አንድ ሰራተኛ የሥራ መሪ ሆኖ ሥራውን ሲመራ በፈጸማቸው ማናቸውም ክንውኖች ምክንያት በተወሰደበት እርምጃ ሉያነሳቸው የሚችላቸው የመብት ጥያቄዎች የሥራ መሪው በሂደት ወደ ሰራተኛ የሥራ መደብ የተዙወረ ቢሆንም እንኳን በፍትሐብሓሩ ድንጋጌዎች የሚገዘ ስለመሆናቸው አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3/1፣3/2/ ወጋገን ባንክ እና አቶ አናጋው ገበየሁ
No summary available.
ሕዲር 13 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወጋገን ባንክ -ነ/ፈጅ ቢንያም ትእግስቴ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አናጋው ገበየሁ -ቀረቡ መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የጉዲዩ መነሻ የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪ ላይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው።የተጠሪ ክስ ይዖት በአጭሩ ከጥቅምት 02 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ በተጠሪ ድርጅት ሥራ አሥኪያጅ ሆነው ሲሰሩ የነበረ እና መጋቢት 28 ቀን 2007 ዓ.ም በክሬዱት ቁጥጥር የሥራ ዖርፍ ተመድበው ሲሰሩ የነበረ መሆኑን፤አመልካች የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ ከሥራ ያሰናበታቸው ቢሆንም የጠቀሳቸው ምክንያቶች ተቀባይነት የላላቸው መሆኑን በመጥቀስ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብል በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ሉከፈላቸው የሚገባ ክፍያ እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዖንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች በሰጠው መልስ ተጠሪው የተሰናበቱት የብድር መያዡ የሆነውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ በሚመለከተው አካል ሳይመረመር እና ሳይፈቀድ በመቀየራቸው፤
ከተቀመጠላቸው የብድር ወሰን በላይ በመበደራቸው፤እራሳቸው ተበዲሪ እንዱሁም ባንኩን በመወከል አበዲሪ በመሆን ውል በመዋዋላቸው ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ጥፊታቸው ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብታቸው በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነው፤ሉከፈላቸው የሚገባ ክፍያም የለም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤት ተጠሪው ንብረት አጥፍተዋል በማለት አመልካች የተከራከረ ቢሆንም ተጠሪ አመልካቹ የጠቀሰውን የታግ ቁጥሩ WB/BU/CA/10-02-002 የሆነ ሰርቨር ሞኒተር አልተረከቡም በመሆኑም አመልካች ይህን አስመልክቶ የሰጠው ምክንያት ተቀባይነት የለውም፤በልላ በኩል አመልካች የጠቀሳቸውን ላልች ጥፊቶች በተመለከተ አመልካች እነዘህ ጥፊቶች መፈጸማቸውን ያወቀው መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም ሆኖ ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው ከ41 የሥራ ቀናት በኋላ ነው፤በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/3 መሰረት አሰሪው ጥፊት መፈጸሙን ካወቀበት ጊዚ ጀምሮ በ30 የሥራ ቀናት ውስጥ በመብቱ ካልተጠቀመ ይርጋ የሚያግደው በመሆኑ ስንብቱ ሕገወጥ ነው፤ተጠሪው በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም ድርጊት የፈጸሙት በተለያየ ጊዚ በመሆኑ እና በድርጅቱ የሰው ሀይል መመሪያ ቁጥር 3.2.2.2 መሰረት ሥልጣንን አለአግባብ መጠቀም ለሁለተኛ ጊዚ ሲፈጸም ከሥራ የሚያሰናብት በመሆኑ የተጠሪ የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ መቋረጡ ተገቢ ነው በመሆኑም የማስጠንቀቂያ ጊዚ ክፍያ ሉከፈል አይገባም በማለት አመልካች ለተጠሪው የካሣ ክፍያ ብር 82,572 / ሰማንያ ሁለት ሺህ አምሥት መቶ ሰባ ሁለት ብር /፤የሥራ ስንብት ክፍያ ብር 55,048 / ሀምሳ አምሥት ሺህ አርባ ሥምንት ብር / በድምሩ ብር 137,620 /አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ ሥድስት መቶ ሀያ ብር / እንዱከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አቤቱታው ውድቅ ተደርጓል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡-ተጠሪው የፈጸሟቸው ጥፊቶች የተፈጸሙት የሥራ መሪ በነበሩበት ወቅት ነው፤ይህንኑ በመጥቀስ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት መቃወሚያ ያቀረብን ቢሆንም ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ተጠሪ ከሥራ ሲሰናበት ሲሰራበት የነበረው የስራ መደብ ነው በማለት መቃወሚያችን ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም፤የተጠሪን ጥፊት በተመለከተ የኢንስፔክሽን ሥራ የተሰራው መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም ቢሆንም ጉዲዩ ወደ ዱስፕሉን ኮሚቴ ተመርቶ የዱስፕሉን ኮሚቴው የውሳኔ ሐሳብ ያቀረበው ሚያዛያ 21 ቀን 2007 ዓ.