አንድ ጠበቃ በገባው ውል መሰረት እስከ መጨረሻው ድረስ ጉዲዩን ከተከታተለና ከሙያው አንጻር እውቀትና ጥረቱን ተጠቅሞ አገልግልት ከሰጠ የተፈለገው ውጤት ባለመምጣቱ ብቻ የተሟላ አገልግልት አልሰጠም ሉሰኝ የማይችል ስለመሆኑ እና በውለ መሰረት የተስማሙበትን የጥብቅና አገልግልት ክፍያ ቀሪ ሉያደርገው የማይችል እነ ወ/ሮ ዘውደ ፍቅሬ እና አቶ አበራ ጌታነህ XXXIII
No summary available.
ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካቾች- 1ኛ- ወ/ሮ ዘውዳ ፍቅሬ - 2ኛ- አቶ ኃ/ሚካኤል ተስፊየ 1ኛ አመልካች በራሳቸው እና ስለ 2ኛ አመልካች ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አበራ ጌታነህ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የጥብቅና አገልግልት ክፍያን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካቾች ላይ በአማራ ክልል ደብረብርሃን ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱ ይዘት ሶስት የተለያዩ ጉዲዮችን በመያዝ እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ለመከራከር የጥብቅና አገልግልት ውል አድርገን ተገቢውን አገልግልት የሰጠሁ ሲሆን በውለ መሰረት ሉከፍለኝ የሚገባውን አበል ያልከፈለኝ በመሆኑ ብር 39,850.00 (ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ሃምሳ) ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መልስ በጥብቅና ውለ መሰረት ተገቢውን አገልግልት አልሰጠም፤
በክርክሩም ያስገኘልን ጥቅም የለም በመሆኑም የጠበቃ አበል ልንከፍል አይገባም፤ በአንፃሩ አገልግልት ሳይሰጥ በመጀመሪያ ደረጃ ከፍያ የወሰደውን ብር 5,650.00 (አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ) እንዱመልስ እንዱወሰን በማለት ተከራክረዋል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ ከሳሽ በዉለ መሰረት አገልግልት ሰጥቻለሁ ይበል እንጂ የቀረቡት ማስረጃዎች በተደረገው የጥብቅና ውል መሰረት እስከመጨረሻው አገልግልት መስጠቱን የሚያስረደ ባለመሆኑ የዲኝነት ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። ተከሳሾች የቅድሚያ ክፍያ ይመለስልን በማለት ያቀረቡት ጥያቄም ሳይቀበለው ቀርቷል።ጉዲዩ በይግባኝ በየደረጃው እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ደርሶ የሰበር ችልቱ በመጨረሻ ባሳለፈው ውሳኔ ተጠሪ ውል በተደረገባቸው በሶስቱም መዛግብቶች እስከ ፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ቅሬታ አቅርቦ የሰበር አቤቱታው አያስቀርብም ተብል የተዘጋ ስለመሆኑ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፃፈው ደብዲቤ መረዲት ይቻላል በማለት ተጠሪ ለሰጠው የጥብቅና አገልግልት በቁርጥ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) አመልካቾች እንዱከፍለት ወስኗል።የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካቾች ነሀሴ 27/2007 ዓ.ም ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ የአገልግልት ክፍያ እንዱከፈለው የተወሰነበትን አግባብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ግራ ቀኙም የስር ሙግታቸውን በማጠናከር በፅሁፍ ተለዋውጠዋል።ከላይ ባጭሩ የገለፅነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን የክልለ ሰበር ችልት የጥብቅና አገልግልት እንዱከፈል ባሳለፈው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት ቢኖር በጭብጥነት ይዘን መርምረናል። በአመልካቾችና በተጠሪ መካከል የጥብቅና አገልግልት ውል ስለመደረጉና ስምምነቱም ተጠሪ ባለው የጥብቅና ሙያ ጉዲዩን እስከ መጨረሻ ድረስ ሉከራከርላቸውና በአንፃሩ ለአገልግልቱ የተጠቀሰውን ዋጋ ሉከፍለ ስለመሆኑ አላከራከረም። አመልካቾች የተሟላ አገልግልት ባልተሰጠበት ብር 20,000.00 እንዱከፈል የክልለ ሰበር ችልት መወሰኑ የህግ ስህተት ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ በሙያው ደንብና ልማድ መሰረት ህግንና ማስረጃን ተንተርሶ እስከመጨረሻ ጉዲዩን በመከታተል በአፈፃፀም እንዱያገኙ ያደረግሁ በመሆኑ የክልለ ሰበር ችልት ማግኘት ከሚገባኝ ባነሰ ርትዕን መሰረት በማድረግ መወሰኑ የሚነቀፍ አይደለም ተብል ውሳኔው እንዱፀና ተከራክረዋል።
እንደመረመርነው ተጠሪ ይዘዋቸው በነበሩ ሶስት የአመልካቾች ጉዲዩች እስከ ፋዳራለ ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርበው የነበረ ስለመሆኑና ለሰበር አያስቀርብም በሚል የመ/፤85891 የተዘጉ ስለመሆኑ ከፍርድ ቤቱ የተፃፈው ደብዲቤ ተጠቅሶ ከተሰጠው ውሳኔ መገንዘብ ይቻላል። በገቡት ውል መሰረት እስከ መጨረሻ ድረስ ጉዲዩን ከተከታተለ እና ከሙያቸው አንፃር እውቀትና ክህልታቸውን ተጠቅመው አገልግልት ከሰጡ የተፈለገው ውጤት ባለመምጣቱ ብቻ የተሟላ አገልግልት አልሰጡም ሉሰኝ የሚችልበት ምክንያት የለም። ስለሆነም ምንም አይነት ክፍያ ሉከፈላቸው አይገባም በማለት አመልካቾች ያቀረቡት ክርክር የውልም ሆነ የህግ መሰረት ስለላለው የምንቀበለው አይሆንም። የነገሩ አጠቃላይ ሁኔታ ታይቶ ተጠሪ ለሰጠው የጥብቅና አገልግልት በቁርጥ ብር 20,000.00 ይከፈል ተብል በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሚባል ህግ ስህተት ባለመኖሩም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ ሰኔ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.