የጋራ ወራሾች ሀብት በሆነ ንብረት ላይ ከእንዲንደ የጋራ ባለሀብቶች ላይ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች የባለድርሻውን ድርሻ ለመያዝ የሚችለ ስለመሆኑ፣ በውርስ ሀብት እና የጋራ ወራሾች ያልተከፊፈለ የውርስ ንብረት መካከል ስላለው ልዩነት የፍ/ሕ/ቁ. 943፣1052፣1053፣1060 እና 1260
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች-፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- ህጻን ሣራ ማርቆስ - ሞግዚት ብርነሽ ሁንዳ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የፍርድ አፈጻጸምን የሚመለከት ክርክር ሲሆን አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ17/07/2007 ዓ.ም.
የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ15/10/2007 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
የክርክሩን አመጣጥ በተመለከተ፡-በስረ ነገሩ ጉዲይ የህጻን ልጃቸውን ቀለብ የአሁኑ 5ኛ ተጠሪ በየወሩ ብር 5,000 (አምስት ሺህ) እንዱከፍለ የአመልካች ሞግዚት ውሳኔ ማሰጠታቸውን፣ በዚሁ ፍርድ መሰረት ለማስፈጸም እንዱቻል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቁጥሩ 213611 የሆነ የአፈጻጸም መዝገብ አስከፍተው የፍርድ ባለዕዲው በአገር ውስጥ የላለ መሆኑን ጠቅሰው ፍርደ የፍርድ ባለዕዲው ከአሁኖቹ 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር ከወላጆቻቸው በጋራ በውርስ ያገኙት በየካ ክፍለ ከተማ በወረዲ 5 የሚገኘው ቁጥሩ 327 የሆነው ቤት በሐራጅ ተሽጦ ከሽያጩ ገንዘብ የፍርድ ባለዕዲው ድርሻ በፍርደ መጠን እንዱከፈላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ፍርድ ቤቱም ይህንኑ ጥያቄ ተቀብል ቤቱ በሐራጅ ተሽጦ ከሽያጩ ገንዘብ ከአንድ አራተኛው ውስጥ ውዝፍ ቀለቡ ታስቦ ለፍርድ ባለመብት እንዱከፈል፣ከውዝፍ ቀለቡ የተረፈው ደግሞ በህጻኗ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀምጦ ዕድሜዋ 18 ዓመት እስኪሞላት ድረስ በየወሩ ብር 5,000 ወጪ እየተደረገ እንዱከፈላት በመዝገብ በ29/11/2006 ዓ.ም.
ትዕዛዝ መስጠቱን፣አፈጻጸሙ በዚህ ሂደት ላይ እያለ የአሁኖቹ 1ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ውርሱ ተጣርቶ የወራሾቹ ድርሻ ባልተለየበት ሁኔታ በውርስ ሀብቱ ላይ የሐራጅ ሽያጭ ትዕዛዝ የተሰጠው አላግባብ ነው በማለት በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 418 ድንጋጌ መሰረት መቃወሚያ ማቅረባቸውን፣የአፈጻጸም ችልቱም የአመልካቿን ሞግዚት አስተያየት ከተቀበለ በኃላ የመቃወሚያ አቅራቢዎቹን ክርክር ተገቢ አድርጎ በመቀበል የሐራጅ ሽያጭ ትዕዛዙ እንዱቋረጥ በመዝገብ በ23/01/2007 ዓ.ም. ብይን መስጠቱን፣በዚህ ብይን ቅር በመሰኘት የህጻኗ ሞግዚት ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የአሁኖቹ 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የፍርድ ባለዕዲ ከሆኑት 5ኛ ተጠሪ ጋር የወላጆቻቸው ወራሾች መሆናቸውን በጋራ በማረጋገጥ የተሰጣቸውን የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ ጉዲዩ በሚመለከተው ክፍለ ከተማ አስተዲደር አቅርበው ከቤቱ ማህደር ጋር እንዱያያዝ ማድረጋቸው መረጋገጡን፣መቃወሚያ አቅራቢዎቹ ላላ ወራሽ ወይም የውርሱ ዕዲ ወይም የሟቾቹ ኑዛዜ መኖር አለመኖሩ አልተረጋገጠም ከማለት በቀር ላላ ወራሽ ወይም የውርሱ ዕዲ ወይም የሟቾቹ ኑዛዜ ስለመኖሩ ያቀረቡት ክርክር እና ማስረጃ አለመኖሩን እና የወራሽነት ማስረጃ አቅርበው ከቤቱ ማህደር ጋር ካያያዙ ከሁለት ዓመት በኃላም ቢሆን መቃወሚያ አቅራቢዎቹ ውርሱ እንዱጣራ ያቀረቡት ጥያቄ አለመኖሩ ውርሱን የማጣራት ፍላጎት እንደላላቸው የሚያመለክት መሆኑን ገልጾ ብይኑን በመሻር አፈጻጸሙ በስር ፍርድ ቤት በ29/11/2006 ዓ.