አንድ ጠበቃ ሕግን የማስከበር ፣ፍትህን የማስገኘትና ለፍትህ አስተዲደሩ የማገዝ ኃላፉነቱን በመተው ተቃራኒ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ መሆኑ ከተረጋገጠ የጥብቅና ፍቃደ ሉሰረዝ የሚችል ስለመሆኑ የአማራ ክልል የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ ምዝገባና የጠበቆች ሥነምግባር ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁ. 75/1994
No summary available.
ህዲር 20 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ አትሁነኝ አልማው ቀረቡ ተጠሪ፡- የአማራ ብሓራዊ ክልል ፍትህ ቢሮ ዐ/ህግ አባይነህ ከበደ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በክልለ የተሰጠ የጥብቅና ፈቃድ እንዱሰረዝ የተሰጠን የዱሲፕሉን ውሳኔ ህጋዊነት የሚመለከት ነው። የድስፒሉን ክሱ የቀረበው አቶ ጓዙሁን አዘዘው የተባለ የድስፒሉን አቤቱታ አቅራቢ ነው። አቤቱታ አቅርበው በባህር ዲር ዙርያ ወረዲ ይነሳ 3ቱ ቀበላ በሟች አቶ ወንዳ ተገኘ የገጠር መሬት ይዞታ ምክንያት ከአቶ በሪሁን ወንዳ ጋር እየተከራከሩኩ እገኛለሁ። አቶ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙርያ ወረዲ የይነሳ 3ቱ ቀበላም ሆነ በኢትዮጲያ ውስጥ ኗሪ አይደለም። አቶ በሪሁን ወንዳ ላለፈት ሰላሳ አንድ አመታት በእስራኤል አገር የሚኖር ሰው ነው። ሆኖም የዱስፒሉን ተከሳሹ ከቀበላው ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር በአገር ውስጥ ከላለ ሰው በይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ በማስመሰል የሀሰት መታወቂያ በማውጣት ከጠበቆች ስነ ምግባር ውጭ ተገቢነት የላለው ስራ በመምራትና ማስረጃ በማቅረብ ፍትህ የሚያጓድል ስራ እያሰራ ስለሆነ ፍትህ ቢሮ ክትትል አድርጎ የእርምት እርምጃ እንዱወስድበት በማለት በጽሁፍ አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች የአቶ በሪሁን ወንዳ ጠበቃ ሆነው በተለያዩ ፍ/ቤቶች የተለያየ ክርክር እያቀረበ መሆኑን ገልፆ፣ የጥብቅና አገልግልት በደንበኛዋ እየሰጠሁ ያለሁት በክልለ ፍትህ ቢሮ የሰነድችና ጠበቆች ማረጋገጫና ምዝገባዎች የስራ ሂደት ተገኝተው ደንበኛዬ ታህሳስ 22 ቀን 2005 ዓ/ም በህጋዊ መንገድ በሰጡኝ የውክልና ሰነድ መሰረት ነው። ለአቶ በሪሁን ወንዳ የቀበላ መታወቂያ አላወጣሁም የውክልና ሰነድም በህገ ወጥ መንገድ አላወጣሁም። ደንበኛዬ በእስራኤል አገር የሚኖር ቢሆንም ትውልዲቸው ባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የይነሳ 3ቱ ቀበላ ነው። ለዱስፒሉን ምክንያት የሆነው ጉዲይ በወረዲ ፍርድ ቤትና በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። ፍትህ ቢሮ ህጋዊነቱን አረጋግጦ በሰጠኝ የውክልና ማስረጃ ምክንያት ልከስስ አይገባኝም በማለት መልስ የሰጠ መሆኑን ተረድተናል።
የክልለ ፍትህ ቢሮ የጠበቆች ዱስፒሉን ጉባኤ በአመልካች ላይ የቀረበው የዱስፒሉን አቤቱታ እውነትነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚመለከታቸውን የባህር ዲር ወረዲ አስተዲደር አካላትና የይነሳ 3ቱ ቀበላ አስተዲደር እንደዚሁም የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዲይ መምሪያ አግባብነት ያለው ማስረጃ እንዱሰጡት ጠይቋል። ከሚመለከታቸው የአስተዲደሩ አካላት ጋር በመሆን ተገቢውን ማጣሪያ ያደረገ መሆኑንና በማጣራቱ ሂደት በ2005 ዓ/ም አቶ በሪሁን ወንዳ ወደ አገር ውስጥ ስለመግባቱም ሆነ ከአገር ስለመውጣቱ መረጃ ያላገኘ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዲይ መምሪያ በጽሁፈ የገለጹለት መሆኑን