አንድ ለፍርድ ማስፈጸሚያ በሐራጅ ይሸጥ የተባለን ንብረት በባለሙያው የተቀመጠውን የሐራጁ መነሻ ዋጋ አነሰ በማለት የሐራጅ ሽያጩ ተከናውኖ ውጤቱ ባልታወቀበት ሁኔታ የተጀመረው አፈጻጸም ቀሪ ይሁን ማለት ተገቢ አቶ ይልማ ፈለቀ እና አቶ ጥበቡ ፈለቀ
No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ይልማ ፈለቀ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጥበቡ ፈለቀ አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው ግራ ቀኙን ያከራከረው የአፈፃፀም ጉዲይ ይፈፀም ከተባለው ፍርድ ይዘት ውጭ እንዱፈፀም የሚገልፅ ዲኝነት ተሰጥቷል ወይስ አልተሰጠም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ በክርክር ሂደት ከተረጋገጠው የፍሬ ነገሮች ጉዲዮች እና አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦና ተመልክቶ ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት በሚል ነው።
በዚህም መሰረት በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙ ከአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባለው ደረጃ በተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ አሁን ለዚህ ሰበር ጉዲይ መነሻ ሆኖ የተያዘውን እና ለአፈፃፀሙ ክስ ምክንያት የሆነውን ጥቅምት 08 ቀን 2005 ዓ.ም በሽማግላ ዳኞች አማካኝነት ጉዲዩ በእርቅ እንዱያልቅ ከማድረጋቸው በፉት እርቅ ባደረጉበት ምክንያት ግራ ቀኙ ከነበራቸው የንግድ ሽርክና ውል የመነጨ የሀብት ድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ምክንያት ጉዲያቸው በፍ/ቤት ቀርቦ በመ/ በሆነው መዝገብ የአሁን ተጠሪ በስሙ ተመዝግበው የሚገኙትን ንብረቶች ለአሁን አመልካች እንዱያካፍል ፍርድ መስጠቱንና በዚህ ፍርድ መሰረት ለማስፈፀም የአፈፃፀም ክስ ቀርቦ በክርክር ላይ እያለ በአፈፃፀም ደረጃ የደረሰውን ጉዲይ አስመልክቶ ግራ ቀኙ በሽማግላዎች አማካኝነት በእርቅ እንዱያልቅ ተስማምተው፤ በሽማግላዎችም ታይቶ አሁን ለዚህ ሰበር ጉዲይ ምክንያት በሆነው ጥቅምት 08 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገው የእርቅ ስምምነት መሰረት የአፈፃፀሙ ክስ እንዱዘጋ መደረጉን ገልፆ ለክርክር የአሁን ተጠሪ ይህ በአዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በሆነው መዝገብ ላይ አስቀድሞ ፍርድ ያገኘ ጉዲይ ነው በሚል የቀረበው ከስርዓት ውጭ የቀረበ ነው፤ ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብነት ያለው ጥቅምት 8 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገው የእርቅ ስምምነት ብቻ ነው የሚል ክርክር ከማቅረባቸው በቀር በግልፅ የካደት ጉዲይ አይደለም።