ም. በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እንዱቀጥል በመዝገብ በ17/07/2007 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱን፣በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁኖቹ 1ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች በተራቸው ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር ወራሾቹ በስምምነት ውርሱን የማያጣሩ ከሆነ ውርስ አጣሪ ሾሞ ውርሱ እንዱጣራ ካደረገ በኃላ በፍርድ ባለዕዲው ድርሻ ላይ ተገቢውን ትዕዛዝ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት ወደ ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመመለስ በመዝገብ በ15/10/2007 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ውርሱ ስላልተጣራ በውርስ ሀብት ላይ ፍርደን ማስፈጸም አይቻልም በሚል በተለይም የህጻን የመብት ጥያቄ ወደ ጎን ተትቶ ውርሱ በቅድሚያ ይጣራ ተብል የመወሰኑን አግባብነት በመዝገብ እና በመዝገብ ከተሰጠው ገዥ የሕግ ትርጉም አንጻር ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ በጋዜጣ ማስታወቂያ ተጠርተው መልስ ባለመስጠታቸው ምክንያት መብታቸው ከታለፈው 5ኛ ተጠሪ በስተቀር አመልካች እና ቀሪዎቹ ተጠሪዎች የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 418 ድንጋጌ መሰረት መቃወሚያ ያቀረቡት እና ከስር ጀምረው የሚከራከሩት የውርስ ማጣራት ሂደት ተከናውኖ ውጤቱ ባልታወቀበት ሁኔታ ፍርደ ከውርስ ሀብቱ ውስጥ የ5ኛ ተጠሪ ነው በተባለው ድርሻ ላይ ሉፈጸም አይገባም በማለት መሆኑን የክርክራቸው ይዘት ያመለክታል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ የሰጠው በዋናነት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 943 (3) ድንጋጌን አነጋገር መሰረት አድርጎ በመያዝ መሆኑን የውሳኔው ይዘት ያመለክታል።በመሰረቱ በውርስ ማጣራት ሂደት በአጣሪው የሚከናወኑት ተግባራት የውርስ ሀብቱ ምን እንደሆነ እና የውርሱ ተቀባዮች እነማን እንደሆኑ መወሰን፣ዕዲዎችን መክፈልና መቀበል፣ሟቹ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግ፣የኑዛዜ ስጦታዎችን መክፈል፣የውርሱን ሀብት ማስተዲደር ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕጉ በቁጥር 944 እና 956 ስር ተደንግጎ ይገኛል።በዳኞች ትዕዛዝ ጊዜው እንዱራዘም ካልተደረገ በቀር የውርሱ የሑሳብ ማጣራት ስራ ሟቹ ከሞተ ከአንድ ዓመት በኃላ የሚዘጋ ስለመሆኑ፣የውርሱ ሑሳብ ማጣራት በተዘጋ ጊዜ ከውርሱ ውስጥ ሆኖ የሚገኘው ንብረት ከወራሹ ላላው ሀብት ጋር የሚቀላቀል ስለመሆኑ፣የጋራ ወራሾችም እንዲለ የውርሱ ሆኖ የሚገኘው ንብረት የጋራ ወራሾች ንብረት እንደሚሆን፣የውርሱ አከፊፈል እስኪፈጸም ድረስ በወራሾቹ መካከል ውርሱ ሳይነጣጠል የሚቆይ ስለመሆኑ፣የጋራ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ባልተከፊፈለት የውርስ ንብረት ላይ ያላቸው መብት በፍትሐብሕር ሕጉ ስለጋራ ባለሀብትነት፣ስለሪምና ስለላልች ግዙፍ መብቶች በሚለው አንቀጽ በተነገሩት ድንጋጌዎች (ከቁጥር 1257 እስከ 1277) መሰረት የሚወሰን ስለመሆኑ እና ከእያንዲንድቹ የጋራ ባለሀብቶች ላይ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች የባለዕዲውን ድርሻ ለመያዝ የሚችለ ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ በቁጥር 1052፣1053፣1060 እና 1260 ድንጋጌዎች ስር በዝርዝር ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ 1ኛ፣2ኛ፣3ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች የአከራካሪው ንብረት የጋራ ወራሾች መሆናቸውን ገልጸው ጥያቄያቸውን ለፍርድ ቤት በማቅረብ የወራሽነት ማስረጃ በ2004 ዓ.ም.
