የዋስትና መብት የሚነፈግባቸው ምክንያቶች ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር እየተመለከቱ ሉመዝኗቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዳታውን የሚፈጽም የማይመስል ነው ተብል ግምት የሚወሰደው በቂና ህጋዊ ሉባለ በሚችለ ምክንያቶች ላሆን እንደሚገባ፤ እንዱሁም ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዲይ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዲዩ ልዩ ባህርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሉገነዘበው የሚችለው ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ ስለመሆኑ የወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67(ሀ) XXXII
No summary available.
የካቲት 08 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሃመድ ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ አይሸሹም መለሰ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ስማቸው ከበደ
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ በግራ ቀኙ መካከል ባለው የወንጀል ክስ ክርክር የቀረበን የዋስትና ጥያቄ የሚመለከት ነው። አመልካች ክሱን እየተመለከተ ለሚገኘው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ከ2ኛው ክስ ነጻ ስለወጣሁና ተከላከል የተባልኩባቸው ክሶች ላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ዋስትና የማያስከለክለ በመሆኑ የዋስትና መብት ይፈቀድልኝ በማለት ጠይቀዋል። ተጠሪ በሰጠው መልስ ተከሳሽ የተከሰሱበት ወንጀል ከአስር ዓመት በላይ የሚያስቀጣ መሆኑን፤ እንዱሁም ነፃ በወጡበት ጉዲይ ይግባኝ የጠየቁበት መሆኑን በማንሳት የዋስትና መብታቸው እንዱነፈግ ተከራክሯል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአመልካች እና 19ኛ ተከሳሽ በሆነው ድርጅታቸው ላይ የቀረቡት 37ኛ፤ 38ኛ፤ 40ኛ፤ 41ኛ፤ 42ኛ፤ 43ኛ፤ 44ኛ፤ እና 45ኛ ክሶች የግብር ዓዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 96 እና 97፤ እንዱሁም የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 49፤
50፤ 102 እና 56 መሰረት ያደረጉ እና በእነዚህ 8 (ስምንት) ክሶች በድምሩ ብር 50,374,960.00 የሚጠጋ የመንግስት የገቢ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ እዲ እንዲለባቸው የሚያሳዩ ግብር አሳውቆ አለመክፈልን እና አሳንሶ ማሳወቅን የሚመለከቱ የወንጀል ክሶች በመሆናቸው፤ በድርጅቱ ላይ የቀረቡትም ክሶች አመልካችን የሚመለከቱ እና በተደራቢነት የሚታዩ በመሆናቸው፤
የተጠቀሱት ድንጋጌዎች በመርህ ደረጃ ዋስትና የሚከለክለ ባይሆንም ተደራራቢ ቅጣትን ሉያስከትለ የሚችለ ተደራራቢ ወንጀልች በመሆናቸው አመልካች ሉከተል የሚችለውን ከፍተኛ ቅጣት በመሸሽ በዋስ ቢወጡ ሉቀርቡ ይችላለ ተብል መገመት አለመቻለን፤ የክሱ የገንዘብ መጠን ከፍተኛ መሆኑና በሃገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረው ተፅእኖ ከፍተኛነት ሲታይ የድርጊቱ አፈፃፀም አደገኛነት እና የወንጀለን ከባድነት ስለሚያስገነዝብ አመልካች በዋስትና ቢወጡ ይቀርባለ ተብል ለመገመት የማያስችል በመሆኑ፤ አመልካች ያላቸውን የኢኮኖሚ አቅም ተጠቅመው ከሃገር አይወጡም የሚለውን ግምት የሚያስተባብል አሳማኝ ምክንያት ያላቀረቡ በመሆኑ፤ በአጠቃላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች አመልካች የዋስትና መብት ቢፈቀድላቸው የዋስትና ግዳታን አክብረው ፍርድ ቤት በየቀጠሮው ይቀርባለ የሚል ዕምነት ሉጣልበት የሚያስችል ሁኔታ የለም ብል ፍርድ ቤቱ ስላመነ የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበልኩም በማለት ብይን ሰጥቷል።
አመልካች ይህን ብይን በመቃወም ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ብይኑን ለመለወጥ የሚያስችል በቂ እና አሳማኝ ምክንያት አልተገኘም ተብል የይግባኝ ማመልከቻው ውድቅ ተደርጓል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን በመቃወም ነው።
