መብቶችና ግዳታዎች እንዱሁም ስለሚጠበቅላቸው የሥራ ሁኔታዎች ዛርዛር መመሪያ ሉወጣ የሚችል መሆኑንም ሁለ አካቷል። እንደዘሁም ይህን አዋጁን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ደንቦችን በሚኒስትሮች ም/ቤት እነዘህን ደንቦች ለማስፈፀም የሚረደ መመሪያዎች በኤጀንሲው አማካኝነት ሉወጡ እንደሚችለም በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 93 የተመለከተ በመሆኑ በአንቀጽ 22 እና በአንቀጽ 93 መሰረት ጊዚያዊ ሰራተኞችን የሚመለከት ዛርዛር ደንብና መመሪያ እንደሚወጣ ተመልክቷል። በዘህም መሰረት በአንቀጽ 2(2) ስለ ጊዘያዊ ሰራተኛ የተሰጠውን ትርጓሜ መነሻ በማድረግ፣ በአንቀጽ 22 እንደ ተመለከተው የመንግስት መ/ቤት ጊዘያዊ ሰራተኛን መቅጠር የሚችልበትን አግባብ አስመልክቶ በአዋጁ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 22 (3) እና አንቀጽ 93 መሰረት በሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በህዲር ወር 2000 የወጣውን የፍደራል መንግስት መ/ቤቶች የጊዚያዊ /ኮንትራት/ ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም መመሪያ መውጣቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ መመሪያ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚፈጸመውን የጊዚያዊ ቅጥር ስርዓቱን ዖርግቶ የነበረ ሲሆን በመመሪያው በጊዚያዊ ቅጥር የተቀጠሩ ሰራተኞቸ ወደ ቋሚነት እንዱሸጋገሩና ጊዚያዊ ቅጥር ለ"ፕሮጀክት" ስራዎች ብቻ እንዱሆንና በዘሁ አግባብ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ህዲር 18 ቀን 2005 ዓ/ም በቁጥር መ80-839/1 ለሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የፃፈ መሆኑን፣ የሲቪል ሲርቪስ ሚኒስቴርም ይህንኑ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተላከውን መመሪያ መነሻ በማድረግ በቁጥር ሲሰሚ30/መ/18/22/459 በ16/04/2005 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ በመስሪያ ቤት በጊዘያዊነት የተቀጠሩት ሰራተኞች ወደ ቋሚ ሰራተኛነት የሚመደቡበትን አግባብ በመመዖርዖር ከደብዲቤው በኋላ በማንኛውም የፋዳራል መንግስት መስሪያ ቤት እጅግ አስፈላጊ ለሆኑና ለአጭር ጊዚ ብቻ የኮንትራት/ጊዘያዊ ቅጥር መፈጸም አስገዲጅ ሁኔታ ከተፈጠረ ጥያቄው በቅድሚያ ለሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር እየቀረበ ተቀባይነት ማግኘቱ መረጋገጥ ያለበት መሆኑን በመግለጽና ከዘህ ውጪ በማንኛውም መልኩ የኮንትራት/ጊዚያዊ ቅጥር መፈፀም ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን የሚያሳይ መመሪያ አስተላልፎል። በመሆኑም የፏብሉክ ሰርቪስ አስተዲደር ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዘህ ረገድ ያስቀመጡት ምክንያት የለም። ከዘህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው በሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በህዲር ወር 2000 የወጣውን የፋዳራል መንግስት መ/ቤቶች የጊዚያዊ /ኮንትራት/ ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም መመሪያ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ሲሆን በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚፈፀም የጊዚያዊ ቅጥር ውል በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሲሰሚ30/መ/18/22/459 በ16/04/2005 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ አግባብ መፈጸሙ ካልተረጋገጠ ሕጋዊ ነው ተብል የሚወሰድ አይደለም።
