የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ መመሪያ መሰረት በማድረግ በማረም የሚጠው ውሳኔ ከተጠየቀ ዲኝነት ውጭ ተሰጥቷል የሚያስብል ስላለመሆኑየቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2002 አንቀፅ 21(1) (ሀ) ፣ ወ/ሕ/ቁ 184(!0 (ለ) እና 194 (1) (ለ) 117877 አቶ ማሰረሻ ገሰሱ እና የፋ/ዓ/ሕግ 22/11/ 2008ዓ.ም 363 77. በሙከራ ደረጃ ለተፈፀመ ወንጀል ቅጣት እንደሚቀንስ በግልፅ በመመሪያ ቁ.2/2006 ላይ ባይደነገገም ነገር ግን በወንጀል ህጉ ቅጣትን በመሰለው እንዱያቀል ለፍ/ቤቱ በተፈቀደበት ሁኔታ መሰረት ቅጣትን አቅል ሉወሰን የሚችል ሰለመሆኑ ፤ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006 አንቀፅ 24 ፣ የወ/ሕ/ቁ 31 እና 180 119500 ወ/ሮ ፀሀይ ውብዬ እና ፋ/ዓ/ሕግ 22/11/ 2008ዓ.ም 367 XXIX 78. ለሽብር ተግባር የሚያገለግል ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል ተፈፅሟል የሚባልበት አግባብ፤ በልዩ ሁኔታ በህግ የማስረዲት ሸክም ወደ ተከሳሽ ከዞረባቸው ወንጀልች ውጭ ፤ ዓ/ህግ የሚያቀርበውን ክስ የወንጀል ደንጋጌውን የሚያቋቁሙት የህጋዊ ፣ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮችን የማሰረዲት ሸክም የመወጣት ግዳታ ያለበት ሰለመሆኑ፤ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 ፣ የወ/ሕ/ቁ 23(2) ፤ የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥ 652 102982 ት/ብ/ክ/መ/ዓ/ሕግ እና አቶ ቡሽራ ያህያ 26/11/ 2009ዓ.ም 371 79. የጉምሩክ ወንጀል ጋር በተያያዘ ፤ተከሳሽ በወንጀለ ጥፊተኛ ባይባልም ንብረቱ የሚወረሰው ሰለድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያሰረዲ አጥጋቢ ማስረጃ መቅረቡን ፍ/ቤቱ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው ስለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 104 እና አዋጅ ቁጥር 859/2006 XXX የወንጀል ተሳትፍ ተመጣጣኝና ተመሳሳይ ቅጣት ሉወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ቁጥር 196(1) ለሰበር ስርዓትም ተፈፃሚነት ያለውና ከተከሳሾች አንደኛው ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ውድቅ የሆነበትና አያስቀርብም የተባለን ተከሳሽ ጭምር ሉያካትት የሚገባ ስለመሆኑ፡የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣22 የወንጀል ሕግ አንቀጽ ፣4፣6 የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 አንቀፅ.3(2) ፀረ ሙስና ኮምሽን
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች- አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች- የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን - ዓቃቤ ህግ አልቀረቡም ተጠሪ- አቶ ልዐል አዲሙ ብዙነህ --ጠበቃ መአሪፍ ሰዑድ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ተጠሪው የኮንትሮባንድ ዕቃ የጫነው መኪና ሾፋር እና ባለቤት ከመሆኑም በላይ ወንጀለ በታወቀበት ጊዜም መኪናውን ያሽከረክር የነበረው እሱ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ በነፃ ይሰናበት መባለ እና፤ መኪናውም የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ሆኖ እያለ ይለቀቅ መባለ ከአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 እና 104 አንፃር ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
እንደመረመርነው የክሱ መነሻ ንብረትነቱ የስር 1ኛ ተከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) በሆነውና እራሱ በሚያሽከረክረው የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-93060 አ/አ በሆነ FSR መኪና ላይ ሆን ብል ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ከ2ኛ ተከሳሽ አቶ ጉላ እንዲለ (ረዲቱ) ጋር በመተባበር የ3ኛ ተከሳሽ አቶ ወገኔ ወርቅነህ ንብረት የሆኑትን 5 ካርቶን ጥፍር መቁረጫ፤
