ወንጀል ፈጽሞ የተከሰሰን ህፃን ደህንነት ሉጠበቅበት ሥለሚችልበት አግባብ ለአዋቂ ጥፊተኞች የተደነገጉት መደበኛ ቅጣቶች ለወጣት ወንጀል አድራጊዎች ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ስለመሆኑ፡- XXXI የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህግ መንግሥት አንቀጽ 36 (2)፣ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 3(1)፣ የአፍሪካ የህፃናት መብቶች ደኅንነት ቻርተር በአንቀጽ 4 (1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 53 (1)፣ 157፣ 168 የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ 171፣180
No summary available.
ህዲር 30 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጰውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- ህፃን አድማሱ አገዘ--ከወልዱያ ማረሚያ ቤት ጉዲይ የምትከታተል እህቱ እየሩሳላም አገዘ ቀርባለች ተጠሪ፡- የአማራ ክልል ዓቃቤ ህግ አቶ ታራቀኝ አረጋ ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች በተከሰሰበት የግብረ ሥጋ ድፍረት ወንጀል በመፈጸም ጥፊተኛ ተደርጎ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በጉባ ላፍቶ ወረዲ ፍርድ ቤት የተወሰነበትን የሰሜን ወል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማጽናቱ እንዱሁም የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በማለት ቅጣቱን አሻሽል የወሰነበትን በመቃወም አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የአሁኑ አመልካች እድሜው 11 (አስራ አንድ) ዓመት ሲሆን በጉባላፍቱ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 0200915 እድሜዋ 13 ዓመት ያልሞላትን የአራት ዓመት ህፃን ልጅ አፀደ ምስጌን አስገድድ ክብረ ንጽህናዋን የደፈራት በመሆኑ በፈጸመው የህፃናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል ተከሷል በማለት በወንጀል ህግ ቁጥር 627(1) መሰረት ክስ ቀርቦበት በዚሁ ጥፊተኛ ተብል በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በማለት የተወሰነበትን በመቃወም ለሰሜን ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ የወረዲ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናት ያሰናበተው በመሆኑ ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ ሰበር ሰሚ ችልቱም ጥፊተኝነቱን በማጽናት አልፍ ቅጣቱ በምን መልክ ይፈጸም የሚለውን በአብላጫ ድምፅ ወደ 5(አምስት) ዓመት ጽኑ እስራት ዝቅ በማድረግ አሻሽል እንዱቀጣ ውሳኔ አስተላልፎል።
የአሁኑ አመልካች እድሜው የ11 (አስራ አንድ) አመት ህፃን መሆኑን ጠቅሶ ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ማስረጃ እንዲልቀረበበት እና ጥፊተኛ ልባል እንደማይገባው እንዱሁም ጥፊተኛ ቢባል እንኳን ቅጣቱን በማረሚያ ቤት ከላልች አዋቂ ታራሚዎች ጋር መታሰር እንደላለበትና በቤተሰቦቹ ሥር ሆኖ ክትትል ላደረግበት እንደሚገባ ገልጾ ቅሬታውን አቅርቧል።
የሰበር ሰሚ ችልት የአመልካች እድሜ 11 ዓመት መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ቅጣቱ በወንጀል ሕግ ቁጥር 157 እስከ 168 ባለት ድንጋጌዎች ለምን መፈጸም እንደላለበት የሥር ፍርድ ቤቶች ሳይገልጹ በመደበኛ የቅጣት ድንጋጌዎች የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለት የክልለ ዓቃቤ ህግ መልስ እንዱሰጥበት ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪም አመልካች ቅጣቱን ከአዋቂ ታራሚዎች ጋር ይፈጸም ቢባል በአመልካች ላይ ሉያስከትል ከሚችለው ጉዲት አንጻር ዕድሜውን መሰረት ያደረገ የቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃ ተፈጻሚ ቢሆን እንደማይቃወም ገልጾ በቁጥር ወየሃ-424/08 በቀን 9/05/2008 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል።