የወሰደ መሆኑ፣ይህንንም የወራሽነት የምስክር ወረቀት የቤቱ ማህደር በሚገኝበት ክፍለ ከተማ አስተዲደር በማቅረብ ከቤቱ ማህደር ጋር እንዱያያዝ ያደረጉ መሆኑ፣የውርስ ሀብቱ የሆነውን ቤትም በይዞታቸው ስር አድርገው እየተገለገለበት መሆኑ በተጠሪዎቹ ያልተካደ እና በስር ፍርድ ቤቶች በተደረገው ክርክርም የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸው።የውርስ ማጣራት ሂደት ተከናውኖ ውጤቱ ባልታወቀበት ሁኔታ ፍርደ ከውርስ ሀብቱ ውስጥ የ5ኛ ተጠሪ ነው በተባለው ድርሻ ላይ ሉፈጸም አይገባም በማለት በደፈናው ከመከራከር በቀር በአከራካሪው ቤት ላይ መብት ያለው ላላ የኑዛዜም ሆነ የሕግ ወራሽ ስለመኖሩ እነዚህ ተጠሪዎች በግልጽ ያቀረቡት ክርክር የለም።እነዚህ ሁኔታዎች ተጠቃለው ሲታዩም 1ኛ፣2ኛ፣3ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች በሕጉ በተመለከተው የውርስ ማጣራት ሂደት ውስጥ ማለፍ ሳያስፈልጋቸው የውርስ ሀብት መሆኑ በተረጋገጠው ቤት ላይ እያንዲንዲቸው እኩል ድርሻ እንዲላቸው ተስማምተው እና ቤቱንም በቁጥጥራቸው ወይም በይዞታቸው ስር አድርገው በቤቱ ላይ በጋራ ባለሀብትነት መብት በማቋቋም እየተገለገለበት መሆኑን መገንዘብ የሚያስችለ ናቸው።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ የሰጠው በዋናነት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 943 (3) ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ሲሆን ይህ ድንጋጌ ከወራሾቹ ከራሳቸው ገንዘብ ጠያቂ የሆኑ ሰዎች የውርሱ ሀብት በሚጣራበት ጊዜ በውርስ ሀብቱ ላይ አንዲችም መብት የላላቸው መሆኑን የሚደነግግ ነው።
በመሰረቱ የውርስ ሀብት እና የጋራ ወራሾች ያልተከፊፈለ የውርስ ንብረት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ከቁጥር 943 እና 1060 ድንጋጌዎች ይዘት በግልጽ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ሀብት የውርስ ሀብት ነው የሚባለው ውርሱ በመጣራት ሂደት ላይ ባለበት ጊዜ ስለመሆኑ የቁጥር 942 ድንጋጌ ያመለክታል።በተያዘው ጉዲይ ግን ወራሾቹ በሕጉ በተመለከተው የውርስ ማጣራት ሂደት ውስጥ ማለፍ ሳያስፈልጋቸው ወራሽነታቸውን አረጋግጠው እና የውርስ ሀብቱንም በይዞታቸው ስር አድርገው እና ወደ ራሳቸው ንብረት ቀላቅለው የጋራ ባለሀብትነት መብት በማቋቋም እየተገለገለበት በመሆኑ አከራካሪው ቤት በቁጥር 1060 ድንጋጌ አነጋገር መሰረት የጋራ ወራሾች ያልተከፊፈለ የጋራ ንብረት እንጂ በቁጥር 942 እና 943 ድንጋጌዎች አነጋገር መሰረት የውርስ ሀብት የሚባል ባለመሆኑ ቁጥር 943 (3) ድንጋጌ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ሉኖረው አይችልም።ቤቱ የወራሾቹ የጋራ ሀብት መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ በቁጥር 1260 (2) ድንጋጌ መሰረት ከጋራ ባለሀብቶቹ መካከል ከአንደኛው ገንዘብ ጠያቂ የሆነ ሰው የዚህኑ የጋራ ባለሀብት ድርሻ የመያዝ መብት ይኖረዋል።
ሲጠቃለል አከራካሪው ቤት የውርስ ሀብት በመሆኑ የውርስ ማጣራት ሂደት ተጠናቆ ውጤቱ ከመታወቁ በፉት ከወራሾቹ ላይ ገንዘብ ጠያቂ ለሆኑ ሰዎች የፍርድ ማስፈጸሚያ ሉውል አይችልም በማለት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ በክርክሩ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች እና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።