የአሁን ተጠሪ ዩኒቨርሲቲ አጥብቆ የሚከራከራው በአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 33(1) እና በደንብ ቁጥር 210/2003 አንቀጽ 6 አግባብ በዪኒቨርስቲው ሰኔት በወጣው ላጂስላሽን መሰረት ቅጥሩ በየሁለት አመት የሚታደስ መሆኑ ሕጋዊ ነው፣ ስንብቱም ጊዚውን ጠብቆ የተደረገ ነው በማለት መሆኑን ተገንዛበናል። ይሁን እንጂ በተጠሪው ቦርድ ለአመልካች ስንብት ምክንያት የሆነው የቅጥር ጊዚ ማብቃቱ ሳይሆን በአመልካች በኩል ተፈጸሙ የተባለ የስነ ምግባር ግድፈቶች ከመሆናቸው በላይ የአዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀፅ 33 (1) አግባብ ቋሚ ቅጥር የሚፈፀመበት አግባብ በዩኒቨርሲተው እና አመልካችን ከመሰለ መምህራን ጋር የሚፈጸመው ቅጥር ጊዘያዊ ቅጥር ነው ብል ለመደምደም የሚያስችል ሁኖ አልተገኘም። የአሁን ተጠሪ ዩንቨርሲቲ በማስተማር ሙያ ጊዚን ወስኖ ከመምህራን ጋር የቅጥር ውል የሚፈጸመው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በዔውቀት፣ ክህልትና አመለካከት የታነፁ ምሩቃንን ለማፍራት የሚያስችል አቅም ያለውን መምህር መሆኑንና አለመሆኑን ለመፈተሽ እንዱረዲው ሲባል ስለመሆኑ ከራሱ ከዩኒቨርስቲው ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 216/2003፣ ለዩኒቨርስቲው በደንብ ቁጥር 210/2003 አንቀጽ 6 በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር በወጣው የዩኒቨርሲቲው "ላጂስላሽን"ም ሆነ ከከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 በአዋጅ ቁጥር 861/2006 እንደተሻሻለው፤ የተመለከተውን ግብና አላማ በማገናዖብ መረዲት የምንችለው ጉዲይ ነው።
የአሁን ተጠሪም ቢሆን በሥር ፍ/ቤት የቅጥሩ ሁኔታ በዩኒቨርሲቲው ላጂስላሽን አንቀጽ 61 መሰረት ቋሚ አይደለም፤ ቅጥር በዘሁ ደንብ መሰረት የተፈፀመ አለመሆኑ እስከ ተረጋገጠ ድረስ ሉሰረዛ የሚችል ነው በሚል አዋጁን፣ደንቡንና የዪኒቪርሲቲውን "ላጂስላሽ"ን ጠቅሶ መከራከሩና ቅጥሩ በጊዚ ተገድቦ እንዱፈፀም መደረጉ በእራሱ ብቻውን ይህ አመልካች ጊዘያዊ /የኮንትራት/ ሰራተኛ ነው በሚለው አቋም ሥር ሉወድቅ የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ሆኖ አልተገኘም።
ስለሆነም በዘህ በተያዖው ጉዲይ በግራ ቀኙ መካከል ተደርጓል የተባለው የቅጥር ውል በሁለት ዓመት ጊዚ ተገድቦ የመደረጉ እውነታ ለትምህርት ጥራት ስኬት ሲባል ቅጥሩ ሉቋረጥ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ታስቦ የተደረገ ነው ካልተባለ በስተቀር የተቆረጠው ጊዚ በእራሱ የቅጥሩ ሁኔታ ጊዚያዊ መሆኑን ጠቋሚ ሆኖ ጊዚያዊ /ኮንትራት/ ሰራተኞች በሚል ትርጓሜ ሥር የሚሸፈን ባለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 515/ 1999 በወጣው የጊያዘያዊ ቅጥር አፈጻጸም መመሪያና ይህንኑ መመሪያ በተመለከተ ቀጥል በተዖረጋው ስርዓት አግባብ ሉገዙ የሚችልበት ሁኔታ የላለ ሁኖ አግኝተናል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የቅጥር ውል ስለጊዚያዊ /ኮንትራት/ ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም በወጣው መመሪያ መሰረት ላሆን ይገባል ብል ለመደምደም እንደማያበቃ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አግባብ ህዲር 2000 ዓ/ም በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ወጥቶ የነበረውና በኋላም በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ጠቅላይ ሚስቴር ጽ/ቤት በቁጥር መ80-839/1 በተላለፈው መመሪያ መነሻ ቀሪ የሆነ እና በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ታህሳስ 16 ቀን 2005 ዓ/ም በቁጥር ሲሰሚ.30/ጠ18/22/459 ባሰራጨው ደብዲቤ መሰረት በመንግስት መስሪያ ቤቶች የጊዘያዊ ቅጥር/ኮንትራት/ ለፕሮጀክቶች ብቻ የሚፈፀም እንጂ አመልካች ለተቀጠሩበት ስራ አይነት ተፈጻሚነት የላለው ስለመሆኑ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች ለአስተዲደር ፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ይግባኝ ይህ ችልት በመ/ እና በላልች በርካታ መዙግብት በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) በየትኛውም ፍርድ ቤት የሚገኝ የዲኝነት አካል የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ከመስጠቱና በህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ከተመለከተው ፍትህ የማግኘት መብት አንፃር ሁለ ሲታይ ጉዲዩ በፋደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ አዋጅ ቁጥር 515/99 አግባብ በተዖረጋው የይግባኝ ስርዓት ታይቶ ሉወሰን የሚገባው ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤቶች ቅጥሩ በጊዚ መገደቡን ብቻ በማየት የአመልካችን ይግባኝ ውድቅ ማድረጋቸው ሕጋዊ ሁኖ አልተገኘም። በመሆኑም የውለን ቆይታ ጊዚ በተመለከተ ቅጥሩ ሕጋዊ ስለመሆኑ ሳይረጋገጥ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተፈጻሚነት አለው ተብል የተያዖው የበታች ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ ከላይ የተዖረዖሩትን ሕጋዊ ምክንያቶችን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 የተቀመጠው በሕግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች በተዋዋይ ወገኖች የአስገዲጅነት ኃይል አላቸው የሚለው ድንጋጌ በቅድሚያ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1678(ለ)፣1711 እና 1716 ስር ስለህጋዊ ውል አመሰራረት የተቀመጡትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ያላገናዖበ ሁኖ አግኝተናል።
ሲጠቃለልም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የቅጥር ውል ጊዘያዊ/ኮንትራት ነው ልባል የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 650/2001 በአዋጅ ቁጥር 861/2006 እንደተሻሻለው ከአንቀፅ 30 እና 33 ጣምራ ንባብና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በመምህራን መካከል የሚደረጉ ውልች በየሁለት አመት እንዱታደሱ ከሚደረጉበት መሰረታዊ ዓላማ፣ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አግባብ ሕዲር 09 ቀን 2000 ዓ/ም ወጥቶ የነበረው የጊዘያዊ ቅጥር ውል አፈጸጸም መመሪያ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ጠቅላይ ሚስቴር ጽ/ቤት በቁጥር መ80-839/1 በተላለፈው መመሪያ መነሻ በከፉል ቀሪ ከመሆኑና በሕግ ጥበቃ ሉሰጣቸው የሚገባቸው ውልች በህጉ አግባብ የተቋቋሙ ናቸው ከሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዖት የተገነዖብን በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፏብሉክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 041/2008 ቀን የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ በቀን 22/10/2008 ዓ.ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ግራ ቀኙ የተከራከሩበትን የቅጥር ውል አፈፃፀም ሆነ የቅጥር ውል አሰራረዛ በሚመለከት በየፉናቸው ያቀረቡትን ክርክር ማስረጃ ለጉዲዩ ተፈፃሚ መሆን ከሚገባው ህግና ደንብ አንፃር በማየት ተገቢውን ዲኝነት መስጠት ይቻል ዖንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት ለፏብሉክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስተዲደር ፍ/ቤት መልሰናል ።
በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ውጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ መዛገቡ ተዖግቷል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.