የክርክሩ ሂደት አጠር ባለመልኩ ከላይ እንደተመዘገበው ሲሆን ጉዲዩን ከስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ፣በዚህ ችልት ከተደረገው ክርክር፣ አጣሪው ከያዘው ጭብጥ እንዱሁም አግባብነት ካለው ህግ አንጻር መርምረናል። አካለ መጠን ያላደረሱ ወጣቶች ወንጀል ፈጽመው በተገኙ ጊዜ የሚደረገው የክስ ሥነ ሥርዓት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 171 እና ተከታዩቹ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። በነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት የምርመራውም ሆነ የክስ ሥነ ሥርዓት የሚመራው በፍርድ ቤት ክትትልና ቁጥጥር ነው። የቀረበው ክስ ከአስር ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እስራት ወይም በሞት የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ አቃቤ ህግ የክስ ማመልከቻውን አዘጋጅቶ እንዱያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዱሚሰጥ በተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 172 (3) ተደንግጓል። እንዱሁም አካለ መጠን ያልደረሰው ወጣት ከአስር ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እስራት ወይም በሞት በሚያስቀጣ ወንጀል በተከሰሰ ጊዜ ፍርድ ቤቱ አካለ መጠን ያልደረሰውን ወጣት የሚረዲው ጠበቃ ያዝለታል በማለት በዚሁ የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 174 (ለ) ላይ ተደንግጓል።
አካለ መጠን ያልደረሰ ወጣት የተከሰሰበትን የሚሰማው ችልት በልላ ነገር ተሰይሞ ከሚያነጋግረው አኳኋንና ሁኔታ የተለየ እንደሆነ የሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 176 (2) ደንግጓል።እነዚህ ድንጋጌዎች የሚያስገነዝቡት አካለ መጠን ያልደረሰ ወጣት በተከሰሰ ጊዜ የወጣቱን እድሜ ባገናዘበ መልኩ ያለውን የአእምሮ ብስለት፣ስለ ጉዲዩ ያለውን አረዲድ፣የሞራል ሁኔታ፣ስለተከሰሰው ህፃን ደህንነት ህግ አውጪው ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ አሟጋች ፍርድ ቤት ስለ ጉዲዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ክርክሩን እንዱመራ ለማድረግ ታስቦ ነው የሚል ድምዲሜ ላይ ያደርሳል። ይህም ስለ ህፃናት መብት ከተደነገገው ከኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲዊ ሪፐብላክ ህገ መንግሥት አንቀጽ 36 (2) ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰደበት ጊዜ በመንግሥታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዲደር ባለሥልጣኖች ወይም በህግ አውጪ አካላት የሕፃናት ደኅንነት በቀደምትነት መታሰብ አለበት በማለት ከተደነገገው ድንጋጌ ጋር የሚጣጣም እንደሆነ ለመመልከት ይቻላል። በህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 3(1) ላይ የሰፈረው ይህ መርህ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት በሚወስዶቸው እርምጃዎች ለህጻናት ጥቅምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው መሆኑን ያሳስባል። የአፍሪካ የህፃናት መብቶች ደህንነት ቻርተር በአንቀጽ 4 (1) ላይ በተመሳሳይ መልኩ ደንገጓል። ወንጀል ፈጽሞ የተከሰሰ ህፃን ደህንነት የሚጠበቀው የህፃኑን ሥነ ልቦና በመጠበቅ፤በክርክር ሂደት የሚደርስበትን መሸማቀቅ በመከላከል፤ እንዲይጨናነቅ በማድረግ፣ አዋቂዎችን በሚያስችለበት ችልት አብሮ እንዲይሆን በማድረግ፤ የሚረዲው ጠበቃ እንዱኖር በማድረግ ነው።