በልላ በኩል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአከራካሪው ቤት ውስጥ የ5ኛ ተጠሪ ድርሻ ለአፈጻጸሙ ሉውል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ቢሆንም 4ኛ ተጠሪ በዚህ ቤት ላይ የውርስ ድርሻ ያላቸው መሆን አለመሆኑ በክርክር ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ሆኖ እያለ የክርክሩ ውጤት ባልታወቀበት ሁኔታ ከቤቱ የሽያጭ ገንዘብ ውስጥ ለአፈጻጸሙ ሉውል የሚገባው አንድ አራተኛው ነው በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል መታረም ያለበት እና ለአፈጻጸሙ ሉውል የሚገባው ከተጠሪዎቹ ቁጥር አንጻር ከቤቱ የሽያጭ ገንዘብ ውስጥ አንድ አምስተኛ ሆኖ የ4ኛው ተጠሪ አንድ አምስተኛ ድርሻ ለጊዜው በሞዳል 85 ተይዞ እንዱቆይ ከተደረገ በኃላ የወራሽነት ክርክሩ የመጨረሻ ውጤት ከታወቀ በኃላ በዚህ በተቀማጩ ገንዘብ ላይ በአፈጻጸም ችልቱ እንደአግባብነቱ ተገቢው ትዕዛዝ እንዱሰጥበት ላደረግ የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
1ኛ፣2ኛ፣3ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች ከወላጆቻቸው በጋራ በውርስ ያገኙት በየካ ክፍለ ከተማ በወረዲ 5 የሚገኘው ቁጥሩ 327 በሆነው ቤት የውርስ ሀብት በመሆኑ ውርሱ ተጣርቶ ውጤቱ እስካልታወቀ ድረስ ከወራሾቹ መካከል አንደ ከሆኑት 5ኛ ተጠሪ ላይ ገንዘብ ጠያቂ በሆኑት አመልካች በአፈጻጸም ሉያዝ አይገባም በማለት በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ15/10/2007 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
አከራካሪው ቤት የወራሾች የጋራ ሀብት እንጂ የውርስ ሀብት ባለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1060 (1) እና (2) እንዱሁም በዚሁ ሕግ በቁጥር 1260 (2) ድንጋጌ መሰረት ከወራሾቹ መካከል የአንደኛው ድርሻ ከዚሁ ወራሽ ላይ ገንዘብ ጠያቂ በሆኑ ሰዎች ሉያዝ ይችላል በማለት ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ17/07/2007 ዓ.ም.
የተሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
በተራ ቁጥር 3 ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ አከራካሪ ቤት በሐራጅ ተሽጦ የ5ኛ ተጠሪ ድርሻ ለአፈጻጸሙ ሉውል ይገባል በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በተራ ቁጥር 3 ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ የ4ኛ ተጠሪን ክርክር በዝምታ በማለፍ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
1ኛ፣2ኛ፣3ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች ከወላጆቻቸው በጋራ በውርስ ያገኙት በየካ ክፍለ ከተማ በወረዲ 5 የሚገኘው ቁጥሩ 327 የሆነው ቤት በሐራጅ ከተሸጠ በኃላ ከሽያጩ ከሚገኘው ገንዘብ ውስጥ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ29/11/2006 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ በገለጸው የአፈጻጸም ስርዓት መሰረት የፍርድ ባለዕዲው የ5ኛ ተጠሪ ድርሻ የሆነው አንድ አምስተኛው ለአፈጻጸሙ እንዱውል፣ሶስት አምስተኛው ለ1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ለእያንዲንዲቸው አንድ አምስተኛ ወጪ ተደርጎ እንዱከፈል፣ቀሪው አንድ አምስተኛ በሞዳል 85 ተይዞ እንዱቆይ ከተደረገ በኃላ የ4ኛ ተጠሪ የአቶ ብሩክ ግርማ የወራሽነት ክርክር የመጨረሻ ውጤት ከታወቀ በኃላ እንደአግባብነቱ ተገቢው ትዕዛዝ እንዱሰጥበት በማለት ወስነናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣እንዱያውቁት ደግሞ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.