በወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ስር የሚገኝን ተጠርጣሪ በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ተጠርጣሪው በከተማው ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ /የመታወቂያ/ አድራሻ የለውም በማለት የዋስትና መብቱን መከልከል ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ፣ አንቀጽ 19/6/፣ 25 እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 69/ሀ/
No summary available.
ህዲር 8 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተክሉት ይመስል ቀነዓ ቂጠታ ክፍለጽዮን ማሞ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- መሐመድ እንድሪስ ተጠሪ፡- የኢትዮጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሀዋሳ ቅርንጫፍ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በዋስ ቢለቀቅ ቀነ ቀጠሮውን አክብሮ ላቀርብ፣ስለማይችል በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ መብቱ ተነፍጎ በማረሚያ ቤት እንዱቆይ በማለት የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ብይን አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም /የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። የጉዲዩ መነሻ ተጠሪ አመልካች አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 168/2/ በመተላለፍ ንብረትነቱ የደርባን ትራስፖርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሆነ የሰላዲ ቁጥር 430 Volvo መኪና የቀረጥና ታክስ መጠናቸው ብር 88,613.33 /ሰማንያ ስምንት ሺ ስድስት መቶ አስራ ሶስት ብር ከሰላሳ ሶስት ሳንቲም/ የሆኑ እቃዎቹን በመጫን ከዱላ ወደ ሀዋሳ መስመር ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ/ም ይዞ ሲጓዝ የተያዘ በመሆኑ የኮንትሮ ባንድ ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ እኔ ረመዲን ፆም ጾሜ እያፈጠርኩ እያለሁ፣ ረዲቱ ሳላየው የጫናቸው እቃዎች ስለሆነ ጥፊተኛ አይደለሁም። የዋስ መብቴ ይከበርልኝ በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ የአመልካችን በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ እቃወማለሁ። ዋስትናውን የምቃወመው ተከሳሹ /አመልካች/ በመታወቂያው ላይ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ኮልፋ ቀራንዮ ወረዲ 13 የቤት ቁጥር 2654 እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በመንጃ ፈቃድ ላይ አዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር 352 እንደሆነ የተገለጸ በመሆኑ ተከሳሹ ሆነ ብል አድራሻውን የሚለዋውጥ በመሆኑ በቀጠሮ ቀን ላይ ላቀርብ ይችላል ብለን ስለማናምን የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መቃወሚያ አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን መቃወሚያ በመቀበል አመልካች የተለያየ አድራሻ ያለው በመሆኑ ላይቀርብ ይችላል በማለት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን አጽንቶታል። አመልካች የመንጃ ፈቃድ ያወጣሁት በ1992 ዓ/ም ነው። በዚያ ጊዜ የምኖርበት የነበረው ቤት ለቅቄዋለሁ። ደርባን ትራንስፖር ኃ/የተ/የግል ማህበር ስቀጠር የምኖርበት የነበረው አድራሻ ደግሞ ከስድስት አመት በፉት ስኖርበት የነበረው ነው። አሁን የምኖረው በልላ ቦታ ሲሆን ይህንን አድራሻዬን ለመርማሪ ፖሉስ አስመዝግቢያለሁ። ስለዚህ በተለያየ ጊዜ ከተለያየ ቦታ መኖሬ በቀጠሮው ቀን ላቀርብ አይችልም ከሚል መደምደሚያ ላይ የማያደርስ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይን ሉሻርልኝ ይገባል በማለት አመልክቷል። ተጠሪ አመልካች ሶስት የተለያዩ አድራሻዎች ያለት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው በወንጀል የተከሰሰው በዋስትና ወረቀት ተለቅቆ ጉዲዩን የመከታተል መብት ያለው መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ንዐስ አንቀጽ 16 ተደንግጓል። ከዚህ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ የምንገነዘበው በወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው በዋስ መለቀቅ መሰረታዊ መብት ሲሆን ህግ አውጭም በልዩ ሁኔታ በህግ በደነገጋቸው ምክንያቶችና ፍርድ ቤቶች የሚቀርብላቸው ክርክር መረጃና ማስረጃ በሚሰጡት ብይን የተከሰሰ ሰው በዋስ የመለቀቅ መብቱ የሚነፈግበት ሁኔታ እንዲለ መገንዘብ ይቻላል።
አመልካች የተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ በዋስ የመለቀቅ መብቱን የሚገድብ አይደለም።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በዋስ ለመለቀቅ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 67/ሀ/ በመጥቀስ ነው። ድንጋጌው ተከሳሹ በዋስ ቢለቀቅ የዋስትና ግዳታውን በማክበር በቀነ ቀጠሮው ላቀርብ የማይችል መሆኑን ፍርድ ቤቱ ካመነ፣ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ለማድረግ የሚችል መሆኑን ይደነግጋል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስትና ግዳታውን አክብሮ ላቀርብ አይችልም ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚደርሰው በዘፈቀድ አይደለም። ዐቃቤ ህግ ተከሳሹ ቀጠሮውን አክብሮ ሉመጣና የዋስትናውን ግዳታ ሉያከብር አይችልም ከሚል መደምደሚያ ላይ ፍርድ ቤቱ ሉደርስባቸው የሚችለ በቂ ምክንያትና መረጃ የማቅረብ ግዳታ አለበት።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች የመንጃ ፈቃድ ያወጣው 1992 ዓ/ም መሆኑን በዚያን ወቅት ይኖርበት የነበረውን አድራሻ የለቀቀ በመሆኑ አሁን ከሚሰራበት ድርጅት ሲቀጠር ይኖርበት የነበረው አድራሻ ከበፉቱ የተለየ መሆኑን፣ የአመልካችን መንጃ ፈቃድና የመስሪያ ቤት መታወቂያ ካርድ በማየት ለመረዲት ይቻላል። አመልካች በ2008 ዓ/ም በተሰጠው የቀበላ ኗሪነት መታወቂያ ካርድ ላይ የተገለጸው አድራሻ ከስድስት አመት በፉት ደርባን ትራንስፖርት ሲቀጠር ይኖርበት ከነበረው አድራሻ የተለያየ መሆኑን ከግራ ቀኙ ክርክር ተገንዝበናል። አመልካች የመንጃ ፈቃድ ሲያወጣ፣ ደርባን ትራንስፖርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲቀጠርና አሁን የሚኖረው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በተለያየ ክፍለ ከተማ፣ ወረዲና የቤት ቁጥር መሆኑ አመልካች ቋሚ አድራሻ የለውም ከሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም።
የመኖሪያ ቤት ከግለሰብ ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች፣ በአመታት ውስጥ ሳይሆን በወራት ወይም በቀናት ልዩነት የተከራዩትን ቤት በተለያየ ምክንያት ለቀው በልላ ክፍለ ከተማ፣ ላላ ወረዲ ላላ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ መሆኑንና በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት እጥረት መኖሩ፣መንግስት በፖሉሲዎቹና ስትራቴጂዎች በግልፅ ያመነውና የአዱስ አበባ የቤቶች ኮንስትራክሽን ልማት ኤጀንሲ በአዋጅ በመቋቋም የጋራ መኖሪያ ቤቶች መምሪያ ቤቶች በመገንባት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑ በግልጽ የሚታወቅና ማስረጃ እንዱቀርብለት የማያስፈልግ ፍሬ ነገር ነው። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች መንጃ ፈቃድ ሲያወጣ የዛሬ አስራ አምስት አመት ይኖርበት የነበረውን አድራሻ አስመዝግቧል። ይህንን መኖሪያ አድራሻው ከስድስት አመት በፉት ደርባን ትራንስፖርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲቀጠር፣ የለቀቀው መሆኑን በመግለጽና አዱሱን አድራሻውን ለመስሪያ ቤቱ አሳውቋል። ባሁኑ ወቅት የሚኖርበት አድራሻ በመ/ቤት ሲቀጠር ካስመዘገበው አድራሻ የተለየ መሆኑን የሚያረጋግጥ የቀበላ መታወቂያ ማቅረቡ፣ አመልካች በአድራሻው ተፈልጎ እንዲይገኝ ሆነ ብል የፈጠረው ዘዳ ሳይሆን፣ አመልካች የራሱ የሆነ ቋሚ መኖሪያ ቤት ስለላለው በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩና ቤት እየተከራየ የኖረ መሆኑን እውነታ /ፍሬ ነገር/ የሚያረጋግጥ ነው።
በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያየ ክፍለ ከተማዎች፣ ወረዲዎች በተለያዩ ጊዜ እየተዘዋወረ ቤት እየተከራዩ የሚኖሩ ሰዎች፣ በዋስ ቢለቀቁ ፣የዋስትና ጉዲያቸውን አክብረው በቀነ ቀጠሮው ቀን ሉቀርቡ አይችለም የሚለውን መቃወሚያና መከራከሪያ ፣ሰዎች አዱስ አበባ ውስጥ የራሳቸው የሆነ የመኖሪያ ቤት ስለላላቸው ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ ቤት እየተከራዩ የሚኖሩ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ የዋስትና መብታቸው እንዲይፈቀድ የሚጠይቅ፣ የሰዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በአዱስ አበባ ከተማ አንድ ቋሚ የሆነ አድራሻና መኖሪያ ቤት ስለላላቸው ብቻ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 19 ንዐስ አንቀፅ 6 የተረጋገጠላቸው በዋስ የመለቀቅ መብት እንዱነፈግ የሚጠይቅ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 25 የተደነገገውን በሕግ ፉት እኩል የመሆንና እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብትን የሚጥስ መቃወሚያና መከራከሪያ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው መቃወሚያ አይደለም። ከዚህ አንፃር አመልካች በተለያየ ጊዜ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች፣ ወረዲዎችና ቤቶች ውስጥ የኖረ መሆኑን የሚያረጋግጡ ሰነድች ማለትም የመንጃ ፈቃድ፣ የሚሰራበት መስሪያ ቤትና የመታወቂያ ካርድና የቀበላ ኗሪዎች መታወቂያ ይዞ መገኘቱ አመልካች በዋስ ቢለቀቅ የዋስትና ግዳታውን አክብሮ በቀነ ቀጠሮው ላቀርብ አይችልም ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 69/ሀ/ ድንጋጌዎች ቋሚ የመኖሪያ ቤት ባለመኖሩ ምክንያት በተለያየ ጊዜ የተለያየ ቦታ እየተዘዋዋረ ቤት እየተከራየ መኖሩን መነሻ በማድረግ ብቻ ተከሳሹን የዋስትና መብቱን ለመንፈግ ታስቦ የተደነገገ ድንጋጌ አይደለም። ከዚህ አንፃር ሲታይ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በዋስትና ለመለቀቅ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ 19 ንዐስ አንቀፅ 6 እና የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 69/ሀ/ ከተደነገገው ውጭ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነዉ በማለት ወስነናል።
አመልካች የተከሰሰበት የሕግ ድንጋጌ በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ መብትን የማያስከለክል በመሆኑና ተጠሪ አመልካች በዋስትና እንዲይለቀቅ ያቀረበው መቃወሚያና መረጃ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 69/ሀ/ መሰረታዊ ይዘትና አላማ ውጭ በመሆኑ፣ አመልካች ለብር 20‚000 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚበቃ ዋስ አቅርቦ ወይም ገንዘብን አስይዞ በዋስ ተለቅቆ ሉከራከር ይገባል በማለት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 75 መሰረት ውሳኔ ሰጥተናል።
የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወንጀል መዝገብ ሰኔ 28 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል ይግባኝ መዝገብ ሐምል 12 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች ብር 20‚000 /ሃያ ሺህ ብር/ በማስያዝ ወይም ለዚህ ገንዘብ የሚበቃ ዋስ በማቅረብ የተከሰሰበትን ወንጀል በዋስ እያቀረበ ይከራከር በማለት ወስነናል። ውሳኔው ለሚመለከተው ክፍል ይፃፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.