No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- የትግራይ ብሓራዊ ክልል ዓ/ህግ -- አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ቡሽራ ያህያ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይ/ሰ/ችልት በመዝገብ ሰኔ 20 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ሉታረምልኝ ይገባል በማለት አመልካች በቁጥር 1043/45/06 ሐምል 10 ቀን 2006 ዓ.ም የተጻፈ 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ክርክሩ የወንጀል ጉዲይን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በትግራይ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ለጉዲዩ መነሻ ምክንያት የሆነው አመልካች /05 ህዲር 06 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ የወንጀል ክስ በአሁኑ ተጠሪና በላልች ሁለት ግለሰቦች ላይ በማቅረባቸው ሲሆን በ1ኛ ክስ የተጠቀሰውና ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ክስ ይዘት በአጭሩ ሲታይ ተጠሪው የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 በአንቀጽ 8 ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ሐምል 16 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ሲሆን ውቅሮ ከተማ በሚገኝ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ለሽብር ተግባር ለማዋል በማሰብ የኢህአዳግ መንግስት የአሜሪካንና የአይሁድች መንግስታት ጥቅም ለማስጠበቅ ፀረ እስላም እንቅስቃሴ የሚያደርግና የእስላም አንድነት ለማጥፊት የሚሰራ መንግስት መሆኑን የሚገልፁ፤ አህባሽ የሳውዱና የምዕራባዊን ተልዕኮ የሚያስፈፅም በእስልምና ሐይማኖት ላይም ክህደት የሚፈፅም ቡድን በመሆኑ ለመንግስትና ለመጅሉስ እውቅና መስጠት የለብንም የሚልና ሁለም የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ በኢህአዳግ መንግስት በፀልት ተቃውሞውን ያቅርብ የሚል ይዘት ያላቸው ለሽብር ተግባር የሚያነሳሱ ሲዱዎችን ይዞ የተገኘ በመሆኑ ለሽብርተኝነት ድርጊት መፈፀሚያነት ንብረት መያዝ ወይም መጠቀም ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነበር።
ተጠሪም ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን አመልካች የሰው ምስክሮችንና ላልች ጠቃሚ ናቸው ያሎቸውን ማስረጃዎች አቅርበው አሰምተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የትግራይ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የአመልካችን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተጠሪ እንዱከላከል ትዕዛዝ ሰጥቶ መከላከያ ምስክሮችን ሰምቷል። በመጨረሻም ተጠሪ በአመልካች ማስረጃ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀፅ 8 ድንጋጌ በመተላለፍ ለሽብር ተግባር የሚያገለግለ ንብረቶችን ይዞ የመገኘት ወንጀል ስለመፈፀሙ የተነገረባቸውን በመከላከያ ማስረጃቸው ማስተባበል አልቻለም በማለት በተከሰሱበት ድንጋጌ የጥፊተኝነት ፍርድ ሰጥቶ ቅጣቱን በመመሪያው መሰረት በማስላት ተጠሪው በስድስት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኖበታል።
የአሁን ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ቅሬታው መልስ ሰጭን ያስቀርባል በማለት ግራ ቀኙን አከራከሮ ሲያበቃ ከተጠሪ ቤት ውስጥ የተገኙት ሲዱዎች የያዙት ንግግር በቴፕ ተደርጎ ሲደመጥ የኢህአዳግ መንግስት ሙስሉሞችን እንደሚጨቁን፤አልሀባሽ የሚባለው የመንግስት ካድሬ እንዲልሆነ፤ነባሩ የእስልምና ሐይማኖት ፈርሶ በአዱስ እንዱተካ እንደሚጠይቅ፤ ውሃብያ ሐይማኖት እንዱስፊፊ እንደሚፈልግ፤መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ እንደሚገባ እና የመጅሉስ ነባር አባላት የመንግስት ፈፃሚዎች ስለመሆናቸው የሚገልፅ መልዕክት የያዘ ለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ መሆኑን ገልፆ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች የሚያቋቁሙት ለሽብርተኝነት ድርጊት መፈጸሚያ እንዱውለ ተጠሪው ንብረት መያዝን ሳይሆን በወንጀል ህጉ አንቀጽ 486(ለ) ስር የሚሸፈን የሐይማኖት ሁከት የመቀስቀስ ወንጀልን ነው በማለት በዚሁ አግባብ የጥፊተኛነት ፍርድ በመስጠት ቅጣቱን አስልቶ ተጠሪ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንን ዲኝነት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይ/ሰ/ችልት ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል ሲሆን አቤቱታው በአጭሩ ተጠሪ የፈጸመው ድርጊት አመልካች ጠቅሶ ያቀረበውን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 8 ሥር የተመለከተውን ወንጀል የሚያቋቁም ሆኖ እያለ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያላግባብ ህጉንና ድንጋጌውን በመለወጥ ወስኗል የሚል ነው።
ሰበር አጣሪው ችልትም መዝገቡን መርምሮ ተጠሪው ጥፊተኛ መባል ያለበት በፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 8 ነው ወይስ በወንጀል ህግ አንቀጽ 486(ለ) ነው? የሚለውን ነጥብ ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ መልስ ያቀረቡ ሲሆን አመልካች የመልስ መልሳቸውን ሉያቀርቡ ባለመቻላቸው መብታቸው መታለፈን ከመዝገቡ ተረድተናል።