ም በመሆኑ ተጠሪን የማሰናበቻ ጊዚ ሉቆጠር የሚገባው ከዘህ ጊዚ ጀምሮ ነው።የበታች ፍ/ቤቶች ጉዲዩን በዘህ አግባብ ተመልክተው መወሰን ሲገባቸው ይህን በመተላለፍ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ችልት መታየት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ለተጠሪው ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ መልሳቸውን በጽሐፍ ሰጥተዋል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ ለስራ ውለ መቋረጥ መንስኤ የሆነው ምክንያት የተፈጸመው ተጠሪ የሥራ መሪ በነበርኩበት ጊዚ ቢሆንም መፍትሓ ሉሰጠው የሚገባው ጉዲይ ተጠሪ ጥፊቱን የፈጸምኩ መሆን አለመሆኑ እና ጥፊቶቹ ከሥራ ለማሰናበት በቂ ናቸው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው፤አመልካቹ ተጠሪን ከሥራ የማሰናበት መብቱም በይርጋ ቀሪ የሆነ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው የሚል ነው።አመልካቹም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።ይህ ችልትም ወደዋናው ጉዲይ ከመገባቱ በፉት ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የተጠሪን አቤቱታ አይቶ የማስተናገድ ሥልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ ስላገኘነው ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካች ለስንብቱ ምክንያት ያደረጋቸውን በተጠሪው ተፈጽመዋል የተባለት ጥፊቶች የተፈጸሙት ተጠሪ የሥራ መሪ በነበሩበት ጊዚ መሆኑን ተጠሪ አልካደም፤ተጠሪው ለዘህ ችልት በሰጡት መልስም ይህንኑ አረጋግጠዋል። አከራካሪው ጉዲይ ለተጠሪ ስንብት ምክንያት የሆኑት ጥፊቶች ተጠሪ የሥራ መሪ በነበሩበት ወቅት የተፈጸሙ ሆኖ የተጠሪ የሥራ ውል ሲቋረጥ ተጠሪ በሰራተኛ የሥራ መደብ ላይ የነበሩ መሆናቸው ጉዲዩን በሥራ ክርክር ችልት እንዱታይ ያደርገዋል? ወይስ አያደርገውም? የሚለው ነው የአዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚነት በአሰሪ እና ሰራተኛ መካከል በሚደረግ በቅጥር ላይ በተመሰረተ የሥራ ግንኙነት ላይ መሆኑን ከአዋጁ አንቀጽ 3/1 ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል።
የአዋጁ አንቀጽ 3/2/ሐ በቅጥር ላይ በተመሰረተ ግንኙነትም ቢሆን አዋጁ በሥራ መሪ ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን ይደነግጋል። ከድንጋጌው ይዖት እና መንፈስ መገንዖብ የሚቻለው የሥራ መሪው የሥራ መሪ ሆኖ ሥራውን ሲመራ በፈጸማቸው ማናቸውም ክንውኖች ምክንያት በተወሰደበት እርምጃ ሉያነሳቸው የሚችላቸው የመብት ጥያቄዎች የሥራ መሪው በሂደት ወደ ሰራተኛ የሥራ መደብ የተዙወረ ቢሆንም አዋጁ ተፈጻሚ ላሆን እንደማይችል ነው።ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዲዩን አይቶ ውሳኔ ለመስጠት የቻለው ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት በሰራተኛ የሥራ መደብ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው በማለት እንደሆነ ግራቀኙ ካቀረቡት ክርክር መገንዖብ ችለናል።ለተጠሪ የሥራ ስንብት ምክንያት የሆነው ጥፊት የተፈጸመው ተጠሪ የሥራ መሪ በነበሩበት ጊዚ በመሆኑ ተጠሪ የሥራ መሪ በነበሩበት ጊዚ በፈጸሟቸው ጥፊቶች ምክንያት የተወሰደባቸው እርምጃ ተገቢ አይደለም በማለት የሚያቀርቡት ማንኛውም የመብት ጥያቄ ሉስተናገድ የሚችለው በፍትሐብሕር ሕጉ ድንጋጌዎች እንጂ በአሰሪ እና ሰራተኛ ሕጉ መሰረት አይደለም። በአጠቃላይ ጉዲዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን የሚያስችል የሥረ ነገር ሥልጣን ሳይኖረው ውሳኔ መስጠቱ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ይህንኑ ሳያርም ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ173531 ሐምል 14 ቀን 2008 ዓ.ም በትዔዙዛ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
ለተጠሪው የሥራ ስንብት ምክንያት የሆኑት ጥፊቶች የተፈጸሙት ተጠሪው የሥራ መሪ በነበሩበት ጊዚ በመሆኑ የአሰሪ እና ሰራተኛ ሕጉን መሰረት በማድረግ በሥራ ክርክር ችልት ክስ ለማቅረብ አይችለም፤ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የስራ ክርክር ችልትም የተጠሪን አቤቱታ ተቀብል የማየት የሥረነገር ሥልጣን የለውም ብለናል።
ተጠሪው ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ክስ የማቅረብ መብታቸውን ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.