No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ፀሀይ ውብዬ አልቀረቡም ተጠሪ፡- የፍደራል/ዓ/ህግ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የመንግስት ማህተምን ያለአግባብ መገልገል ሙከራ ወንጀል የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት በአመልካች እና አብረዋቸው በተከሰሱ ተከሳሾች ላይ ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የአሁን አመልካች ላይ የቀረበው ክስ ይዘት ተከሳሽ ለመንግስት ስራ የሚውል ማህተምን ያላግባብ ለመገልገል አስባ በዐ/ህግ 3ኛ ምስክር አማካኝነት ለወ/ሮ ሜሮን ሚካኤል (1ኛ ተከሳሽ) 1000 ብር ከፍላ የኢት/ንግድ ባንክን ማህተም ከባንኩ ሰርቃ እንድታመጣላት ካደረገች በኃላ በምስክሯ ጥቆማ የተያዘች በመሆኑ የወ/ህ/አ 27(1) እና 363 (1) (ለ) የተመለከተውን በመተላለፍ የመንግስት ማህተም ያለአግባብ መገልገል ሙከራ ወንጀል ተከሰላች የሚል ነው።
አመልካች (የስር ተከሳሽ) በክሱ የተገለፀውን የወንጀል ድርጊት አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት በመካዲቸው ዐ/ህግ ማህተሙ የጠፊበት የኢት/ን/ባንክ ሱማላ ተራ ቅርንጫፍ ሰራተኞችን ጨምሮ 3 ምስክሮችን አሰምቷል። ፍ/ቤቱ ከዐ/ህግ ምስክሮች 1ኛ ተከሳሽ የሆኑት ወ/ሮ ሜሮን ሚካኤል በተጨማሪ ምስክርነት ሰምቶ አመልካች ክሱ የቀረበበትን የወንጀል ድርጊት ለመፈፀማቸው የተመሰከረባቸው በመሆኑ እንዱከላከለ ብይን የሰጠ ሲሆን አመልካች የሰው መከላከያ ማስረጃ የለኝም በሚሮን ሚካኤል የግል ስልክ በወቅቱ ስለመደወላ ከኢት/ቴላኮም ዝርዝር ቀርቦ ይታይልኝ ብለዋል።
ፍ/ቤቱ ከሰኔ ወር መጀመሪያ እስከ ሐምል ወር መጨረሻ 2006 ዓ/ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ወ/ሮ ሜሮን ሚካኤል በግል ስልካቸው የተደወለ የስልክ ቁጥር ዝርዝር እንዱቀርብ ባዘዘው መሰረት ከኢት/ቴላኮም በቀረበው ዝርዝር ወ/ሮ ሜሮን ሚካኤል በሚጠቀሙበት ስልክ ቁጥር አመልካች በሚሰሩበት የመከላከያ ሚ/ር የቢሮ ስልክ ቁጥር ላይ ተደውል የነበረ መሆን አለመሆኑን ባያሳይም ወ/ሮ ሜሮን ሚካኤል ስልክ ላይ ተከሳሽ አልደወለችም ብል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚያዲግት ነው በማለት አመልካች (ተከሰሽ) በተከሰሱበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ ናቸው ብል በመወሰን የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያያት በማገናዘብ በቅጣት አወሰሰን መመሪያው ቅጣቱን በማስላት በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ቅሬታቸውን ለፋ/ክልል ፍ/ቤት በይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር አመልካች ላይ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔን በማፅናት ወንጀለ በሙከራ ደረጃ የቀረ እና በመንግስትና በህዝብ ላይ የደረሰ ጉዲት ባለመኖሩ ስር ፍ/ቤት የወንጀለን ደረጃ በቀላል ደረጃ መመደብ ሲገባው መካከለኛ ደረጃ መመደቡ ተገቢ አይደለም ብል የወንጀለን ደረጃ በቀላል ደረጃ በመመደብ መነሻ ቅጣት 3 ዓመት ወስኖ በ2 ማቅለያ ምክንያቶች ቅጣቱ ወደ 2 ዓመት ፅኑ እስራት በማሻሻል ወስኗል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተፈፀመ ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት በመጥቀስ እንዱታረምላቸው የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች በስር ፍ/ቤቶች ጥፊተኛ ተብለው ቅጣት የተወሰነባቸው በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የህግ አንቀጽ የሚያቋቁም ድርጊት መፈፀማቸው በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጦ መሆን አለመሆኑን እና በዚህ ጉዲይ በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበሩትና ወ/ሮ ሜሮን ሚካኤልን በአመልካች ክስ በማጣሪያ ምስክርነት ጠርቶ የመስማቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ ምክንያት ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች ተከሰው ጥፊተኛ የተባለት የወ/ህጉን አንቀጽ 27(1) እና 363 (1) ‛ለ“ የተመለከተውን ተላልፈው ለመንግስት ስራ በተዘጋጀ ማህተም ያለ አግባብ መገልገል ሙከራ ወንጀል ሲሆን የድንጋጌው ይዘት ለመንግስት ስራ ጉዲይ ብቻ የሚታተምበትን የመንግስትን ወይም የመንግስታዊ አካላት የአንደን ማህተም ያለአግባብ የተገለገለ እንደሆነ ከ3 ዓመት እስከ 10 ዓመት ሉደርስ በሚችል ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ይደነግጋል። አመልካች ለኢት/ንግድ ባንክ ሱማላ ተራ ቅርንጫፍ መገልገያነት የተዘጋጀውን የመንግስት ማህተም በተጠሪ 3ኛ ምስክር እና በስር 1ኛ ተከሳሽ በሆኑት የባንኩ ተላላኪ ሰራተኛ አማካኝነት ማህተሙን ተቀብለው የባንኩ ተላላኪ ሰራተኛ ለሆኑት የስር 1ኛ ተከሳሽ ብር 1000 መላካቸው ስር ፍ/ቤት በቀረበው ማስረጃ በማረገጋጥ አመልካች ላይ ያሳለፈው የጥፊተኛነት ውሳኔ በህጉ አግባብ በመሆኑ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም በልላ በኩል አመልካች የተከሰሱት እና የጥፊተኛነት ውሳኔ የተላለፈባቸው በሙከራ ደረጃ በቀረ ወንጀል በመሆኑ በወ/ሕ/አንቀጽ 31 እንደተመለከተው ተከሳሹ ጥፊተኛ በተባለበት የሙከራ ወንጀል ድርጊት የደረሰ ጉዲት ከላላ በወ/ህ/ቁ. 180 በተመለከተው መሰረት ቅጣቱን በመሰለው እንደሚያቀል የተደነገገ በመሆኑ እና በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ቀደም ሲል እንደነበረው የቅጣት አወሳሰን በሙከራ ደረጃ ለተፈጸመ ወንጀል ቅጣት እንደሚቀንስ በግልጽ ባይመለከትም በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንቀጽ 24 ስር በወንጀል ህጉ ቅጣትን በመሰለው እንዱያቀል በፈቀደ ጊዜ ፍ/ቤቱ በመመሪያው ሳይወሰን ቅጣትን በማቅለል እንደሚወሰን የተመለከተ በመሆኑ እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም በተመሳሳይ በ
አስገዲጅነት ያለው የህግ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ ወንጀለ በሙከራ ደረጃ የቀረ መሆኑን መሰረት በማድረግ የስር ፍ/ቤት ቅጣቱን በመሰለው ማቅለል ሲገባው ይህን በማለፍ በቀረቡለት 2 ማቅለያ ምክንያቶች ላይ ብቻ በመወሰን የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ሉታረም የሚገባው በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 6/11/2007 ዓ/ም በዋለው ችልት እና የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 18/2/2008 ዓ/ም የሰጡት የጥፊተኛነት ውሳኔ እና ትዕዛዝ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 195(2) (ለ) መሰረት ፀንቷል።
የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት ያሳለፈው የቅጣት ውሳኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ወንጀል በሙከራ ደረጃ የቀረ እና በመንግስት ላይ የደረሰ ጉዲት ባለመኖሩ የወ/ህጉን አንቀጽ 27(1)፣31፣ 180፣ እና 363(1) (ለ) እንዱሁም የተሻሻለውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 24 መሰረት በማድረግ ለአመልካች ስር ፍ/ቤት የተያዘላቸውን ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችንም ከግምት በማስገባት አመልካች ለፈፀሙት ጥፊት ከዚህ ጉዲይ ጋር በተያያዘ የታሰሩበት የሚታሰብላቸው ሆኖ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ የስር ፍ/ቤትን የቅጣት ውሳኔ በመሻሻል ወስነናል።
አመልካች ታስረው የሚገኙበት ማ/ቤት በዚህ በተሸሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈጽም ይፃፍ ብለናል መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.