3 ብርድ ልብስ እና ሁለት ጎማ ጭኖ መስከረም 4 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ከሃረር ወደ መሃል አገር ሲጓዝ አዋሽ ጉምሩክ ኬላ በፍተሻ ተይዟል በሚል በሶስቱም ተከሳሾች ላይ የወንጀል ህግ ቁጥር 32(1)(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91/2/ ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል።
ተጠሪ ድርጊቱ መፈፀሙን ገልፆ ነገር ግን እኔ አልፈፀምኩትም ጥፊተኛም አይደለሁም በማለት ክድ የተከራከረ ሲሆን፤ 2ኛ ተከሳሽ (ረዲቱ) በበኩለ ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ እቃዉን ጭኛለሁ ኮንትሮባንድ መሆኑን አላወኩም አይቼ ባለመጫኔ ጥፊተኛ ነኝ 1ኛ ተከሳሽ አያውቅም ነበር ብሎል። 3ኛ ተከሳሽ በበኩለ ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ ንብረቱ የእኔ ነው ጥፍር መቁረጫ ኮንትሮባንድ መሆኑን ባለማወቅ ፈፅሜያለሁ ማወቅ ነበረብኝ ጥፊተኛ ነኝ በማለት አምኗል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የገቢ ረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን እንደ ክሱ ድርጊቱን ስለመፈፀማቸው አምነዋል በማለት ባመኑት መሰረት ጥፊተኛ ብል ቅጣት ወስኗል። 1ኛ ተከሳሽን በተመለከተ የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች በወቅቱ ፍተሻ ሲደረግ ተጠሪ የሚያሽከረክረው መኪና ላይ ዕቃውን ማግኘታቸውን ከመመስከራቸው ውጭ እንደ ክሱ አቀራረብ ሆነ ብል ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ጥቅም ለማስገኘት ብል የፈፀመው ለመሆኑ አለማረጋገጣቸውን፤ ተከሳሹም ዕቃው መገኘቱን ሳይክድ በእኔ እውቅና አልተጫነም በማለት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ ማሰማቱን፤ የቀረቡት የመከላከያ ምስክሮች በእለቱ ከተከሳሽ ጋር የራሳቸውን መኪና ይዘው የሽንኩርት ጭነት ጭነው ሳይለያዩ ተከታትለው መጓዛቸውን አሰበ ተፈሪ ላይ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን አንድ ላይ እራት ሲበለ ረዲቱ (2ኛ ተከሳሽ) አለመኖሩን እና 3ኛ ተከሳሽ አሰበ ተፈሪ ከተማ ላይ የተሳፈረ መሆኑን፤ 1ኛ ተከሳሽ ዕቃው በፍተሻ ሲገኝበት ጉድ ሰራኝ አሰበ ላይ ተማሪ ነው ብል ያሳፈረው ሰው ብል ሲናገር እንደነበርና በማያውቀው ሁኔታ እራት በሚበለበት ሰዓት 2ኛ ተከሳሽ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ድርጊቱን መፈፀሙን ማስረዲታቸውን፤ እንዱሁም 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ዕቃውን የጫኑት 1ኛ ተከሳሽ ሳያውቅ እንደነበር የሰጡት የዕምነት ቃል የመከላከያ ማስረጃውን እንደሚያጠናክር፤ ተጭኖ ለነበረው ጎማ የዕጅ በዕጅ ሽያጭ ደረሰኝ መቅረቡን በመጥቀስ ተጠሪ ድርጊቱን ሆነ ብል ወይም በቸልተኝነት ያልፈፀመው ስለመሆኑ፤ ይልቁንም ሉጠረጥር ወይም ሉገምት በማይችልበት ሁኔታ ከእውቅናው ውጭ የተፈፀመ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል በማለት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 149(2) መሰረት በነፃ እንዱሰናበት ወስኗል። ተጠሪ በነፃ የተሰናበተ በመሆኑም የተያዘውን መኪና በተመለከተ በአዋሽ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በአስተዲደር የገንዘብ ቅጣት ተቀጥቶ እንዱለቀቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች ይህን ውሳኔ እና ትዕዛዝ በመቃወም ለአፊር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ በወንጀለ ጥፊተኛ ልባል የሚችለው በመላ ሃሳቡ እና እውቀቱ ለፈፀመው ተግባር እንጂ ከእሱ እውቅና ውጭ ላልች ሰዎች በፈፀሙት ተግባር አብሮ ስለነበር ብቻ ኃላፉ እና ተጠያቂ የሚሆንበት ምክንያት የለም፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ ስለተሰጠ ብቻ በድርጊቱ ምንም አይነት ተሳትፍ ያልነበረውን ባለንብረት በማያውቀውና ባልተመሰከረበት ነገር ጥፊተኛ ማድረግ ስለማይገባና የዓቃቤ ህግን ክስና ማስረጃ በሚገባ ስለተከላከለ ከክሱ በነፃ እንዱሰናበት መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አፅንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የክልለ ፍርድ ቤቶች ባሳለፈት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት ለማሳረም ነው። አመልካች ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ ከፍ ሲል በመግቢያው የተጠቀሰው ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። በዚህ መሰረት ተጠሪ የስር ክርክራቸውን በማጠናከር መልስ የሰጡ ሲሆን አመልካቹም የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት ውሳኔዎችና አግባብነት ካላቸው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማያያዝ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ተጠሪ ተከላክሎል ተብል በነፃ እንዱሰናበት በመወሰኑ፤ እንዱሁም ተሸከርካሪውን በተመለከተ ተጠሪ አስተዲደራዊ ቅጣት ተቀጥቶ እንዱለቀቅለት በተሰጠው ትዕዛዝ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን በስር ፍርድ ቤት በማስረጃዎች ከተረጋገጡት ፍሬ ጉዲዮች እና አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
አመልካች በቅሬታቸው ክሱን አስረድተው እያለ እና ተጠሪም የቀረበበትን ክስ በአግባቡ ባልተከላከለበት ሁኔታ በነፃ መሰናበቱ እንዱሁም ተሸከርካሪው በተጠሪ ሲሽከረከር የነበረ ከመሆኑም ላላ የስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ጥፊተኛ መባላቸው በመኪናው የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙን ስለሚያረጋግጥ በአዋጁ አንቀፅ 104 መሰረት የውርስ ትዕዛዝ ለመስጠት ከበቂ በላይ ምክንያት እያለ ተሸከርካሪው እንዱለቀቅ ትዕዛዝ መሰጠቱ የህግ ስህተት ነው በማለት ተከራክረዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው የመኪናው ሹፋር እና ባለቤት ብሆንም ተዋዉዬ በህጋዊ መንገድ የጫንኩት ሽንኩርት ብቻ መሆኑን አጣርቼ ከተጓዝኩ በኋላ የስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች የእኔን አለመኖር ሽፊን በማድረግ ደብቀው እና እንዲይታይ በማድረግ የኮንትሮባንድ ዕቃውን መጫናቸውን የስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃዎች እና 2ኛና 3ኛ ተከሰሳሾ በዕምነት ከሰጡት ቃል አረጋግጠው ያሳለፈት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት ስለላለ ውሳኔው ሉፀና ይገባል ብለዋል።
በመሰረቱ የወንጀል ተጠያቂነት የሚኖረው በወንጀል ህጉ አንቀፅ 23(2) ሥር የተመለከቱት ህጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ሲሆን በተያዘው ጉዲይም ሞራላዊ ፍሬ ነገሩ የተሟላ መሆን ያለመሆኑን በመመልከት ውሳኔ መስጠት የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል። በወንጀል ህጉ አንቀፅ 57 እንደተመለከተው ለድርጊቱ ኃላፉ ላሆን የሚገባው ሰው አስቦ ወይም በቸልተኝነት አንድ ወንጀል ካላደረገ በቀር በወንጀል ጥፊተኛ የማይሆን ሲሆን፤
የፈፀመው ድርጊት በህግ የሚያስቀጣ ቢሆንም ምንም ጥፊት ያላደረገ ሆኖ ሲገኝ ሉፈረድበት አይገባም። ከዚህም ላላ በቸልተኝነት ወንጀል ማድረግን በተመለከተ ማንም ሰው በቸልተኝነት የወንጀል ተግባር አድርጓል የሚባለው ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል እያወቀ አይደርስም በሚል ግምት ወይም ባለማመዛዘን፤ ወይም ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ስለመሆኑ ከወ/ህጉ አንቀፅ 59(1) ግልፅ ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ ከፍ ሲል እንደተገለፀው በአመልካች ምስክሮች የተረጋገጠው ተጠሪ በሚያሽከረክረው መኪና ላይ ዕቃው በፍተሻ መገኘቱ ብቻ ስለመሆኑ፤ ከዚህ ውጭ እንደ ክሱ አቀራረብ ሆነ ብል ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ጥቅም ለማስገኘት ብል የፈፀመው ለመሆኑ አመልካች በማስረጃ አለማረጋገጡን፤ በአንጻሩ ተጠሪ በመከላከያዎቹ በእለቱ የሽንኩርት ጭነት ጭነው ከላልች አሽከርካሪዎች ጋር ሳይለያዩ ተከታትለው ይጓዙ እንደነበር፤ አሰበ ተፈሪ ላይ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን አንድ ላይ እራት ሲበለ ረዲቱ (2ኛ ተከሳሽ) ተጠሪ ያለመኖሩን አጋጣሚ ተጠቅሞ ተማሪ ነው በማለት 3ኛ ተከሳሽን ያሳፈረ መሆኑን፤ 1ኛ ተከሳሽ ዕቃው በፍተሻ ሲገኝበት ጉድ ሰራኝ አሰበ ተፈሪ ላይ ተማሪ ነው ብል ያሳፈረው ሰው ብል ሲናገር እንደነበር፤ በአጠቃላይ ዕቃው ተጠሪ በማያውቀው ሁኔታ በጉዞ መሃል ተደብቆ መጫኑን የስር ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል።