ከስርዓት ውጭ የቀረበ ክርክር በመሆኑ ምክንያት አንድ ክርክር ውድቅ ላደረግ የሚችለው ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ መነሻና ዋነኛ ዓላማ የሆነውን የተከራካሪ ወገን የመደመጥ መብት ለማስከበር ሲባል ክርክርና ማስረጃ ስርዓቱን ጠብቆ በሚደረግበት ፍ/ቤት እና የክርክር ደረጃ እንዱቀርብ ለማድረግ ነው። ይህ አሁን በአሁን አመልካች በኩል የጉዲዩን አመጣጥና መነሻ ለማስረዲት ሲባል የቀረበው ክርክር ጉዲይ በፍ/ቤት ቀርቦና ታይቶ በመዝገብ ፍርድ የተቋጨበት ነው የሚል እስከሆነና ይህም አሁን ክርክር ከተነሳበት ጉዲይ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው እስከሆነ ድረስ ፍሬ ነገሩ እንደተባለው አይደለም፤ ሐሰት ነው የሚባል ከሆነ ይህንኑ በቀላል ለመግለፅ እና ለማስረዲት የሚቻል እንጅ ከሕግ ሐሳብ ውጭ በመራቅ የተሟላ የክርክር ሂደትን ጠብቆ በሙግት ደረጃ ነጥሮ እንደማይወጣ ጉዲይ ተቆጥሮ በደፈናው በስርዓት ውጭ ያቀረበ ነው ለማለት የሚያበቃ አይደለም። በዚህም የተነሳ እና ከክርክሩ መገንዘብ እንደሚቻለው ለአፈፃፀሙ ምክንያት የሆነውና በሽማግላዎች ፉት ጥቅምት 02 ቀን 2005 ዓ.ም ባደረጉት የእርቅ ስምምነት ላይ የካርታ ቁጥር 0442/2001 በሚል የተገለፀው የንግድ ቤት ለግራ ቀኙ የሽርክና ስራ ውል በመነጨ የአሁን ተጠሪ ግማሽ ድርሻ ለአሁን አመልካች ሉያካፍል ይገባል ተብል ፍርድ ያረፈበት ይህንኑም ፍርድ በማስፈፀም የአፈፃፀም ክስ ከቀረበ በኋላ አፈፃፀም ደረጃ የቀረበውን ክርክር በዚሁ የእርቅ ስምምነት አቋርጠው የእርቅ ስምምነት እንደተካው ተደርጎ በእርቅ ስምምነት መሰረት እንዱፈፀም የተደረገ ስለመሆኑ እስካልተካደ ድረስ የካርታ ቁጥር 0442/2001 በሚል የተጠቀሰው ስህተት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 2008 እንደተመለከተው በእርቁ አፃፃፍ ጊዜ የተፈፀመ የአፃፃፍ ስህተት ነው ከሚባል የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው አይደለም። የአሁን ተጠሪም ይኽው ንብረት ክፍፍል የሚደረግበት ከዚህ በፉት ፍርድ ያረፈበት በኋላም በሽምግልና የእርቁ ሰነደ ላይ የተጠቀሰውና ክፍፍል የሚደረግበት ንብረት መሆኑን ተቀብል የንብረቱ ግምት በሽማግላዎች የእርቅ ሰነድ ከተመለከተው ሉያንስ አይገባም፤ በተከታዩም ቀጠሮ ይህ ክፍፍል የተደረገበት ንብረት በባድ መሬትነት የሚታወቅ እንጅ ቤት የላለው መሆኑን የከተማው አስተዲደር አስቀድሞ የሰጠውን ማረጋገጫ ቀይሮ ማስረጃ ሰጥቶኛል ስለዚህ ባድ መሬት የህዝብና የመንግስት ስለሆነ ላካፍል አይገባም በሚል መከራከራቸውን ከመረጋገጡ በቀር በካርታ ቁጥር 0442/2001 በሚል የተሰየመው ንብረት አከራካሪ ሆኖ ከተገኘው ንብረት የተለየ ነው በሚል ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባለው የክርክር ደረጃ ያቀረበው የማስተባበያ ክርክና ማስረጃ የለም።
አልተገኘም ስለሆነም ከዚህ በፉት አስቀድሞ በፍርድ ተቋጭቶ ያደረው የግራ ቀኙ ጉዲይ በአፈፃፀም የክስ ደረጃ ደርሶ እያለ በግራ ቀኙ ስምምነት የአፈፃፀሙ ጉዲይ ጥቅምት 08/2005 ዓ.ም በሽማግላዎች አማካኝነት በተደረገው የእርቅ ስምምነት መሰረት እንዱፈፀም አድርገው መሰማማታቸው የተረጋገጠ ጉዲይ ለመሆኑና በዚህም የእርቅ ስምምነት መሰረት በእርቅ ሰነደ ላይ የአሁኑ ተጠሪ ለአመልካች በድርሻነት ሉያካፍል ይገባል በማለት የተገለፀውን ገንዘብ ከእነ መጠኑ የአሁኑ ተጠሪ ስለመክፈለ ተረጋግጦ ቀሪውን ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የንግድ ቤት በሽምግልና ዳኞች የእርቅ ስምምነት መሰረት ሽማግላዎች አሽጠው ድርሻ ድርሻቸውን ለማከፊፈል ባደረጉት ጥረት ያጋጠመውን መጓተት በማሳየት ቀሪው ተግባር በፍርድ ቤት እገዛ እልባት እንዱያገኘ የተደረገበት አስቀድሞ በፍርድ የተቋጨው እና በአፈፃፀም ደረጃ ደርሶ የአፈፃፀሙ ጉዲይ በእርቅ ሰነደ መሰረት እንዱመራ የተደረገበት የዚያው ተከታይ እና ቅጥያ ነው ከሚባል በቀር እራሱን እንደቻለ ፍርድም ሉቆጠር የሚችል አይደለም።