ክርክሩ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ተጠናቋል። እኛም አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንጻር ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም ከተጠሪው ቤት የተገኙት ሲዱዎች ለሽብርተኝነት ድርጊት መፈፀሚያነት እንዱውለ ታስበው የተያዙ ለመሆናቸው በፍሬ ነገር ደረጃ አመልካች አረጋግጧል ወይ? የሚለው ጭብጥ ምላሽ ማግኘት ያለበት መሆኑን ተገንዝበናል።
ኢትዮጵያ በ2001 ዓ.ም ያወጀችው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ለሽብር ድርጊት በቂ የህግ ማዕቀፍ ለመስጠት ታስቦ ከመደበኛው የወንጀል ህግ በተሻለ ሁኔታ ከሽብር ጋር የሚገናኙ ድርጊቶች ወንጀል በማድረግ የሽብር ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር ለማስቻል ታስቦ የወጣ አዋጅ ነው።
ስለሆነም አመልካች ለክርክራቸው መሰረት ያደረጉት የፀረ ሽብርተኝት አዋጅ አንቀጽ 8 ድንጋጌ ለሽብርተኝነት ድርጊት መፈፀሚያነት እንዱውል ንብረት መያዝ ወይም መጠቀምን ወንጀል አድርጎ ደንግጎታል። የድንጋጌውን ሙለ ይዘት ስንመለከት ማንኛውም ሰው የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈፀም ወይም እንዱፈፀም ለማመቻቸት እንደሚውል እያወቀ ወይም እንዱውል በማሰብ ማናቸውንም ንብረት የያዘ ወይም የተጠቀመ እንደሆነ የንብረቱ መወረስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአምስት እስከ ሃያ ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል በማለት ደንግጓል።
አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ማስረጃ አቅርቦ ያረጋገጣቸው ፍሬ ነገሮች የተጠሪው ቤት ብርበራ ተደርጎ ሲዱዎች መገኘታቸው፤ እነዚህ ሲዱዎች የያዙት መልዕክትም ሲደመጥ የኢህአዳግ መንግስት ሙስሉሞችን እንደሚጨቁን፤አልሀባሽ የሚባለው የመንግስት ካድሬ እንደሆነ፣ ነባሩ የእስልምና ሐይማኖት ፈርሶ በአዱስ እንዱተካ እንደሚጠይቅ፤ ውሃብያ ሐይማኖት እንዱስፊፊ እንደሚፈልግ፤መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ እንደሚገባ እና የመጅሉስ ነባር አባላት የመንግስት ተልዕኮ ፈፃሚዎች ስለመሆናቸው የሚገልፅ መልዕክት የያዙ ለመሆናቸው የሚያስረደ ሲሆኑ ተጠሪው እነዚህን ሲዱዎች የያዟቸውን መልዕክቶችና ሲዱዎችን የሽብርተኝነት ተግባር እንዱፈፀም ለማመቻቸት አስቦ የያዘ ለመሆኑ የሚያረጋግጡ ፍሬ ነገሮች ለመኖራቸው አመልካች ማስረጃ የመስማትና የማጣራት ሥልጣን ላላቸው የሥር ፍርድ ቤቶች ባቀረቡት ማስረጃ አላረጋገጡም።
ወንጀልና አፈፃጸሙን በተመለከተ በሚደነግገው የኢፋዱሪ የወንጀል ህግ በአንቀጽ 23(2) ሥር እንደተደነገገው የሚያስቀጣ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት ወንጀለን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፤
ግዙፊዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው መገኘት አለባቸው። በልዩ ሁኔታ በህግ የማስረዲት ሸክም ወደ ተከሳሽ ከዞረባቸው ጥቂት ወንጀልች ውጭ በወንጀል የክርክር ሂደት በበቂና አሳማኝ ሁኔታ ፍሬ ነገርን የማስረዲት ሽክም በዐ/ህጉ ላይ የተጣለ ኃላፉነት ለመሆኑ ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 141 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ የሚቻል ነው።
ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያለው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 8 ሥር የሚገኙ ፍሬ ነገሮች የማስረዲት ሸክም በልዩ ሁኔታ ወደ ተከሳሹ የዞረ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ወንጀለን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፤ግዙፊዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች የማስረዲት ሸክሙን የመወጣት ግዳታ እንዲለበት መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም አመልካች በተጠሪው እጅ ከላይ የተገለፀውን መልዕክት የያዙ ሲዱዎች መገኘታቸውንና በሲዱዎች ያለው መልዕክት ሲደመጥ ከላይ የተገለፀው መሆኑን በማስረዲቱ ብቻ አመልካች የያዛቸው ሲዱዎችም ሆኑ በውስጣቸው የነበሩት መልዕክቶች ለሽብረተኝነት ተግባር ለማመቻቸት የታሰቡ ነበሩ ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የትግራይ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪው ስለመፈጸሙ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 8 ሥር የሚሸፈን ወንጀልን ያቋቁማለ በማለት መወሰኑ አመልካች የማስረዲት ሸክሙን ባልተወጣበት ሁኔታ የተወሰነ ስለነበር የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ተጠሪው የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈፀም ወይም እንዱፈፀም ለማመቻቸት እንደሚውል እያወቀ ወይም እንዱውል በማሰብ ማናቸውንም ንብረት የያዘ ወይም የተጠቀመ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ በውጤት ደረጃ የሚከተለውን ወስነናል።
የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል ይግባኝ በመዝገብ ሰኔ 20 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 195(2)(ለ)(2) በውጤት ደረጃ ፀንቷል።መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.