በዚህ መሰረት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉም ሆነ የወንጀል ህጉ ለህፃናት ወንጀል ፈጻሚዎች ከአዋቂዎች የተለየ የምርመራ፣ የክስ፤ የፍርድ እና የቅጣት ሁኔታን ማስቀመጥ ያስፈለገው ህገ መንግሥቱ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው አህጉራዊ እና ዓለም አቀፊዊ ስምምነቶች ላይ ከተደነገጉ የህፃናት መብቶች በእጅጉ ለማያያዝ ታስቦ ነው። የዚህም አስፈላጊነት መደበኛ የክርክር ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ሳይሆን በህፃናት ላይ ለጥፊተኝነት የሚወሰን ቅጣት ማስተማርና ማረም እንጂ መበቀል እንዲይሆን ታሳቢ አድርጎ ህፃናት በአከባቢያቸው አብሮዋቸው የሚውለው፣ የሚያዩት፣የሚማሩበት በተለይም በምርመራ፣ ክስ፣ ፍርድ እና የቅጣት አፈጻጸም ላይ ጥንቃቄ ካልተደረገ እነርሱን ከመጉዲት አልፍ የመጡበትን ማኅበረሰብ፣አካባቢና ሀገር የሚጎዲ ማንነት እንዲይከሰት ነው።በተጨማሪም ህፃናት እራሳቸውን የሚጠብቁና የሚቆጣጠሩ ባለመሆናቸው ያጠፈት ጥፊት ቢኖር እንኳ እኩል ከአዋቂዎች ዓይነት የቅጣት አፈጻጸም ከመከተል ይልቅ ስለወደፉት መልካም አስተዲደግ እና ደኅንነታቸው ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ ነው።
ይህን ዓላማ ለማሳካትም ሲባል ከህገ መንግሥት አንቀጽ 36 (2) እና (3)፣ ከአህጉሩና ዓለም አቀፍ ስምምነት ሰነድች በተጨማሪ በዝርዝር የኢፋዳሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 157 እስከ 168 እና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ 171 እስከ 180 ላይ ዝርዝር የምርመራ፣ የክስ፣ የፍርድ እና የቅጣት አፈጻጸም ድንጋጌዎችም ሥራ ላይ እንዱውለ የማድረግ ኃላፉነትና ግዳታ የተጣለው በፍርድ ቤት ላይ ነው። በልላ አነጋገር በወንጀል ለተከሰሱ ህፃናት ምቹ የሆነ የክርክር መሰማት ሥርዓትን ማስጠበቅና ማስከበር በዓለም አቀፍ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን፣ በአፍሪካ የህፃናት መብቶች ቻርተር፣ በኢፋዳሪ ህግ መንግሥት፣በወንጀል ህግ እና በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት በተደነገገው መሰረት የፍርድ ቤት ኃላፉነት ነው። የተያዘውን ጉዲይ የተመለከተው የጉባላፍቶ ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚያመለክተው ከላይ የተገለጹትን ሥነ ሥርዓታዊ ድንጋጌዎች ተከትል የተደረገ ክርክር አይደለም። ፍርድ ቤቱ በዚህ ረገድ የሥነ ሥርዓት ግድፈት እንደፈጸመ መገንዘብ ተችሎል።
የጥፊተኝነት ውሳኔን በተመለከተ አመልካች የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት የፈጸመ መሆኑ በሥር ወረዲ ፍርድ ቤት በማስረጃ ተረጋገጦ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
ቅጣትን በተመለከተ እድሜያቸው ከዘጠኝ እስከ አስራ አምስት ዓመት የሞላቸው ወንጀል ያደረጉ ወጣቶች የሚወሰንባቸው ቅጣቶቸና የጥንቃቄ እርምጃዎች ከአንቀጽ 157 እስከ 168 የተደነገጉ ብቻ ናቸው። ለአዋቂ ጥፊተኞች የተደነገጉት መደበኛ ቅጣቶች ለወጣት ወንጀል አድራጊዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፤ ከአዋቂዎችም ጋር አይታሰሩም በማለት የወንጀል ህግ አንቀጽ 53 (1) ይደነግጋል። በወንጅል ህግ አንቀጽ 168 (2) ወጣቱ የፈጸመውን ወንጀል ከባድነትና ጥፊቱንም በፈጸመበት ጊዜ የነበረውን የዕድሜ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ታስሮ የሚቆይበትን የጊዜ ልክ ፍርድ ቤቱ ይወስናል። ጊዜውም ከአንድ ዓመት ሳያንስ እስከ አስር ዓመት ሉደርስ ይችላል በማለት ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሚወሰነው ቅጣት ከአንድ ዓመት እስከ አስር ዓመት ሲሆን የሥር አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶችን የቅጣት ውሳኔን በማሻሻል አመልካች በአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። ቅጣቱንም