አንድ ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ ስራ በሚለቅበት ጊዚ የሰላሳ ቀናት የማስጠንቀቂያ ጊዚ አለመስጠቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ለሰራተኛው ከሚከፈለው ክፍያ ከሰላሳ ቀናት ክፍያ ያልበለጠ ካሳ ለአሰሪው ሉከፍል የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 31፤አንቀጽ 45
No summary available.
ታህሳስ 06 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- አዱስ ጋዛና ፕላስቲክ ፊብሪካ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነ/ፈጅ ዖገየች ግደይ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ኃይላ የቀረበ የለም … ከተባለ በኋላ ቀረቡ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መቅረብ ምክንያት የሆነው በተጠሪ ክስ አቅራቢነት የተጀመረውን ክርክር ሲመለከት የቆየው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከአሁን ተጠሪ ዔዲ አለብህ በማለት የቀነሱትን ብር 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ ስርዓቱን ተከትለው የተቀነሰ ባለመሆኑ ለተጠሪ እንዱመልሱላቸው የሰጠውን ውሳኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ተመልክቶ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በፋዳራለ ሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ ሉታረምልኝ ይገባል በማለት አመልካች ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ 02 ገጽ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
አቤቱታቸው ከሥር ፍርድ ቤቶች የመዛገብ ግልባጭ ጋር ተገናዛቦ ከተመረመረ በኋላ ተጠሪው ሥራቸውን በራሳቸው ፈቃድ ሲለቁ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 31 መሰረት የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ሳይሰጡ ሥራ በመልቀቃቸው በፈቃዲቸው አንድ ወር ደመወዛ ከከፈለ በኋላ ከላልች ክፍያዎች ጋር ቀላቅለው የአንድ ወር የማስጠንቀቂያ ጊዚ ክፍያን ጭምር በመጠየቃቸው ገንዖቡ እንዱመለስላቸው የተወሰነበት አግባብ ተጠሪ ባለበት ሉጣራ የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ታዛዖው መልስ ያቀረቡ ሲሆን አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ክርክሩ በዘህ አግባብ ተጠናቋል እኛም ጉዲዩ ለሰበር እንዱቀርብ ከተወሰነበት ነጥብ አንፃር ጉዲዩን በመመልከት አመልካች ከተጠሪ የቀነሱት ብር 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ እንዱመልሱለት የተወሰነበት አግባብ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
እንደመረመረነውም ለሰበር አቤቱታው መቅረብ ምክንያት የሆነው ብር 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ የተጠሪ የወር ደመወዛ ሲሆን አመልካች የሚከራከሩት ተጠሪው በራሳቸው ፈቃድ ሥራ ሲለቁ የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ መስጠት ከህግ የመነጨ ግዳታ እያለባቸው ይህንኑ ሳይፈፅሙ ሥራ በመልቀቃቸው የአንድ ወር ደመወዛ ያስከፈሎቸው መሆኑን ጠቅሰው አከፊፈለም ተጠሪው አምነውበት በፈቃዲቸው ገቢ ያደረጉት ስለመሆኑ ይከራከራለ። ተጠሪ በበኩላቸው በአመልካች ፊብሪካ ሲሰሩት የነበረው ሥራ በፈቃዲቸው የለቀቁት የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ከመሆኑም በላይ ገንዖቡን ገቢ ያደረጉት ተገደው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል እንዱፀናላቸው ይከራከራለ። በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክር ወቅት ይህንኑ ገንዖብ ተጠሪ የአንድ ወር የማስጠንቀቂቂያ ጊዚ ሳይሰጡ ሥራ ስለለቀቁ አመልካች ቀንሰው ያስቀሩ ለመሆናቸው አስመዛግበዋል።
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ ሥራ በሚለቅበት ጊዚ ለአሰሪው የሰላሳ ቀናት የማስጠንቀቂያ ጊዚ ላሰጥ እንደሚገባ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 31 ሥር የተደነገገ ሲሆን ሰራተኛው ይህንን ማስጠንቀቂያ ጊዚ ለአለመስጠቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ለሰራተኛው ከሚከፈለው ክፍያ ከሰላሳ ቀናት ክፍያ ያልበለጠ ካሳ ለአሰሪው ሉከፍል እንደሚገባም በአዋጁ አንቀፅ 45 ሥር ተደንግጓል። የዘህ ካሳ አከፊፈል ሰራተኛው ለአሰሪው የማስጠንቀቂያ ጊዚ ያለመስጠቱ ሥልጣን ባለው አካል ተረጋግጦ ካሳው ሲወሰን የሚከፈል መሆኑን መረዲት ተገቢ ነው። ከሥር መዛገቡ መገንዖብ የሚቻለው አመልካች በተጠሪው በኩል በህግ የተቀመጠው የማስጠንቀቂያ ጊዚ እንዲልተሰጣቸው ያላረጋገጡ ከመሆኑም በላይ ገንዖቡን ቀንሰው ያስቀሩት ራሳቸው ለመሆናቸው አምነዋል። አመልካች ከክፍያዎቹ እንዱቀንስባቸው ያቀረቡት ፈቃድ ስለመኖሩም በጽሐፍ በተጠሪው ተፈርሞ የተረጋገጠ ማስረጃ በዘህ ረገድ ሥልጣን ለተሰጣቸው የሥር ፍርድ ቤቶች አልቀረበም። ይልቁን አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያስመዖገቡት ተጠሪው የአንድ ወር ጊዚ ማስጠንቀቂያ ባለመስጠታቸው ብር 2,000/ሁለት ሺህ ብር/ ቀንሰን አስቀርተናል የሚል ነው። አሰሪው ከሰራተኛው ክፍያ ውስጥ የራሱን ጉዲይ ራሱ በመዲኘት ገንዖብ ቀንሶ ለማስቀረት የሚፈቅድ ግልፅ ህግ በላለበት ሁኔታ አመልካች ለተጠሪው የሚከፈል ክፍያን ቀንሰው ማስቀረታቸው ተገቢነት የላለው ከመሆኑም በላይ ተጠሪው ከሚከፈላቸው ገንዖብ ውስጥ አከራካሪ የሆነው ገንዖብ እንዱቀነስ መስማማታቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠሪ በፊርማቸው ያረጋገጡበት ሰነድ ሳይቀርብ ቀንሰው ያስቀሩትን ገንዖብ ለተጠሪው እንዱመልሱ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ ሐምል 15 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠውና በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት የፀናው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔው መፅናቱን አውቆ እንደ ፍርደ እንዱያስፈፅም የዘህ ችልት ውሳኔ ይተላለፍለት ብለናል።
በዘህ ችልት የወጣ ወጭና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.