አመልካች ህዲር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የተከሰሱባቸው የወንጀል ክሶች በመርህ ደረጃ የአመልካችን የዋስትና መብት የሚያስነፍጉ ስላለመሆናቸው የሥር ፍርድ ቤት ተቀብል ነገር ግን ክርክሩ ከተጠናቀቀ በኋላ አመልካች ጥፊተኛ ቢባለ ሉያስከትልባቸው ከሚችለው ቅጣት አንፃር አመልካች ከሃገር ሉሸሹ ይችላለ የሚለውን ግምት መነሻ በማድረግ የዋስትና መብት የመከልከለን አግባብነት፤ እንዱሁም ከሃገር ሉሸሹ ይችለ ይሆናል የሚል ግምት ቢወሰድም እንኳ ከሀገር ለመሸሽ የማይችለበትን ሥርዓት ማስፈፀም እየተቻለ መሰረታዊ የሆነውን የዋስትና መብት ለመንፈግ የተሰጠው ምክንያት እንደህጉ አነጋገር በቂ ምክንያትን የተመረኮዘ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ከዚህ ቀደም በሰበር መ/ ከሰጠው ትርጉም አንፃር ማየት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ይቅረብ ተብሎል። በዚሁ መሰረት ግራ ቀኙ የስር ክርክራቸውን በማጠናከር በፅሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለፅነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ የማድረጋቸውን አግባብነት መርምረናል። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 19(6) በግልፅ እንደተመለከተው የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት ያላቸው ሲሆን ዋስትና ሉከለከል የሚችለው በህግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ነው። በህጉ ከተደነገጉት ልዩ ሁኔታዎች መካከል በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67(ሀ) ሥር የተደነገገው ተጠቃሽ ነው። በድንጋጌው ሥር እንደተመለከተው ተከሣሹ የዋስትና ግዳታውን ሉፈጽም አይችልም ተብል ሲገመት ዋስትና መከልከል ይቻላል።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ በዋስ ቢለቀቁ ተመልሰው ሉቀርቡ አይችለም የሚል ግምት ለመውሰድ እና ዋስትና ለመከልከል የሚያስችል ማስረጃም ሆነ ምክንያት ሳይኖር፤ ይልቁንም ከፍተኛ ባለሃብት በመሆናቸው በቢሉዮን የሚቆጠር ሃብት የሚያንቀሳቅሱ እና አንደኛ ደረጃ ግብር ከፊይ ተብለው መሸለማቸውን፤ እንዱሁም ከፍተኛ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ሁለ ለፍርድ ቤቱ ተገልፆ በገሃድ ቀርቦ እያለ ምንም ማፍረሻ ማስረጃ ሳይቀርብ በደፈናው አይቀርቡም የሚለውን ግምት ሉያስተባብለ አልቻለም በማለት መደምደሙ፤ እንዱሁም ጉልህ ግምት ቢኖር ያንን እንዲፈርስ ወይም እንዲስረዲ እንኳ እድል ሳይሰጥ የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑ በዚህ መልኩ የተሰጠው ብይን ተሽሮ ዋስትና ሉፈቀድ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ነገር ግን ተከሣሹ የዋስትና ግዳታውን ሉፈጽም አይችልም ለማለት የሚያስችል በበቂ ምክንያት የተደገፈ ግምት ካለ ይህ በመኖሩ ብቻ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 67/ሀ/ መሰረት ዋስትና መከልከል የሚቻል ሲሆን በተያዘው ጉዲይ በስር ፍርድ ቤት አመልካች የዋስትና መብት የተከለከለት የዋስትና ግዳታን አክብረው ፍርድ ቤት በየቀጠሮው ይቀርባለ የሚል ዕምነት ሉጣልበት የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ በመቀበለ ነው። ፍርድ ቤቱ እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሰው በአመልካች እና በድርጅታቸው ላይ የቀረቡትን ተደራራቢ ክሶች፤ ክሶቹ የያዙትን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እና ወንጀለም ግብር አሳውቆ ካለመክፈል እና አሳንሶ ከማሳወቅ ጋር የተያያዙ ወንጀልች መሆናቸውን፤ እነዚህ ከፍተኛ ቅጣትን ሉያስከትለ የሚችለ ተደራራቢ ወንጀልች በመሆናቸው፤ የድርጊቱ አፈፃፀም አደገኛነት እና የወንጀለ ከባድነት ሁለ ሲታይ አመልካች በዋስትና ቢወጡ ይቀርባለ ተብል ለመገመት የማያስችል መሆኑን፤ እንዱሁም አመልካች ያላቸውን የኢኮኖሚ አቅም ተጠቅመው ከሃገር አይወጡም የሚለውን ግምት የሚያስተባብል አሳማኝ ምክንያት ያላቀረቡ መሆኑን በማንሳት ነው።
የወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67(ሀ) በዋስትና ወረቀት የተመለከቱትን ግዳታዎች አመልካች የሚፈጽሙ የማይመስል እንደሆነ በዋስትና የመለቀቅ ማመልከቻውን መቀበል የማይቻል ስለመሆኑ ቢደነግግም ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከልከል ግምቱን መነሻ የሚያደርግባቸው ሁኔታዎች በግልጽ አልተመለከቱም። በመሆኑም አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዳታውን የሚፈጽም የማይመስል ነው ተብል ግምት የሚወሰደው በቂና ህጋዊ ሉባለ በሚችለ ምክንያቶች ላሆን እንደሚገባ፤ እንዱሁም ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዲይ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዲዩ ልዩ ባህርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሉገነዘበው የሚችለው ተደርጎ ሉወሰድ እንደሚገባ ይህ ሰበር ችልት በመዝገብ እና ላልችም ተመሳሳይ መዛግብት ውሳኔ ሰጥቷል። ስለሆነም በወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67 መሰረት የዋስትና መብት የሚነፈግባቸው ምክንያቶች ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር እየተመለከቱ ሉመዝኗቸው የሚገባቸው ናቸው።
በተያዘው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ያልተቀበለው የዋስትና መብት ቢፈቀድላቸው የዋስትና ግዳታውን አክብረው ፍርድ ቤት በቀነ ቀጠሮው ይቀርባለ የሚል ዕምነት ሉጣልበት የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ነው። ለዚህ በምክንያትነት የተጠቀሰው ከፍ ሲል እንደገለፅነው የቀረቡት ክሶች ተደራራቢነት፤ ክሶቹ የያዙትን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን፤ የወንጀለ አይነት እና የድርጊቱ አፈፃፀም፤ ሉያስከትል የሚችለው ከፍተኛ ቅጣት፤ እንዱሁም አመልካች ያላቸውን የኢኮኖሚ አቅም ተጠቅመው ከሃገር አይወጡም የማያሰኝ ሁኔታ አለመኖሩን ነው።
እነዚህ ምክንያቶች ለግምቱ መነሻ እንዲይደረጉ በህጉ ክልከላ ካለመኖሩም በላይ በምክንያትነት ተቀባይነት ሉኖራቸው አይገባም የሚባልበት ሁኔታ ባለመኖሩ የስር ፍርድ ቤት በተጠቀሰው ምክንያት እና ግምት ላይ ተመስርቶ በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ማመልከቻውን ባለመቀበል በመወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈጽሟል ለማለት አልተቻለም።
በልላም በኩል ቅሬታው ለሰበር ችልት ሲቀርብ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ከዚህ ቀደም በሰበር መ/ ከሰጠው ትርጉም አንፃር ለማየትም እንዱቻል ተብል ቢሆንም በተጠቀሰው መዝገብ ተከሳሹ የብዙ ሃገር ፓስፖርትና ቪዛ በእጁ ስለሚገኝ ብቻ የዋስትና ግዳታውን አክብሮ ላቀርብ አይችልም ለማለት የሚያስችል በቂ መንደርደሪያ ምክንያት ስላለመሆኑ፤ እንዱሁም የዋስትና ግዳታውን አክብሮ እንዱቀርብ የሚያደርግ ትዕዛዝ መስጠት እንደሚቻል የተወሰነበት ከመሆኑ ውጭ በሁለቱ መዛግብት የቀረበው ክርክር እና ዋስትና ለመከልከል መንደርደሪያ የተደረጉት ምክንያቶች ተመሳሳይ ናቸው የሚባለ ሆነው አላገኘናቸውም።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት በህጉ ተቀባይነት የላቸውም የማይባለ ምክንያቶች ላይ በመመስረት አመልካች የዋስትና መብት ቢፈቀድላቸው የዋስትና ግዳታውን አክብረው ፍርድ ቤት በየቀጠሮው ይቀርባለ የሚል ዕምነት ሉጣልበት የሚያስችል ሁኔታ የለም በማለት በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ማመልከቻውን በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67/ሀ/ መሰረት ባለመቀበል በመወሰኑ፤ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የይግባኝ ማመልከቻውን ባለመቀበል በመወሰኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወ/መ/ ጥቅምት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የተሰጠው ብይን፤ እንዱሁም በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ይ/መ/ ጥቅምት 15 ቀን 2009 ዓ.ም የተላለፈው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 75/2/ መሰረት በአብላጫ ድምፅ ፀንቷል። መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.