በመሆኑም የካርታ ቁጥር 0442/2001 በሚል ጥቅምት 08 ቀን 2005 ዓ.ም ለተደረገው የእርቅ ሰነድ ላይ የተደረገው የካርታ ቁጥር አጠቃቀስ በአፃፃፍ ስራ ምክንያት የተከሰተ ግድፈት መሆኑን የስር የአዲማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገንዝቦ ያው በፉትም ሆነ በኋላ ስለእርቁ ጉዲይ በተደረሰው ስምምነት ላይ የተጠቀሰው ንብረት እንጂ ላላ የተለየ ንብረት አለመሆኑን በማረጋገጥ የአፃፃፍ ስህተቱ እንዱረታም አድርጓል ከሚባል በቀር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ እንዲሰፈረው ትችት ለአፈፃፀም መነሻ የሆነው የፍርድ ይዘት በአፈፃፀም የክርክር ጉዲይ ላይ እንዱለወጥ ተደርጓል የሚያሰኝ አይደለም።
የአሁን ተጠሪ በበኩለ አፈፃፀሙን ከዲር ለማድረስ ሲል ፍ/ቤቱ ባከናወነው የባለሙያ ግምት ስራ ውጤት አስቀድመን በስምምነታቸው ለተገለፀው የንብረቱ ግምት መጠን በታች ላሆን አይገባም በሚል ያቀረቡትን የመከራከሪያ ነጥብ እንደተመለከትነው በእርግጥም በእርቅ ሰነደ ላይ የተመለከተው የንብረቱ ግምት ብር 1‚000‚000.00 /አንድ ሚሉዮን ብር/ ግምት ሽማግላዎች ሸጠው በሚል ተጠቅሶ እያለ ፍ/ቤቱ ይህንኑ በሽማግላዎች አማካኝነት የተደረሰውን የንብረት ክፍፍል ስራ ከዲር ለማድረስ ሲል የመሸጫ ዋጋውን እንደገና ሲያስገምት ከዚሁ በሰነደ ከተገለፀው በታች ስለመሆኑ የተካደ ጉዲይ አይደለም።
ይሁን እንጅ የዚህ አነስተኛ ሆኖ የተያዘው የንብረት ግምት ለሐራጅ ሽያጭ ሥራ ሲባል የተያዘ የመሸጫ መነሻ ዋጋ ነው የሚባል እንጂ ንብረቱ በዚሁ በባለሙያ ግምት መሰረት እንዱሸጥ የተደረገ መሆኑን አያመለክትም በዚሁ ግምት መሰረት ሉሸጥ የሚችል ነው የሐራጅ ውጤት ከመታወቁ በፉት ለመደምደም የሚቻል አይደለም። ስለሆነም ውጤቱ እንደስጋታቸው ሆኖ ከተገኘ ከውጤቱ በኋላ ስርዓቱን ጠብቀው እንዱታረም ከማድረግ በቀር የተጀመረውን የአፈፃፀም ጉዲይ ግን ቀሪ ለማድረግ የሚያበቃ የክርክር ይዘት ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት የፍርድ ሀተታዎች አንፃር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በፊ/ በቀን 19/12/2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ተሽሯል። የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እንደቅደም ተከተለ በፍይል በቀን 26/02/2006 እና በፊይል በቀን 11/03/2006 ዓ.ም የሰጡት ዲኝነቶች ፀንተዋል።
በስር የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጀመረው የአፈፃፀም ክርክር ጉዲይ ሉቀጥል ይገባል መባለ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ለየራሳቸው ይቻለ
የዚህ የክርክር ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ በሚል በዚህ የሰበር መዝገብ ላይ ጥቅምት 05 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
No topics extracted.