ከዚህ የክርክር ሂደት መገንዘብ የሚቻለው ፍሬ ነገሩን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዘን በህጉ ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ድርጊቱን ሆነ ብል ወይም በቸልተኝነት ያልፈፀመው ስለመሆኑ፤ በአንፃሩ ከነበረው ሁኔታ እና ከተጠሪ የሹፋርነት ኃላፉነት አንፃር ሉጠረጥር ወይም ሉገምት በማይችልበት ሁኔታ ከእውቅናው ውጭ የተፈፀመ መሆኑን በማረጋገጥ ውሳኔ መስጠታቸውን ነው። ይህ ደግሞ ተጠሪ አስቦ ወይም በቸልተኝነት ልባል በሚችል መልኩ ጥፊት መፈፀሙን የሚያሳይ አይደለም።
በመሆኑም ተጠሪ አስቦ ወይም በቸልተኝነት የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት ማድረጉ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ጥፊተኛ ልባል ይገባ ነበር በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር የወንጀል ህጉን አንቀጽ 23(2)፤ 57፤ 58 እና 59 ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
ላላው የክርክር ነጥብ ተሽከርካሪውን በተመለከተ በተሰጠው ትዕዛዝ ተፈፀመ የተባለውን የህግ ስህተት የሚመለከት ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪ ከቀረበባቸው የኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ በነፃ ተሰናብተዋል። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነውና በተጠሪ ሲሽከረከር የነበረው መኪና የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ መገኘቱ ተረጋግጦ 2ኛ ተከሳሽ (ረዲቱ) እና 3ኛ ተከሳሽ (ባለንብረቱ) ጥፊተኞች ተብለው የተቀጡ ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104 መሰረት መኪናው መወረስ ነበረበት በሚል ነው።
በመሰረቱ ተከሳሽ በነፃ የተሰናበተ እንደሆነ ተሽከርካሪው ሉወረስ የሚቻልበት ሁኔታ በአዋጁ አንቀጽ 104/3/ሀ/ ስር በተለየ ሁኔታነቱ (exceptional situation) ተመልክቷል። የተለየ ሁኔታነቱ መሰረታዊ ምክንያት ደግሞ የንብረት ውርስ ከወንጀል ቅጣቶች አንደ መሆኑ እና ቅጣት የሚመጣው የወንጀል ጥፊተኝነትን ተከትል መሆኑ ነው። ለዚህም ነው ጥፊተኛ ባይባልም ንብረቱ የሚወረሰው ‘ስለድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያስረዲ አጥጋቢ ማስረጃ መቅረቡንና ፍ/ቤቱ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው’ የሚወሰን ስለመሆኑ በድንጋጌው ይዘት የተመለከተው አዱሱ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ያሻሻላቸው እና አዱስ ያካተታቸው ድንጋጌዎች ይዘትም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። በዚህ መሰረት የማጓጓዣ ባለቤቶች ጥፊት ሳይፈፅሙ በመጓጓዣው ወንጀል በመፈፀሙ ብቻ ተጥል የነበረው የገንዘብ ቅጣት ሁለ እንዱቀር ተደርጓል።
ከዚህ አንፃር በዚህ መዝገብ የቀረበውን ክርክር ስንመለከት የስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ጥፊተኛ ሆነው የተቀጡት በመኪናው የኮንተሮባንድ ዕቃ ጭነው በመገኘታቸው ሲሆን በስር ፍ/ቤት በቀረበው እና በተረጋገጠው ፍሬ ነገር ተጠሪ በወንጀለ አፈፃፀም ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሃሳብ ወይም ቸልተኝነት ነበረው ሉያሰኝ የሚችል ሁኔታ እንዲልነበር ተመልክቷል።
ከዚህ አንፃር በህጉ አነጋገር የተጠሪ ንብረት የሆነው መኪና እንዱወረስ ለማድረግ ፍ/ቤቱን ሉያሳምን የሚችል ማስረጃ በአመልካች በኩል ያልቀረበ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም የተጠሪ መኪና እንዱወረስ በአመልካች የቀረበው ጥያቄ በስር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ባለማግኘቱ በህጉ ረገድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት ተፈፅሟል ማለት አልተቻለም። ተከታዩንም ወስነናል።
በአፊር ብ/ክ/መንግስት የገቢረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ16/03/2007ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ፤ እንዱሁም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ይ/መ/ቁ 3079 በ27/04/2007 ዓ.ም የተላለፈው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195(2) (ሀ) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ።