በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዞ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት /ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በህብረት የያዙት እና ያልተከፊፈለት በሆነ ጊዜ ከተከፊዮቹ አንደ ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዲዲሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለእዲው እንደቀረበ ተቆጥሮ የተቀዲሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 443፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 126/1/፣ 1386-1409
No summary available.
ሕዲር 22 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
ጉዲዩ የፍርድ አፈጻጸምን የሚመለከት ክርክር ሲሆን አመልካቾቹ አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡትም ለፍርድ አፈጻጸሙ ምክንያት የሆነው መኖሪያ ቤት ክፍፍል መፈጸም የሚገባው በሀራጅ ተሽጦ ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ በፍርድ በማጽናት በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ፡- የ1ኛ አመልካች ባለቤት የነበሩት አቶ ሞገስ ጌታሁን በሞት መለየታቸውን ተከትል በተነሳው የውርስ እና የጋራ ንብረት ክፍያ ክርክር በዋግኽምራ ዞን በሰቆጣ ከተማ በቀበላ 02 ክልል በሟች ስም ተመዝግቦ ይታወቅ ከነበረው ቤት ውስጥ ግማሹ የአሁኗ 1ኛ አመልካች ድርሻ ሆኖ ቀሪው ግማሽ ደግሞ ከሟች ለሚወለደት ሰባት ልጆች እንዱከፊፈል ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን፣ ይህንን የስረ ነገር ፍርድ ለማስፈጸም 1ኛ አመልካች በፍርድ ባለመብትነት ተሰይመው ባደረጉት እንቅስቃሴ በከተማው አስተዲደር በቀረበው የዋጋ ግምት መሰረት የቀሪዎቹን ወራሾች ድርሻ 1ኛ አመልካች ከፍለው እና ከወራሾቹ መካከል የአሁኑ ተጠሪ ቤቱ በጨረታ መሸጥ ከሚገባው በቀር ግምቱን ለመቀበል አልስማማም በማለታቸው ድርሻቸው በሞዳል 85 እንዱያዝ ተደርጎ የቤቱ ስመሀብት አፈጻጸሙን በያዘው የሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደ 1ኛ አመልካች የተዛወረ መሆኑን፣ 1ኛ ተጠሪ በዚህ ትዕዛዝ ባለመስማማት በየደረጃው ያቀረቡት ክርክር በመጨረሻ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ፍርድ ቤቶችን የአፈጻጸም ትዕዛዝ ሽሮ ቤቱ ከተቻለ በዓይነት፣ ካልተቻለ ግራ ቀኙ እርስ በእርስ በሚያደርጉት ጨረታ፣ ይህም ካልተቻለ ለ3ኛ ወገን በጨረታ እንዱሸጥ በመዝገብ ቁጥር 03-08523 በ26/04/2007 ዓ.ም. ውሳኔ የሰጠ መሆኑን፣ የወረዲው ፍርድ ቤትም በዚሁ አግባብ ቤቱ በጨረታ እንዱሸጥ ለማስቻል የጨረታ ማስታወቂያ እንዱወጣ ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑን፣በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት 1ኛ አመልካች ያቀረቡት ይግባኝ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ02/10/2007 ዓ.ም.
በትዕዛዝ የተዘጋ እና አቤቱታቸውም በክልለ ሰበር ችልት በመዝገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም. በተሰጠ በፍርድ ተቀባይነት ያጣ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካቾች ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ አመልካቾቹ በአከራካሪው ቤት ላይ ያላቸው የጋራ ድርሻ በጣም ብዙ ሆኖ እያለ እና የተጠሪው ድርሻ ግን በድርሻቸው ብቻ የታጠረ ሆኖ እያለ፣ ይህንኑ ከግምት በማስገባትም 1ኛ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ በቀር ለቀሪው እያንዲንደ ወራሽ ግምቱን ከፍለው ቤቱን በስማቸው አዛውረው እያለ የአሁኑ ተጠሪ ግምቱን ለመቀበል ባለመስማማታቸው ብቻ ቤቱ በሀራጅ እንዱሸጥ የመታዘዙን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
በስረ ነገሩ ፍርድ መሰረት ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ በቤቱ ላይ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ እንዱወጣ በወረዲው ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
አመልካቾቹ ከአከራካሪው ቤት ላይ አለን የሚለትን አብላጫ ድርሻ መሰረት በማድረግ ቤቱን ማስቀረት የሚችለበት የሕግ አግባብ አለ ወይስ የለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ 1ኛ አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ከአከራካሪው ቤት በሚስትነታቸው ያላቸው ድርሻ ግማሽ ሆኖ እያለ እና የሰባት ወራሾች ድርሻ ከሆነው የቤቱ አጋማሽ ውስጥ ደግሞ 1ኛ አመልካች ሞግዚት የሆኗቸው 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች እያንዲንዲቸው አንድ ሰባተኛ ድርሻ ያላቸው ሆኖ እያለ እንዱሁም ከተጠሪው ውጪ ላለት ቀሪ ወራሾች 1ኛ አመልካች ድርሻቸውን ከፍለው እያለ ከቤቱ አጋማሽ ውስጥ አንድ ሰባተኛ ድርሻ ብቻ ላላቸው የአሁኑ ተጠሪ ጥቅም ብቻ ሲባል ወደ 1ኛ አመልካች ስም ተዛውሮ የነበረው ቤት በሀራጅ እንዱሸጥ የተሰጠው ትዕዛዝ ፍትሐዊ አይደለም የሚል መሆኑን የአቤቱታቸው ይዘት ያመለክታል። ይሁን እንጂ የክልለ ሰበር ችልት የአፈጻጸም ሂደቱን አስመልክቶ ቀደም ሲል ቤቱ ከተቻለ በዓይነት፣ ካልተቻለ ግራ ቀኙ በመካከላቸው በሚያደርጉት ጨረታ፣ ይህም ካልተቻለ ደግሞ ለ3ኛ ወገን በጨረታ እንዱሸጥ በመዝገብ ቁጥር 03-08523 በ26/04/2007 ዓ.