አቶ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የይነሳ 3ቱ ቀበላ ነዋሪ አለመሆኑን የቀበላው አስተዲደር በፅሁፍ የገለጽ መሆኑን፣ አቶ በሪሁን ወንዳ በአንድ ወቅት ከእስራኤል አገር በመጣበት ጌዜ የይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የቀበላ መታወቂያ እንዱሰጠው ጠይቆ የነበረ መሆኑና የቀበላው ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ማይሰጠው መሆኑን የባይነሳ ሶስቱ ቀበላ አስተዲደር ተነገረው መሆኑ፣አቶ በሪሁን ወንዳ የባይነሳ ሶስቱ ቀበላ ነዋሪ መሆኑን ሚያረጋግጥ መታወቂያ ያለው መሆኑን በመግለፅ ለባህርዲር ዙሪያ ወረዲ የመሬት አስተዲደርና የአካባቢው ጽ/ቤት መታወቂያ ይዞ የአቀረበው አመልካች መሆኑን እንዲረጋገጠ በመግለጽና አመልካች ከዚህ በፉት የጥብቅና ፈቃድ ለማውጣት የሀሰት ማስረጃ /የስራ ልምድ ተጠቅሟል የሚል ክስ ቀርቦበትና ይህም ተረጋግጦ በቢሮ ኃላፉ ውሳኔ ሳይቀጣ የታለፈ መሆኑን ገልፆ የአመልካች የሀሰት መታወቂያ በመጠቀም የተሟጋችነት ውክልና ማስረጃ የወሰደና አርሶ አደሮችን በመከላከል በከፍተኛ እንግልት በመዲረግ ከባድ የድስፒሉን ጥፊት ፈጽሟል በማለት የአመልካች የጥብቅና ፍቃድ እንዱሰረዙና ስሙ ከጠበቆች መዝገብ እንዱሰረዝ የሚል የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ የድስፒሉን ጉባኤውን የውሳኔ ሀሳብ የቢሮ ኃላፉ ተቀብል አጽድቆታል። ውሳኔ በክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይገባኝ ሰሚ ችልት ሰበር ችልት ጸንቷል።
አመልካች ሰኔ 18 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በ2005 ዓ/ም አቶ በሪሁን ወንዳ ወደ አገር ውስጥ መጥቶ የነበረ መሆኑን አቤቱታ አቅርበው ክድ ያቀረበው ክርክር የለም።
የኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዲይ መምሪያ አመልካች አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 አ/ም ወደ አገር ውስጥ የገባም ሆነ የወጣ ስለመሆኑ መረጃ አላገኘንም ከማለት ውጭ ወደ አገር ውስጥ ያልገባ ስለመሆኑ የሰጠው ማስረጃ የለም። ከዚህ አንፃር አመልካች በዱስፒሉን የተከሰሱበትን ጥፊት ስለመፈጸሜ በበቂ ሁኔታ ሳይረጋገጥብኝ በከባድ የድስፒሉን ጥፊት ጥፊተኛ መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የዱስፒሉን ጉባኤው አመልካች በድስፒሉን ባልተከሰስኩበትና ያልተከራከርኩበትን ጉዲይ ማለትም ከዚህ በፉት ከጥብቅና ፈቃድ አወጣጥ ላይ የሀሰት ማስረጃ ተጠቅሟል ተብዬ የተከሰሰኩበትንና በቢሮ ኃላፉው ውሳኔ ያለምንም ቅጣት በነፃ የተሰናበትኩበትን ጉዲይ በመጥቀስ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ የሰጠብኝ በመሆኑ ውሳኔው የመከራከር መብቴን ያጣበበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
ስለሆነም አመልካች የጥብቅና ፈቃዳን እንዱሰርዝ የተሰጠው ውሳኔ ከህግ አግባብ ውጭ የተሰጠና የድስፒሉን ጥፊት ስለመፈጸሜ በበቂ ሁኔታ ሳይረጋገጥብኝ የተሰጠ ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
አመልካች ደንበኛውን በ2005 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ የገባ መሆኑን የማያስረዲ ማስረጃ እንዱያቀርብ በጉባኤው ብቻ ሳይሆን በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እድል ተሰጥቶት አላቀረበም። አመልካች የጥብቅና ፈቃድ ሲያወጣ ፈጽሟል ተብል ተከሶበት የነበረው የድስፒሉን ጥፊትና ጉባኤው አጣርቶ የደረሰበት እውነት በጉባኤው ውሳኔ ከመገለጹ ውጭ ውሳኔው የጥፊተኝነትንም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ለመወሰን ጥቅም ላይ አልዋለም ስለሆነም አመልካች