የወልዲያ ማረሚያ ቤት እንዱያስፈጽም በአብላጫ ድምፅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አነስተኛው ድምፅ የአመልካችን አቆያየት በተመለከተ የወንጀል ህግ ቁጥር 168 (1) ሀ) ላይ ከወንጀለ ከባድነት አንጻር ወንጀለኛው ወደ ፀባይ ማረሚያ ተቋም ሉላክ እንደሚችል ቢገልጽም ይህ ዓይነት የማረሚያ ተቋም በአሁኑ ጊዜ የላለ መሆኑ ግልጽ ነው። የወንጀል ህግ ቁጥር 53 (1) ደግሞ በዚህ እድሜ ክልል የሚገኙ ወንጀለኞች ከአዋቂዎች ጋር አይታሰሩም በማለት ግልጽ የሆነ ክልከላ አስቀምጧል። ይህ ከመሆኑ አንጻር አመልካች ወደ ማኅበረሰቡ እንዱቀላቀል ተደርጎ ፀባዩ በፖሉስ ክትትል ላደረግበት ሲገባ ግልጽ የሆነውን የህግ ክልከላ በመተላለፍ አብላጫው ደምፅ አመልካች ከአዋቂዎች ጋር እንዱታሰር መወሰኑ ተገቢነት የለውም በማለት ከአብላጫው ድምፅ ተለይቷል።
የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አጣሪ አቤቱታውን ሲያስቀርብ የአመልካች እድሜ 11 ዓመት መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ቅጣቱ በወንጀል ሕግ ቁጥር 157 እስከ 168 ባለት ድንጋጌዎች ለምን መፈጸም እንደላለበት የሥር ፍርድ ቤቶች ሳይገልጹ በመደበኛ የቅጣት ድንጋጌዎች የመወሰኑን አግባብነት መመርመር ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለት ጭብጥ የያዘውም የአነስተኛውን ድምፅ ልዩነት ሀሳብ ህጋዊ መሰረት ያለው መሆኑን ተመልክቶ ነው ወደ ሚል ድምዲሜ ያደርሰናል።
እኛም የስር ፍርድ ቤት ሁለት ዳኞች በልዩነት ያነሱትን እንዱሁም አጣሪው የያዘውን ጭብጥ የምንስማማበት ነው።
ይህ እንዲለ ሆኖ ይህ ችልት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተገቢውን ባለሙያ በመመደብ ስለ አመልካቹ ህፃን ጠባይ፣ ስለአስተዲደጉ፣ ስለኑሮውና ስለህይወቱ እንዱሁም የአካልና የአእምሮ ሁኔታውን አስጠንቶ ውጤቱን እንዱያቀርብ ሚያዝያ 6 ቀን 2008 ዓ/ም ትዕዛዝ ሰጥቷል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ትዕዛዝ መሰረት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሙያ በመመደብ በወልዱያ ማረሚያ ቤት ስለሚገኘው ህፃን አድማሱ አገዘ ሁኔታ ያጠናውን ጥናት በቁጥር ሂ/4-9-3/17920 ሐምል 19 ቀን 2008 ዓ/ም በተጻፈ መሸኛ ደብዲቤ ልኳል። ጥናቱም ከአመልካቹ፣ ከቤተሰቦቹ፣ ከጓደኛው፣ ከጎራቤቶቹ እና ከማረሚያ ቤቱ ሙያተኞች የተገኘ መረጃ እንደሆነ ሲገልጽ የሚከተለትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ለመውሰድ የሚረደ ሃሳቦች ለማግኘት እንዲስቻለ ያመለክታል። እነዚህም፡-
አመልካች ወንጀለን መፈጸሙን ባያምንም ከዚህ በኃላ ፀባዩን ለማሻሻልና ትምህርቱ ላይ ብቻ ሙለ ትኩረቱን ለማድረግ ማቀደ፣
ህፃኑ ከቤተሰቡ እና ከጓደኞቹ ተለይቶ ማረሚያ ቤት መግባቱ ከባድ እንደሆነ በመረዲቱ እና ለወደፉት ከወንጀል ነክ ነገሮች ለመራቅ ማቀደ፣
ህፃኑ ወደ ወላጅ እናቱ ጋር ለመኖር ከተመለሰባቸው ምክንያቶች አንደ በሥራ ጫና ምክንያት ትምህርቱን ላለማቋረጥ ባደረገው ትግል ከወላጅ አባቱ እና ከእንጀራ እናቱ ጋር አለመስማማት ተፈጥሮ መሆኑ፣
ከማረሚያ ቤቱ ሙያተኞች ለመረዲት እንደተቻለው ህፃን አድማሱ/አመልካቹ/ ታዛዥ እና ምክርም የሚሰማ መሆኑ፤
ከቤተሰቦቹ፣ ከጓደኛው እና ከመኖሪያ አካባቢው የተገኘውም መረጃ አመልካች በባህሪይው ጨዋ እና ምስጉን እንደሆነ እና ከዚህ በፉት በወንጀል ድርጊት ተከሶም ሆነ ጥፊተኛ ተብል እንደማያውቅ የሚያሳይ በመሆኑ፣