ም. ውሳኔ የሰጠው 1ኛ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ ውጪ ላለት ላልች ወራሾች ድርሻቸውን ሰጥተው ቤቱን በስማቸው ካዛወሩ በኋላ በመሆኑ የተጠሪው ድርሻ ከቤቱ አጋማሽ ውስጥ አንድ ሰባተኛ ብቻ ሆኖ እያለ ቤቱ በሐራጅ ይሸጥ መባለ ተገቢ አይደለም የሚለ ከሆነ የሰበር አቤቱታቸውን በወቅቱ በስርዓቱ መሰረት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርበው ተገቢውን ውሳኔ ማሰጠት ይገባቸው የነበረ ከመሆኑ በቀር በክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረት ጉዲዩ ወደ ወረዲው ፍርድ ቤት ተመልሶ የአፈጻጸም ሂደቱ ከቀጠለ በኃላ ወደኋላ ተመልሰው ቤቱ በሀራጅ እንዱሸጥ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ ፍትሀዊ አይደለም በማለት አሁን እያቀረቡ ያለት ክርክር ስነ ስርዓታዊ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም አፈጻጸሙን የያዘው የሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በክልለ ሰበር ችልት በመዝገብ ቁጥር 03-08523 በ26/04/2007 ዓ.ም.
የሰጠውን ውሳኔ ተከትል በስረ ነገሩ ፍርድ መሰረት ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ በቤቱ ላይ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ እንዱወጣ የሰጠው እና በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ከአከራካሪው ቤት 1ኛ አመልካች ግማሽ ድርሻ፣2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ደግሞ ከቤቱ አጋማሽ ውስጥ እያንዲንዲቸው አንድ ሰባተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑ አላከራከረም። ይህም 1ኛ አመልካችም ሆኑ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ከቀሪዎቹ ወራሾች ጋር የአከራካሪው ቤት የጋራ ባለሀብቶች መሆናቸውን መገንዘብ የሚያስችል ነው።በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዞ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በሕብረት የያዙት እና ያልተከፊፈለት በሆነ ጊዜ ከተካፊዮቹ አንደ ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዲዲሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለዕዲው እንደቀረበ ተቆጥሮ የተቀዲሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 443 ይደነግጋል። ከስነ ስርዓት ሕጉ በተጨማሪም የጋራ ባለሀብቶች የሆኑ ሰዎች ያልተከፊፈለውን የጋራ ንብረት ከማንኛውም ሶስተኛ ወገን በፉት ቀዲሚ ሆነው በግዥ የማስቀረት ሕጋዊ መብት ያላቸው ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1261 (1) የተደነገገ ሲሆን ይህ መብት ተግባራዊ የሚደረግበት ስርዓትም በዚሁ ሕግ ከቁጥር 1386 እስከ 1409 ተደንግጎ ይገኛል። በመሆኑም አመልካቾቹ አከራካሪውን ቤት ለማስቀረት የሚችለት በቤቱ ላይ በሚከናወነው ጨረታ መሰረት ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፉ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ መሰረት በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች በተጠበቀላቸው የቀዲሚነት መብት በመገልገል ነው። በቀጣይ የአፈጻጸሙ ሂደት አመልካቾቹ ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፉ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ መሰረት በማድረግ የቀዲሚነት መብታቸውን ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ በሰበር አቤቱታቸው እንደሚከራከሩት ከአሁኑ ተጠሪ ውጪ ላለት ላልች ወራሾች ድርሻቸውን ከፍለው በቤቱ ላይ ያላቸውን ድርሻ ከፍ ያደረጉ መሆን አለመሆኑ፣ ጨረታውን ካሸነፈበት የዋጋ መጠን ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ተቀንሶ ገቢ ማድረግ የሚገባቸው የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ እና መሰል የአፈጻጸም ጉዲዮች ፍርደን በሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት ተስተናግደው ተገቢው ትዕዛዝ የሚሰጥባቸው ይሆናል።
ሲጠቃለል አመልካቾቹ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 443 እንዱሁም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1261 (1)፣ 1386 እስከ 1409 በተደነገገው የቀዲሚነት መብታቸው የመገልገል መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ አከራካሪው ቤት በሀራጅ እንዱሸጥ በወረዲው ፍርድ ቤት የተሰጠው እና በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በዋግኽምራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ 3 በ02/10/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ በፍርድ በማጽናት በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የስረ ነገሩ ፍርድ ያረፈበት ቤት በሀራጅ ይሸጥ መባለ በአግባቡ ነው በማለት ወስነናል።
አከራካሪው ቤት በሀራጅ በሚሸጥበት ጊዜ አመልካቾቹ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 443፣ እንዱሁም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1261 (1)፣ 1386 እስከ 1409 በተደነገገው የቀዲሚነት መብት የመገልገል መብት አላቸው በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት፣ ለዋግኽምራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ይላክ።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ06/07/2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.