ከባድ የድስፒሉን ጥፊት መፈጸሙ ተረጋግጦ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ስለሆነ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በግራ ቀኙ የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸውን እኛም የክልለ ፍትህ ቢሮ አመልካች የጥብቅና ፈቃድ እንዱሰረዝ በማለት የሰጠው ውሳኔ በህግ አግባብ የተሰጠ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የተሟጋችነት ውክልና ወስድ የእርሻ መሬት ይዞታን በተመለከተ የተለያየ ክርክር የሚከራከርለትና አመልካች የጥብቅና አገልግልት የሚሰጠው አቶ በሪሁን ወንዳ በባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ ባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ እንዲልሆነ አቶ በሪሁን ወንዳ ከሰላሳ አንድ ዓመት በላይ በቋሚነት የሚኖረው በእስራኤል አገር እንደሆነ ተረጋግጧል። በእስራኤል አገር የሚኖረው አቶ በሪሁን ወንዳ መተዲደሪያው የእርሻ ስራ ሳይሆንና የቀበላው ኗሪ ባልሆነበት ሁኔታ አቤቱታ አቅራቢው ከሰላሳ አመት በላይ በይዞታው አድርጎ ሲጠቀምበት በኖረው የእርሻ መሬት ባለይዞታ የመሆኑን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አቤቱታ አቅርባው ሳያውቅ ያወጣ መሆኑን ገልጾ በሀሰት ለአቶ በሪሁን ወንዳ የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዱሰረዝለት አቤቱታ አቅርበው ለባህር ዲር ዙሪያ የመሬት አስተዲደርና አካባቢ ጽ/ቤት ማመልከቱንና አቶ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የባይነሳ ሶስቱ ቀበላ ኗሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ የቀበላ መታወቂያ እንዱያቀርብ ሲጠይቅ አመልካች አቶ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ ለወረዲው መሬት አስተዲደርና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ይዞ በመቅረብ የሰጠ መሆኑ የወረዲው የመሬት አስተዲደርና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በሰጠው ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን የድስፒሉን ጉባኤው ከሰጠው ውሳኔ ተረድተናል።
ከላይ በዝርዝር የተገለጸው ፍሬ ጉዲይ አመልካች ደንበኛው አቶ በሪሁን ወንዳ በእስራኤል አገር የሚኖርና የባህር ዲር ዙሪያ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ እንዲልሆነ እያወቀ አቶ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ እንደሆነ የሚገልጸውን ሀሰተኛ መታወቂያ ስለ እርሻ መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ለሚሰጠውና ውሳኔ ለሚሰጠው ክፍል ወስደው ያስረከቡ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አቤቱታ አቅርበው አመልካች ከቀበላው ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር ሀሰተኛ መታወቂያ በበሪሁን ወንዳ ስም በማውጣት ሀሰተኛ ማስረጃ በመጠቀም ከጠበቆች ስነ ምግባር ውጭ እየተከራከረው መሆኑን ገልፆ እውነታው እንዱጣራለት ስለጠየቀ ጉባኤው አመልካች ታህሳስ 22 ቀን 2005 ዓ/ም ከአቶ በሪሁን ወንዳ ተሰጥቶኛል የሚለው የተሟጋችነት የውክልና ሰነድ ትክክለኛነት የማጣራት ስራ የስራ መሆኑን ተረድተናል። በተደረገው የማጣራት ስራ በ2005 ዓ/ም አቶ በሪሁን ወንዳ አመልካች ወደ አገር ውስጥ የገባም ሆነ የወጣ ስለመሆኑ መረጃ ያልተገኘ መሆኑ የኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዲይ መምሪያ በጽሁፍ አረጋግጧል። አመልካች ይህ ማስረጃ ደንበኛው አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ያልገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ አይደለም በማለት የሚከራከር መሆኑን አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት ካቀረበው የሰበር ክርክርና የሰበር ማጣሪያ ችልት ከያዘው ጭብጥ ተረድተናል።
የአመልካች ደንበኛ አቶ በሪሁን ወንዳ ቋሚ የመኖሪያ ቦታው እስራኤል አገር መሆኑን አመልካች ክድ ያልተከራከረ ከመሆኑም በላይ አቶ በሪሁን ወንዳ እስራኤል አገር ኗሪ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል። አመልካች የዱስፒሉን አቤቱታ አቅርበው አቶ በሪሁ ወንዳ በ2005 ዓ/ም ወደ አገር ቤት የመጣ መሆኑን ክድ አልተከራከረም የሚል መከራከሪያ ከማቅረቡ ውጭ ደንበኛው በ2005 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ የገባ ወይም ከአገር የወጣ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ለጉባኤውና ለይ/ባይ ሰሚ ችልት ያላቀረበ መሆኑን የክልለ ፍትህ ቢሮ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡትን ውሳኔ በማገናዘብ ተረድተናል። በመሰረቱ አመልካች የዱስፒሉን አቤቱታ አቅራቢው አቶ ጓድይሁን አዘዘው የአመልካች ደንበኛ በ2005 ዓ/ም ወደ አገር ቤት የመጣ መሆኑን ባቀረበው አቤቱታ ላይ እንዲልካደ በመግለጽ ያቀረበው ክርክር አቤቱታ አቅርበው የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም ጽፍ ያቀረበውን ፍሬ ጉዲይና የገለጸውን እምነት የሚሳይ ክርክር ሆኖ አላገኘነውም።
የዱስፒሉን አቤቱታ አቅራቢው አቶ በሪሁን ወንዳ ወደ አገር ቤት የመጣ ስለመሆኑ በአቤቱታው አልገለጸም። አቤቱታ አቅራቢው አቶ በሪሁን ወንዳ በእስራኤል አገር እንደሚኖርና አንድ ወቅት ወደ አገር ቤት መጥቶ እንደነበር ወደ አገር ቤት በመጣበትም ጊዜ ከህግ ውጭ እሱ በማያውቀው ሁኔታ ከሰላሳ አምስት ዓመት በላይ በእጅ አድርጎ የሚጠቀምበትን የእርሻ መሬት የአቶ በሪሁን ወንዳ መሆኑን የማያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያስመጣበት መሆኑን የይዞታ ደብተሩ እንዱሰረዝለት ለሚመለከተው አካል ሲያመለክት አመልካች በእስራኤል አገር የሚኖረው በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ መሆኑን የሚገለጽ ሀሰተኛ መታወቂያ በማስወጣትና ሀሰተኛ ማስረጃ በመጠቀም እየተከራከረው በመሆኑን በዱስፒሉን ጉዲይ እንዱታይ የሚገልጽ ነው። አቶ በሪሁን ወንዳ አመልካች ሀሰተኛ መታወቂያና ሀሰተኛ የተሟጋችነት ውክልና አምጥቷል ከተባለበት ጊዜ በፉት በአንድ ወቅት ወደ አገር ቤት መጥቶ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ነዋሪ መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ እንዱሰጠው የቀበላውን አስተዲዲሪ ጠይቆ የነበረ መሆኑንና የቀበላው አስተዲደርም መታወቂያው አይሰጥህም የሚል ምላሽ እንደሰጠው የዱስፒሉን ጉባኤው ከቀበላው አስተዲደር ጋር ባደረገው ማጣራት እንዲረጋገጠ በውሣኔው በግልፅ አስፍሯል። አቤቱታ አቅራቢው አቶ በሪሁን ወንዳ በአንድ ወቅት ወደ አገር ቤት መጥቶ የነበረ መሆኑን ባቀረበው አቤቱታ መግለፁ አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 ዓ.ም ወደ አገር ቤት የመጣ መሆኑን በአቤቱታው ያመነና የገለፀ መሆኑን የሚያረጋግጥ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ አቤቱታ አቅራቢው አቶ በሪሁን ወንዳ ለዱስፒሉን ክስ መነሻ የሆኑት ድርጊቶች ከመፈፀማቸው በፉት ወደ አገር ቤት መጥቶ የነበረ መሆኑ በአቤቱታው ላይ የገለፀው ፍሬ ጉዲይ ዕውነትነት ያለው መሆኑን በቀበላው አስተዲደርም የተረጋገጠ መሆኑ ሲታይ አቤቱታ አቅራቢው በአቤቱታው ላይ ትክክለኛውን ፍሬ ጉዲይ ያሰፈረ መሆኑን ከሚያረጋግጥ ውጭ አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 ዓ.ም ወደ አገር ቤት የመጣ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ መከራከሪያና ሰነድ አይደለም።
የዱስፒሉን አቤቱታ አቅራቢው የዱስፒሉን ክስ ዋና ይዘት አመልካች በባህር ዲር ዙሪያ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ነዋሪ ላልሆነው አቶ በሪሁን ወንዳ የቀበላው ነዋሪ መሆኑን የሚያረግጥ መታወቂያ በማውጣት ሀሰተኛ የውክልና ሰነድ በመጠቀም እየተሟገተኝ ነው የሚል ነው።
አመልካች ከአቶ በሪሁን ወንዳ የተሟጋችነት የውክልና ሥልጣን ተሰጥቶኛል የሚለው ታህሣሥ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ነው። ይህ ከሆነ አመልካች የተሟጋችነት ውክልና ሰጥቶኛል የሚለው በሪሁን ወንዳ በ2005 ዓ.ም ወደ አገር ውስጥ የገባ መሆኑን በጭብጥነት ይዞ ጉባኤው ማጣራቱ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 ዓ.ም ወደ አገር ውስጥ የገባና ከአገር የወጣ መሆኑ አከራካሪ ጭብጥ ከሆነ ስለ ጉዲዩ መረጃ የመያዝና መረጃ የመስጠት ሥልጣን ያለው አካል መጠየቁ የግድ አስፈላጊ ነው።
አንድ ሰው ወደ አገር ውስጥ ስለመግባቱና ከአገር ስለመውጣቱ ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርገውና ወደ አገር ውስጥ የሚገባም ሆነ ከአገር የሚወጣ ሰው ማሟላት የሚገባውን ሥርዓት ያሟላና የጉዞ ሰነድችን የያዘ መሆኑን የማረጋገጥ ሥልጣን ያለው የደህንነት የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዲይ ባለሥልጣን መሆኑን በኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር 354/95 ተደንግጓል። በአዋጅ ቁጥር 354/95 አንቀፅ 16 ባለሥልጣኑ የኢሚግሬሽን ኦፉሰሮችን በመመደብ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትንም ሆነ ከአገር የሚወጡ ሰዎች መንገደኞች የሚከታተልና መረጃ የሚይዝ ስለመሆኑ በውጭ አገር የሚኖር ሰው ወደ አገር ውስጥ ሲገባም ሆነ ሲወጣ አስፈላጊ የጉዞ ሰነድች የያዘ መሆኑንና ከአገር ሲወጣ ሉይዘው የሚገባውን ማናቸውንም መረጃ እንደሚይዝ ከድንጋጌው ይዘት ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ከውጭ አገር ወደ አገር ቤት አንድ ሰው ተጓጉዞ ሲመጣና ሲወጣ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጡ መንገደኞችን ያሣፈረ ማናቸውም ማጓጓዣ የመንገደኖችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚመለከተው የኢሚግሬሽን ኦፉሰር የመስጠት ግዳታ ያለበት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 354/95 አንቀጽ 17 ተደንግጓል።
ከዚህ አንፃር ሲታይ የአመልካች ደንበኛ አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 አ.ም ወደ አገር ውስጥ ስለመግባቱም ሆነ ስለመውጣቱ የተገኘ መረጃ የላለ መሆኑን ገልፆ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዲይ መምሪያ ለዱስፒሉን ጉባኤው የሰጠው መግለጫ በአዋጅ ቁጥር 354/95 በሚደነግገው መሰረት የአመልካች ደንበኛ በ2005 ዓ.ም ወደ አገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ የገባ ስለመሆኑ ማስረጃ የላለ መሆኑን የሚሳይ ነው። የአመልካች ደንበኛ በአዋጅ የተደነገጉትን መስፈርቶች በማሟላት በ2005 ዓ.ም ወደ አገር ውስጥ የገባና ከአገር የወጣ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለመኖሩ በራሱ የአመልካች ደንበኛ ከአገር የወጣ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለመኖሩ በራሱ የአመልካች ደንበኛ በ2005 ዓ.