የአመልካች ወላጅ እናትም ህጻኑ ወደ ወንጀል ድርጊት ሉገባ የቻለው በተለያየ ቦታ በማደጉ ከአስተዲደግ ክፍተት እና ከቤተሰብ ክትትል እና ቁጥጥር ማነስ ላሆን እንደሚችል በማመን ወደፉት ኃላፉነታቸውን በሚገባ ለመወጣት እንዲቀደ የገለጹ መሆኑ እና የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ቤተሰቡ ተበዲይን ለመካስ ጥረት ማድረጋቸው በጥናቱ የተካተቱ ነጥቦች ናቸው። እነዚህ የጥናት ውጤቶች በአመልካች ላይ ሉወሰድ የሚገባው ቅጣት ምን ላሆን እንደሚገባ ግንዛቤ የሚሰጡ ሆነው ተገኝተዋል።የወንጀል ህግ ቁጥር 157 አስከ 168 ላይ የተመለከቱት የቅጣት እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ተፈጻሚ ሲሆኑም የወጣቱን ፀባይ እና የቀድሞ ባህሪው ምን እንደሚመስል መገንዘብ እንደሚያስፈልግ የደነገገ ሲሆን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 177 (2) ድንጋጌም ይህንን ያረጋግጣል። ከዚህ አንጻር አመልካች የፈጸመው የወንጀል ድርጊት ከእሱ ዕድሜ በታች ላይ የምትገኘው ህፃን ልጅ ላይ ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸሙ ወንጀለ ከባድ የሚባል ነው። ከዚህ አንጻር አመልካች ጥፊተኛ ተብል የቅጣት እርምጃ መወሰደ ተገቢነት ቢኖረውም የቅጣት አፈጻጸም ሲታይ በምን መልኩ ተፈጻሚ መሆን አለበት የሚለው ጉዲይ ከአመልካቹ እድሜ እና ስለ ነበረው ባህሪ እና መልካም ፀባይ በመነሳት ከወንጀል ህግ ቁጥር 157 እስከ 168 አኳያ የተለያዩ እርምጃዎች ተፈጻሚ መሆን እንደሚገባቸው ህጉ ያስቀመጠ በመሆኑ የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት ከአዋቂ የህግ ታራሚዎች ጋር ይፈጽም ቢባል ወደፉት በአመልካች ላይ ሉያስከትልበት ከሚችለው የሞራል እና የተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች አኳያ ታይቶ ሉወሰን የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም ከላይ በዝርዝር እንደተገለጸው የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የክስና የክርክር ሂደት የመሩበት አካሄድ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት፣ የወንጀል ህጉን መሰረታዊ ድንጋጌዎች እና በህገ መንግሥቱ ስለህፃናት የተቀመጡ መርሆችን የተከተለ ካለመሆኑም ባሻገር ፍርድ ቤቶቹ ቅጣቱን ሲወስኑ እንዱሁም ቅጣቱ ከአዋቂ ታራሚዎች ጋር እንዱፈጸም ትዕዛዝ መስጠታቸው ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የጉባ ላፍቶ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 0200915 በቀን 04/06/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ፣የሰሜን ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0205865 በቀን 10/06/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ፣የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በቁጥር 03-10537 ሐምል 28 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195/2/ለ/2/ መሰረት ተሻሽሎል።
የወንጀል ህግ ቁጥር 168/1/ሀ/ ከወንጀለ ከባድነት አንጻር አካለ መጠን ያልደረሰ ወንጀል አድራጊ ወደ ፀባይ ማረሚያ ተቋም ሉላክ እንደሚችል ቢደነግግም ይህ ዓይነት ማረሚያ ተቋም በአሁኑ ጊዜ ያልተሟላ ሲሆን የወንጀል ህግ ቁጥር 53/1/ ደግሞ በዚህ እድሜ ክልል የሚገኙ ወንጀል አድራጊዎች ከአዋቂዎች ጋር አይታሰሩም በማለት ደንግጓል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች አንጻር አመልካች ወደ ማኅበረሰቡ እንዱቀላቀል ተደርጎ በፖሉስ ክትትል ላደረግበት ይገባል። በመሆኑም በሥር ፍርድ ቤቶች የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ በወንጀል ህግ ቁጥር 171 እና 192 መሰረት ታግድ እንዱቆይ ተወስኗል።
ስለ አመልካቹ መልካም አስተዲደግና ባህርይ ክትትል እንዱያደርጉ ለአመልካቹ እናትና አባት እንዱገለጽ ታዟል፤ ይጻፍ።
አመልካች ከማረሚያ ቤት ወጥቶ በማኅበረሰቡ ውስጥ በሚቆይበት ጊዜ ለፈተና በተሰጠው ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን ባህርይ እንደከታተል ለሚገኝበት ወረዲ ፖሉስ በጽሁፍ እንዱገለጽ ታዟል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለወልድያ ማረሚያ ቤት በመሸኛ እንዱደርሰውና አመልካቹንም እንዱፈታው የመፍቻ ዋራንት እንዱጻፍ ታዟል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.