ም በህጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ አልገባም ብል ለመደምደም የሚያስችል ማስረጃ ነው። ይህ ከሆነ አመልካች ደንበኛው በ2005 ዓ.ም በህጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገባና ከአገር የወጣ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን በማቅረብ ወይም አመልካች ደንበኛው ህጋዊ መስፈርቶችን ሣያሟላ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገባና ከአገር የወጣ መሆኑን የሚሳይ ማስረጃ በማቅረብ ያቀረበበትን ማስረጃ ካላስተባበለ አቶ በሪሁን ወንዳ በ2005 ዓ.ም አገር ውስጥ አልነበረም። አመልካች ታህሣሥ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ከፍትህ ቢሮ የወሰደው የተሟጋችነት የውክልና ሰነድ አመልካች አቶ በሪሁን ወንዳ የባህርዲር ከተማ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ ስለመሆኑ የሚገልፀውን ሀሰተኛ መታወቂያ በመጠቀምና ላላውን ሰው በሪሁን ወንዳ አስመስል በማቅረብ የወሰደው ሀሰተኛ የውክልና ማስረጃ ነው በማለት የዱስፒሉን ጉባኤው የደረሰበትን የማስረጃና የፍሬ ጉዲይ መደምደሚያ ለመቃወም የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረት የላለው መሆኑን የሚሳይ ነው።
አመልካች ደንበኛው በ2005 ዓ.ም ህጋዊ መስፈርቶችን በማሟላት ወይም ከህግ አግባብ ውጭ ድንበር ጥሶ ወደ አገር ቤት መጥቶ የነበረ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም።
ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ደንበኛው በ2005 ዓ.ም ወደ አገር የገባና ከአገር የወጣ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ካለው ማስረጃውን እንዱያቀርብ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 345 መሰረት እድል ሰጥቶት አመልካች ማስረጃውን ሉያቀርብ ያልቻለ መሆኑን በውሣኔው በግልፅ አስፍሯል። ከዚህ አንፃር ሲታይ የክልለ ፍትህ ቢሮ አመልካች ደንበኛው በሪሁን ወንዳ በእስራኤል አገር ኗሪ መሆኑን እያወቀ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ኗሪ መሆኑን የሚገልፀውን የሀሰት መታወቂያ መጠቀሙንና የሀሰት የተሟጋችነት የውክልና ሰነድ በመያዝ ክርክር እያቀረበ መሆኑን ገልፆ አመልካች በክልለ የጥብቅና ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባና የጠበቆችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 75/1994 የሚጥስ ከባድ የዱስፒሉን ጥፊት ፈፅሟል በማለት የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰበር ችልት በማፅናታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች የዱስፒሉን ጉባኤው ከዚህ በፉት ተከሳሽ በቢሮ ኃላፉው ውሣኔ በነፃ የተሰናበተበትን ጉዲይ በውሣኔ ውስጥ መግለፁን ምክንያት በማድረግ ባልተከሰሰኩበት ጉዲይ ጥፊተኛ ተብዬ ተቀጥቻለሁ የሚል የሰበር መከራከሪያ አቅርቧል። በእርግጥ ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ በሰጠው ውሣኔ አመልካች የክልለ 2ኛ ና 1ኛ ደረጃ የጥብቅና ፈቃድ ሲያወጣ አግባብነት የላለው የሥራ ልምድ ተጠቅሟል የሚል የዱስፒሉን ክስ ቀርቦበትና ሁኔታው ተጣርቶ አመልካች የጥብቅና ፈቅድ የወሰደው አግባብነት የላለው የሥራ ልምድ መሆኑን ተረጋግጦበት እንደነበርና የቢሮ ኃላፉው ቀደም ብለው በነበሩት የቢሮው አመራሮች ተምኖበት የተሰጠው መሆኑንና ፈቃደ ቢሰርዝ ለአመልካች ላይ የሚደርሰው ማህበራዊ እና ቤተሰባዊ ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ቅጣት ሣይወሰንበት የቀረ መሆኑን በውሣኔው ገልፆል። የልዩነት ሀሳብ ይኸ ሀሳብ በዱስፒሉን ውሳኔ ላይ መፃፈ ተገቢ አይደለም በሚል ምክንያት የተፃፈ መሆኑን ተገንዝበናል።
የዱስፒሉን ጉባኤው የአመልካች ማህደር ሲመረምር ከማህደሩ ጋር ተያይዞ ያገኘውን ፍሬ ጉዲይ በውሣኔው ውስጥ መግለፅ በክልለ አዋጅ ቁጥር 75/1994 የተከለከለ ተግባር ሆኖ አላገኘነውም። በአንፃሩ የዱስፒሉን ጉባኤው አመልካች ማህበር ጋር ተያይዞ የሚገኘውን የሥነ ምግባር ሁኔታ መግለፁ በአዋጅ አንቀጽ 21 ንዐስ አንቀጽ 5 ጉባኤው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጠበቃው ላይ የሚጣለውን ቅጣት በመወሰን የወንጀል ሪከርድ የጠበቃውን የግል ማህደር ወይም ላላ ተመሣሣይ ማስረጃ የማስቀረብ የማሰማትና የመመርመር ሥልጣን የተጠቀመ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጉባኤው በአመልካች ማህደር ተያይዞ ያገኘውን ፍሬ ጉዲይ በውሣኔው ከመግለፁ ውጭ ይህን ፍሬ ጉዲይ ቅጣቱን አቅልልም ሆነ አክብድ ለመወሰን ያልተጠቀመበት መሆኑን ከውሣኔው ተረድተናል። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች ጉባኤው ማህደሩን ሲመረምር ያገኘውን ግኝት በውሣኔው ውስጥ መግለፁ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንደሆነ በመግለፅ ያቀረበው አቤቱታ የአዋጅ ቁጥር 75/94 አንቀጽ 21 ድንጋጌዎች ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀጽ 4፣ የፋዳራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 456/97 በክልለ መሬት አስተዲደር አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 እና በደንብ ቁጥር 51/99 መሰረት የገጠር የእርሻ መሬት ይዞታ በስጦታም ሆነ በውርስ የማግኘት መብት የላለው በእስራኤል አገር ነዋሪ የሆነውን አቶ በሪሁን ወንዳ የባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የባይነሳ 3ቱ ቀበላ ነዋሪ እንደሆነ ተደርጎ በሀሰት ተዘጋጅቶ የተሰጠውን መታወቂያ እያወቀ ለባህር ዲር ዙሪያ ወረዲ የመሬት አስተዲደርና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ያቀረበና ይህንኑ መታወቂያ በመጠቀም አቶ በሪሁን ወንዳ ወደ አገር ውስጥ ባልገባበት በአገር ውስጥ በላለበት ታህሣሥ 22 ቀን 2005 ዓ.ም የሀሰት የተሟጋችነት ውክልና በማውጣት አቤቱታ አቅራቢውንና ላልች አርሶ አደሮችን በመክሰስ ከፍተኛ እንግልት ያስከተለና ዕውነት እንዲይወጣና ፍትህ እንዱዛባ የሚደርግ ጥፊት የፈፀመ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የክልለ ፍትህ ቢሮ የጠበቆች የዱስፒሉን ጉባኤና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተረጋግጧል።
አመልካች የፈፀመው የዱስፒሉን ጥፊት እጅግ ከባድና በአዋጅ ቁጥር 75/1994 አንቀጽ 13 ንዐስ አንቀጽ 2(መ) እና በላልች አግባብነት ያላቸውን የአዋጁን ድንጋጌዎች የጣሰ አመልካች ሕግን የማስከበር ፍትህን የማስገኘትና ለፍትህ አስተዲደሩ የማገዝ ኃላፉነቱን ወደ ጎን በመተው ተቃራኒ የሆነ ተግባር የፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ይኸም በመሆኑ አመልካች ላጠፊው ከባድ የዱስፒሉን ጥፊት የጥብቅና ፈቃደ እንዱሰረዝ በማለት የክልለ ፍትህ ቢሮ የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ማፅናታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የጠበቆች የዱስፒሉን ጉባኤና የቢሮ ኃላፉ የሰጠው ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.